Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

ለቡና ዘርፍ አዲስ አማካሪ ምክር ቤት ሊቋቋም ነው

$
0
0

የቡና ዘርፍን ለመለወጥ የሚያግዙ አዳዲስ አሠራሮችና ሕጎች ላይ ቡና ላኪዎችና ሌሎችም ባለድርሻዎች ከመንግሥት ጋር ሊመክሩ ነው፡፡ በቡናው ዘርፍ ከሚጠቀሱት ውስጥ ከፍተኛ የውሳኔ አካል ይሆናል የተባለ አዲስ አማካሪ ምክር ቤትም ለማቋቋም መመሪያ እየተዘጋጀ መሆኑም ታውቋል፡፡  

ከኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ልማትና ግብይት ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የቡናውን ዘርፍ በአዲስ አሠራር ለመቀየር የታሰበው ሪፎርም ለመተግበር ያስችላሉ በተባሉ ጉዳዮች ላይ የሚደረገው የምክክር መድረክ በነገው ዕለት ይካሄዳል፡፡

መድረኩ በቅርቡ የቡና ባለድርሻ አካላት ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ስምምነት የተደረሰባቸውን ጉዳዮች ለመተግበር ያስችላል ተብሏል፡፡ በቡና ግብይት ወቅት ከምርት እስከ ወጪ ንግድ መዳረሻ ድረስ ያለውን አጠቃላይ አሠራር በአዲስ ለመቀየር የሚያስችለው ሪፎርም በቡና ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት መፈጸም ስለሚገባቸው ተግባራትና እነዚህን ለማስፈጸም የወጡ ሕጎች ይፋ የሚደረጉበት መድረክ እንደሚሆንም ይጠበቃል፡፡

ከአዳዲሶቹ ሕጎች መካከል የቡና ግብይትና የላኪዎች ፈቃድ አሰጣጥን የሚመለከተው መመሪያ አንዱ ነው፡፡ የቡና የግብይት ሰንሰለትን ለማሳጠር የሚያስችሉ አሠራሮችም በመመሪያዎቹ ይካተታሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የታሰበውን ሪፎርም ለማሳካትና በዘርፉ የሚታየውን ችግር ተከታትሎ ለመፍታት ብሎም የቡና ዘርፉን ወደሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ ያስችላል የተባለ አዲስ አማካሪ ምክር ቤት እንደሚያቋቁም ባለሥልጣኑ ይፋ አድርጓል፡፡  

የቡና ዘርፍ አማካሪ ምክር ቤቱ ከመንግሥትና በቡና ዘርፍ ከተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተወካዮች እንመዲካተቱበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቡና ምርምር ሥራ ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎችም የዚህ ምክር ቤት አባላት እንደሚሆኑ ተጠቅሷል፡፡  

የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ የተመጣጠነ ውክልና ኖሮት እንደሚቋቋም የሚጠበቀው አማካሪው ምክር ቤት፣ የሚቋቋምበት አግባብና አጠቃላይ የሚሠራቸውን ሥራዎች በዝርዝር የሚያትት ሕግ እየተረቀቀ ሲሆን፣ በቅርቡ ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳኒ ረዲ ገልጸዋል፡፡ ይህ መመሪያ ከፀደቀ በኋላ አማካሪ ምክር ቤቱ ተቋቁሞ ቡናን ሪፎርም ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት ከፍተኛ ኃላፊነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በቡና ምርምር፣ በግብይት ሥርዓቱ፣ በኤክስቴንሽን ሥራዎች፣ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምርምር አጀንዳዎችን የመቅረስ ሥራዎችን ይሠራል፡፡ የግብይት ሥርዓቱ ላይ የሚታዩ ችግሮች ላይ በመምከር አመራር ይሰጣል ተብሏል፡፡ፈጻሚነቱንም ይከታተላል፡፡

በቅርቡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በተደረገ ውይይት ወቅት እንደተገለጸው፣ ለቡና እንቅፋት የተባሉ ጉዳዮች በዘርፉ ተዋናዮች ጥያቄ ቀርቦባቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩም የተነሱት ችግሮች በሙሉ እንደሚስተካከሉ ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ከተጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ የቡና ግብይት ሥርዓቱ ረዥምና የተንዛዛ መሆን አንዱ ነው፡፡ የኮንትሮባንድ ንግድ አለመገታቱም ተጠቅሶ ነበር፡፡ የምርት ዝግጅትና የግብይት ሒደቱ ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግና ረዥም ጊዜ የሚወስድ መሆኑ እስካልተስተካከለ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚሉ ነጥቦችም ተነስተው ነበር፡፡ 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles