እህል ነጋዴዎች በቆሎና ማሽላ ላይ በተጣለው ዕገዳ ምክንያት ወደ ውጭ መላክ አልቻልንም አሉ
ከምሥራቅና ከደቡባዊ አፍሪካ የመጡ ገዥዎች ከኢትዮጵያ ግዥ ፈጽመዋል...
View Articleየሰባት ወራት የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ቅናሽ አስመዘገበ
የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሲጠበቅ 1.4 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት የታየው የወጪ ንግድ አፈጻጸም እንደወትሮው ማሽቆልቆል አሳይቷል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ይጠበቅ የነበረው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ2.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ቢሆንም፣ አፈጻጸሙ ግን ከ1.4 ቢሊዮን ዶላር ብዙም ፈቅ ሳይል...
View Articleየሐዋሳ ንግድ ምክር ቤት ዋና መሥሪያ ቤቱን የሚገነባበት ቦታ ተረከበ
የሐዋሳ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃውን ለመገንባት የሚችልበትን ቦታ ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ንግድ ምክር ቤቱ የራሱን ሕንፃ ለመገንባት ቦታ እንዲሰጠው ጥያቄ ካቀረበ ዓመታት ቢቆጠሩም፣ በቅርቡ ከሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምላሽ አግኝቷል፡፡ ለሕንፃ ግንባታው ምቹ...
View Articleየሜትር ታክሲዎችና የትራንስፖርት ባለሥልጣን ፍጥጫ አላባራም
‹‹ሳይሞከር እንዴት ነው አያዋጣም የሚባለው?››ትራንስፖርት ባለሥልጣን‹‹በማን ኪሳራ ነው የሚሞከርብን?››የሜትር ታክሲ ማኅበራት...
View Article‹‹የውኃ ታሪፍን ለመጨመር የተሻለ አገልግሎት መስጠት የግድ ይላል››
አቶ ዋና ዋኬ፣ የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተርአቶ ዋና ዋኬ በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ለዓመታት አግልግለዋል፡፡ ከሁለት ዓመት በፊት የውኃ ሀብት ልማት ፈንድ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከመሾማቸው ቀድሞ ለስምንት ዓመታት ያህል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ነበሩ፡፡ አባል ብቻም ሳይሆኑ በበጀትና...
View Articleየኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ኢኮኖሚያዊ ድርሻ እያደገ መምጣቱ ተገለጸ
170 የአገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች የተሳተፉበት ዓውደ ርዕይ ነገ ይጠናቀቃል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በአማካይ 28.7 በመቶ ዕድገት እየተመዘገበበት እንደመጣና የኢኮኖሚ ድርሻውም 8.5 በመቶ መድረሱን የኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ወ/ሮ አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር) ገለጹ፡፡ ሚኒስትሯ ይህንን የገለጹት አምስተኛውን...
View Articleበረሀብ ቸነፈር የተመቱ ሕዝቦች በአስከፊ ዕልቂት አፋፍ ላይ ይገኛሉ
ኢትዮጵያ ለ5.6 ሚሊዮን ሰዎች ዕርዳታ የሚሰጠኝ አላገኘሁም ብላለችበሶማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኬንያ፣ በኢትዮጵያ እንዲሁም በየመን የተንሰራፋው ችግር ወደ ችጋርና ረሀብ በመሻገር የሰውና የእንስሳት ነፍስን እያጠፋ ይገኛል፡፡ የየመን ጉዳይ በጦርነት ሳቢያ የተቀሰቀሰ የሰብዓዊ ቀውስ ሲሆን፣ በምሥራቅ አፍሪካ አገሮች...
View Articleየወጪ ንግዱ ያሳየው ማሽቆልቆል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን በስብሰባ ወጥሯል
ላኪዎች ነገ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ለስብሰባ ተጠርተዋል የንግዱ ማኅበረሰብ በጥናት ላይ የተመረኮዘ መትፍሔ እንዳቀርብ ዕድሉን አላገኘሁም ይላልየአገሪቱ የወጪ ንግድ እያሳየ ያለው ማሽቆልቆል እየተባባሰ በመምጣቱ፣ መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት የሚያስችሉ የአጭር ጊዜ ዕርጃዎችን መውሰድ እንደሚጀምር...
View Articleንግድ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ላይ የሚያሳልፈው ውሳኔ እየተጠበቀ ነው
-የአማራ ክልል ንግድ ምክር ቤት ዕግድ ወጥቶበታልየአገሪቱን የንግድ ማኅብረሰብ የሚወክለው የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲያወዛግብ የቆየውን ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ የንግድ ሚኒስቴርን ውሳኔ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡ይህ የተገለጸው የንግድ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ለወራት...
View Articleየአገር ውስጥ ተቋራጮች በመንገድ ግንባታ ከፍተኛውን ድርሻ ቢይዙም በገንዘብ የውጭዎቹ ብልጫውን ወስደዋል
አገር በቀሎቹ የ92 ቢሊዮን ብር ሲደርሳቸው የውጮቹ የ114 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክቶችን አግኝተዋልበዳዊት ታዬየኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ1989 ዓ.ም. ጀምሮ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ድረስ በጠቅላላው 604 የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ለውጭና ለአገር ውስጥ ተቋራጮች በማስተላለፍ አስገንብቷል፤ እስገነባም...
View Articleየቱሪዝም አባት አቶ ሀብተሥላሴ ታፈሰ የሚታወሱበት የ13 ወር ፀጋ መለያ
‹‹እኔ ያደግሁት ውጭ አገር ነው፡፡ የትም ዓለም ላይ 13 ወር የለም፡፡ ፒራሚድ ሲታይ ግብፅ ነው፡፡ አይፈልታወር ሲታይ ፈረንሣይ ነው፡፡ የነፃነት ሐውልት ሲታይ አሜሪካ አለ፡፡ እኛ የምንታወቅበት የለንም ነበር፡፡ ሁሉ ነገር ከዘር፣ ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ ሳላውቀው አንድ ወቅት ላይ የ13 ወር ደመወዝ...
View Articleከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለኦሞ ኩራዝ ስኳር ፕሮጀክቶች የመስኖ ግንባታ ሊካሄድ ነው
ንግድ ባንክ ለፕሮጀክቱ አሥር ቢሊዮን ብር አበድሯልበደቡብ ክልል በመስኖ ልማት ዘርፍ ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ እንደሆነ የተጠቀሰውና 185 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የኦሞ ኩራዝ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ዋና የቦይ፣ የመስኖ ካናሎችንና ተያያዥ ግንባታዎችን ለማከናወን ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው ስምምነት...
View Articleመፍትሔ ያጡ በካይ ወንዞችና አትክልቶች
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት ትልቅ ሃይማኖታዊ መሠረት ካላቸው አንዱ የዓቢይ ፆም ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ፆመ እኩሌታው ተጋምሶ ወደ ፍጻሜው እየተቃረበ በሚገኘው በዚህ የፆም ወቅት፣ ምዕመናን ነፍሳቸውንና ሥጋቸውን በመጎሰም ለንስሐና ለመልካም ዋጋ የሚተጉበት ጊዜ ነው፡፡ ስለ ፆሙ መተንተን...
View Articleበኢትዮጵያ የግብርና ኤክስቴንሽን መስክ ፈር ቀዳጁ ሳሳካዋ ግሎባል
በጃፓናዊው ምግባረ ሰናይ ዮኢሺ ሳሳካዋ አማካይነት የተመሠረተው ሳሳካዋ አፍሪካ አሶሲዬሽን እንዲሁም በሥሩ የሚተዳደሩ ሳሳካዋ ግሎባል 2000 እየተባሉ በየአገሮቹ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን በመመሥረት በአፍሪካ መንቀሳቀስ ከጀመረ 30 ዓመታት አስቆጥሯል፡፡ ተቋሙ ወደ አፍሪካ እንዲመጣ ምክንያት የሆነው...
View Articleትራንስፖርት አቅራቢዎች ወደ ካርቱም የሚደረገው ጉዞ ከታቀደው በላይ አራት ቀናት እየወሰደባቸው እንደሚገኝ ገለጹ
-የፍተሻ ኬላዎች መብዛት ጉዞውን ካራዘሙ ችግሮች ዋናዎቹ ናቸው- ወደ ሱዳን የሚገቡ መኪኖች ሦስት ሺሕ ብር ይጠየቃሉ ከአዲስ አበባ ካርቱም፣ ከካርቱም አዲስ አበባ በደርሶ መልስ ሕዝብ የማመላለስ አገልግሎትን በቅርቡ የጀመሩ ተሸከርካሪዎች እስካሁን ከ400 በላይ መንገደኞችን ቢያጓጉዙም ሁለት ቀናት ይፈጃል የተባለው ጉዞ...
View Articleአዲስ የዲቪዲና የሲዲ ማምረቻ ፋብሪካ በአዲሱ የቴዲ አፍሮ አልበም ሥራውን እንደሚጀምር ይፋ አደረገ
ከ50 ሚሊዮን ብር ብላይ ወጪ የተደረገበት ዘመናዊ የሲዲና የቪሲዲ ማምረቻ ፋብሪካ ማሟሻውን የቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲስ አልበም በማድረግ ለማተም ትዕዛዝ መቀበሉ ተገለጸ፡፡ቆልያ ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማኅበር ተብሎ የተሰየመው የሲዲና የዲቪዲ ማምረቻው ባለፈው ሳምንት ሥራ መጀመሩ ይፋ ሲደረግ እንደተገለጸው፣...
View Articleበአደባባዮች ላይ የተላላፊ መንገዶች ግንባታ ለማካሄድ የዲዛይን ሥራዎች እየተገበዳዱ እንደሚገኙ ተገለጸ
የቦብ ማርሌ ኪነ ቅርጽ የሚገኝበት አደባባይ የሚፈርስ በመሆኑ ምትክ ቦታው እየተጠበቀ ነውለአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መጨናነቅ በማስከተላቸው እንዲፈርሱ ከተባሉና ተላላላፊ መንገድ ከሚገነባቸው መካከል አንዱ የሆነው የቦሌ ሚካኤል አደባባይ የተላላፊ መንገድ ዲዛይን መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ የቦብ ማርሌ ኪነ ቅርፅ ከሚገኝበት...
View Articleለቡና ዘርፍ አዲስ አማካሪ ምክር ቤት ሊቋቋም ነው
የቡና ዘርፍን ለመለወጥ የሚያግዙ አዳዲስ አሠራሮችና ሕጎች ላይ ቡና ላኪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ከመንግሥት ጋር ሊመክሩ ነው፡፡ በቡናው ዘርፍ ከሚጠቀሱት ውስጥ ከፍተኛ የውሳኔ አካል ይሆናል የተባለ አዲስ አማካሪ ምክር ቤትም ለማቋቋም መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑም ታውቋል፡፡ ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ልማትና ግብይት...
View Article የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር የቦርድ አባላት ምርጫ ሊያደርግ ነው
ከተቋቋመ አምስት ዓመታት ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበር፣ ለቀጣይ ሦስት ዓመታት ማኅበሩን የሚመሩ የቦርድ አባላት ምርጫ መጋቢት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ሊያካሂድ መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ስዩም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ለቦርድ አባልነት ለመወዳደር በራሳቸው ፍላጎት፣...
View Article