Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

የደን ዘርፍ ኢንቨስትመንት አናሳ መሆን ከውጭ ለሚገቡ የእንጨት ውጤቶች መበራከት አስተዋጽኦ እያደረገ ነው

$
0
0

 

- በየዓመቱ 350 ሺሕ ቶን ወረቀት ከውጭ ይገባል

ባለሀብቶች በደን ዘርፍ ውስጥ የሚያደርጉት ተሳትፎ አናሳ በመሆኑ፣ ከውጭ የሚገቡ ልዩ ልዩ የደን ውጤቶች ምርት በየጊዜው እየጨመረ ሲመጣ በአንፃሩ የአገር ውስጥ ምርቶች እየቀነሱ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

 በገበያ ተኮር የደን ውጤቶችና በእንጨት ማቀናበሪያ ኢንዱስትሪዎች ልማት ዙሪያ መጋቢት 23 ቀን 2009 ዓ.ም በተዘጋጀው የግሉ ዘርፍ የምክክር መድረክ ወቅት፣ ባለሀብቶች የደን ሀብትን በመጠቀም እያደገ ከሚገኘው የእንጨት ፍላጎትና የአገሪቱ ተጠቃሚነት አኳያ የሚታየው ክፍተት እያደገ መጥቷል፡፡ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ የእንጨት ውጤቶች ፍላጎት እየጨመረ ከመምጣቱም ባሻገር የከተሞች መስፋፋት፣ የግንባታ ሥራዎች መስፋፋት እንዲሁም ከአገር ውስጥ ምርቶች ይልቅ ለውጭዎቹ ምርቶች ያለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ፣ የአገሪቱ የደን ሀብት በሚፈለገው መጠን ጥቅም ላይ እንዳይውል ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገልጿል፡፡

በዚህ ምክንያት ከውጭ ለሚገባው የእንጨት ምርት በዓመቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሶ፣ በተለይም ካቻምና በተደረገ ጥናት በዓመት ከ182 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጓል ተብሏል፡፡

የደን ባለሙያው ሙሉጌታ ልመን (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ የአገር ውስጥ የእንጨት ምርት ፍላጎት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ባለሀብቶች በዘርፉ ቢሰማሩ ፍላጎትን ከሟሟላት አልፈው ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ማመንጨት የሚችሉበት የደን ሀብት በስፋት አገር ውስጥ ይገኛል፡፡ ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመቀነስ ደን ማልማት ትልቅ አማራጭ እንደሆነ ባለሙያው አስታውቀው፣ በየዓመቱ የሚገባውን ከ350 ሺሕ ቶን በላይ የወረቀት ምርት መቀነስ እንደሚቻል ለሪፖርተር አብራርተዋል፡፡ በአንፃሩ ኢንቨስተሮች ዘርፉን እንዳይቀላቀሉ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችም በመድረኩ ተነስተዋል፡፡

በ2007 ዓ.ም. የወጣው አዋጅ በዘርፉ የባለሀብቶችን ተሳትፎ የሚደገፍ ቢሆንም በኢንቨስትመንት ለመሠማራት ሲፈለግ፣ የመሬት አቅርቦት፣ የሕግ አፈጻጸም እንዲሁም የፋይናንስ ጉዳዮች ዋንኛ ችግሮች ሆነው እንደሚቀርቡ ተጠቅሷል፡፡ በዘርፉ በሰፊው ለመሠማራት የ310 ሺሕ ሔክታር መሬት ለኢንዱስትሪ ደን ልማት የሚውል መሬት መካለል እንደሚኖርበት ተገልጾ፣ የሚጠይቀው የኢንቨስትመንት መጠንም በጠቅላላው 356 ዶላር እንደሚገመት አቶ ሙሉጌታ በውይይቱ ወቅት አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም ወደ ማልማቱ ሥራ የሚገቡ ባለሀብቶች ለ78 ሺሕ ኢትዮጵያዊያን የሥራ ዕድል እንደሚፈጠሩ፣ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች የደን ውጤቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማመንጨት እንደሚቻል ተብራርቷል፡፡ ይሁንና እስካሁን ለሱዳንና ለደቡብ ሱዳን 26,260 ሜትር ኩብ የደንና የእንጨት ውጤቶች መላክ እንደተቻለ ታውቋል፡፡

በአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ የሚኒስትሩ ተወካይ አቶ ግርማቸው ሥዩም እንዳብራሩት፣ በ2007 ዓ.ም.  የወጣውን የደን ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችለውን አዋጅ ማሻሻል እንደሚያስፈልግ፣ የግሉን ዘርፍ በማጠናከር ፍላጎትና አቅርቦትን ለማጣጣም እንዲቻልም ባለሀብቶች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ድጋፍ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

የዘርፉ ተዋናዮችና ባለሀብቶች የታክስ፣ የመሬት አቅርቦት፣ የፋይናንስ ችግሮችን ጨምሮ በኢትዮጵያ በሚገኙት ደኖች ላይ የባለቤትነት ጉዳይ እንዲሁም የደን ውጤቶችን በሚያቀነባብሩ ፋብሪካዎች ግንባታ ላይ የሚታዩ ችግሮች እንዲቀረፉላቸው ሲጠይቁ ተደምጠዋል፡፡ የደን ሀብትን ለግንባታ ሥራዎችና ለኃይል ፍጆታነት ከመጠቀም ባሻገር ዛፎችንና ልዩ ልዩ ዕፅዋትን ለመድኃኒትነት ማዘጋጀነት በአገሪቱ የተለመደ ተግባር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት፣ ከ6,600 በላይ የዕፅዋት ዝርያዎች እንዳሉ ከእነዚህም ውስጥ 1/5ኛው በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡

በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ 420,000 ካሬ ኪሎ ሜትር ወይንም 35 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ መሬት በደን የተሸፈነ ነበር፡፡ በቅርቡ በዘርፉ የተከናወኑ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን፣ በሕዝብ ቁጥር መጨመርና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ የደን ሽፋኑ ወደ 15.93 በመቶ አሽቆልቁሎ ይገኛል፡፡ ይህ አኃዝ ግን በቅርብ በተደረገ ጥናት የተሻሻለ በመሆኑ እንጂ በዝርው ሲነገር የቆየው የደን ሽፋን መጠን ከሦስት በመቶ እንደማይበልጥ ነበር፡፡

የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2001 ባወጣው ትርጓሜ መሠረት የደን ሀብት ተብለው ሊቆጠሩ ከሚችሉና በኢትዮጵያ ከሚገኙ የዕፅዋት ዝርያዎች መካከል አነስተኛ ደኖች ወይም ጫካዎች፣ ቀርከሃና ሌሎች ተክሎች የሚካተቱ ሲሆኑ፣ 35.15 ሚሊዮን ሔክታር መሬት እንደሚሸፍኑም ይገመታል፡፡

የዓለም የምግብና የእርሻ ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2007 ባጠናው ጥናት መሠረት፣ እ.ኤ.አ ከ1973 እስከ 1990 በነበሩት ዓመታት ውስጥ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን መጠን ከ54,410 ወደ 45,055 ካሬ ኪሎ ሜትር ዝቅ ማለቱን፣ ይህ መጠን በየዓመቱ ሲለካም በ1410 ካሬ ኪሎ ሜትር በሚደርስ አስደንጋጭ መጠን መቀነሱን ጥናቱ ማመላከቱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የደን ዘርፍ ምልከታ ጥናት እንደሚያሳየው፣ የኢትዮጵያ አጠቃላይ የደን ምርት ፍላጎት በ2033 ዓ.ም. 215.8 ሚሊዮን ሜትር ኩብ እንደሚደረስ ሲገመት፣ ጥናቱ ከተካሄደበት እ.ኤ.አ ከ2013 መነሻ በማድረግ ሲሰላም የ42 በመቶ ጭማሪ እንደሚኖር ተገምቷል፡፡

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles