የግል መድን ኩባንያዎች ዕድገት በሀብትና በትርፍ ውጤት እያስመዘገቡ መምጣታቸውን አስታወቁ
- አዋሽ ትልቁን የገበያ ድርሻ ይዣለሁ ይላል- ሉሲ የገበያ ድርሻውን ማሳደጉን ገለጸ- ዓባይ ትርፉን 51 በመቶ አሳድጓልየኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ በሚፈለገው መጠን እንዳላደገ ሲነገር ቆይቷል፡፡ ከባንክ ኢንዱስትሪው የዕድገት መጠን አንጻር በንጽጽር ሲታይም፣ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ዕድገት አዝጋሚ ሆኗል፡፡...
View Articleየጃፓን መንግሥት ድጋፍ ሲያደርግበት የቆየውን የቡና ጥራት መፈተሻ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ አስረከበ
ከስምንት ዓመታት በፊት ወደ ጃፓን በተላከ ቡና ላይ የተገኘውን የፀረ ተህዋስያንና ፀረ አረም መከላከለያ ኬሚካል መነሻ በማድረግ የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ የኤክስፖርት ቡና ጥራት መፈተሻ የላቦራቶር ፍተሻ ማካሄጃ ፕሮጀክት ተክሎና ባለሙያዎችን መድቦ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ...
View Articleወጋገን ባንክ ከ375 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ አገኘ
በ2008 በጀት ዓመት 375.6 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ያስታወቀው ወጋገን ባንክ፣ ካቀደው የተጣራ ትርፍ ውስጥ 92 በመቶ ማሳካቱን ገለጸ፡፡ባንኩ ሐሙስ፣ ህዳር 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ወቅት ይፋ እንዳደረገው፣ በበጀት ዓመቱ ያገኘው የተጣራ ትርፍ ከቀደመው ዓመት የ6.6 በመቶ ብልጫ...
View Articleየንግድ ዓውደ ርዕዮች ከአቅም በላይ የሚጭኑት ዋጋ
ከዓመት በፊት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተዘጋጀ የንግድ ዓውደ ርዕይ የማዕከሉ አዳራሾች በተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ ነጋዴዎች እንዲሁም በደንበኞች ተሞልዋል፡፡ በደንበኞች ከተከበቡ ድንኳኖች መካከል ባህላዊ የቆዳና የሰውነት ክብደት መቀነሻ መድኃኒቶች በአንዱ እየተሸጠ ነው፡፡ መድኃኒቶቹን ቀምሞ የሚዘጋጀው...
View Articleየፋይናንስ ተቋማት ለሕንፃ ግንባታ አግላይ የጨረታ መሥፈርቶችን በማውጣት እየተወቀሱ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ ‹‹ሰማይ ጠቀስ›› የሚባሉ ሕንፃዎችን የሚገነቡ የፋይናንስ ተቋማት ቁጥር እየተበራከተ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት መናኸሪያ መንደር እንደሚሆን በሚታመነው ‹‹ሠንጋተራ›› አካባቢ አሥር ባንኮችና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ቦታ ተረክበው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃዎችን የገነቡና ለማስገንባት...
View Articleአዋሽ ባንክ በአዲስ ዓርማ ሊመጣ ነው
- ስያሜውንም ያሻሽላልከደርግ ውድቀት በኋላ የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለግል ዘርፉ ሲከፈት የመጀመሪያው የግል ባንክ በመሆን ኢንዱስትሪውን የተቀላቀለው አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ነው፡፡ ከአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ በኋላ ኢንዱስትሪውን የተቀላቀሉት አብዛኛዎቹ ባንኮች ከዋናው ስያሜያቸው ቀጥሎ ‹‹ኢንተርናሽናል›› የሚለውን...
View Articleእናት ‹‹ጠንቃቃዋ›› አበዳሪ
በባንክ ኢንዱስትሪ እንደ ዋና ተግባር የሚቆጠረው የተቀማጭ ገንዘብን በማሰባሰብ ብድር ሰጥቶ ትርፋማ መሆን ነው፡፡ ከባንኮች ዓመታዊ ትርፍ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደውም ከሚሰጡት ብድር የሚያገኙት የብድር ወለድ ነው፡፡መረጃዎች እንደሚያሳዩት 16ቱ የግል ባንኮች በ2008 በጀት ዓመት ከ88 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር...
View Articleየአቢሲኒያ ባለአክሲዮኖች ካፒታላቸውን አራት ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰኑ
የአቢሲኒያ ባንክ ባለአክሲዮኖች የባንካቸውን ካፒታል ወደ አራት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ከባንኩ አመራር የቀረበላቸውን ሐሳብ ተቀብለው አፀደቁ፡፡ ባለአክሲዮኖቹ ባለፈው ቅዳሜ ባካሄዱት ጠቅላላ ጉባዔ የባንኩን ካፒታል ወደ አራት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ መወሰናቸው፣ አቢሲኒያ ባንክን ከግል ባንኮች በተፈቀደ ካፒታል መጠን...
View Article65 ሚሊዮን ብር የወጣባቸው አገር አቋራጭ አውቶቡሶች ሥራ ሊጀምሩ ነው
ፋልከንኮች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ 65 ሚሊዮን ብር የወጣባቸውን አዳዲስ አውቶቡሶች ለአገር አቋራጭ የትራንስፖር አገልግሎት ሊያሰማራ ነው፡፡ አውቶብሶቹ የቻይናው ዞንግ ቶንግ ኩባንያ ምርቶች ሲሆኑ፣ የአንዱ ዋጋም ሦስት ሚሊዮን ብር ገደማ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ከተደረጉት...
View Articleየንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ ትርፍ ለሁለተኛ ጊዜ ቀነሰ
በመድን ሥራ አገልግሎት ከግል የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል ከቀዳሚዎቹ አምስት የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ንብ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በ2008 በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ቀንሷል፡፡ኢንሹራንስ ኩባንያው ባለፈው ቅዳሜ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ይፋ ያደረገው ዓመታዊ ሪፖርት...
View Articleሁለት ወጣቶች የዓመቱን ምርጥ የሥራ ፈጠራ ዕውቅና አገኙ
የኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ማዕከል በውበት ማሠልጠኛና በዲኮር ዲዛይን ሥራ ለተሰማሩ ሁለት ስኬታማ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የዓመቱ ምርጥ ወጣት ሥራ ፈጣሪ በሚል ዕውቅና ሰጠ፡፡ ዕውቅና የተሰጣቸው ምሕረት ምትኩና ደሳለኝ ሸዋንግዛው የተባሉ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ናቸው፡፡ ባላቸው የፈጠራ አመለካከት፣ ስትራቴጂክ አስተሳሰብ፣...
View Articleጁሚያ ለሆቴል ተጠቃሚዎች የኦንላይን የክፍያ ሥርዓት መጠቀም ጀመረ
በኦንላይን ሆቴል ቡኪንግ ላይ የሚሠራው ጁሚያ ትራቭል በደንበኞችና በሆቴሎች መካከል ያለውን የክፍያ ሥርዓት እዚያው በኦንላይን ለመጨረስ የሚያስችለውን የቨርቹዋል ክሬዲት ካርድ ቴክኖሎጂ መጠቀም ጀመረ፡፡ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ከ600 ሆቴሎች ጋር አብሮ የሚሠራው ጁሚያ ከዚህ ቀደም ክፍያ የሚፈጽመው በኦንላይን ባለመሆኑ ብዙ...
View Articleየኢትዮ ላይፍ ጉዞና 120 በመቶ ዕድገት የታየበት የካሳ ጥያቄ
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀኔራል ኢንሹራንስ ኩባንያ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የአገሪቱን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ለመቀላቀል ሲንደረደር ከሌሎች ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በተለየ የራሴ የሚለውን አዲስ ነገር ይዞ ነበር፡፡ሁሉም የአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች እስካሁንም ድረስ እንደሚያደርጉት ሕይወትና ሕይወት ነክ ያልሆኑ የመድን...
View Articleኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዓመታዊ ትርፍ በ37 በመቶ ቀንሷል
ኦሮሚያ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በ2008 በጀት ዓመት ያገኘው ትርፍ ከቀዳሚው ዓመት በ37 በመቶ ቀነሰ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2009 ዓ.ም. የኢንሹራንስ ኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርቱን ይፋ ባደረገበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በ2008 ዓ.ም. ከታክስ በፊት 33.39 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ይሁን እንጂ...
View Articleኅብረት ባንክ በተጠናቀቀው ዓመት
ከሌሎች የአገሪቱ የግል ባንኮች አመሠራረት አንፃር ሲታይ ኅብረት ባንክ በተለየ መንገድ የተቋቋመ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ከጥቂት ባንኮች በስተቀር አብዛኞቹ ባንኮች ከተመሠረቱ በኋላ እንደ እህት ኩባንያ የሚቆጥሯቸውን የኢንሹራንስ ኩባንያዎች በመፍጠር የሚንቀሳቀሱ ሲሆን፣ ኅብረት ባንክ ግን ከኅብረት ኢንሹራንስ ቀድሞ...
View Articleሸውራራ ዕቅዶች ዋጋ ማስከፈላቸውን ቀጥለዋል
የአዲስ አበባ (ሰበታ) ጂቡቲ የባቡር ሃዲድ ግንባታ ሲጀመር መስመሩ የገቢና ወጪ ንግድ ማቀላጠፍ የሚያስችል በመሆኑ በርካቶችን ያስደሰተ ፕሮጀክት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ባለቤትነት በሁለት የቻይና ኩባንያዎች የተገነባው ይህ የባቡር መስመር በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ፣ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር...
View Articleየዕድገት ተስፋ የተሰነቀበት የኢትዮጵያና የቱርክ ትብብር
ከሁለት ሳምንታት በፊት በቱርክ ኢስታንቡል ከተማ የቱርክ አፍሪካ ኢኮኖሚክና ቢዝነስ ፎረም ለሁለት ቀናት ተካሂዶ ነበር፡፡ በፎረሙም ከተገኙት በርካታ የአፍሪካ አገሮች ተወካዮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ከግማሽ በላይ ያህሉ በሚኒስትሮች ደረጃ የተሳተፉበት ሲሆን፣ ፎረሙንም የቱርክ ፕሬዚዳንት ሪሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ተገኝተው...
View Articleየአዋሽ ባንክ ድንበር ተሻጋሪ ውጥን
የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ይካሄዳል በተባለ ቁጥር የሚፈጠሩ ውዝግቦች ይታወሳሉ፡፡ የቦርድ ዳይሬክተር ለመሆን የሚደረገው ፉክቻ ለተከታታይ ዓመታት በግልጽ ሲንፀባረቅ ቆይቷል፡፡ ቅዳሜ ኅዳር 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ባንኩ በጠራው ጠቅላላ ጉባዔ አዳዲስ የቦርድ ዳይሬክተሮች ምርጫ ቢያካሂድም፣ በቀደሙ...
View Articleፕሬዚዳንቱን ባሰናበተ ማግሥት ቡና ባንክ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ከተመሠረተ ሰባተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡ የ2008 በጀት ዓመት የሥራ ክንውኑን ይፋ ለማድረግ የባንኩን ባለአክሲዮኖች በመጥራት ጠቅላላ ጉባዔውን እሑድ፣ ኅዳር 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዷል፡፡ሰኔ 2001 ዓ.ም. የተቋቋመውን ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ ለሰባት ዓመታት...
View Articleንብ ባንክ ከግል ባንኮች ይልቅ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ አበዳሪ ሆኖ ተገኝቷል
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ቀዳሚ ከሚባሉት ስድስት የግል ባንኮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ዘልቋል፡፡ ባለፉት ስድስት ዓመታት ሲመዘገብ የቆየው የባንኩ የትርፍ ዕድገት ግን የተለየ አካሄድ ይዞ መዝለቁን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡በአምስት ዓመታት የባንኩ እንቅስቀቃሴ ወቅት በአማካይ የተመዘገበው የትርፍ...
View Article