Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

ኢትዮጵያ በነዳጅ ገበያ መረጋጋት 30 በመቶ ወጪ እያዳነች መሆኑ ታወቀ

$
0
0

በዓለም የነዳጅ ገበያ መቀዛቀዝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት ሦስት ዓመታት፣ በየዓመቱ ከ20 እስከ 30 በመቶ የሚሆን የውጭ ምንዛሪ ኢትዮጵያ እያዳነች መሆኑ ታወቀ፡፡

እ.ኤ.አ. ከ2014 ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ቀድሞ ከነበረበት ዋጋ 50 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱ ይታወቃል፡፡ በ2014 አንድ በርሜል ነዳጅ ይሸጥ ከነበረበት 114 ዶላር በከፍተኛ መጠን በማሽቆልቆል እስከ 50 ዶላር ድረስ ወርዷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪውን የሚያውለው ለነዳጅ ምርት ግዥ ሲሆን፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመቀነሱ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ወጪ እያዳነች መሆኑን ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የንግድ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ለምሳሌ በ2007 ዓ.ም. አገሪቱ ከነበራት የውጭ ምንዛሪ ለነዳጅ ወጪ የተደረገው 68 በመቶ ያህሉ ነው፤›› በማለት ይገልጻሉ፡፡ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2007 ዓ.ም. ሦስት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ የገዛ ሲሆን፣ ለዚህ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በዚህ ሥሌት አገሪቱ በወቅቱ የነበራት አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ክምችት 4.2 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡

በ2008 ዓ.ም. የዓለም የነዳጅ ዋጋ መረጋጋቱን በመቀጠሉ ለነዳጅ ወጪ የተደረገው፣ አገሪቱ በወቅቱ ከነበራት የውጭ ምንዛሪ ክምችት 47 በመቶ ያህሉን እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ወቅት የነበረው የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ቀደም ሲል ከነበረበት በአንድ ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በየዓመቱ ማዳን የተቻለውን የውጭ ምንዛሪ ሲያስቀምጡም፣ ‹‹በ2008 20.1 በመቶ፣ በ2009 እስከ 30 በመቶ ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

መንግሥት በነዳጅ ዋጋ መረጋጋት ያገኘውን ጥቅም ለደመወዝ ጭማሪ የተጠቀመ ሲሆን፣ አብዛኛውን የወሰደው ግን በአገሪቱ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው የድርቅ አደጋ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመርዳት ነው፡፡

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles