Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all 720 articles
Browse latest View live

እያገገመ ከሚገኘው ቱሪዝም ዘርፍ የ2.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኘ

$
0
0

 

  • በዓመቱ የ3.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይጠበቅበታል

በአገሪቱ በተከሰተው ፖለቲካዊ ትኩሳት ምክንያት በውጭ ጎብኝዎች መቀነስ ችግር ውስጥ የገባው የቱሪዝም ዘርፍ፣ በማገገም ላይ እንደሚገኝና በሦስተኛው ሩብ ዓመት የተመዘገበው የቱሪስት ፍሰት ከቀደሙት ስድስት ወራት አኳያ ጭማሪ እንዳሳየ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ የዘጠኝ ወራት አፈጻጸምን በማስመልከት ለጋዜጠኞች ይፋ ባደረጉት መረጃ መሠረት፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተመዘገበው የቱሪስቶች ቁጥር 686223 እንደሆነ ታውቋል፡፡ በሦስተኛው ሩብ ዓመት ብቻ የተመዘገው የቱሪስቶች ቁጥር 246869 ሲሆን፣ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 233032 እንዲሁም በሁለኛው ሩብ ዓመት 206327 ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ተወስቷል፡፡

ምንም እንኳ የዘጠኝ ወራት አጠቃላይ የዘርፉ አፈጻጸም ከመጀሪያዎቹ ስድስት ወራት አኳያ ሲታይ ለውጥ አሳይቷል ቢባልም፣ ከዓምናው ተመሳሳይ የዘጠኝ ወራት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ግን ቀንሶ መገኘቱን አቶ ገዛኸኝ ይፋ አድርገዋል፡፡ በተለይም በመጀሪያዎቹ ሁለት የሩብ ዓመታት ወቅት ዘርፉ ከዜሮ በታች (-) 8.25 በመቶ ማስዝገቡ ሲጠቀስ፣ በሦስተኛው ሩብ ዓመት ግን ዕድገቱ ተሻሽሎ የ5.8 በመቶ ዕድገት ማሳየት እንደቻለ ተገልጿል፡፡ ይሁንና ካለፈው ዓመት ዘጠኝ ወራት አኳያ የ3.64 በመቶ ወይም የ25888 ጎብኝዎች ቅናሽ መመዝገቡን ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአሁ ወቅት በየወሩ ከ76 ሺሕ በላይ ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ያመላከቱት አቶ ገዛኸኝ፣ በዚህ ዓመት የሚጠበቀው የቱሪስት ቁጥር አንድ ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ መታቀዱን አስታውሰዋል፡፡ ይሁንና ከመስከረም እስከ ጥር ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው የጎብኚዎች ቁጥር የሚመዘገብበት ወቅት ሲሆን፣ በተለይ መጪው ጊዜ ክረምት እንደመሆኑ መጠን የታቀደውን መጠን ማሳካት መቻሉ አጠራጥሯል፡፡

ሚኒስቴሩ በሚከተለው ስሌት መሠረት አንድ ቱሪስት ወደ ኢትዮጵያ በሚመጣበት ወቅት በአማካይ 16 ቀናት ቆይታ በማድረግ በትንሹ 234 ዶላር ወጭ እንደሚያደርግ ይታሰባል፡፡ በዚህ ስሌት መሠረት እንዲሁም ወደ አንድ ሚሊዮን ቱሪስት (ለትራንዚት የሚመጣውን ጨምሮ፣ ለስብሰባና ለመዝናናት የሚመጡትን ያካትታል) እንደሚመጣ ታሳቢ በተደረገው መሠረት፣ በዓመቱ ሊገኝ የሚችለው ጠቅላላ የዘርፉ ገቢ ከ3.74 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ ባለፈው ዓመት ከ800 ሺሕ በላይ ቱሪስቶች አገሪቱን ጎብኝተው ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ ገቢ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

በአገሪቱ በተከሰቱ ፖለቲካዊ ቀውሶች ምክንያት ችግር የገጠመው ይህ ዘርፍ፣ በተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና በብሔራዊ ፓርኮች ላይ በደረሰው ጉዳት በተለይም አገሮች ባወጧቸው የጉዞ ክልከላዎችና ማሳሰቢያዎች ሳቢያ መቀዛቀዝ ሲያሳይ መቆየቱ ይጠቀሳል፡፡

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች የዘርፍ ማኅበር በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ በሆቴሎች የተለመደው የመኝታ ክፍሎች ይዞታ በአማካይ 67 በመቶ እንደነበር፣ ይሁንና በቀውሱ ሳቢያ የ20 በመቶ ቅናሽ መመዝገቡን ማኅበሩ አስታውቋል፡፡ ይኸው ቅናሽ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ባለበት መቀጠሉን የጠቀሰው ማኅበሩ፣ በዚህ ሳቢያም የ380 ሚሊዮን ብር ኪሣራ ሆቴሎች እንዳጋጠማቸውና መንግሥትም ይህንን ኪሳራቸውን የሚሸፍኑበት ወይም የሚያካክሱበት መፍትሔ እንዲፈልግላቸው እንደጠየቁ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

ርብርቦሽ ሲደረግ መቆየቱን፣ ዘርፉ በቀውስ ውስጥ እንደመሆኑ መጠን ቀውሱን የማብረድ ዕርምጃዎች ሲወሰዱ እንደነበር አቶ ገዛኸኝ ጠቅሰዋል፡፡ ምንም እንኳ የተወሰዱ ዕምጃዎችና ሲደረጉ የቆዩ እንቅስቃሴዎች ለውጥ አምጥተዋል ቢባልም የሚፈለገውን ያህል ለውጥ እንዳልመጣ ተናግረዋል፡፡

በቱሪዝም መስክ ከተወሰዱ ዕርምጃዎች መካከል ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ያደረጓቸው ሹም ሽሮች ይጠቀሳሉ፡፡ በሚፈለገው ደረጃ ለውጥ አላመጡም የተባሉት የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለሥልጣን ኃላፊዎች ተነስተው በምትካቸው አዳዲስ ኃላፊዎች መተካታቸው ይታወሳል፡፡

 

Standard (Image)

በደኅንነትና በጥበቃ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያነጣጠረ ዓውደ ርዕይ ሊካሄድ ነው

$
0
0

 

በተለያዩ የንግድና የሚንቀሳቀሱባቸውን የአገልግሎት ዘርፎች ለይተው በመዘጋጀት ላይ ከሚገኙ ዓውደ ርዕዮች መካከል አንዱ የሆነው የደኅንነትና የጸጥታ ትርዒት ነው፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ሴፍቲ ኤንድ ሴኩሪቲ ኤክስፖ 2009፤›› በሚል መጠሪያ የሚካሄድ አዲስ የንግድ ትርዒት ዝግጅት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

በደኅንነትና በጥበቃ አገልግሎት መስክ እንዲሁም የአገልግሎቱ ግብዓት አቅራቢዎችን ታሳቢ በማድረግ የሚጋጀው ይህ የንግድ ትርዒትና ባዛር ከሰኔ 22 እስከ 24 2009 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የንግድ ትርዒቱ አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡

የንግድ ትርዒቱን ለማካሄድ ዝግጅት እያደረገ ያለው ቤታሆን አድቨርታይዚንግና ኢቨንት ዝግጅት የተባለ ኩባንያ ሲሆን፣ የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ማንአክሎት እንደገለጹት የንግድ ትርዒቱ ከደኅንነትና ከጥበቃ አገልግሎት ጋር የተያያዘ አገልግሎት ከሚሰጡ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር በትብብር የሚቀርብ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ እንዲህ ዓይነት የንግድ ትርዒት ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ የንግድ ትርዒቱ አዘጋጆች እንደገለጹት፣ በንግድ ትርዒቱ ላይ በጠቅላላው ከ100 ያላነሱ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እንደ አቶ ካሳሁን ገለጻ፣ ይህንን ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት ከተነሳሱበት ምክንያቶች አንዱ በአገሪቱ ከሚካሄዱት የልማት እንቅስቃሴዎች አንፃር ደኅንነታቸው በአስተማማኝ ደረጃ የተጠበቀ እንዲሆን የማድረግ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ፡፡ እንዲህ ያሉትን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍና ይበልጥ ዘመናዊነት እንዲላበሱ ለማድረግ የሚያስችል አሠራር እንዲሰርጽ፣ የደኅንነትና የፀጥታ ተግባራት ላይም ግንዛቤ እንዲስፋፋ ለማገዝ ሲባል የሚሰነዳ ዓውደ ርዕይ ነው ብለዋል፡፡

በንግድ ትርዒቱና ባዛሩ ወቅት በዘርፉ የሚመረቱና ለአገልግሎት የሚቀርቡ ልዩ ልዩ ምርቶችን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ ተገበያዮች ግብይት የሚፈጽሙበትን መድረክ ማመቻቸትንም ያጠቃልላል፡፡ በዓውደ ርዕዩና ባዛሩ ወቅት የሚሳተፉ ድርጅቶች፣ ከአውሮፓ ኪንግደም፣ ከእስያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ እንዲሁም ከአፍሪካ አኅጉራት የሚውጣጡ ሲሆን፣ በጥቅሉ ከ23 አገሮች የተውጣጡ ኩባንያዎችና በዘርፉ የሚታወቁ ከ50 ያላነሱ ባለሙያዎችም ይሳተፋሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በሙያው ውስጥ የሚገኙ ከ50 ያላነሱ ተሳታፊዎች ስለ ኢንዱስትሪው ወቅታዊ ጉዳዮችና ስለመሳሰሉት ይዘቶች በመነጋገር የልምድ ልውውጥ ያደርጋሉ ተብሏል፡፡

የሴፍቲ ኤንድ ሴኩሪቲ ኤክስፖ 2009 ሲካሄድ ዋናው ዓላማ በጥበቃና በደኅንነት ዙሪያ ኢትዮጵያ ምን ደረጃ ላይ እንደምትገኝ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ኤምባሲዎች፣ ከፍተኛ የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ የንግዱ ዘርፍና የማኅበረሰቡን ሁኔታ ያገናዘበ የደኅንነትና የጥበቃ ትኩረት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል በሚሉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በዘርፉ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ማካሄድን ያካተተ ተልዕኮ ያለው መድረክ እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡

ሴፍቲ ኤንድ ሴኩሪቲ በዋናነት አገልግሎት የሚሰጥባቸው መንገዶች በሰው ኃይል፣ በኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ በእንስሳት በመሳሰሉት አማካይነት ሲሆን፣ ሳይንስና ዘመናዊነት እያደገ በመምጣቱ ከዚህ ቀደም በሰዎችና በእንስሳት ላይ በአብዛኛው ጥገና የነበረውን አሠራር የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች በአብዛኛው ተመራጭ እየሆኑ በመምጣታቸው እነዚህን ምርቶች በሚገባ ለማስተዋወቅ ይረዳል ተብሏል፡፡ በንግድ ትርዒቱ ላይ ኤክስሬይ (የሰውነት መፈተሻ መሣሪያ) ስክሪኒንግ (የዕቃ መፈተሻ) የተሽከርካሪ መፈተሻ፣ ሲስተም ማዛመቻ ወይም አንዱን ከሌላው ማሰባጠሪያ (ሲስትም ኢንተግሬሽን) ልዩ ልዩ መስሎችን ቀርፀው የሚያስቀሩ የደኅንነት ካሜራዎች፣  የኤሌክትሪክ አጥርና ሌሎችም የደኅንነትና የጥበቃ ማሽነሪዎችን የሚያመርቱ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የእሳት አደጋ ሲከሰት ማሳወቂያና መከላከያ፣ እሳት የማይደፍረው በርና መስኮት፣ ጥይት የማይበሳው መስታወት፣ በርና መስኮት ልዩ ልዩ ሳይንሳዊና ዘመናዊ የጥበቃ መሣሪያዎች አምራችና አቅራቢዎችንም ያጠቃለለ ዓውደ ርዕይ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የሴፍቲና የሴኩሪቲ ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ ነው ያሉት ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፣ የደኅንነት ጉዳይ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ዘመናዊ አገልግሎትንና ተደራሽነቱን ለማስፋት የመንግሥት አካላትን ኅብረተሰቡና የዘርፉን ባለድርሻ አካላት ለማገናኘት ጭምር ታስቦ ነው፡፡ በዘርፉ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋትም ኤግዚቢሽኑ የበኩሉን ሚና ይጫወታል የሚለውን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ሴፍቲ ኤንድ ሴኩሪቲ ኤክስፖ 2009›› የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች፣ ቴክኖሎጂውን በሕጋዊነት የሚጠቀሙበትንና ለኅብረተሰቡ የሚያስተዋውቁበት የሴኩሪቲ ሴፍት ቴክኖሎጂ ለሚፈልጉ በቀላሉ በርካታ የምርት አማራጮች የሚቀርቡበት መድረክ ይሆናል፡፡ ይህ የንግድ ትርዒት በቋሚነት ከደኅንነትና ከጥበቃ አገልግሎት ጋር የተያያዘ አገልግሎት ከሚሰጡ መንግሥታዊ ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰነዳ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ 

Standard (Image)

ሊፋን ሞተርስ ለሜትር ታክሲዎች የጥገና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ከፈተ

$
0
0

በአዲስ አበባ የሜትር ታክሲዎችን ከቀረጥ ነፃ በማስገባት ለሚንቀሳቀሱ ባለንብረቶች የሽያጭ አገልግሎት የሰጠው የቻይናው ሊፋን ሞተርስ ኩባንያ፣ እስካሁን ለሸጣቸው 825 ሊፋን ሥሪት ሜትር አገልግሎት ድኅረ ሽያጭ የጥገና አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ይፋ አድጓል፡፡

በያንግፋ ኩባንያ ሥር የሚተዳደረው ሊፋን ሞተርስ ሊፋን ሥሪት ሜትር ታክሲዎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ከአንድ ዓመት በፊት ለሽያጭ ያዋለ ሲሆን፣ ለሊፋን ሜትር ታክሲዎች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የጥገና ማዕከል ይፋ ያደረገው ትናንት ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ወቅት ነበር፡፡

በአንድ ጊዜ እስከ 50 ተሽከርካሪዎች ያስተናግዳል የተባለው አዲሱ የጥገና ማዕከል ሲመረቅ እንደተገለጸው፣ የሜትር ታክሲዎች ከዚህ ቀደም ሲያረቀቡት የነበረውን የጥገና አገልግሎት ዕጦት ቅሬታ ሊፈታላቸው እንደሚያስችል ታምኖበታል፡፡

አዲሱ የጥገና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ለሚቀርቡለት የአገልግሎት ጥያቄዎች ተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚጠይቅም የኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተናግረዋል፡፡

በምረቃ ሥርዓቱ ወቅት ከ18ቱ የሜትር ታክሲ ማኅበራት የተውጣጡ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፣ የጥገና አገልግሎቱን በማስመልከት ከዚህ ቀደም ያጋጠማቸውን ችግር እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከሜትር ታክሲዎች ማኅበራት ጋር በመነጋገር ሲፈጠሩ የነበሩ ክፍቶችን ለመሙላት ሲሠሩ እንደቆዩም በዕለቱ ከተደረገው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የኩባንያው ኃላፊዎችም ከጥገና አገልግሎት ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የነበሩ ችግሮች እንደማይደገሙ ቃል ገብተው፣ በአዲሱ ማዕከል ስለሚሰጧቸው አገልግሎቶችም በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

ከሜትር ታክሲዎች ባለንብረቶች በቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ ለሜትር ታክሲዎች አገልግሎት ብቻ የሚውል የጥገና ማዕከል የተከፈተው ታክሲዎቹ ለጥገና ሲመጡ መዘግየት እንዳይፈጠርና በፍጥነት ለማስተናገድና የሚፈለገውን አገልግሎት ሰጥቶ በአፈጣኝ ወደ ሥምሪት እንዲመለሱ ለማስቻል ጭምር እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡ ይህ የጥገና ማዕከል ከ825 የሊፋን ሜትር ታክሲዎች በተጨማሪ በቅርቡ ርክክብ የሚፈጸምባቸውን 40 የሜትር ታክሲዎችም የጥገና አገልግሎት እንዲያገኙ በማሰብ የተደራጀ ነው፡፡ የሊፋን ሞተርስ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ማርክ ቹ እንደገለጹት፣ በኢትዮጵያ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ውስጥ ሊፋን የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እየጎላ መጥቷል፡፡ እስካሁን ለገበያ ሲያቀርባቸው ከቆዩ አገልግሎቶች በተጨማሪ ለሜትር ታክሲዎቹ እንዲውል ያስገነባው ማዕከልም ለሚያደርገው እንቅስቀሴ አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

ከመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት አኳያ ለቀረበው ጥያቄ፣ ኩባንያው በቂ መለዋወጫዎችን  እንዳቀረበና የአቅርቦቱን ሥራ ሌሎች  ተቋማትም  እንዲሳተፉበት  ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ አገልግሎቱን የሚሰጡ የመለዋወጫ ዕቃ አቅራቢዎች ወደ ገበያ እስኪገቡ ድረስ ግን ያንግፋ ማቅረቡ እያቀረበ ይቀጥላል፡፡

እንደ ኩባንያው የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ ሊፋን ሞተርስ ለጥገና አገልግሎት  የሚጠቀምበትን ቦታ ከግለሰቦች በመከራየት የመሠረተው ነው፡፡ ሆኖም አገልግሎቱን የበለጠ ለማድረግ ዋና መሥሪያ ቤቱን ጨምሮ የጥገና፣ የማሳያ ማዕከል እንዲሁም የሽያጭ ሥራዎችን አንድ አጠቃልሎ የሚይዝ ሕንፃ ለመገንባት ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ዕውን እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት 11 የተለያዩ ሞዴል ያላቸው የሊፋን መኪኖች በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ኩባንያው በሺዎች የሚቆጠሩ መኪኖችን በአገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ ይገኛል፡፡ በዱከም ከሚገኘው የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን የመገጣጠሚያ ፋብሪካውን በመመሥረት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሊፋን ሞተርስ፣ ወደ ውጭ ገበያ የመግባት ፍላጎት እንዳለውና ኢትዮጵያ ውስጥ የገጣጠማቸውን መኪኖች ለጎረቤት አገሮች የማቅረብ ውጥን እንዳለው መግለጹ ይታወሳል፡፡

በአገር ውስጥ በገጠመው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ያሰበውን ያህል መሥራት እንዳልቻለ ደጋግሞ ሲገልጽ የቆየው ኩባንያው፣ ባገለገሉ መኪኖች የተያዘው ገበያም አሳሳቢ እንደሆነበት መጥቀሱ አይዘነጋም፡፡ በኢትዮጵያም ሆነ በምሥራቅ አፍሪካ በተለይም በኬንያ በብዛት የሚነዱት ያገለገሉ መኪኖች መሆናቸው እንደ ሊፋን ላሉ አምራቾች የገበያ ድርሻን እየተሻሙ ማሽቸገራቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ይደመጣል፡፡

      በአንጻሩ በአገር ውስጥ የሚገጣጥሙ ኩባንያዎች ከውጭ ሙሉ በሙሉ ተገዝቶ ከሚገባው አዲስ መኪና አኳያ ብዙም የዋጋ ልዩነት አለማሳየታቸው እያስተቻቸው ይገኛል፡፡ አብዛኞቹም መጠነኛ የታክስ ማበረታቻን ጨምሮ ልዩ ልዩ ድጋፎች ቢደረጉላቸውም የሚፈለገውን ያህል የዋጋም ሆነ የገበያ ልዩነት ማሳየት አለመቻላቸው፣ ተፈላጊነታቸው ላይ ተፅዕኖ እንዳሳደረ ይታመናል፡፡ 

Standard (Image)

የተቀዛቀዘ የኢኮኖሚ ዕድገት ከ550 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦችን ወደ ተባባሰ የድህነት አዘቅት ሊጥል እንደሚችል ተመድ ይፋ አደረገ

$
0
0
  • የደሃ አገሮችን የልማት ጥያቄዎች ለማሟላት በዓመት እስከ ሦስት ትሪሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ የተስተናገደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፋይናንስ ለልማት ጉባዔን ወቅታዊ ሁኔታ የገመገመው የተመድ ግብረ ኃይል፣ ድህነትና ረሃብ ከዓለም ይጠፋሉ ተብለው በሚጠበቁበት እ.ኤ.አ. በ2030 ከ550 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦች ለዚሁ ችግር ተጋላጭ ሊሆኑ የሚችሉበት አዝጋሚ የኢኮኖሚ ዕድገት እየተመዘገበ መሆኑ ሥጋት እንዳሳደረበት ተመድ ይፋ አድርጓል፡፡

ድህነት ከዓለም እንደሚጠፋ ተስፋ በሚደረግበት ወቅት ከግማሽ ቢሊዮን በላይ ሕዝቦች በድህት አረንቋ ውስጥ ለመኖር እንደሚገደዱ ሥጋቱን የገለጸው ተመድ፣ በሥሩ የሚገኙ ኤጀንሲዎችን በማስተባበር፣ ግብረ ኃይል አቋቁሟል፡፡ የበይነ ኤጀንሲዎቹ ሪፖርት እንደሚያመለክተው በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሕዝቦች በድህነት አረንቋ ውስጥ መውደቅ ሰበብ እንደሚሆን የተፈራው የዓለም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከዓመት ዓመት አዝጋሚነቱ በመባባሱ ነው፡፡

በተመድ የዚህ ዓመት የፋይናንስ ለልማት ሪፖርት መሠረት ታዳጊ አገሮች እጅጉን ተጎጂዎች ከሚባሉት ውስጥ እንደሚመደቡ ሥጋት ፈጥሯል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ ተቋም (UNCTAD) ምደባ መሠረት ከ44 ያህል ያለደጉ ወይም በማደግ ላይ ካሉ አገሮች ውስጥ ከ30 በላይ የሚገኙት በአፍሪካ በመሆኑ፣ በእነዚህ አገሮች ውስጥ የሚታየውን ዘገምተኛ ለውጥ ይበልጥ ሊጎዳው እንደሚችል ተመድ ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ አስፍሯል፡፡ በትንበያዎች መሠረት በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ውስጥ ይኖራል ተብሎ የሚጠበው የዓለም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከሦስት በመቶ አይልጥም፡፡ የዓለም ንግድ እየተቀዛቀዘ መምጣጡ ደግሞ በሸቀጦች ዋጋ መውደቅ ሲደቆሱ የቆዩትን ደሃ አገሮች ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚጥል ከመፈራቱም ባሻገር፣ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጓዝበት ከመጣው የሁለት በመቶ አማካይ ዓመታዊ ዕድገት በተጨማሪ ካቻምና የአሥር በመቶ ቅናሽ ማስመዝገቡም ሥጋቱን አባብሶታል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ አገሮች የቱንም ያህል ድህነትን ለመዋጋት ቢነሱ፣ ለዚሁ የሚረዱ እንቅስቃሴዎችን ቢያደርጉ፣ ሉላዊነትን መሠረት ያደረጉ ለውጦችና የቴክኖሎጂ ዕድገቶች ቢመዘገቡም፣ አሁንም ግን የምግብ ዋስትና ችግር፣ የውኃ አቅርቦት እጥረት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ግጭቶችና ሌሎችም ግዙፍ ፈተናዎችን ለውጦችን እየተገዳደሩ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

ካቻምና አዲስ አበባ ያስተናገደችውን ሦስተኛውን ፋይናንስ ለልማት ጉባዔን መነሻ ያደረገው የተመድ ሪፖርት፣ ከጉባዔው ወዲህ የታዩትን ለውጦች የሚፈትሽ ነው፡፡ በአዲስ አበባው ጉባዔ ወቅት 17ቱን የተመድ ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት፣ ብሎም የመሠረተ ልማት ችግሮችን ለመቅረፍ እስከ 1.5 ትሪሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ይፋ ተደርጎ ነበር፡፡ ይህ ገንዘብ ባላደጉት አገሮች ውስጥ ብቻ የሚታየውን ክፍተት የሚጠቁም ሲሆን፣ በመላው ዓለም ያለው የመሠረተ ልማቶች አለመሟላት ችግር ከሦስት እስከ አምስት ትሪሊዮን ዶላር ይገመታል ይላል፡፡

በመሆኑም እንዲህ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት አስቸኳይ የረዥም ጊዜ ኢንቨስትመንት እንዲደረግ የሚጠይቀው ተመድ፣ የዓለም የኢኮኖሚ መቀዛቀዝን ሊያነሳሱ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች እንዲደረጉ አሳስቧል፡፡

ከአምስት ሺሕ በላይ ታዳሚዎች የተገኙበት የካቻምናው የአዲስ አበባ የፋይናንስ ለልማት ጉባዔ፣ እ.ኤ.አ. እስከ መጪው 2030 ድረስ የሚዘልቁት የልማት አጀንዳዎች ይፋ የተደረጉበት፣ 17ቱን የልማት ግቦች ለማስፈጸምም የሚጠይቀው የፋይናንስ መጠን በድብስብሱ እስከ ሦስት ትሪሊዮን ዶላር መሆኑ የተገለጸበት ነበር፡፡ ከዚህ ባሻገር በስብሰባው ወቅት ድሆች ወይም ታዳጊ አገሮች ራሳቸውን መደጎም እንዲጀምሩ የተጠየቀበት መድረክ እንደነበርም ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ከፍተኛ ታቃውሞ በተደመጠባቸው፣ የዓለም የሲቪክ ማኅበራት ድምፃቸውን ካሰሙባቸው ነጥቦች መካከልም ያደጉ አገሮች ኩባንያዎች በታዳጊ አገሮች ላይ የሚያደርሱት የታክስ ማጭበርበር፣ የትርፍ ማሸሽ ተግባራት እንዲሁም የገንዘብ ስወራ ወንጀሎች መፍትሔ እንዲሰጥባቸው የጠየቁበት አግባብ ይታወሳል፡፡

በትልልቅ ድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎች አማካይነት ከአፍሪካ አገሮች በዓመት እስከ 70 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ እንደሚሸሽ ጥናቶችን ይጠቁማሉ፡፡ በቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ተቦ ምቤኪ የሚመራው የአፍሪካ ከፍተኛ ፓነል፣ በዚሁ በድንበር ተሻጋሪ ኩባንያዎች አማካይነት ከአፍሪካ አሥር ዋና ዋና አገሮች እየተሰወረ እንደ ስዊዝ ባንክ ባሉ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት የሚጋዘው ገንዘብ በትንሹ ከ70 እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር ይገመታል፡፡ ከአሥሩ ዋና ዋና ተጠቂ አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ የምትመደብ ሲሆን፣ በየዓመቱም እስከ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ በኩባንያዎች አማካይነት እያጣች እንደምትገኝ የፓናሉ ጥናታዊ ሪፖርት አመላክቷል፡፡

እንዲህ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ ተመድ ጥብቅ አሠራሮችን መከተል እንደሚገባው የሲቪክ ማኅበራቱ ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳ በተመድ ሪፖርት መሠረት ለታዳጊ አገሮች የልማት ጥያቄዎች ሦስት ሚሊዮን ዶላር ያህል ገንዘብ ያስፈልጋል ቢልም፣ እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳንና የመንን የመሳሰሉ ያሉ ከፍተኛ የድርቅ እንዲሁም የረሃብ አደጋ ያንዣበባቸው አገሮች ለደረሰባቸው የምግብ እጥረት ቀውስ ያገኙት ምላሽ ደካማ ሆኖ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ በሁለት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ከ18 ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት ቢጋለጥም፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተገኘው ምላሽ ቀዝቃዛ መሆኑ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ በዚህ ዓመት ከ7.8 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለዕለት ደራሽ ዕርዳታ በመጋለጡ ከ950 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ይፋ ተደርጓል፡፡

 

 

 

 

Standard (Image)

የመነመኑ ዛፎች

$
0
0

 

የአገሪቱ የደን ሀብት በብዛት ከሚገኝባቸው ክልሎች መካከል ኦሮሚያ ቀዳሚውን ድርሻ እንደምትይዝ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይኸው የደን ሀብት ለዘመናት ተጠብቆ ከቆየባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች አንዷ ደግሞ የጭልሞ መንደር ነች፡፡

ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴነትን የተላበሰች፣ ውኃ የማይጠማት ጭልሞ፣ እንደ ስሟ ከከራራ ፀሐይ ይልቅ ደመናማ የአየር ሁኔታ የሚበዛባት ነች፡፡ ከዚህ ሁኔታዋ ተነስተው ይመስላል ቀደምት ነዋሪዎቿ ጭልሞ ብለዋታል፡፡ በደን የተሸፈነች በመሆኗ፣ ሙቀታማ አየር የማይበግራት፣ ጨለምለም ማለቱ የሚስማማት ለመሆኗ መስካሪ ስያሜ ተላብሳለች፡፡ ከባህር ጠለል በላይ በ2,600 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ በመሆኗም ቅዝቃዜ መለያዋ ነው፡፡ ደናማ በመሆኗ ግን ብዙ ታሪክ አይታለች፡፡ በርካታ ገድሎች የተፈጸሙባት ስትሆን የደን ይዞታዋ ከአፄ ምንሊክ ዘመን በፊትም የታፈረ እንደነበር ነዋሪዎቿ በኩራት ይናገራሉ፡፡

ከአዲስ አበባ 85 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀው ጭልሞ፣ ከ500 ያላነሱ አባወራዎችንና ከ3,000 ያላነሱ ነዋሪዎችን ያስጠለለች፣ የግብርና ሥራዎች እንደ ለማምነቷ ብዙም የማይሞክሯት፣ አብዛኛው ነዋሪዋ በደን ውጤቶች ገቢ የሚተዳደርባት ስትሆን፣ እንደ ጊንጪ ያሉ ከተሞችም አጎራባቿ ናቸው፡፡

ይሁንና የጭልሞ ደን ምንም እንኳ አሁን ባለበት ሁኔታ አነስተኛ ይዞታን እንደሚሸፍን ቢነገርለትም፣ የጭልሞ ነዋሪዎች ግን ከመቶ ዓመታት በፊት የነበረውን ከፍተኛ ይዞታ ማመናመን ከጀመሩት መካከል ጣልያኖች ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ ይናራሉ፡፡

ደን አራቋቹ የእንጨት መሰንጠቂያ

አቶ አበራ ተፈስሁ፣ በጭልሞ ጋጂ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር የደን ኅብረት ሥራ ዩኒየን የቦርድ ሰበሳቢ ናቸው፡፡ እንደ አቶ አበራ ገለጻ በዘመነ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምንሊክ ጊዜ የጭልሞ ደን ይዞታ በመግሥት የሚጠበቅ፣ መጠኑም ከ22 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ያካልል ነበር፡፡ እስከ ኢሕአዴግ መግቢያ ድረስ በመንግሥት ጥበቃና ይዞታ ሥር የነበረው የጭልሞ ደን፣ ጣልያኖች ዳግመኛ በንጉሠ ነገሥት አፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ዳግመኛ ለወረራ ሲመጡ የደኑ ይዞታ ተጋላጭ ሆኗል፡፡ በ1928 ዓ.ም. ጣልያኖቹ በመጡ ጊዜ ከሰፈሩባቸው አካባቢዎች አንዷ ጭልሞ ነበረች፡፡ በዚህ ምክንያት ቀድሞ የነበረው 22 ሺሕ ሔክታር ወደ 12 ሺሕ አሽቆልቁሏል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በአካባቢው የነበሩ ጣልያኖች ጭልሞ ደን ላይ አደጋ ጣይ መሣሪያዎችን በማምጣታቸው ነው፡፡ የእንጨት መሰንጠቂያ ማሽኖች፡፡ አቶ አበራ ይቀጥላሉ፡፡

ሰባት የእንጨት መሰንጠቂዎችን በጣልያን በማስመጣት ደኑን የገዘገዙት ጣልያኖች፣ ከአምስት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የጭልሞን ደን በግማሽ ሊቀንሱት ችለዋል፡፡ ከጣልያኖች መውጣት በኋላ የደርግ መንግሥት በሕይወት የተፈረውን የጭልሞን ደን በዘበኛ ለማስጠበቅ ቢመክርም ከጥፋት ሊያድነው አልቻለም፡፡ የደን ሀብቱ እጅጉን እየተራቆተ የመጣው ደግሞ የመንግሥት ለውጥ በተደረገበት ወቅት ነበር፡፡ ደርግ ሥልጣን ለቆ፣ ኢሕኣዴግ በተተካበት በ1983 ዓ.ም. ሁሉም ነዋሪ በደን ጭፍጨፋ ተግባር ውስጥ እንደተሳተፈ አቶ አበራ ያስታውሳሉ፡፡ በመሆኑም ተመናምኖ አሁን ላይ የቀረው የደን ሽፋን መጠን 4,000 ሔክታር ላይ ቀርቷል፡፡ ይህንንም ያረጋገጠው ፋርም አፍሪካ የተባለ ግበረ ሰናይ ድርጅት በ1989 ዓ.ም. ባደረገው ጥናት እንደሆነ አቶ አበራ ጠቅሰዋል፡፡

አሳታፊ የደን ጥበቃ ጥቅሞች በነዋሪቹ ሲገለጽ

በመሆኑም በጭልሞ ደን ዙሪያ የሰፈረው ነዋሪ ደኑን ከነጭራሹ እንዳያጠፋው አሳታፊ በሆነ የደን ጥበቃ ሥራና ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ፣ ኅብረተሰብ አቀፍ አሳታፊ የደን አስተዳደር እንቅስቃሴ እንዲደረግ ፋርም አፍሪካ ሲጥር መቆየቱን አቶ አበራ አብራርተዋል፡፡ በመሆኑም 12 የደን ማኅበራት ተመሥረተው፣ ከእነዚህ ውስጥም ስምንቱ ወደ ዩኒየን አድገው ሕዝቡ ከደን ውጤቶች ተጠቃሚ የሚሆንበትን አሠራር መተግበር ጀምረዋል፡፡ ድሮ ደን የመንግሥት ነው ይባል በነበረበት ወቅት ሰው እንዳሻው ይቆርጥ የነበረውን የቀነሰው አሁን በማኅበር ተደራጅቶ ደኑ የራሱም እንደሆነ በማወቁ ነው የሚሉት አቶ አበራ፣ በመሆኑም የማኅበርና የዩኒየን አባላት፣ ነባር ያልሆኑ እንደ ባህር ዛፍ፣ የፈረንጅ ጥድ ያሉ ቋሚ ያልሆኑ ዛፎችን በማልማት እየሸጠ፣ 70 በመቶውን ለራሱ፣ 30 በመቶውን ለመንግሥት እያሰረከበ እንደሚጠቀም አብራርተዋል፡፡ ይህም ቢሆን በርካታ አሰፍስፎ የሚጠብቅ የውስጥና የውጭ ጨፍጫፊ ሲያንዣብብ ውሎ የሚያድርበት የደን መንደር በመሆኑ ሁሌም በተጠንቀቅ መጠበቅ ግድ ነው፡፡

ዛሬም ድረስ በአዲስ አበባ የሚገኙ እንደ ሰባተኛ አካባቢ ያሉ የኮርኒስ እንጨት፣ የጣውላ ዓይነቶችና ልዩ ልዩ የደን ውጤቶች የሚሸጡባቸው አካባቢዎች መነሻቸው እንደ ጭልሞ ያሉ በቅርብ ርቀት የሚገኙ የደን ሀብቶች መገኛ ሥርፍራዎች መሆናቸውን የሚጠቅሱት የአካባቢ ነዋሪዎች፣ አሁንም ድረስ በእንጨት ሥራ ላይ የተሰማሩ አካላት የደን ይዞታውን እንደሚፈታተኑት ይገልጻሉ፡፡

የሰባት ልጆች አባት የሆኑት አቶ ደጉ ወልደ ጊዮርጊስ፣ በጭልሞ አካባቢ ተወልደው ያደጉ የነበረውን የኖረውን የሚያውቁ ናቸው፡፡ እንደ አቶ አበራ ሁሉ አቶ ደጉም ሕዝብ አሳታፊ የደን አስተዳደር በመምጣቱ በደን ይዞታው ላይ የተንዣበበው አደጋ በጥቂቱም ቢሆን ጋብ እንዳለ ይናገራሉ፡፡ ደኑ በመኖሩ ምክንያት ምንጊዜም ንፁህ ውኃ እንደሚጠጡ፣ የውኃ አቅርቦትም ያለችግር እንደሚያገኙ አቶ ደጉ ይገልጻሉ፡፡ ደኑ በመኖሩ ከብቶች ያለ ችግር ዓመቱን ሙሉ ሣር ያገኛሉ፡፡ ‹‹ከብቶቻችን ምንም ባይወፍሩ እንኳ አይሞቱብንም፤›› ያሉት አቶ ደጉ፣ የደኑ ጥቅም በማኅበር በመሆን በመጠበቁ ምክንያት ሁሉም የጭልሞ ነዋሪ የሣር ቤቱን ወደ ቆርቆሮ ክዳን መለወጥ መቻሉም ከደን ተጠቃሚነቱ መገለጫዎች መካከል እንደሚመደብ ይጠቅሳሉ፡፡

ከብቶች የሚበሉት የሚጠጡት ካለማጣቸው፣ ሕዝቡም የውኃ ጥም ሳይኖርበት፣ የደርግ መንግሥት ተክሏቸው ከነበሩ የውጭ የጥድ እንዲሁም የባህር ዛፎች ሽያጭ ተጠቃሚነት፣ ሕዝቡም ችግኝ እያፈላ ከሚተክላቸውና ሲደርሱ እየቆረጠ ከሚሸጣቸው ዛፎች ባሻገር በደኑ ዙሪያ የሚገኘው የጭልሞ ነዋሪ የጓሮ አትክልቶችን እያመረተ እንደ ጊንጪ ላሉ አጎራባች ከተሞች በመሸጥ እንደሚጠቀም አቶ ደጉ አብራርተዋል፡፡ የማገዶም ችግር ጭልሞን አያውቃትም ያሉት አቶ ደጉ የደጉ ርጋፊ እንደልብ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል ብለዋል፡፡ አብዛኞቹ ነዋሪዎች ልጆቻቸውን የሚያስተምሩትም ከደኑ በሚያገኙት ጥቅም እንደሆም ጠቅሰዋል፡፡

የማኅበር አባላት ባዋጡት መጠን በየዓመቱ ስለሚያገኙት የትርፍ ድርሻ ክፍፍል አቶ አበራ ማብራሪያ አላቸው፡፡ መመዝገቢያ ከ200 እስከ 400 ብር በመክፈል ልክ እንደ አክሲዮን ማኅበር ባለ አኳኋን ድርሻ ገዝተው የሚገቡ አባላት፣ እንደ አቅማቸው የአክሲዮን ድርሻ ከመግዛት ባሻገር፣ በሚያደርጉት ተሳትፎ ማለትም በችግኝ ማፍላት፣ በደን ጥበቃ ሥራዎች፣ ማኅበራቱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሚያደርጓቸው ተሳትፎች ሁሉ እየተመዘኑ የጥቅም ድርሻቸው ተሰልቶ ይሰጣቸዋል፡፡ ዝቅተኛው 58 ከፍተኛው እስከ 200 አባላት ያሏቸው ማኅበራት በዩኒየን የታቀፉበት የጭልሞ ጋጂ ኅብረት ሥራ፣ ካቻምና 130 አባላት ላሉት ማኅበር አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሺሕ ብር መስጠቱን አቶ አበራ ያስታውሳሉ፡፡ በመሆኑም አንድ አባል በነፍስ ወከፍ በዓመት ከ12,000 እስከ 5,000 ብር የትርፍ ድርሻ የማግኘት ዕድል አለው፡፡ ከዚህም በሻገር አባላት በየጓሯቸው የፖም (አፕል) ዛፍ ተክለው ተጠቃሚ እንደሆኑም ተብራርቷል፡፡

የጭልሞ ነዋሪዎች የመሬት ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ የላቸውም የሚሉት አቶ አበራ፣ በጭልሞ ነዋሪው ደን እየጠበቀ ከላይ በነዋሪዎቹ የተብራሩትን ዓይነት ከደን የሚገኙ ተጓዳኝ ጥቅሞችን በመካፈል የሚኖር እንጂ እንደሌሎች አካባቢዎች በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ነዋሪ እንዳልሆነም ተጠቅሷል፡፡ በመሆኑም ቋሚ የሰብል እርሻ ሥራ ባይካሄድም ሌሎች ተጓዳኝ ሥራዎች ግን አልታጡም፡፡

ሥራ አጥነት የደን ህልውና አደጋ

አቶ አበራም ሆኑ አቶ ደጉ የደኑን ህልውና እየተፈታተኑ ይገኛሉ ካሏቸው ችግሮች መካከል የሥራ አጥነት ችግር ይጠቀሳል፡፡ ሥራ የሌላቸው ወጣቶች ከደኑ ጋር ቀን ተሌት ሲጋጩ ይውላሉ ያሉት አቶ አበራ፣ የገቢ ምንጭም ሆነ የሚተዳደሩበት የሌላቸው ወጣቶች ጥብቁ ደን ቢቆረጥ በውድ ዋጋ እንደሚሸጥ ስለሚያውቁም ጾም እያደሩ ደኑ ቆሞ ሲያዩት እንደሚፈታተናቸው መገመት ቀላል ነው ይላሉ፡፡ በመሆኑም ለወጣቶቹ ሥራ የሚያስገኙ እንቅስቃሴዎች ላይ መንግሥት ቢበረታ ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡

አቶ ደጉም ቢሆኑ ይኸው የወጣቶቹ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰው፣ መንግሥት እንደ ፋብሪካ ያለ፣ ወይም ወጣቶች ሥራ ሠርተው ራሳቸውን ችለው የሚኖሩበትና የሚለወጡበት ዕድል ካፈጠረ የጭልሞ ደን ከሥጋት ቀለበት እንደማይወጣ ሥጋት ገብቷቸዋል፡፡ በዚያም ላይ ደን አላግባብ የቆረጡ ሰዎች ሲያዙ ተገቢው የሕግ ውሳኔ ስለማሳጥባቸው፣ ክትትልና ድጋፉም አነስተኛ በመሆኑ በማኅበር ተደራጅተው ደኑን እየጠበቁ በሚተዳደሩ አባላት ሞራል ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አቶ ደጉ አሳስበዋል፡፡ እንዲህ ያለው አካሄድ ደግሞ ባለፈው ዓመት እንደተከሰቱ የፖለቲካ ተቃውሞች ሲነሱ ተጎጂ ከሚሆኑት መካከል ደንና በውስጡ የሚኖሩ እንስሳት በመሆናቸው ለደኑም ለነዋሪውም ህልውና ሲባል ሁሉ አቀፍ የመንግሥት ድጋፍ መደረግ እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡

የጄኔራሉ ዛፍ

በጣልያን ወረራ ዘመን ባለትልቅ ስም፣ ባለብዙ ገድለኛ መሆናቸው ከሚነገርላቸው፣ ታሪክ ከሚዘክራቸው ባለሟሎች መካከል በቅርቡ ከዚህ ዓለም የተለዩት የጄኔራል ጃገማ ኬሎ ገድል ይኖራል፡፡ በጭልሞ ከባለሟሎቻቸው ጋር የሠሩት ጀብዱ እንዲሁም ጣልያንን ያንጣጡበት ታሪክ ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ ይወራል፡፡ በጭልሞ ከ350 በላይ ባንዳዎች፣ የጣልያን ወታደሮችና አለቆቻቸው ጉድ የሆኑበት ገድል ትልቅ ሥፍራ አለው፡፡ ደራሲው ፍቅረ ማርቆስ ደስታ በጻፈው የበቃው መብረቅ በሚል ርዕሥ በጻፈው፣ የጄነራሉ የሕይወት ታሪክ ውስጥ ይኸው የጀግንነት ክራሞታቸው ተክተቧል፡፡ ይሁንና በጭልሞ ደን ውስጥ ከአናቱ በላይ የዳስ ቤት የሠሩበት ትልቁ ዋርካ አሁንም ድረስ ይገኛል፡፡ ከጥብቅ ደኑ ውስጥ ፈንጠር ብሎ የሚታየው ግዙፉና ሰልካካው ዋርካ፣ በወቅቱ አግድ የተቀሰቱበትን እንደ መሰላል መወጣጫ ያገለገሉ ፌሮ ብረቶችን እያወጣቸው ቢሆንም አሁንም ድረስ ግን ለጀግኖቹ አርበኞች ምስክር የሆነበትን አሻራ አላጣም፡፡ 

       የጭልሞ ነዋሪዎች አንድ ትልቅ ታሪክ እየተቀባበሉ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ በዕድሜ የበሰሉ አባቶች በልጅነታቸው እየወጡ ይጫወቱበት እንደነበር የሚናሩለት ዋርካ ታሪክ ከሠሩ ሰዎች ተካፋይ ስለመሆኑ ይመሰክሩለታል፡ ‹‹ጄኔራል ጃገማ ከዛፉ ላይ ሆነው አነጣጥረው በመቶክስ የጣልያን ወታደሮች መሪን ሲጥሉት፣ ተከታዮቻቸው ደግሞ እስከ አዲስ ዓለም አባረው የጣልያንን መቱት፤›› ይላሉ፡፡ የጄኔራሉ ዛፍ በአሁኑ ወቅት እስከ 280 ዓመታት የሚገመት ዕድሜ እንዳስቆጠረ በአሜካኖች የተደረገ ልኬት ይጠቀሳል፡፡ ለጄኔራል ጃገማ ኬሎ ሐውልት የማቆም እንቅስቃሴ በነዋሪው ዘንድ መጀመሩም ተሰምቷል፡፡ 

የዓለም ባንክ ድጋፍ

እንዲህ ያሉ ታሪከኛ ዛፎችን ለትውልድ ለማቆየት እንዲቻል፣ የአገሪቱ አብዛኛው የደን ሀብት በሚገኝባት ኦሮሚያ አዲስ የደን ጥበቃ ፕሮጀክት ይፋ ከተደረገ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ የዓለም ባንክ በኦሮሚያ ለተጀመረው የደን መልከዓ ምድር ፕሮግራም የ18 ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ለግሷል፡፡ በባንኩ የተፈጥሮ ሀብቶች አስተዳደር ባለሙያ ሚስተር ስቴፈን ዳኒዮ እንዳስታወቁት፣ የዓለም ባንክ የሰጠው ድጋፍ እንደ ጭልሞ ያሉ ጥብቅ ደኖችን ከጥፋት ለመከላከል ብሎም ለመጪው ትውልድም እንዲተርፉ ለማድረግ እንዲያግዝ በማሰብ የሰጠው ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዓለም ባንክን ጨምሮ፣ የኖርዌይና የአሜሪካ መንግሥት ለደን ጥበቃና ልማት ሥራዎች የሚሰጡት ድጋፍ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው የገለጹት ደግሞ በኢትዮጵያ የብሔራዊ ሬድ ፕላስ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪው ዶ/ር ይተብቱ ሞገስ ናቸው፡፡ ዶ/ር ይተብቱ እንዳሉት፣ ደን ባለባቸው አካባቢዎች የሚታዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያ እንቅስቃሴዎች ደን ከማገኝባቸው ይልቅ ለነዋሪዎቹም ለአገር ኢኮኖሚም ትልቅ ድርሻ እያበረከቱ እንደሚገኙ ያብራራሉ፡፡ ደን ያለበት ሥፍራ በአብዛኛው የውኃ አካላት የሚገኙበት፣ ተፋሰሶች ለእርሻ ሥራዎችም ሆነ ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባራት ያላቸው ሚና ሚዛን አይለካውም፡፡ ይሁንና አግባብ ያለው አጠቃቀም ሊኖር እንደሚገባም ያስጠነቅቃሉ፡፡ ደን ስላለ ብቻ እንደልብ እየጨፈጨፉ ለማገዶም፣ ለቤት ሥራም ወዘተ. መፍለጡ ደኑን ከማመናመን አልፎ የመሬት መራቆትና ለምነት እያባባሰ የሚገኝ አደጋ ነው ይላሉ፡፡ የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ አቅም በደን ሀብቷ እንደሚታገዝ የሚያምኑት ዶ/ር ይተብቱ፣ ሕዝቡ ለደን አጠቃቀም ተገቢ ግንዛቤ እንዲኖረው፣ አለአግባብ እያደገ ያለው የሕዝብ ቁጥርም መላ ሊበጅለት እንደሚገባ የሚማጸኑትም የደን ሀብት ላይ እየደረሰ ካለው ውድመት አኳያ ነው፡፡ በዚያም ላይ ‹‹የውጭ ሰዎች እንርዳችሁ ደኖቻችሁን ተንከባከቡ ሲሉን እኛም በጥበቃውና ለትውልድ በማስተላለፉ ላይ ልንጠነክር ይገባናል፤›› ብለዋል፡፡

የደን ሽፋን ሙግቶች

በአገሪቱ የተተከሉ አምስት ቢሊዮን ችግኞች እንዳሉ እነዚህንም ወደ 15 ቢሊዮን እንዲጨምሩ መንግሥት ማቀዱ ሲነገር ይደመጣል፡፡ ይሁንና ምን ያህሉ ፀደቁ? የሚለው የጠያቂው ትውልድ ሙግት የሚያረጋግጡት ግን ከሚተከሉት ውስጥ የሚጸድቁት ጥቂት መሆናቸው ነው፡፡ አንዱ ችግኝ እንደው በጥቂቱ አንድ ብር ይወጣበታል ቢባል አምስት ቢሊዮን ብር እንዲሁ ሜዳ ላይ ከስሎ ቀረ ማለት አይደለም ወይ? ይህ ገንዘብ ስንት ሥራ በሠራ ነበር የሚሉ ቆርቋሪ ጥያቄዎች ለመንግሥት አካላት ሲቀርቡም ይደመጣል፡፡

ዶ/ር ይተብቱ አበክረው እንደሚገልጹት፣ በአሁኑ ወቅት የአገሪቱ ጠቅላላ የደን ሽፋን 15.5 በመቶ እንደሆነ በተጨባጭ ሳይሳዊ ዘዴዎች ተረጋግጧል፡፡ ይሁንና ይህ መጠን ከዛሬ አሥር ዓመት በፊት ምን ያህል ነበር ብለውም ይጠይቃሉ፡፡ ሊኖር ከሚገባው ይልቅ ምን ያህል ሊቀንስ እንደቻለ ማሰቡ ይበጃል ይላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በዓመት 92 ሺሕ ሔክታር መሬት የደን ሽፋን እየተመነጠረ እንደሚገኝ በመግለጽ አገሪቱ የቱንም ያህል የደን ልማትና ክብካቤ ሥራዎችን ብትሠራም፣ አሳሳቢ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ ማሳያ እንደሆነም ይናገራሉ፡፡  በኢትየጵያ ትርጓሜ መሠረት ደን የሚባለው ግማሽ ሔክታር የሚሸፍን፣ ቁመቱ እስከ 20 በመቶ የጥላ ሽፋን ወይም ካኖፒ ያለውና ቁመቱ ከሁለት ሜትር በላይ የሆነ ሁሉ ደን ይሰኛል፡፡ ይህ ቆላና ደጋውን የአገሪቱን ክፍሎች አካቶ ሲሰላ ሽፋኑ 15 በመቶ ነው ቢባልም በየዓመቱ ከሚታጣው 92 ሺሕ ሔክታር መሬት ውስጥ እየተተካ ያለው የደን መጠን ከ20 ሺሕ ሔክታር በላይ እንደማይሸፍን አረጋግጠዋል፡፡

በመሆኑም የደን ልማት የብልጽናችን መሠረት በመሆኑ ሁሉም በየፊናው በሚሰማራበት የሙያ መስክ፣ ሕፃናትም ከልጅነት ዕድሜ ጀምሮ ደን የህልውና ዋልታ መሆኑን እያወቁ እንዲመጡ መደረግ አለበት ያሉት ዶ/ር ይተብቱ፣ እየለማ ከሚገኘው ይልቅ እየተጨፈጨፈ ያለው የደን ሀብት ከፍተኛ በመሆኑ ሁሉም ጉዳዬ ሊለው እንደሚገባ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

 

 

Standard (Image)

በመድን ገበያው ፉክክር ያሽቆለቆለውን የዓረቦን ምጣኔ የሚቆጣጠር መመሪያ እየተጠበቀ ነው

$
0
0

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያሽቆለቆለ የመጣውን የመድን ኩባንያዎች የዓረቦን ምጣኔና አንዳንድ አሠራሮችን ያስተካክላል የተባለ መመሪያ ለማውጣት መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪው እንቅስቃሴ በተለይ የዓርቦን ምጣኔ በየጊዜው እያየለ በመጣው ከፍተኛ ፉክክር ሳቢያ እያሽቆለቆለ በመሆኑና በአገሪቱ መድን ኢንዱስትሪ ውስጥ አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደሩ፣ ይህንን ችግር ለማስተካከል ያስቻላል የተባለ ብሔራዊ ባንክ ይፋ እንደሚያደርግ እየተጠበቀ ነው፡፡

ጥቂት የመድን ሽፋን የሚሰጥባቸው አገልግሎቶች ዋጋቸው (ዓርቦን) ላይ ያለውን ማሽቆልቆል ለመግታትና ለማስተካከል፣ የችግሩን ምንጭም ለማየት የሚያስችል ጥናት በሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ላይ ለማድረግ የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ማኅበርም ይህንን ጥናት እንዲያቀርብ እየሠራ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

ጥናቱ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያወጣው ለሚጠብቀው መመሪያ ግብዓት እንዲሆን ታስቦ የሚካሔድ ሲሆን፣ ማኅበሩ ጥናቱን እንዳጠናቀቀ ለብሔራዊ ባንክ እንደሚያቀርበውም ታውቋል፡፡ የዓርቦን ምጣኔ ላይ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ብሔራዊ ባንክም እንቅስቃሴ እያደረገ ስለመሆኑ የሚጠቅሱት ምንጮች፣ በየጊዜው እያሽቆለቆለ የመጣው የዓረቦን ምጣኔ መድን ድርጅቶችን ሳያከስር እንዲሁም አደጋ ሳያስከትል ለመግታት እንደሚያስችል ይታመናል፡፡

እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ብሔራዊ ባንክ እንደሚያወጣ ከሚጠበቀው መመሪያ ጎን ለጎን፣ በዓርቦን ተመን አሠጣጥ ላይ ተጨማሪ ዕርምጃዎችም ይፋ ሊደረጉ እንደሚችሉ ኩባንያዎቹ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

በአብዛኛው በተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ላይ ያደላው የአገሪቱ መድን አሰጣጥ፣ የዓርቦን ምጣኔው እያሽቆለቆለ በመምጣቱ በአገሪቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ገቢና ዓመታዊ ትርፍ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ባልተገባ ውድድር ኢንዱስትሪው እየተጎዳ ስለመሆኑም የሚገልጹ አሉ፡፡ በኢንዱስትሪው ውስጥ 17 ሲኖሩ፣ የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ በገበያው ላይ ተፅዕኖ እያሳረፈ ያለውን የዓርቦን ተመን ለማስተካከል ጥረት እንዲደረግና ጥናት ቀርቦ ዕርምጃ እንዲወስድ በጋራ መወሰናቸውም ታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የተወሰኑ የግል መድን ኩባንያዎች ኢንዱስትሪው የሚታየውን የገበያ መቀዛቀዝ በመንተራስ መፍትሔ ለማግኘት ከፍተኛ ባለአክስዮኖችን በመጥራት መምከር እንደጀመሩም ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለገበያው መቀዛቀዝ ምክንያት ከሚደረጉት አንዱ የዓርቦን ተመን ምጣኔ ሲሆን በቅርቡ የወጣ ጥናት እንደሚያሳየውም የዓርቦን ዋጋ በየጊዜው ማሽቆልቆሉ ሳያንስ፣ እንደ ተሽከርካሪ መለዋወጫ ያሉ ዕቃዎች ዋጋ መናሩም ለኢንዱስትሪው ፈተና ሆኗል፡፡ በዚሁ ጥናት መሠረት ሞተር ነክ የሆኑ የኢንሹራንስ ሽፋኖች ላይ ጎልቶ ታይቷል፡፡

ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ 17 ኩባንያዎችን ያፈራው የኢትዮጵያ መድን ኢንዱስትሪ፣ ሁሉም ኩባንያዎች ተደምረው ያስመዘገቡት ዓመታዊ ትርፍ አንድ ቢሊዮን ብር ላለማስመዝገቡ አንዱ ማሳያ ይኸው የዓርቦን ምጣኔ እየቀነሰ መምጣቱ ነው፡፡ ከአሥር ዓመት በፊት ለአንድ ፈሳሽ ማመላለሻ ተሽካርካሪ የመድን ሽፋን እንዲያገኝ የሚከፈለው ዓረቦን የመኪናው ጠቅላላ ዋጋ በ3.75 በመቶ ተባዝቶ ነበር፡፡ አሁን ግን ዋጋው ከዕጥፍ በላይ ቀንሶ እስከ 1.5 በመቶ ባለው ተመን እየተባዛ በሚገኝ የስሌት ዋጋ መሠረት ሽፋን እየተሰጠበ በመሆኑ፣ ለዓረቦን የሚከፈለው ዋጋ በእጅጉ እየቀሰነ ለመምጣቱ አስረጅ ሆኗል፡፡

ለግል ተሽከርካሪዎችም ቢሆን ከአሥር ዓመት በፊት የዓርቦን መጠኑ የመኪናው ዋጋ በ1.5 በመቶ የሚባዛ ነበር፡፡ አሁን ግን ይህ መጠን ከአንድ በመቶ በታች ወርዷል፡፡ የአብዛኞቹ የተሽከርካሪ መድን የዓረቦን ዋጋ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ እያሽቆለቆለ ቢመጣም በአንፃሩ ግን ከፍተኛ የመድን ካሳ ክፍያ እየተጠየቀበት የሚገኘው ይኸው የተሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ መሆኑ ደግሞ ክስተቱን እንቆቅልሽ አድርጎታል፡፡ 

Standard (Image)

ተመሳስለው በተሠሩ የኤቲኤም ካርዶች ሳቢያ ንግድ ባንክ አገልግሎት ለማቋረጥ መገደዱ ታወቀ

$
0
0

 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሌሎች ባንኮች ጋር በጋራ በኔትወርክ በመተሳሰር የየትኛውም ባንክ ደንበኞች ሲገለገሉበት የቆዩትን የካርድ ክፍያ አሠራር ለማቋረጥ የተገደደው ተመሳስለው በተሠሩና በተጭበረበሩ ካርዶች ምክንያት እንደነበር ብሔራዊ ባንክ ይፋ አደረገ፡፡

 ንግድ ባንክ አሠራሩን ሳይታሰብ ለማቋረጡ ምንም ዓይነት መረጃ ሳይሰጥ ቢቆይም፣ በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዘጠኝ ወር ሪፖርት ለተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ለማወቅ እንደተቻለው፣ አገልግሎቱ በጊዜያዊነት ተቋርጦ የነበረበት ዋነኛ ምክንያት የንግድ ባንክን የኤቲኤም ካርዶች አስመስሎ በመሥራት በሌሎች ባንኮች ገንዘብ ለማውጣት ሙከራዎች ሲደረጉ በመገኘታቸው ነው፡፡

 በሐሰተኛ የኤቲኤም ካርዶች ገንዘብ ለማውጣት የሚደረገውን ውንብድና ለመቆጣጠር አገልግሎቱ በጊዜያዊነት እንዲቋረጥ መደረጉም ተጠቅሷል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሥጋት ለመቀነስና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የሁሉንም ባንኮች የጋራ አሠራር በማዕከል የሚቆጣጠረው ኢትስዊች አክሲዮን ማኅበር፣ ከኤቲኤም ካርዶች ጋር በተያያዘ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት በጉዳዩ ላይ ከኢንዱስትሪው አመራሮች ጋር እየመከረ ስለመሆኑ ይኸው ሪፖርት አመልክቷል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ችግር ለመቅረፍም እንደ መፍትሔ የተወሰደው ሁሉም ባንኮች ወጥ በሆነ አሠራር የኤቲኤም ካርዶችን የመጠቀም ሥርዓት ዘርግተው ከማጭበርበር ጋር የተያያዙ ሥጋቶችን ለመቀነስ መሥራት እንደሚባቸው የገዥው ባንክ አስታውቋል፡፡

ንግድ ባንክ ግን አገልግሎቱን አቋርጦ ቢቆይም በሐሰተኛ ካርዶች የሚፈጸመውን ገንዘብ የማውጣት ሙከራ ለመከላከል የሚያስችል አሠራር በመዘርጋቱ አገልግሎቱ ዳግም እንዲጀመር አድርጓል ተብሏል፡፡ ማጭበርበሮችን ለመከላከል የሚያስችል ማስተካከያዎችን እንዳደረገም ተጠቅሷል፡፡

ኢትስዊች ከጥቂት ወራት በፊት ይፋ ባደረገው ሪፖርት መሠረት፣ ከተለያዩ ኤቲኤሞች ገንዘብ ካወጡ ከ420 ሺሕ በላይ ደንበኞች ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ ከደንበኛቸው ውጭ በሚገኙ ሌሎች ባንኮች እንደተጠቀሙ ታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ባንኮች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተከሏቸው ከሦስት ሺሕ በላይ የኤቲኤም ማሽኖች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ1,330 የሚበልጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተከላቸው ናቸው፡፡ ንግድ ባንክ የዚህ ዓመት የዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙን የሚያሳየው ሪፖርት ውስጥ እንዳካተተው፣ የኤትኤም ካርድ የሰጣቸው ደንበኞቹ ቁጥር ከ3.5 ሚሊዮን በላይ ደርሰዋል፡፡ ይሁንና ካለፈው መጋቢት 2009 ዓ.ም. መጨረሻ ጀምሮ የባንኩን ካርድ የያዙ ደንበኞች ከሌሎች ባንኮች ኤቲኤሞች ገንዘብ ማውጣት የሚችሉበትን አሠራር አቋርጦታል፡፡ ስለአገልግሎቱ መቋረጥ በይፋ መግለጫ ባይሰጥም፣ ለወራት የተቋረጠው አገልግሎት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የባንኩ ደንበኞች በሌሎች ባንኮች አማካይነት ገንዘብ እንዳያወጡ አግዷቸው ቆይቷል፡፡

የአገልግሎቱ መጓደልም ከደንበኞች አልፎ ባንኩንም እንደጎደለው ይነገራል፡፡ ሌሎች ባንኮችም ከእንዲህ ዓይነቱ የገንዘብ ማንቀሳቀሻ ዘዴ ያገኙ የነበረውን ገቢ አሳጥቷቸዋል፡፡ ችግሩ ግን ይህ ብቻም ሳይሆን፣ ባንኩ አቋርጦት የቆየውን አገልግሎትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ባንኮች በጋራ የኤቲኤም አገልግሎት ለመስጠት የተዘረጋው አሠራር ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከንግድ ባንክ የተገኘው መረጃ ግን ተቋርጦ የነበረው አገልግሎት በድጋሚ መጀመሩን አስታውቋል፡፡ የባንኩ ደንበኞች በሌሎች ባንኮች ኤቲኤሞች አማካይነት ገንዘብ ከሒሳባቸው ማውጣት የሚችሉበት አሠራር ከማክሰኞ፣ ግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ መጀመሩን ኢትስዊች አረጋግጧል፡፡   

ከአገሪቱ ባንኮች ሁሉ ከፍተኛ የኤቲኤም ተጠቃሚዎች ያሉት ንግድ ባንክ፣ ከሌሎች ባንኮች ኤቲኤሞች ገንዘብ ለማውጣት አለመቻላቸው በተለይ ሁሉንም ባንኮች በማዕከል የሚያስተባብረው ኢትስዊች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሮበታል፡፡

ባንኩ አገልግሎቱን አቋርጦ በመቆየቱ ሳቢያ፣ የባንኩን ካርድ ይዘው በሌሎች ኤቲኤም ማሽኖች ለመጠቀም ሲደረጉ የቆዩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙከራዎችም እንዳይሳኩ አድርጓል፡፡ በመሆኑም የንግድ ባንክን ካርድ የያዙ ደንበኞች የባንኩ ኤቲኤሞች ያሉበትን አካባቢ እያፈላለጉ ለመጠቀም አስገድዷቸዋል፡፡ አገልግሎቱ በተቋረጠባቸው በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሳምንታት ብቻ ከ150 ሺሕ በላይ ያልተሳኩ ሙከራዎች ተፈጽመዋል፡፡ ባንኩ አገልግሎቱን ለማቋረጥ ስለተገደደበት ምክንያት ይፋ ሳያደርግ መቆየቱም አስተችቶታል፡፡ 

Standard (Image)

ቀርፋፋውን ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት ንግድ ምክር ቤት የቢዝነስ ሩጫ አሰናድቷል

$
0
0

 

መንግሥት በአገሪቱ የኢኮኖሚ መቀዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ኢንዱስትሪ መር ጉዞ ጀምሬያለሁ ካለ ሰነባቷል፡፡ በመጀመርያውም ሆነ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች እየተተገበሩ ቢሆንም፣ በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት ሊመዘገብ አልቻለም፡፡

በጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት ከማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ከጠቅላላው የአገራዊ ኢኮኖሚ ድርሻው ከአምስት በመቶ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ቢሆን ሊመዘገብ የቻለው የግንባታ ዘርፉ በ8.5 በመቶ በማደጉ ነው፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት የግምገማ ሪፖርት እንሚያሳየውም በኢንዱትሪ ዘርፍ ውስጥ ዋናው የዕድገት አንቀሳቃሽ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ነበር፡፡

በዚሁ ግምገማ መሠረት የአገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ድርሻ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ አገሮችም ሳይቀር በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም ከግብርና ዘርፍ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱትሪ ዘርፍ የሚደረገውን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚደረገው ርብርብ መስፋፋት እንዳለበት የሚጠቁም ነው፡፡ ዘርፉ ተፈላጊውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ደግሞ የግል ባለሀብቱ ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ይሰመርበታል፡፡  

የግል ባለሀብቶች ግን በሚፈለገው መጠን ወደ አምራች ዘርፉ እየመጡ አለመሆናቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡ እንደ ንግድ ምክር ቤት ያሉ የግሉ ዘርፍ ወኪል ተቋማትም አባሎቻቸውም ሆኑ ሌሎች አካላት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚያግዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደማይታዩ ይነገራል፡፡

በመንግሥት ውጥን በቀላል ማኑፋክቸሪንግ መስክ ኢትዮጵያን የአፍሪካ እንብርት  ለማድረግ እንዲቻል የግሉ ዘርፍ አስተዋጽኦ እንደጠበቀ ሁኖ ዘርፉን ወደ ማኑፋክቸሪንግ እንዳይመጣ ያላስቻሉ ምክንያቶች እንዳሉ፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ይገልጻሉ፡፡ ችግር ሆነው ከሚታዩት አንዱ በቂ የግንዛቤ ሥራ አለመሠራቱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ቢዘገይም ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት እንዲደረግበት በማሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ማዘጋጀት ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ‹‹ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ!›› በሚል ርዕሥ ያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ማሟሻ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የንግድ ትርዒትና ኩነት ዳይሬክተሮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ባግናወርቅ ወልደ መድኅን እንደሚጠቅሱት፣  ለኢኮኖሚው ዋልታ በሆነው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ባለሀብቶች ገብተው እንዲሠሩ የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም የሚያጠግብ ለውጥ አልመጣም፡፡ ስለዚህ በተለየ ዘዴ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ የቢዝነስ ሩጫ ለማሰናዳት ተነስተናል ይላሉ፡፡ እንደሳቸው ገለጻ፣ የግሉ ዘርፍ በሚጠበቀው መጠን ወደ ማኑፋክቸሪንግ ያልገባበት አንዱ ችግር ግንዛቤ ማስጨበጥ ስላልተቻለ ነው፡፡  

ወ/ሮ ባግናወርቅ አባባላቸውን ለማጠናከር በቢዝነሱ ዓለም በተለይም በአስመጪነት ከ60 ዓመታት በላይ የቆዩ፣ የአንድ አንጋፋ ነጋዴን ተሞክሮ በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፡፡

‹‹እኝህ አዛውንት ነጋዴ ይህንን ያህል ዓመት ፍሪጅ በማስመጣት ሲሠሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ፍሪጅ እያስመጡ ይሸጣሉ፡፡ ይህንን ሲሠሩ ነው ያረጁት፡፡ ልጆቻቸውም ይህንኑ ሥራ ቀጥለዋል፡፡ የተለወጠነ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ፍሪጁን እዚህ እንዲገጣጠም ባያደርጉ ራስዎንም አገርዎንም ይጠቅማሉ ስንላቸው፣ ‹ይህንን ማነገረኝ ታዲያ?› ነበር ያሉት››፡፡  

ስለዚህ ባለሀብቱ ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲገባ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ አልተሠራም የሚለው ምክንያት የሚያስኬድ በመሆኑ፣ ንግድ ምክር ቤቶችም ድርሻቸውን ለመወጣት፣ ‹‹ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ!›› በሚል ርዕሥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳ የቢዝነስ ሩጫ የግንዛቤ ውድድር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመጪው እሑድ፣ ግንቦት 27 ቀን 2009 የሚካሄደው ይህ ሩጫ፣ በየዓመቱ በቋሚነት ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን፣ ሩጫው 3,000 ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል፡፡ እስካሁንም ከ2,000 በላይ መመዝገባቸው ታውቋል፡፡

አቶ ሰለሞን ስለሩጫው እንደገለጹት፣ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የኢንዱስትሪ በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ የአገር ውስጥ ባለሀብቱ ተሳታፊ እንዲሆን መንደርደሪያ ሊሆን እንደሚችል ታስቦ የተሰናዳ ነው፡፡

እስካሁን በነበረው አካሄድ በተለያዩ ስብሰባዎች የምክክር መድረኮችና በተመሳሳይ መንገዶች የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪ በመግባት ኢንቨስት እንዲደርጉ መረጃው ቢተላለፍም፣ በታሰበው ልክ ባለሀብቱ ተሳታፊ ሊሆን አይችልም፡፡

በኢንዲስትሪው ዘርፍ የውጭ ኢንቨስተሮች አብላጨውን ድርሻ ሲይዙ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ግን ወደ ዘርፉ ለመግባት ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ በመሆኑ ይህ እንዲለወጥ የሚረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር የተሰናዳ የሩጫ ውድድር ነው፡፡ ዘርፉን ለማገዝ በተገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሳይቀር የውጭ ባለሀብቶች ብልጫውን እየወሰዱ ነው ያሉት አቶ ሰሎሞን፣ ይህ አካሄድ ሥጋት እንደሚያሳድር ይናገራሉ፡፡ አገራዊውን ባለሀብት በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚኖረውን ተሳትፎ በማቀጨጭ አደጋ ላይ ሊጥል ስለሚችል ባለሀብቱ ዓይኑን ወደ ኢንዱስትሪው እንዲጥል የተለየ ነገር እናድርግ በሚል ለኢንዱስትሪ እንሩጥ በማለት አዘጋጅተነዋል ብለዋል፡፡

ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር እንዲረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫው  የሩጫ ፕሮግራም በቂ አይደለም ያሉት ወ/ሮ ባግናወርቅ፣ ሌሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችም ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡ መጪውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ያገናዘበ፣ አገራዊ ጠቀሜታ ያለውን ሥራ ለመሥራት ሌሎች ዘዴዎችን መጠቀም አለብን ይላሉ፡፡

አቶ ሰለሞን እንደሚጠቅሱት ዘርፉን ለመቀላቀል ችግር የሚያጋጥማቸው ከሆነም ችግሩን ለመፍታት የንግድ ምክር ቤቱም እገዛ ያደርጋል፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በተለያዩ የምክክር መድረኮች ችግሮችን በማሳየት መፍትሔ እንዲሰጥባቸው ለማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል ያሉት አቶ ሰለሞን፣ የንግዱ ኅብረተሰብ በኢንዱስትሪ ውስጥ በመግባት ኢንቨስትመንቱን ማስፋፋት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የንግድ ማኅበረሰቡን ጨምሮ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ አትሌቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም አካላት ይሳተፉበታል የተባለው የቢዝነስ ሩጫ አምስት ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ በጋንዲ ሆስፒታል በኩል በሜክሲኮ አደባባይ ዞሮ ቡናና ሻይ ሕንፃ ሲደርስ ይጠናቀቃል፡፡

Standard (Image)

ማራቶን ሞተርስ የሃዩንዳይ መኪኖችን ለመገጣጠም ስምምነት ተፈራረመ

$
0
0

 

  • በዓመት እስከ 2500 ተሽከርካሪዎች የሚገጣጥም ፋብሪካ ይተክላል

ማራቶን ሞተርስ ኢንጂነሪንግ በአገር ውስጥ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም ከደቡብ ኮሪያው ሃዩንዳ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ፡፡ የሁለቱ ኩባንያዎች ስምምነት ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ እንደቆየ ነው፡፡

ማራቶን ሞተርስ ስድስት ዓመታት በፈጀ ሒደት ውስጥ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለመትከል የኢንቨስትመንት ፈቃድ ከማውጣት ባሻገር፣ የቦታ ጥያቄ አቅርቦ እስኪሰጠው ሲጠባበቅ መቆየቱ ተገልጾ፣ እነኚህን ሒደቶች በማጠናቀቅ ከሃዩንዳይ ኩባንያ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚችልበትን ድርድር ካጠናቀቀ በኋላ ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችለውን ስምምነት አድርጓል፡፡

ሰኞ መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ሳሪስ አካባቢ በሚገኘው የመኪና ዕቃዎች መለዋወጫና የሽያጭ ማሳያ አዳራሽ ውስጥ በተካሄደ ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ አካባቢ ለመገጣጠሚያ ፋብሪካው መገንቢያ የ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ማግኘቱን የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መልካሙ አሰፋ አብራርተዋል፡፡

የተሽከርካሪ መገጣጠሚያውን ለመገንባት ግማሽ ቢሊዮን ብር የኢንቨስትመንት ካፒታል በማስመዝገብ ፈቃድ ያገኘው ማራቶን ሞተርስ፣ መገጣጠሚያው ሲጠናቀቅ በዓመት ከ2,000 እስከ 2,500 ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ለማቅረብ ማቀዱን ገልጿል፡፡

ስምንት ዓይነት ሃዩንዳይ ሠራሽ ሞዴሎችን በመያዝ ሥራ እንደሚጀምር የሚጠበቀው መገጣጠሚያ፣ የመጀመሪያው ምርት በመጪው ዓመት ጥር ወር ገደማ ለገበያ እንደሚያቀርብም አቶ መልካሙ ገልጸዋል፡፡

ከሚያስመጣቸው ሞዴሎች ውስጥ ኢዮን ባለ 800 ሲሲ የቤት አውቶሞቢልን ጨምሮ፣ ኤስዩቪ፣ የሰዎችና የአነስተኛ ጭነት ማጓጓዣ መኪናዎችን ለገበያ እንደሚያቀርብ ኩባንያው አስታውቋል፡፡

ዘመናዊ ፋብሪካ ለመገንባት የሚያስችሉና ለመገጣጠሚያ የሚውሉ ማሽኖችን ከደቡብ ኮሪያ በማስመጣት ወደ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ኩባንያው፣ ሥራውን የሚከታተሉ የሃዩንዳይ ኩባንያ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሚመጡም ኃላፊዎቹ አስረድተዋል፡፡  

ማራቶን ሞተርስ እስካሁን ለገበያ ሲያቀርባቸው የቆዩት ከውጭ ሙሉ በሙሉ ተሠርተውና ተገጣጥመው የሚመጡ (Completely Built up) የነበሩ ሲሆኑ እነዚህ መኪኖች በአገር ውስጥ ሲገጣጠሙ ግን እስከ 30 በመቶ የሚሆነውን ግብዓት ከዚሁ በመጠቀም በአንድ ተሽከርካሪ ከ15 እስከ 18 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ለማምጣት እንደሚቻል አቶ መልካሙ ተናግረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ለአብነት ኢዮን የሚባለው የቤት አውቶሞቢል ሞዴል የሚሸጥበት ዋጋ 425 ሺሕ ብር ሲሆን፣ በአገር ውስጥ ተገጣጥሞ ሲቀርብ ግን የ16 በመቶ ቅናሽ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

‹‹አዳዲስ የቤት አውቶሞቢሎችን በአገር ውስጥ ገጣጥሞ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ከውጭ የሚገቡ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር በመቀነስ የመንገድ ላይ አደጋንና የበካይ ጋዞች ልቀትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል፤›› ብለዋል፡፡

እንደ አቶ መልካሙ ማብራሪያ፣ መገጣጠሚያ ፋብሪካው ሥራ ሲጀምር ለመኪና ግብዓት የሆኑ ማለትም እንደ ባትሪ፣ ጎማ፣ የሰው ኃይልና ሌሎችም ተዛማጅ ግብዓቶች በአገር ውስጥ እንደሚሟሉ ይጠበቃል፡፡

ወደፊት በአገር ውስጥ የሚታየው የዘርፋ መስፋፋትና የኢንዱስትሪው ዕድገትን ተከትሎ የተሽከርካሪ ግብዓቶችን ከሃዩንዳይ ኩባንያ ጋር በመነጋገር ተመጣጣኝ መለዋወጫ ከአገር ውስጥ ምንጮች ለማቅረብ የሚቻልበት አቅም ከተፈጠረ፣ ከውጭ የሚገባውንም የሞተር አካል ለመቀነስ እንደሚቻል ተብራርቷል፡፡

በአንድ ሊትር ነዳጅ እስከ 26.7 ኪሎ ሜትር ርቀት መጓዝ የሚችሉ ተሽከርካሪዎችን ከስምንት ወራት በኋላ ገጣጥሞ ለገበያ ለማቅረብ የተነሳው ማራቶን ሞተርስ፣ ትልልቅ የጭነት ተሽከርካሪዎችንም ለማገጣጠም ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡ ይሁንና በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን በአስተኛና መለስተኛ አውቶሞሎች እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

ማራቶን ሞተርስ የሚገነባው ፋብሪካ የሕንፃ ተቋራጭ ሠራተኞችን ጨምሮ ለ500 ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡ የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም የተነሳው ማራቶን ሞተርስ ወደ ሥራው ለመግባትና ፈቃድ ለማግኘት ከሁለት ዓመት በላይ እንደወሰደበት አስታውሷል፡፡

መገናኛ አካባቢ ከሚገኘው የመለዋወጫና የሽያጭ ማሳያ በተጨማሪ ሳሪስ ሠፈር ውስጥ ባስገነባው ሕንፃ የሃዩንዳይ ምርት ማሳያና የመለዋወጫ ዕቃ ሸጫና መገጣጠሚያ ማዕከሉን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል፡፡

በአፍሪካ የሃዩንዳይ ተሽከርካሪዎችን ገጣጥመው ለገበያ በማቅረብ ከሚጠቀሱ አገሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡ 60 ሺሕ የሃዩንዳይ መኪኖች ለገበያ ከሚቀርቡባት ደቡብ አፍሪካ ባሻገር፣ አልጄሪያ 50 ሺሕ መኪኖችን በየዓመቱ ለገበያ በማቅረብ ከቀዳሚዎቹ መካከል ተሠልፋለች፡፡

Standard (Image)

በንግድ ባንክና በልማት ባንክ መካከል የሚዋልሉ የብድር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት አልቻሉም

$
0
0

 

ባለፈው ወር አጋማሽ አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ደብዳቤዎች ወጪ ተደርገው ነበር፡፡ ደብዳቤዎቹ የደረሷቸው ደግሞ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የብድር ጥያቄዎችን ያቀረቡ ተበዳሪዎች ናቸው፡፡ የብድር ጥያቄዎቻቸው ተገምግመው፣ ብድር ለማግኘት የሚያስችላቸው የመጨረሻው ዕርከን ላይ ቢቃረቡም ድንገት ግን ‹‹የፕሮጀክት ብድር ጥያቄ መቋረጡን ስለማሳወቅ›› በሚል ርዕስ ለብድር ፈላጊዎቹ የተጻፈው ደብዳቤ ያልተጠበቀ ዱብ ዕዳ ነበር፡፡

ሚያዝያ 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተላለፈ ውሳኔ መሠረት፣ ንግድ ባንክ ለሥራ ማስኬጃ የሚቀርቡ የብድር ጥያቄዎች ላይ ብቻ አተኩሮ እንዲሠራ በመታዘዙ ምክንያት፣ ለፕሮጀክት የሚቀርቡ ብድሮችን እንደማያስተናግድ የሚጠቅስ መልዕክት የያዘ ደብዳቤ ተሰራጭቷል፡፡ ይኸው ደብዳቤ የብድር ጥያቄዎች የግምገማ ሒደት መቋረጡንም አስታውቋል፡፡ ነገር ግን የፕሮጀክት የብድር ጥያቄዎች ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቢቀርቡ ሊስተናገዱ እንደሚችሉም ይጠቅሳል፡፡

ለብድር ፈላጊዎቹ የተጻፈው ደብዳቤ ከመሰራጨቱ ቀደም ብሎ ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክ በፕሮጀክት ፋይናንስ ላይ አተኩሮ እንዲሠራ ንግድ ባንም በሥራ ማስኬጃ ብድሮች ላይ እንዲያተኩር የሚያስገድድ መመሪያ አስተላልፎ ነበር፡፡ ንግድ ባንክ ለፕሮጀክት ሥራዎች የሚሰጠውን ብድር እንዲያቆም በምትኩ ልማት ባንክ ለፕሮጀክት ያበድር የሚለው ትዕዛዝ የደረሳቸው የሁለቱም ባንኮች የሥራ ኃላፊዎች ግርታ ውስጥ ቢገቡም፣ ንግድ ባንክ የተላለፈውን ትዕዛዝ መተግበር ጀምሯል፡፡

ያልተጠበቀው የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ለጅምር ፕሮጀክቶቻቸው ማስፈጸሚያ ከንግድ ባንክ ብድር እንደሚያገኙ እምነት አድሮባቸው የነበሩት ላይ ድንገተኛ መርዶ ከመሆኑ ባሻገር፣ ከአንድ ወር ቆይታ በኋላም አሁንም ድረስ ብዥታው እንደረበበ ይገኛል፡፡ የተወሰኑ ብድር ፈላጊዎች በተነገራቸው መሠረት ወደ ልማት ባንክ ቢሄዱም ጥያቄያቸውን ሊስተናገድ ባለመቻሉ ሥጋት አድሮባቸዋል፡፡  

ለሚገነቡት ሆቴል ማጠናቀቂያ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ጠይቀው ምላሽ በመጠባበቅ ላይ የነበሩና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለሀብት ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የተላለፈው ውሳኔ ያልጠበቁት ከመሆኑም በላይ ንግድ ባንክን ተማምነው የጀመሩት ሥራ ላይ ጫና አሳድሯል፡፡

እንደ ባለሀብቱ ገለጻ፣ ለጀመሩት ግንባታ ማስፈጸሚያ የብድር ጥያቄ ከማቅረባቸው በፊት ብድሩን ለማግኘት በቅድሚያ የፕሮጀክቱን 50 በመቶ ግንባታ ማጠናቀቀቅ ነበረባቸው፡፡ ብድር የጠየቁበት ቅርንጫፍ መሐንዲሶችም የፕሮጀክቱን 50 በመቶ እንደተጠናቀቀ፣ ለቀረው የግንባታ ሥራ እንዲውል ብድር ማግኘት እንደሚችሉ ተረጋግጦ፣ አስፈላጊ ሒደቶች በሙሉ ተሟልተው ብድሩን ለማስለቀቅ ውል ለመፈራረም በሚዘጋጁበት ወቅት የፕሮጀክ ብድር መቋረጡን የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሷቸዋል፡፡ እንደ እኚሁ ባለሀብት ሁሉ ከሆቴል ባሻገር ለትምህርት ቤት፣ ለፋብሪካና ለመሳሰሉት ፕሮጀክቶች ብድር የጠየቁ ደንበኞች ግራ ተጋብተዋል፡፡

 ‹‹ብድር ለማግኘት የሚጠበቅብኝ የፕሮጀክቱን 30 በመቶ ግንባታ ማጠናቀቅ ነበር፡፡ ብድሩን በአስተማማኝ መንገድ ለማግኘትና ባንኩም የበለጠ እምነት እንዲኖረው ስል ከዚህም ከዚያም በማለት ገንዘብ አሰባስቤ የግንባታውን ሥራ 50 በመቶ አድርሼው ነበር፤›› ያሉት ባለሀብት፣ ያቀረቡትን የብድር ዳር ለማድረስ ከዘጠኝ ወራት በላይ እንደፈጀባቸው፣ ያቀረቧቸው ማስረጃዎችና የፕሮጀክቱ ትልመ ሐሳብ ፋይናንስ ከማግኘት እንደማያግዳቸው ግልጽ ቢሆንም፣ ባንኩ ግን የፕሮጀክት ብድር ቀርቷል በማለቱ እስካሁን ወጪ ያደረጉት ገንዘብ መና ሊቀር ይችላል የሚል ሥጋት አሳድሮባቸዋል፡፡ ልማት ባንክም ለሆቴል፣ ለሆስፒታልና ለመሳሰሉት ፕሮጀክቶች ብድር አልሰጥም ማለቱን በመስማታቸው ይባስ ማጣፊያው እንዳጠራቸው ይናገራሉ፡፡

 ‹‹ልማት ባንክ እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አያስተናግድም የሚል ምላሽ በመስጠቱ ብድር ወደ ጠየቅንባቸው ቅርንጫፎች ተመልሰን አቤት ብንልም ይህ የብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ነው ተብለናል፤›› ይላሉ፡፡ እሳቸው ብድር በጠየቁበት መቐለ ከተማ የሚገኘው የልማት ባንክ ቅርንጫፍም እንደ እሳቸው ያሉ የብድር ጥያቄዎችን ለማስተናገድ አቅም እንደሌለው ስለተረዱ፣ የፕሮጀክት ብድር ጥያቄዎችን ያስትናግዳል መባሉ ከምን የተነሳ ነው? በማለት እንዲጠይቁ ገፋፍቷቸዋል፡፡

የኮሌጅ ባለቤት የሆኑ ሌላኛው ብድር ፈላጊም ኮሌጃቸውን ለማሳደግ ያቀረቡት የብድር ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ ለብዙ ጊዜ ሲጠብቁ ቆይተው ቀርቷል የሚል ውሳኔ መተላለፉ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡

ከአስተያየት ሰጪዎቹ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ብሔራዊ ባንክም ሆነ ንግድ ባንክ እንዲህ ያለውን ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ቢያንስ ግምገማ ላይ የነበሩና የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሱ ጥያቄዎች እንዲስተናገዱ መፍቀድ ነበረባቸው ይላሉ፡፡ ለፕሮጀክቶች ብድር መስጠት ያለበት ልማት ባንክ ቢባልም ባንኩ ግን የሚቀርቡለትን ጥያቄዎች እንደማያስተናግድ እየታወቀ ስለምን እንዲህ ይዳረጋል? በማለት የደረሰባቸውን እንግልት በምሬት አስታውቀዋል፡፡ ‹‹የብድር ጥያቄያችን ምላሽ ማጣት የለበትም ያሉ ከሐዋሳ፣ ከመቐለ፣ ከባህር ዳርና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ባለሀብቶች ጉዳያቸውን ለባንኩ ኃላፊዎች በግንባር ቢያቀርቡም ለአቤቱታቸው ምንም ምላሽ እንደላገኙ ተናግረዋል፡፡ አንዳንድ የባንኩ ኃላፊዎች በብሔራዊ ባንክ ውሳኔ ግር መሰኘታቸውን ቢገልጹላቸውም፣ ከተላለፈው መመሪያ ውጪ መሥራት እንደማይችሉ እንደነገሯቸው ጠቅሰዋል፡፡  

እንዲተገበር የተፈለገው አሠራር በአጭሩ ሲገለጽ፣ ልማት ባንክ ለፕሮጀክት ብድር እንዲሰጥ ፕሮጀክቱ ሥራ ከጀመረ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ደግሞ ንግድ ባንክ እንዲያበድር የሚያዝ ነው፡፡

አዲሱ የብድር አሰጣጥ ለፕሮጀክት ፋይናንስ የሚለው ገንዘብ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ውስጥ ተመላሽ የሚደረግ ብድር እንደሆነ ያስቀምጣል፡፡ የረዥም ጊዜ የሚባለው በ20 ዓመታት ውስጥ የሚከፈል ሲሆን፣ መካከለኛው ደግሞ ከሦስት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚጠቃለል ነው፡፡

በዚህ መሠረት የአጭር ጊዜ የሥራ ማስኬጃ ብድር የማቅረብ ሥራ የንግድ ባንክ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ብድርም ከአንድ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ይሆናል ማለት ነው፡፡

 ሁለቱ የመንግሥት ባንኮች የተቋቋሙበትን ዓላማ ለማፈጸም እንዲሠሩ የሚጠይቀው ብሔራዊ ባንክ፣ ምንም እንኳ ተቋማቱ በሜዳቸው ይጫወቱ ቢልም ሳይታሰብ ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የብድር አሰጣጥ ሥርዓት ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት በመገንዘብ ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን መልሶ እንዲያይላቸው ባለሀብቶቹ እየጠየቁ ነው፡፡

ብሔራዊ ባንክን ለማነጋገር ሞክረው እንዳልተሳካላቸው የገለጹ ባለሀብቶች፣ አሁንም ጥያቄ ማቅረባቸውን እንደሚቀጥሉበት አስታውቀዋል፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ ንግድ ባንክ እንዲቋረጥ ያደረገው የብድር ጥያቄ በቢሊዮኖች የሚገመት ገንዘብ ሲሆን ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ባሻገርም የውጭ ኩባንያዎች ጥያቄም እንደሚገኝበት  ታውቋል፡፡

 

Standard (Image)

ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የተፈጥሮ ማዕድን ውኃ ፋብሪካ በደብረ ብርሃን ሥራ ጀመረ

$
0
0

 

በደብረ ብርሃን ከተማ ጫጫ አካባቢ በ30 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባና በሰዓት 12 ሺሕ ጠርሙስ ውኃ የማምረት አቅም ያለው ፋብሪካ በ83 ሚሊዮን ብር ወጪ ተቋቁሞ ሥራ ጀመረ፡፡

ታምሬና ቤተሰቡ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤትነት የተቋቋመው ፋብሪካ፣ አልፋ የተፈጥሮ የማዕድን ውኃ የሚል ሥያሜ የተሰጠውን የታሸገ ውኃ በማምረት ገበያውን የተቀላቀለው ከጥቂት ቀናት በፊት ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በ0.6 ሊትር፣ በአንድና በሁለት ሊትር በማሸግ የሚያቀርበው ውኃ ምንም ዓይነት ኬሚካልም እንደማይጨመርበትና የእጅ ንክኪ ሳይኖረው እንደሚመረት የአልፋ የተፈጥሮ ማዕድን ውኃ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጣሰው አብተው አስታውቀዋል፡፡

አቶ ጣሰው እንዳሉት፣ ከአዲስ አበባ በ110 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ደብረ ብርሃን ከተማ አቅራቢያ፣ ጫጫ ከተባለው አካባቢ በሚገኘው የከርሰ ምድር ውኃ ላይ በተደረገ ጥናት ውኃው ከፍተኛ የጥራት ደረጃዎች ያሉትና በማዕድን ይዘቱም የዓለም የጤና ድርጅት መሥፈርቶችን በሚያሟላ ደረጃ አሟልቷል፡፡ በመሆኑም ለአዋቂዎች ብቻም ሳይሆን ለጨቅላ ሕፃናት ምግብ ማብሰያነት ጭምር መዋል የሚችል መሆኑ ተረጋግጦ፣ የጥራትና የተስማሚነት ምዘናዎችን በማለፍ ማረጋገጫ ከመንግሥት እንደተሰጠው አቶ ጣሰው ገልጸዋል፡፡

የአልፋ ማዕድን ውኃ የምርት ጥራትና ቁጥጥር ኃላፊ አቶ ወንድሙ ከበደ በበኩላቸው፣ የማዕድን ውኃ ክሎራይድን ጨምሮ ምንም ዓይነት ኬሚካል ሳይጨመርበት በዘመናዊ የውኃ ማጣሪያዎች ጥራቱ ተጠብቆ እንደሚመረት አብራርተዋል፡፡ እንደ አቶ ወንድሙ ገለጻ ከሆነ፣ ጥሬ ውኃው ከከርሰ ምድር ተስቦ ወደ ማጣሪያ የሚገባው ውኃ ከአክቲቭ ካርቦን ማጣሪያ ጀምሮ እስከ ኦዞን ማጣሪያ ድረስ ባለው ረዥም ሒደት ውስጥ በማለፍ ሙሉ ሙሉ የተጣራ የተፈጥሮ ውኃ እየተመረተ ይገኛል፡፡

የውኃ ማምረቻው የሚለቀው ጥቅም ላይ የዋለው ውኃም በአካባቢ ላይ ምንም ዓይነት ተፅዕኖ የማያስከትል መሆኑ ተረጋግጦ የሚለቀቅ ሲሆን፣ ንፁህ በመሆኑም በፋብሪካው አቅራቢያ ለሚገኙ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ማምረቻነት እንዲውል መታሰቡን አቶ ወንድሙ አብራርተዋል፡፡ ወደፊት ኩባንያው በአትክልትና ፍራፍሬ አምራችነት የመሰማራት ዕቅድ ያለው በመሆኑም ጥቅም ላይ የዋለውን ንፁህ ውኃ ዳግመኛ የመጠቀም ፍላጎት እንዳለውም አክለዋል፡፡

ለምርት ማሸጊያነት የሚጠቀምባቸውን የፕላስቲክ ጠርሙስ መሥሪያ ፕሪ-ፎርም እንዲሁም የጠርሙስ ክዳን ከአገር ውስጥ አምራቾች እንደሚያገኝ ያስታወቁት ኃላፊዎቹ፣ የምርት መግለጫ ኅትመቶችን ግን ከውጭ እንደሚያስመጣ ጠቅሰዋል፡፡

ፋብሪካው ችግር ከሆኑበት መካከል የውጭ ምንዛሪ እጥረት አንዱ ሲሆን፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ችግር ግን በጣም አሳሳቢ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ይሁንና ይህንን ችግር ለመቀነስ 800 ኪሎ ቮልት ኃይል ያለው ጄነሬተር ለመትከል መገደዱን አቶ ጣሰው ተናግረዋል፡፡

በ93 ሠራተኞች ሥራ የጀመረው አልፋ ውኃ በሙሉ አቅሙ በሦስት ፈረቃ ማምረት ሲጀምር በቀን 290 ሺሕ ያህል ጠርሙሶችን የማምረት አቅም እንደሚኖረው ሲጠቀስ ይህንን በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጀምር ተጠቅሷል፡፡ በመጪው ዓመት ማስፋፊያ በማካሄድ በ60 ሚሊዮን ብር ወጪ በሰዓት 18 ሺሕ ጠርሙስ ለማምረት የሚችልበትን ፕሮጀክት እንደሚተገብር አቶ ጣሰው አብራርተዋል፡፡ በማስፋፊያው ወቅት አሁን የሚመሩትን ጨምሮ 18 ሊትር ውኃ መያዝ የሚችል ጠርሙስም ለገበያ ታሽጎ እንደሚቀርብ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ከዚህም ባሻገር ወደ ጂቡቲ ውኃ ለመላክ የሚያስችለውን ጥናት ለማካሔድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ተብራርቷል፡፡ የጂቡቲ ገበያን ተመራጭ ከሚያደርጉት መካከል ከደብረ ብርሃን በ90 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሸዋ ሮቢት በኩል የሚያልፈው የባቡር መስመር ለውጭ ገበያ ዋናው ታሳቢ ነው፡፡

ታምሬና ቤተሰቡ ኩባንያ በአብዛኛው በመጠጥ አከፋፋይነት ሥራ ከ1996 ዓ.ም. ጀምሮ በአብዛኛው በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች ሲንቀሳቀስ የቆየ ሲሆን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የሲም ካርድና የቫውቸር ዋና አከፋፋይ በመሆን እየሠራ የሚገኝ ኩባንያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከ60 በላይ የታሸገ ውኃ ለማምረት የተመዘገቡ ፋብሪካዎች እንዳሉ ሲታወቅ ከእነዚህ ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ምርት እንደጀመሩና ገበያው ውስጥ እንደሚገኙ ይገመታል፡፡  

 

Standard (Image)

‹‹የመድን ኩባንያዎች ውድድር ዓረቦንን በመቀነስ ላይ ብቻ ማተኮሩ ራሳቸውን ወደ መብላት ይወስዳቸዋል››

$
0
0

 

አቶ አሰግድ ገብረ መድኅን፤ የኢንሹራንስ ባለሙያ

አቶ አሰግድ ገብረ መድኅን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሒሳብ አሠራር ተመርቀዋል፡፡ ከዚሁ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተጨማሪ ዲግሪያቸውን ከዚያም የማስትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝተዋል፡፡ የተለያዩ የኢንሹራንስ ትምህርቶችንም ተከታትለዋል፡፡ ወደ ሥራው ዓለም የተቀላቀሉት ከ17 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባልደረባነት ነው፡፡ በዚሁ መሥሪያ ቤት ከገንዘብ ተቀባይነት እስከ ዲስትሪክት ዳይሬክተርነት ድረስ ባለው ኃፊነት ለ15 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅም ነበሩ፡፡ የመድን ድርጅት የቦርድ አባል ሆነውም ለሰባት ዓመታት አገልግለል፡፡ ከመድን ድርጅት ከለቀቁ በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት በብርሃንና በኢትዮ ላይፍ ኩባንያዎች ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች  ሠርተዋል፡፡ የአገሪቱ መድን ኢንዱስትሪ ለውጥ ያሻዋል የሚሉት አቶ አሰግድ፣ ኢንዱስትሪው ማደግ ያለበትን ያህል እንዳላደገ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ጎላ ያሉ ችግሮች እየታዩበት እንደመጣ ስሚነገር፣ ዳዊት ታዬአቶ አሰግድን በመድን ኢንዱትሪው ልዩ ልዩ ችግሮች ዙሪያ አቶ አሰግድን አነጋግሯቸዋል፡፡ 

ሪፖርተር፡- የአገሪቱን የመድን ኢንዱስትሪ እንዴት ይገልጹታል?

አቶ አሰግድ፡- የአገራችን የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ በበርካታ ችግሮች የተበተበ ነው፡፡ ኢንሹራንስ እዚህ አገር ውስጥ ብዙም የተወለደ አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ በንጉሡ ዘመን የነበሩት ኩባንያዎች በነጮች የተመሠረቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ኩባንያዎች የመንግሥት ለውጥ ሲደረግ በደርግ ተወርሰው፣ በወቅቱ ብቸኛው የአሁኑ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተመሠረተ፡፡

በንጉሡ ጊዜ የነበረው የሊበራሊዝም አስተሳሰብ ይመራ የነበረው ካፒታሊዝም ሳያ ውድድር ላይ ተመሥርቶ የተጀመረው የመድን አሠራር፣ ባህሪውንና ይዘቱን ሳይለቅ በዕዝ ኢኮኖሚ ውስጥ ለማለፍ ተገደደ፡፡ ከአንዱ ወደ ሌላኛው ሥርዓት መሻገር የነበረባቸው የመድን ዕውቀቶች፣ የአሠራር ባህሎች፣ ልምዶችና ዲሲፕሊኖች ሌላ መልክና ቅርፅ በያዘ ርዕዮተ ዓለም ውስጥ ወደቁ፡፡ በዕዝ ኢኮኖሚ መዋቅር ውስጥ በወቅቱ የተቋቋመው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አሠራርም በዚሁ ሥርዓት መነጽር የተቃኘ ሆነ፡፡ የሞኖፖል ቅርፅ ያዘ ማለት ነው፡፡ በንጉሡ ዘመን የነበሩት ግን የውድድር መንፈስ የያዙ ነበሩ፡፡ የሠለጠነው ዓለም የመድን ፖሊሲዎች የሚሸጡበት ወቅት ነበር፡፡ መድን ድርጅት ሲፈጠር ግን ገበያው በሞኖፖል ተያዘ፡፡ ይህም ኢንዱስትሪውን ውድድር አልባ አደረገው፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የመድን ተገልጋዮች በሁለት የተለያዩ ርዕዮተ ዓለማት ውስጥ ወደቁ ማለት ነው፡፡ እንዲህ ያለው ታሪክ በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው አካሄድ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ብዬ አምናለሁ፡፡ 

ሪፖርተር፡- ተፅዕኖው በምን መልኩ እንደሚገለጽ ቢያብራሩት?

አቶ አሰግድ፡- ውድድሩ ቀርቶ በሞኖፖል ሲያዝ፣ የኢንሹራንስ ዓረቦን ዋጋ በአንድ ኢንሹራንስ ኩባንያ ብቻ ተቀርፆ የሚቀርብ ሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ የመንግሥት ሥርዓት ውስጥ ኢንዱስትሪው በድጋሚ ነፃ ሲደረግ እንደገና ለተገልጋዩ በውድድር ላይ ተመሥርቶ ቀረበ፡፡ እንዲህ ያለው አካሄድ የኢንሹራንስ አሠራሩ ሒደት የተቀያየረና የተዘበራረቀ እንዲሆን ያደርገዋል ማለት ይቻላል፡፡ አንዳንድ ሰነዶችን ወደኋላ ሄደን ስናይ፣ በንጉሡ ጊዜ የነበሩ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎች፣ ከፖሊሲዎቹ ጋር ተያይዞ ለደንበኞች የሚቀርብላቸው መግለጫ፣ የሒሳብ አሠራር ሥርዓቱ፣ የሰው ኃይል አጠቃቀሙ፣ ሥራን ከደንበኛ ወደ ኩባንያዎቹ የሚያደርሱት የመሐል ተዋናዮች ሁሉ የምዕራባውያንን የአሠራር ቅኝት የተከተሉ ነበሩ፡፡

ሪፖርተር፡- ኢንዱስትሪው በተለያዩ ሥርዓቶች ውስጥ ማለፉ ከኢንዱስትሪው ጉዞ አኳያ ያስከተለው ለውጥ በምን መልኩ ይገለጻል?

አቶ አሰግድ፡- የኢንሹራንስ ዕውቀት ወደ መቀጨጩ፣ ቋንቋውም በተገቢ ሁኔታ ወደ ኅብረተሰቡ አለመድረሱ፣ በአንድ የኢንሹራንስ ኩባንያ ጥላ ሥር መውደቅ፣ የራሱን ተፈጥሯዊ ዕድገት አለማሳየቱ፣ ደንበኞች የሚፈልጓቸው ፖሊሲዎች እንደልብ እንዳይገኙና ያሉት ብቻ እንዲቀጥሉ አድርጓል፡፡ የአልግሎት ብዝኃነት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ በሞኖፖል ስትሠራ ሁሉን ራስህ ነህ የምትቀርበው፡፡ ዋጋውንም የምትወስነው አንተ ነህ፡፡ የገበያ ጥናት አካሂደህ ደንበኞች የሚፈልጉትን ዲዛይን አድርገህ ካላቀረብህ ተመሳሳይና ልማዳዊ ፖሊሲዎች እንደነበሩ ይቀጥላሉ ማለት ነው፡፡ ልማዳዊ ነው ሲባል የኢንሹራንስ ባህርይና ለዛ ለብዙ ዓመታት ሳይለዋወጥ ተመሳሳይ ሆኖ ከቀጠለ ፈጣን ለውጥ የለውም ማለት ነው፡፡ የኢንሹራንስ ተጠቃሚውን ፍላጎት እያዩ አዳዲስ ፖሊሲዎችን እያዘጋጁ አለመሄድ ማለት ነው፡፡ ውድድር ሲኖር ግን ኩባንያዎች የተሻለ የኢንሹራንስ አገልግሎት ያቀርባሉ፡፡ የተገልጋዮችን ፍላጎት የተከተለ አገልግሎት ይዘው ይመጣሉ፡፡ በኢትዮጵያ ሁኔታ ግን ያኔም ሆነ ከዚያም በፊት የኢኮኖሚ ማዕቀፉ የካፒታል ምሥረታን የሚከለክል ነበር፡፡ ሰዎች ሀብት ለመፍጠር ያላቸውን ፍላጎት ይዘጋል፡፡ ሰዎች ሀብት ካልፈጠሩ ዕድገት የለም ማለት ነው፡፡ ዕድገት ከሌለ ኢንሹራንሱም ይጎዳል፡፡ ኢንሹራንስ ድጋፍ ሰጭ ነው፡፡ ኢኮኖሚውን የሚቆጣጠር  ነው፡፡ ይኼ ባለመኖሩ ግን የኢንሹራንስ ዕድገቱን አንድ ቦታ እንዲገታ አድርጎታል ማለት ነው፡፡ በሞኖፖል ተይዞ ስለቆየም ዕድገቱ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

ሪፖርተር፡- ከንጉሠ ነገሥቱ በኋላ በለውጡ ምክንያት ኢንዱስትሪው በሞኖፖል ስለተያዘ ዕድገቱ ቢጓተትም ደርግ ከወደቀ በኋላ ግን በሩ ዳግመኛ ለውድድር ተከፍቷል፡፡ ይህም ሆኖ ኢንዱስትሪው እንደሚፈለገው አላደገም፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ ቢያብራሩ?

አቶ አሰግድ፡- አሁን ለውድድሮች ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ነገር ግን አሁን ያለው የኢንሹራንስ ሥራ በአራት መሠረታዊ ችግሮች ውስጥ የወደቀ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ የቆይታውን እና የሚገባውን ያህል ለውጥ አልመጣም፡፡

ሪፖርተር፡- የተፈለገውን ለውጥ ሊያመጣ ያልቻለበት ምክንያት ምንድን ነው? እንደ ዋና ዋና ችግሮች የሚጠቅሱትስ ምንድናቸው?

አቶ አሰግድ፡- ለምሳሌ የተቀየረ የኢንሹራንስ ፖሊሲ የለም፡፡ በአብዛኛው ተመሳሳይ አገልግሎቶች ናቸው ያሉት፡፡ የበሰለ የኢንሹራንስ ምርምርና ጥናት አይካሄድም፡፡ በዚህ የተነሳ ደንበኞች የሚፈልጉትን አላገኙም፡፡ ስለኢንሹራንስ ጠቀሜታ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በጣም አዝጋሚ ነው፡፡ ተቋማዊ ያልሆነ፣ አንዳንዱ እንደውም ኢንሹራንስም የማይመስል አገልግሎት አለ፡፡ ይኼ አገልግሎቱ ላይ የሚታይ ችግር ነው፡፡ ስለዚህ የምርት ልማትና ምርምር በእጅጉ ያልታየበት ሆኖ መቀጠሉ የኢንዱስትሪ ችግሮች ናቸው፡፡ አሁን የምናየው የውድድር መንፈስ በዓረቦን ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ከፍተኛ የአረቦን ቅናሽ ውድድር አለ፡፡ ይህ ጥቂቶች ገበያውን የሚጫኑበት ባህሪይ (ኦሊጎፖሊ) ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ባለው ገበያ  ውስጥ የዋጋ ጦርነት አለ፡፡ የዋጋ ጦርነት ብቻም ሳይሆን ሌሎች በርካታ የመወዳደሪያ ስልቶች መኖር ነበረባቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ የኢንዱስትሪው የካሳ ክፍያ አስተዳደር እጅግ አሰልቺ ነው፡፡

ሌላው ችግር የሰው ኃይል አጠቃቀሙ ነው፡፡ ኢንሹራንስ ምን እንደሆነ የሚያውቁ አገሮች በነበሩበት ዘመን፣ ኢትዮጵያ የመድን ኢንዱስትሪ ነበራት፡፡ ይሁንና የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዕውቀት ደረጃ አሳሳቢ፣ እንዲያውም እጅግ አሳፋሪ እየሆነ መጥቷል ሊባል ይችላል፡፡ ትልቅ የዕውቀት ችግር አለ፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ በዚህ ኢንዱስትሪ ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ቀዳሚ ከሆነች ዘግይተው ከኋላ በጀመሩ አገሮች በኢንዱስትሪው መቀደሟስ ለምንድን ነው?

አቶ አሰግድ፡- ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለማደግ የሚያስቀምጡት ራዕይ ነው፡፡ የኩባንያዎች ራዕይ ምንድነው? እንደ ሌሎች የቢዝነስ ዘርፎች በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ትርፍ እንደልብ እያገኙ መውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ኢንሹራንስ በዳበረ ካፒታልና ኢንቨስትመንት መታገዝ አለበት፡፡ አንድ የኢንሹራንስ ኩባንያ በቂ ካፒታል ሊኖረው ይገባል፡፡ የሥጋት ቁጥጥሩ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ አገልግሎቱም ዕውቀት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡ ለምን ሊደክም ቻለ ከተባለም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው ቁጭ ተብሎ በበሰለና በሠለጠነ መንገድ ለረዥም ጊዜ ውጤት ሊያመጣ በሚያስችል ደረጃ በሰው ሀብት ልማት ላይ አልተሠራም፡፡

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች መሠረታዊ ለውጥ የሚመጣው በሰበሰቡት ካፒታል ብቻ ሳይሆን፣ ካፒታሉን በሚያንቀሳቅሰው የሰው ጭንቅላት ጭምር ነው፡፡ ኢንሹራንስ ይበልጡኑ በሰው ልጅ ጭንቅላት ላይ የተንጠለጠለ ሥራ ነው፡፡ በባህሪው የማይጨበጥ ስለሆነ፣ ይህንን አገልግሎት በደንበኞች ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ኃይል ማፍራቱ ላይ ብዙ መሠራት አለበት፡፡ ግን አልተሠራም፡፡ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች ላይ የመተካካት ዕቅድ የለም፡፡ ሌላው ለአገሪቷ የሚመጥን ኢንስቲትዩትም የለም፡፡   

ሪፖርተር፡- የሥልጠና ተቋም ማለት ነው?

አቶ አሰግድ፡- አዎን፡፡ የኢንሹራንስ ማሠልጠኛ የለም፡፡ ኢንሹራንስ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ መሰጠት አለበት፡፡ የኢንሹራንስ ማሠልጠኛ ተቋም ያለመኖሩ በኢንዱስትሪው ዕድገት ላይ ተፅዕኖ አሳርፏል፡፡ ከዚህ ቀደም ግን አንድ ተቋም ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥር የነበረው የባንክና የኢንሹራንስ ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ተቋምን ማለትዎ ነው?

አቶ አሰግድ፡- አዎን፡፡ ይህ ማሠልጠኛ ተቋም ወደ ፋይናንስ አካዴሚ እንዲያድግ ተሞክሮ ሕንፃዎችም ተገንበተው ነበር፡፡ አካዴሚው በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የኢንሹራንስ ትምህርት ሊሰጥበት የታሰበ ነበር፡፡ የባንክና የኢንሹራንስ ባለሙያዎችን ለማሠልጠን ያስችላል ተብሎ የታነፀ ነበር፡፡ ግን በመንገድ ቀረ፡፡ ኢንሹራንስና ባንክ ከ50 ዓመታት በላይ ዕድሜ ቢኖራቸውም እንደ አገር ይህንን ዘርፍ የሚደግፍ አንደም ኢንስቲትዩት የለም፡፡ የፋይናንስ ዘርፉ የሚፈልገውን ጥያቄ የሚያሟላ አቅርቦት ያለው ተቋም የለም፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች አያስተምሩም፡፡ የተወሰነ ኮርስ ነው የሚሰጡት፡፡ ስለዚህ ዘርፉን የሚመግብ ብሔራዊ የትምህርት ተቋም የለም፡፡ ከዓመታት በፊት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ማሠልጠኛም ተዘግቷል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበሩ ባለሙያዎች ሥራቸውን ሊያራምዱ የቻሉት በነበረው ማሠልጠኛ በዲፕሎማ ደረጃ የኢንሹራንስ ትምህርት ይሰጥ ስለነበር በዚያ ታግዘው ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- የማሠልጠኛው የትምህርት አሰጣጥ እንዴት ነበር?

አቶ አሰግድ፡- በዚያን ወቅት የነበረው ተቋም በተለያዩ የኢንሹራንስ ምርቶች የታገዘ ትምህርት ይሰጥ ነበር፡፡ በዲፕሎማና በሰርተፍኬት ደረጃ የሚሰጡ የኢንሹራንስ ትምህርቶች ነበሩ፡፡ የመድን ሥራ ፖሊሲዎች ላይ ጥልቅ ሥልጠና የሚሰጥበትም ነበር፡፡ እሱ አሁን የለም፡፡ ሌላው በቀደመው ጊዜ ኩባንያዎች ከሰው ኃይል ብቃት ጋር የሚከተሉት አንድ አሠራር ነበራቸው፡፡ ይኽም ተማሪዎችን ከዩኒቨርሲቲ ይወሰዱና ያሠለጥናሉ፡፡ እንደ ቴሌ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ተቋማት ከዩኒቨርሲቲ የወሰዷቸውን ተማሪዎች በተቋሞቻቸው ለወራት ያሰለጥናሉ፡፡  መድን ድርጅት የተቀበላቸውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢንሹራንስ ትምህርት ዘርፍ ብቻ በየአገልግሎት ዓይነቱ ያሠለጥናቸው ነበር፡፡ እነዚህ ተማሪዎች ተምረው ፈተናውን አልፈው ሥራ ላይ ሥልጠና በመውሰድ ሥራውን እንዲለማመዱ ተደርገው በዚያው መሠረት ወደ ሥራ ይገቡ ነበር፡፡ ጨምሮ በዚያ መንገድ መጥተን እንደገና በተልዕኮና በመሳሰሉት ያገኘነው ትምህርት አሁን ለምንገኝበት ደረጃ አድርሶናል፡፡

ሪፖርተር፡- እንዲህ ያለው የሰው ኃይል ማፍሪያና ማጎልበቻ አሁን ቀርቷል ማለት ነው?

አቶ አሰግድ፡- አዎ እነዚህም ቀርተዋል፡፡ እንዲህ ያሉ ሥልጠናዎች ኢንዱስትሪው ያለበትን ክፍተት በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ ያግዙ ነበር፡፡ ነገር ግን በሰው ኃይል ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሀብት መፍጠር እንደሆነ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ በቅርቡ ግን በብሔራዊ ባንክ በኩል እያንዳንዱ የኡንሹራንስ ኩባንያ ከዓመት በጀቱ ሁለት በመቶውን ለሥልጠናና ልማት እንዲያውል ተደንጎበታል፡፡ ይህ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ኩባንያዎቹ ራሳቸው ይህንን ማድረግ ነበረባቸው፡፡ በኢንዱስትሪው ውስጥ ልዩነት ማምጣት ከፈለጉ ለውጥ የሚያመጡት የሰው ኃይላቸውን በማብቃት ነው፡፡ በአንፃሩ ግን የሰው ኃይሉ አይበረታታም፡፡ ትኩረት አይሰጠውም፡፡ ዓለም ግን እየተቀየረ ነው፡፡ አዳዲስ ዕውቀቶች፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች፣ አዳዲስ አሠራሮች  እየመጡ ነው፡፡ የበፊቶቹ እየወጡ ነው፡፡ እኛ ግን በነበረው እየሔድን ነው፡፡ የሰው ኃይሉ እንዳያድግ እንቅፋት የሆነው ራሱን የቻለ ተቋም በዘርፉ አለመኖሩ ነው፡፡ እዚሁ አጠገባችን እንደ ኬንያ ያሉ እንደ ደቡብ አፍሪካ ያሉ አገሮች ኢንስቲትዩቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ አገሮች በየዩኒቨርሲቲዎቻቸው ውስጥ የባንክና የኢንሹራንስ ትምህርት በዲግሪ ያስተምራሉ፡፡ እኛ አገር ውስጥ ግን ይህ የለም፡፡ የነበረውም እየተዳከመ ሄዷል፡፡

ሪፖርተር፡- ከገለጻዎ ለመረዳት እንደሚቻለው የሰው ኃይል ልማቱ ላይ አለመሠራቱ ክፍተት ፈጥሯል፡፡ ስለዚህ ለኢንዱስትሪው መንቀራፈፍ በተለይ በሞተር ኢንሹራንስ ላይ ተንጠላጥሎ ለመቆየቱ ምክንያት በሰው ኃይል ማብቃት ላይ አለመሠራቱ ሊሆን ይችላል ማለት ነው?

አቶ አሰግድ፡- በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በብዙዎቹ አገሮች ኩባንያዎች ውስጥ ትኩረት የሚሰጠው ቶሎ ዓረቦን መሰብሰብ የሚቻልባቸው አገልግሎቶች ላይ ነው፡፡ በቀላሉ ገንዘብ የምታገኝበትና የአንድ ዓመት ፖሊሲ በብዛት የምታገኝበት የሞተር ኢንሹራንስ ነው፡፡ 90 በመቶው በሞተር ኢንሹራንስ የሚንቀሳቀስ ገበያ ነው፡፡ ኢንሹራንስ ማለት  የሞተር ኢንሹራንስ ብቻ የሚመስላቸው አሉ፡፡ ኢንሹራንስ እሱ አይደለም፡፡ እስከ ጠለፋ ዋስትና ድረስ ይጓዛል፡፡ ሞተር ኢንሹራንስ የገነነው ለኅብረተሰቡ የተገለጸበት መንገድ ችግር ስላለበት ነው፡፡ ጥቂት ኩባንያዎች ናቸው የሠራተኛ ጉዳት ሽፋን ሲሰጡ የነበሩት፡፡ በአገራችን ግንዛቤ ሀብት የማፍራት አንዱ መገለጫ መኪና መግዛት ነው፡፡ መኪና አደጋ ያደርሳል፡፡ የቃጠሎ ኢንሹራንስ ከመኪና እኩል ሊሸጥ ይችል ነበር፡፡ ስለዚህ ከዕውቀት ማጣት ሳቢያም ከፍተኛ የሆነ የኢንሹራንስ ምርት ሥራ ውስጥ አልገባንም፡፡ የምናያቸውም ቢሆንም ያኔ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የነበሩ እንደ ኃይል ማመንጫ ላሉት ሽፋን የሚሰጣቸው በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ነበር፡፡ ይህም የሆነው ሞኖፖል ይሠራ ስለነበር ነው፡፡ በንጉሡ ጊዜ ግን ከሞተር ኢንሹራንስ ውጭ የተለያዩ ፖሊሲዎች ይሸጡ ነበር፡፡

ሪፖርተር፡- አሁን ባሉት የኢንሹራስ ኩባንያዎች የማይተገበሩ ከሚባሉት ውስጥ ለምሳሌ የሚጠቅሱት አለ?

አቶ አሰግድ፡- አዎን፡፡ ለምሳሌ የቤት ፖኬጅ ፖሊሲ ይሸጥ ነበር፡፡ የቃጠሎ ኢንሹራንስ ፖሊሲ ይሸጥ ነበር፡፡ ለቤት ንብረቶችህ ዋስትና የሚሰጡ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎች ይሸጡ ነበር፡፡ እነዚህ ፖሊሲዎች የነጮቹ ነበሩ፡፡ የንጉሡ ጊዜ የኢንሹራንስ ፖሊሲዎችን እንደናሙና አውጥቶ ማየት ይቻላል፡፡ አንዳንድ አገሮች ኢንሹራንስ ምን እንደሆነ በማያውቁበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የኢንሹራንስ ፖሊሲ ይሸጥ ነበር፡፡ ሌላው ኢንሹራንስ በጣም ፈጣን ለውጥ ሳይኖረው እንዳይቀጥል ያደረገው የኢንሹራንስ ትምህርት የወሰዱ ሰዎች ዘርፉን አለማስተዋወቃቸው ነው፡፡ የሚሰጡት አስተያየት አይደመጥም፡፡

ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ ውስጥ 17 የመድን ኩባንያዎች አሉ፡፡ ከአብዛኛዎቹ ኩባንያዎች እንደሚደመጠው የኩባንያዎቹ የዓረቦን መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደመጣ ነው፡፡ ባለፉት አሥር ዓመታት እስከ ሦስት እጥፍ የቀነሱ አሉ፡፡ ይህ የዓረቦን ቅናሽ ምን ያመለክታል?

አቶ አሰግድ፡- ሁለት ነገር አለ፡፡ የኢንሹራንስ መሠረታዊ ዓረቦን የምንለው አለ፡፡ ይኼ ለዓመታት ተሠርቶ የሚመጣ ነው፡፡ ይህ ግን የማይለወጥ መሆን የለበትም፡፡ እዚህ ላይ ክርክሩና ዕውቀቱ ሁለት ነው፡፡ አንድ ቦታ ላይ የቆመ መሆን የለበትም፡፡ ያለማቋረጥ መውረድም የለበትም፡፡ መጠናት አለበት፡፡ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ማኅበር በዚህ ዙሪያ ባለሙያ ቀጥሮ ጥናት እያስጠና መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ጥናቱ አገር ውስጥ ያሉትን የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የዓረቦን ሁኔታ የዳሰሰ ሊሆን ይችላል፡፡ ዝቅተኛ የዓረቦን ዋጋ ሊቀመጥላቸው የሚገባቸው የኢንሹራንስ ዘርፎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ሥጋቱን ሊመጥን የሚችል ዓረቦን ያስፈልጋል፡፡ መተንተንና መታወቅ ያለበት ነገር ሥጋቱን ሊመጥን የሚችል ዓረቦን እንዴት ነው የሚንቀሳቀሰው የሚለው ነው፡፡ አንድ ደንበኛ ኢንሹራንስ ገብቶ እሱ ያስመዘገበው አደጋ ስለሚያደርሰው ጉዳት አይደለም፡፡ ኢንሹራንስ አንድ ለአንድ አይደለም፡፡ በአንድ ደንበኛ ብቻ የሚተዳደር የኢንሹራንስ ኩባንያ የለም፡፡ ዓረቦኑ ወደ ስብስብ የመጡ ደንበኞችን በሙሉ አስተናግዶ ከስብስቡ ውስጥ በጣም ጥቂት ዕድለኛ ያልሆኑት የሚያስመዘግቡትን የአደጋ ወጪና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ሸፍኖ አትራፊ መሆን አለበት፡፡

ስለዚህ ዓረቦኑ ለአደጋው ሥጋት ተመጣጣኝ መሆን አለበት፡፡ በገበያ ተፈላጊም መሆን አለበት፡፡ ለሥጋቱ ተመጣጣኝ ይሆናል ብለህ የዓረቦኑን ዋጋ ብትሰቅለው ማንም አይገዛህም፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለው ደንበኛ ስለ ኢንሹራንስ ግንዛቤ ያለው ነው፡፡ አሁን ባለው ቴክኖሎጂ ባነሰ ዋጋ ሰፋ ያለ ጥቅም ማግኘት የሚፈልግ ነው፡፡ ደንበኛው ይኼ አመለካከት አለው፡፡ ስለዚህ ስታጠና ሊያዋጣህ የሚችለውን ዓረቦን መስጠት አለብህ፡፡ ሊያዋጣ ይችላል ያልከውን የዓረቦን ዋጋ ስታስቀምጥ ውድድርም አለብህ፡፡ የተለያዩ ኩባንያዎች የተለያየ መነሻ አያላቸው፡፡ አንዳንዱ የራሱ ሕንፃ አለው፡፡ አንዳንዱ ተከራይቶ ነው የሚሠራው፡፡ የአንዳንዱ የሰው ኃይልና የሚከፍለው የደመወዝ መጠን እና የሚጠቀምበት ቴክኖሎጂም ይለያያል፡፡ እነዚህን ወጪዎች አስልተህ የዓረቦን ዋጋህን ታሰላለህ፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ እንዴት ነው የሚብራራው?

አቶ አሰግድ፡- ሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋ ስትሄድ ዓረቦን ወረደ ይላሉ፡፡ ይኼ ስህተት ነው፡፡ ኢንሹራንስ ዓረቦንም ወርዶ ብዙ ተሠርቶ ወጪህን ተቆጣጥረህ አሸናፊ የምትሆንበት የአሠራር ሥርዓት አለው፡፡ ውድድሩ የገበያ ባህሪይ ነው፡፡ የኦሊጎፖሊ ገበያ ላይ እንደዚህ ዓይነት ጦርነት ይኖራል፡፡ ነገር ግን እኔ እንደማምነው አረቦን መሆን ያለበት ሥጋቱን የሚመጥን መሆን እንዳለበት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ባለፉት አሥር ዓመታት እየወረደ የመጣው የዓረቦን መጠን አሁን በሚታየው መጠንም ወርዶ እየተሠራበት ነው፡፡ ኩባንያዎቹም አትራፊ ናቸው፡፡ ቅናሹ እየሰፋ መምጣቱ ግን ለኢንዱስትሪው አደጋ ሆኗል እየተባለ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ብሔራዊ ባንክም ደርሷል፡፡ ሥጋቱ የብዙዎች የሆነው ለምንድነው? ያልተገባ ዋጋ እየተሰጠ ነው የሚባለውስ ለምንድነው?

አቶ አሰግድ፡- ሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያ አንድ ዓይነት ዓረቦን ሊኖረው አይገባም፡፡ ውድድር መኖር አለበት፡፡ የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን የበለጠ እያከሰራቸው ያለው ሁለተኛውን ክንፍ የኪሳራ ክፍያ ሥርዓታቸውን መርሳታቸው ነው፡፡ የዋጋ ንረት አለ፡፡ ዓረቦኑ ግን ከዋጋ ንረቱ አኳያ አልተስተካከለም፡፡ ብዙ አደጋ ግን እየደረሰ ብዙ ካሳም እየተከፈለ ነው ፡፡ ይኼ ነው ትልቁ ነጥብ እንጂ የሥር መነሻው ተመን አይደለም፡፡ ተመኑን እንዲህ አድርግልን ብሎ ወደ ብሔራዊ ባንክ መሄድ ተገቢ አይደለም፡፡ ነፃ የገበያ ሥርዓት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በነፃ ገበያ ሥርዓት መመራት እንዳለበት ግልጽ ነው፡፡ ብሔራዊ ባንክም የዓረቦን ዋጋውን ተመን ሊያስቀምጥ ይችላል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ አሁን እየታየ ያለው ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱ ግን አደጋ አለው የሚለው ጎልቶ እየተሰማ ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡

አቶ አሰግድ፡- አዎ ብሔራዊ ባንክ ዋጋ ይተክላል ብዬ አላስብም፡፡ አይጠበቅበትም፡፡ ኩባንያዎች ግን አሸናፊ ሆነው ለመውጣት የራሳቸውን ሥራ መሥራት አለባቸው፡፡ ሌላ አካል ሠርቶላቸው አይደለም አትራፊ የሚሆኑት፡፡ የራሳቸውን ዓረቦን ቀርጸው የሚሸጡ ከሆነ ወጪያቸውን ተቆጣጥረው አሸንፈው ይወጣሉ፡፡ በነገራችን ላይ አሜሪካን ፕሮግሬሲቭ የሚባል የኢንሹራንስ ኩባንያ አለ፡፡ ይህ ኩባንያ ሞተር ኢንሹራንስ ላይ ብቻ ነው የሚሠራው፡፡ በጣም አትራፊ ኩባንያ ነው፡፡ በየጊዜው ዓረቦኑን ያስተካክላል፡፡ የዋጋ ንረት ሲከሰት ለዚያም ማስተካከያ አለው፡፡ ለደንበኞቹም ቅናሽ የሚያደርገበት አሠራር አለው፡፡ የዓረቦን ዋጋው መውረዱን ብቻ ነው ብዙዎቹ እያወሩ ያሉት፡፡ እኔ የምስማማበት ግን የካሳ ክፍያ ሒደታችን የተባባሰ በመሆኑ የበለጠ እየወረደ ያለውን ዓረቦን እንዲባባስ ማድረጉ ላይ ነው፡፡ በፍጥነት የካሳ ክፍያ ላይ ብንሠራ በፍጥነት የመለዋወጫ ዋጋቸው ሳይንር የመካስ ዕድል ይኖረናል፡፡ አንድ መኪና አደጋ ቢደርስበት በወር ውስጥ ብጠግን አሁን የምጠግንበት ዋጋና ከወር በኋላ የምጠግንበት ዋጋ ይለያያል፡፡ ስለዚህ የካሳ ክፍያውን ፈጣን በማድረግ አሁን ባለውም ዓረቦን ቢሆን ከሙስና በፀዳ አሠራር አትራፊ ይሆናሉ፡፡ እያከሰራቸው ያለውን ይኸኛውን ጉዳይ ረስተውታል፡፡ ይኼ የተረጋገጠ  ነገር ነው፡፡   

ሪፖርተር፡- በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ ከሚጠቀሱት ተቋማት በተለይ ከባንኮች አንፃር ሲታይ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች አካሄድ ዕድገቱ አዝጋሚ ነው፡፡ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ያሳዩት ውጤት ከባንኮች ጋር ሲመዛዘን በፍፁም የሚገናኝ አይደለም፡፡ የዓረቦን ዋጋው እየወረደ መምጣቱም ኢንዱስትሪውን ሊጥለው ይችላል ይላሉ፡፡ በእርግጥ የዓረቦን እየወረደ መምጣት ምክንያት በአሁኑ ወቅት ሥጋት አለ?

አቶ አሰግድ፡- የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውድድር ዓረቦንን በመቀነስ ብቻ መሆኑ ወይም አንድ ነገር ላይ ያጠነጠነ መሆኑ ራሳቸውን ወደ መብላት ይወስዳቸዋል፡፡ ኢንዱስትሪው ተጠፍንጎ የተያዘው በሌሎችም በርካታ ችግሮች ጭምር ነው፡፡ ዓረቦን አንደኛው ማሳያ ነው፡፡ ያልተገባ የካሳ ክፍያም እየከፈሉ ነው፡፡ በኢንሹራንስ ካሳ ክፍያ መክሰርም ማትረፍም አይቻልም፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ ምን ማለት እንደሆነ ቢገልጹት?

አቶ አሰግድ፡- የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ዋና ዓላማ አንድ ደንበኛ አደጋ ሳያደርስ ወደ ነበረበት ቦታ መወሰድ ነው፡፡ ነገር ግን እየወሰዱት አይደለም፡፡ የ1990 ሞዴል መኪና ዘንድሮ አደጋ ቢደርስበት እናስጠግናለን፡፡ ያገለገለ መኪና ነው፡፡ ዕድሜው የገፋ መኪና ነው፡፡ አዲስ ዕቃ ከገበያ አምጥተን ነው የምንቀይረው፡፡ የአሮጌውን የዕርጅና ተቀናሽ ከአዲሱ ላይ ቀንሰን ነው በጥሬ ገንዘብ የምንከፍለው፡፡ እንደፈለገን ብንቀንስም በዚህ አሠራር ደንበኞችን አትራፊ እናደርጋለን ማለት ነው፡፡ ዓረቦኑ ለዋጋ ንረት ማስተካከያ የለውም፡፡ ካሳ ክፍያው ግን ሁሌም በንረት ውስጥ ነው፡፡ የአገልግሎትና የዕቃ ዋጋ ግን እየጨመረ ነው፡፡ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ይህንን ማመጣጠን አለባቸው፡፡ የሚያመጣጥኑትም ሳይቀንሱ ብዙ በመሥራት የካሳ ክፍያቸውን ቢያስተካክሉ፣ አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዘው ቢመጡ የተሻለ አማራጭ ይፈጥራሉ፡፡ እኔ በጣም እየገረመኝ ያለው በዓረቦን መውረድ ላይ ብቻ ያጠነጠኑ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ በጣም ስህተት ነው፡፡  ብዙ ስትሠራ ታገኛለህ፡፡ አሁን ያለው እኮ የዛሬ 40 ዓመት በኢትዮጵያ መድን ድርጅት የነበረ መሠረታዊ ዋጋ ነው፡፡ አሁን እኮ እየተቀነሰ ያለውም ከዚህ ነው፡፡ ስለዚህ ኩባንያዎች ራሳቸውን ወደ መብላት እየሄዱ ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ የሕይወት ኢንሹራንስ ሽፋን መጠኑ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ አምስት በመቶ አካባቢ ነው፡፡ በሌላው ዓለም ግን ከጠቅላላው የኢንሹራንስ ሽፋን አብላጫውን እጅ የያዘው የሕይወት ኢንሹራንስ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ለምን ተለየ? አምስት በመቶ ላይ ብቻ ለምን ቆመ?

አቶ አሰግድ፡- ሌላው ዓለም ይህንን ገንዘብ በተለያየ መንገድ ኢንቨስት አድርጎ ተጨማሪ ትርፍ የሚያገኝት ዕድል አለው፡፡ እዚህ አገር ግን የለም፡፡ ለኢንቨስትመንቱ ምቹ የሆኑ የፖሊሲ ማዕቀፎች የሉም፡፡ ስለዚህ በሕይወት ኢንሹራንስ የሰበሰብከውን ዓረቦን ልታደርግ የምትችለው ነገር በጊዜ ገደብ ታስቀምጣለህ፡፡ ከዚህ የምታገኘው የወለድ ጥቅም ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ላይ ከባንክ ከምታገኘው ወለድ ውጭ በዚያ ዓረቦን ልትጠቀምበት የምትችልበት ዕድል የለም፡፡ ስለዚህ አላደገም፡፡

ሪፖርተር፡- ለሕይወት ኢንሹራንስ እጅግ ዝቅተኛ ሽፋን ምክንያት ይህ ብቻ ነው?

አቶ አሰግድ፡- ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ካፒታሉም እያለ አላደገም ለማለት ነው፡፡ ሌላው ችግር ደግሞ ከፍተኛ የግንዛቤ ክፍተት ነው፡፡ በዚህ ዙሪያ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሠሩት ነገር የለም፡፡ የሕይወት ኢንሹራንስ ፕሮጀክቶችም ልማዳዊ ናቸው፡፡ የዛሬ 50 ዓመት የነበሩ የሕይወት ኢንሹራንስ ፕሮጀክቶች ናቸው ዛሬም እየተሸጡ ያሉት፡፡ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ሁሉም የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሚሸጡት እነዚህኑ ነው፡፡ ተለዋዋጭነት ይጎለዋል፡፡ ለደንበኞች ምቹ ፖሊሲዎች የለም፡፡

ሪፖርተር፡- በዚህ ዘርፍ ኩባንያዎቹ መሸጥ የሚችሏቸው የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲዎች ወይም አገልግሎቶች ካሉ?

አቶ አሰግድ፡- ለምሳሌ በኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርት ቤቶች ተስፋፍተዋል፡፡ ልጆች ትምህርት ቤት ነው የሚውሉት፡፡ ነገር ግን ለትምህርት ቤት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ፖሊሲ የለም፡፡ በስፖርቱም ዘርፍ ስንሄድ ስፖርቱ እየሰፋ ነው፡፡ የአንድ ስፖርተኛ ዋጋ በሚሊዮን ብር ደረጃ እያደገ ነው፡፡ ይህንን የሚሸፍን የኢንሹራንስ ፖሊሲ የለም፡፡ የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ከሰው ሕይወት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሕይወትን ከእምነት ጋር በማያያዝ ለረዥም ጊዜ የቆየ ማኅበረሰብ ስለሆነ፣ ይህንን አመለካከት ለመቀየር ኢንሹራንስ ኩባንያዎች የሠሩት ነገር የለም፡፡ ግንዛቤ የማስጨበጡ ሥራ በተለመዱ ነገሮች ላይ ያጠነጠነ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- መፍትሔው ታዲያ ምንድን ነው?

አቶ አሰግድ፡- የኢንሹንስ ኩባንያ እንዲያድግ አሁን ዓለም የደረሰበትን የኢንሹራንስ አስተሳሰብ የተከተለ መሥረታዊ ለውጥ ያስፈልገዋል፡፡ ሥር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል፡፡ ለውጡ ጥገናዊ ለውጥ ሳይሆን፣ ሥር ነቀል ለውጥ መሆን ይኖርበታል፡፡ ዓረቦን ላይ በመሥራት ብቻ ዘርፉን የትም አያደደርሰውም፡፡ ዓረቦንን በማስተካከል የትም መድረስ አይቻልም፡፡ ዓረቦን አንድ ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ ቆሼ ላይ ለደረሰው አደጋ አንድም ኩባንያ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይህ የሚያሳየው ዘርፉ እዚህ ድረስ የወረደ መሆኑን ነው፡፡ ለዚህ ነው ለውጥ የሚያስፈልገው፡፡ ኢንዱስትሪው በዕውቀት ላይ የተመሠረተ አመራር ሊኖረው ይገባል፡፡ ኢንሹራንስ ዕውቀት ነው፡፡ በዘልማድ ወይም በቆይታ የሚመራ አይደለም፡፡ በኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ መታጠቅ አለበት፡፡ ይህ ከሆነ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ 

ሪፖርተር፡- እንዲህ ያለውን ለውጥ ለማምጣት ኩባንያዎች በራሳቸው መንገድ መሥራታቸው እንዳለ ሁኖ ኢንዱትሪውን ለመለወጥ እንደ ብሔራዊ ባንክ ያሉ የሚመለከታቸው ተቋማት ሚና ምን መሆን አለበት?

አቶ አሰግድ፡- ኢትዮጵያ አድጋለች፡፡ ትልቅ ነች፡፡ ባንኮች በቢሊዮን ደረጃ እያተረፉ ነው ብለናል፡፡ እዚህ ደረጃ የደረሱት ስለሠሩ ነው፡፡ ኢኮኖሚው ሲያድግ፣ ዕድገቱ ባለበት ቦታ ሁሉ ስለሄዱ ነው፡፡ ይህም ቢሆን መሠረታዊ የሆነ ችግር አለው፡፡ ባንክ ውስጥ ያለውን ገንዘብ ሰዎች ካልተበደሩት ገቢ አይኖራቸውም፡፡ የባንኮች ዋና ገቢ አበድረው ከሚያገኙት የወለድ ገቢ የሚገኝ ነው፡፡ ኢንሹራንሱ ጋር ስንመጣ ይህንን ሊያሠራ የሚችል በኢትዮጵያ ስፋት ልክ የተዳረሰ አይደለም፡፡ ብሔራዊ ባንክ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አስቀምጧል፡፡ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ኢንቨሰት የሚያደርጉበት ዕድል የለም፡፡

ሪፖርተር፡- የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከካፒታላቸው ከ15 እስከ 20 በመቶ ለተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ላይ እንዲያውሉ ብሔራዊ ባንክ ይፈቀዳል እኮ፡፡

አቶ አሰግድ፡- እሱ አዎን አለ፡፡ ለኢንቨስትመንት ባዋሉት መጠን ሲታይ ግን ትንሽ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የብሔራዊ ባንክ መመርያ ትክክል ነው፡፡ በዚህ ደረጃ መገደቡም ትክክል የሚሆንበት ምክንያት ይኖራል፡፡ የደንበኛን የፖሊሲ ገንዘብ ሰብስበህ እንደፈለክ ማድረግ አይገባም፡፡ መቆጣጠሩ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ተቀይራለች፡፡ ሜዳው ተቀይሯል፡፡ ሀብት እየተፈጠረ ስለሆነ የአደጋው ሥጋት ተቀይሯል፡፡ ስለዚህ ኢንሹራንስ ኩባንያዎችን ከማሠር ይልቅ ፈታ ያለ አሠራር መኖር፣ የኢንቨስትመንት አቅማቸውም ሰፋ ማለት አለበት፡፡ በተለያዩ የአጭር ጊዜ ኢንቨስመንቶች ውስጥ እንዲገቡ መፈቀድ አለበት፡፡ ኩባንያዎች የተለያዩ ኢንቨስትመንት ሥራ ውስጥ ገብተው አትራፊ ሆነው የሚወጡበት ዕድል ቢፈጠር፣ በተለያዩ አክሲዮን ኩባንያዎች ውስጥ አክሲዮን ገዝተው ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ በንጉሡ ጊዜ የባንክ ኢንሹራንስ የሚባል ነገር ነበር፡፡ ገንዘብ ይቀበላሉ፡፡ ለተበደረው ሰው የኢንሹራንስ ሽፋን ይሰጣሉ፡፡ ይህ አሠራር እኮ ኢትዮጵያ ውስጥ ነበር፡፡ ደርግ ሲገባ ግን ቀረ፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራሮች መፈቀድ አለባቸው፡፡ ሌላው ዘርፉ እንዲያድግ ተቆጣጣሪው አካል መቀየጥ አለበት፡፡ በተቆጣጣሪው አካል ውስጥ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ያሉበት ክፍል ያስፈልጋል፡፡ አሁን ያለው ካፒታል ግን የትም አያደርሳቸውም፡፡ የአገራችንን የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከኬንያ ኩባንያዎች ጋ ሲወዳደሩ በጣም አነስተኛ ናቸው፡፡ ስለዚህ የካፒታል መጠናቸው መቀየር አለበት፡፡ በዚህ ላይ ብሔራዊ ባንክ ይሠራል ብዬ አስባለሁ፡፡

 

Standard (Image)

ንብ ኢንሹራንስ ያወጣው የሕንፃ ግንባታ ጨረታ ክፍተት እንዳለበት ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይፋ አደረገ

$
0
0

የንብ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታን ለማካሄድ የተጀመረው የመሠረት ቁፋሮ ለማካሄድ የወጣውን ጨረታ በማገድ ሒደቱን ሲመረምር የቆየው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የጨረታ ሒደቱ ክፍት ታይቶበታል አለ፡፡

ግንቦት 3 ቀን 2009 ዓ.ም. ሊካሄድ የነበረው የመሠረት ቁፋሮ የጨረታ ሥነ ሥርዓትን በማገድ አስቸኳይ የመከላከል ምርመራ ሲያካሂድ የቆየው ኮሚሽኑ፣ የደረሰበትን የጥናት ውጤትም ለኢንሹራንስ ኩባንያው አስታውቋል፡፡ በምርመራው መሠረት ኮሚሽኑ ካሰባሰባቸው መረጃዎች በመነሳት የጨረታው ሒደት ክፍተቶች እንደነበሩት መረዳቱን ኮሚሽኑ የጻፈው ደብዳቤ ይጠቅሳል፡፡

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ‹‹በጥናቱ ከተሰበሰቡት መረጃዎች አንፃር ሲታይ በሒደቱ ላይ የተለያዩ ክፍተቶች መኖራቸውን ለመረዳት ተችሏል፤›› በማለት በጥናት ውጤቱ የተገኘውን ውጤት አስፍሯል፡፡

ተቋማት ልዩ ሁኔታዎች እስካልገጠሙዋቸው ድረስ ግዥዎችን በርካታ ብቃት ያላቸው አቅራቢዎችን ሊጋብዝ በሚችል መልኩ ተቀርጾ በሚከናወን ግልጽ የገበያ ውድድር ላይ ማከናወናቸው እንደሆነ ደብዳቤው አስፍሯል፡፡

ንብ ኢንሹራንስ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃውን ለማስገንባት ሲነሳ፣ የተከተለው የግዥ ሒደት የግንባታ ሥራውን ሊያከናውኑ የሚችሉ በርካታ ተቋማት ቢኖሩም፣ ውድድርን በሚገድብ አኳኋን የተወሰኑ ተጫራቾች እንዲያሳተፉ የተደረገበት የጨረታ ሥርዓት ላይ ክፍተት ማግኘቱን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በዚህ የጨረታ ሒደት እንደ ክፍተት የተቆጠረው ሌላኛው ተግባር፣ የሕንፃ ግንባታ ጨረታውን ወይም ግዥውን በጥቅል ከማድረግ ይልቅ በመከፋፈል እንዲሠራ የተደረገበት አሠራር ነው፡፡ በጥቅል ሳይሆን በመከፋፈል እንዲሠራ የተወሰነበት አግባብም በአሳማኝና አስገዳጅ ምክንያት እንዳልተደገፈ የኮሚሽኑ ደበዳቤ ጠቅሷል፡፡ ይህ በመሆኑም የተቋሙን የዋጋና የጥራት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ካለማስቻሉ በተጨማሪ፣ ግልጽ አሠራርን በማጥፋት ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ችግሮች የሚዳርግ አካሄድ ተከትሏል በማለት ይገልጻል፡፡  

የፀረ ሙስና ኮሚሽን የምርመራ ውጤት፣ የግንባታ አማካሪ ድርጅት ቅጥርን በተመለከተ የታዩ ችግሮችንም አመላክቷል፡፡ በኮሚሽኑ ድምዳሜ መሠረት፣ ‹‹የአማካሪ ቅጥር ሁኔታ ከሚከናወነው የግንባታ ሥራ ጋር አማካሪው የነበረው የወቅቱ ብቃት ያልተገናዘበ እንደነበር ለማየት ተችሏል፤›› ብሏል፡፡ ይህ በመሆኑም ንብ ኢንሹራንስ ግዥውን ያከናወነበት መመርያ በውስጡ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉበት መገንዘቡን ኮሚሽኑ ለኩባንያው በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ ከጨረታ ሒደቱ ጋር በተያያዘ በምርመራ ካጣራቸው ጉዳዮች ባሻገር ንብ ኢንሹራንስ ከዚህ በኋላ ማካሄድ ይገባዋል ያላቸውን ነጥቦችም በምክረ ሐሳብ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም በአክሲዮን ኩባንያው የሚካሄዱ ግዥዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማከናወንና ግልጽነት የሰፈነበት አሠራር ከማስፈን አኳያ፣ ኢንሹራንስ ኩባንያው አሳታፊ የግልጽ ጨረታ ግዥ ዘዴን የመጀመሪያ አማራጩ አድርጎ መፈጸሙ እንደሚገባው ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡  

ከዚህም ባሻገር ወደፊት በሚከናወኑ ግዥዎች ተጫራቾች ለሥራው ያላቸውን ተመጣጣኝ የብቃት ደረጃ በመመዘን ማሳተፉ ትኩረት እንዲሰጥበት የሚያሳስበው የኮሚሽኑ ደብዳቤ፣ የግዥ መመሪያውን በማማሻል ግልጽነት የተላበሰ ሥርዓት በኩባንያው ውስጥ እንዲዘረጋ የማድረግ ግዴታ በኩባንያው ላይ መጣሉንም ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን የኩባንያው የጨረታ ግዥ በትክክል እንዲከናወን ለማድረግ ያግዛሉ ያላቸውን ሦስት ነጥቦችም አስቀምጧል፡፡ ይህም ግልጽ የገበያ ውድድር ላይ ተመሥርተው የሚደረጉ ግዥዎች ተቋማት ልዩ ሁኔታዎች እስካላጋጠሟቸው ድረስ ግዥዎችን ብቃት ያላቸው አቅራቢዎችን ያለገደብ ሊጋብዝ የሚችል አሠራር ሊተገበር እንደሚገባም አሳስበሷል፡፡ ግልጽነት የተላበሰ የገበያ ውድድር፣ የተሻለ የዋጋና የጥራት ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካሄድ ስለሚፈጠር ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ተጠቃሚነት እንደሚያመጣ በመጥቀስም ኮሚሽኑ ምክሩን ለግሷል፡፡

እንደኮሚሽኑ ማብራሪያ ከሆነ፣ ግልጽ ጨረታ ማለት ያልተገቡ ገደቦች የማይደረጉበት፣ በገበያ ውድድር ላይ በተመሠረተ ግዥ ዝቅተኛ መመዘኛውን የሚያሟሉ በርካታ ተወዳዳሪዎችን የሚጋብዝ አሠራር ነው፡፡ በመሆኑም ይህ አሠራር በግንባታው ዘርፍ ውስጥ በሚገኙ ተዋናዮች መካከልም ሆነ በተወሰኑ ተጫራቾች እርስ በርስ መመሳጠር ሊፈጠር የሚችል የኪራይ ሰብሳቢነት ችግርን እንደሚቀርፍ አስፍሯል፡፡ ባልተበጣጠሰ መንገድ በግልጽ ውድድር ላይ ተመሥርቶ የሚከናወን ግዥ፣ በአግባቡ እስከተከናወነ ድረስ ለሙስናና ለኪራይ ሰብሳቢነት የመጋለጥ አደጋው አነስተኛ መሆኑ ከሌሎች የግዥ ዘዴዎች ተመራጭ ያደርገዋል በማለት፣ በተከፋፈለ አሠራር የሚካሄድ ግንባታ ሊኖረው የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖም አብራርቷል፡፡  

ይሁንና አስገዳጅ ሁኔታዎች ሲከሰቱ ግን ለድርድር በማቅረብ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚረዱ የግዥ አማራጮችን መጠቀም የግድ የሚሆንበት አጋጣሚ እንደሚኖር ኮሚሽኑ አስታውሶ፣ የንብ ኢንሹራንስ የጨረታ ሒደት ግን አስገዳጅ ሁኔታዎች በሌሉበት ጊዜ የተከተለው አካሄድ በመሆኑ ክፍተቶች አሉበት ብሏል፡፡

ፀረ ሙስና ኮሚሽን የቅድመ መከላከል ምርመራ በማካሄድ የደረሰበትን ውጤት ያሳወቀበት ምክንያት፣ ንብ ኢንሹራንስ የሕንፃ ግንባታውን ለሁለት በመክፈል በተናጠል ለመገንባት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ያልተገባ እንደሆነ የሚጠቁም መረጃ ማግኘቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ኮሚሽኑ የደረሰውን መረጃ በመያዝ አጠቃላይ የጨረታ ሒደቱን ለመገምገም አስቸኳይ የመከላከል ጥናት አካሂዷል፡፡

ንብ ኢንሹራንስ የዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃውን ለሁለት ከፍሎ ለማሠራት መፈለጉና በመጀመሪያ ምዕራፍም ቁፋሮ ለማካሄድ ያወጣው ጨረታ፣ ሥራውን መሥራት የሚችሉ ተቋራጮች እንዳይሳተፉ የሚያደርግ ጨረታ አውጥቷል የሚል ጥቆማ ለኮሚሽኑ መድረሱ ለምርምራው መንስዔ ከሆኑት ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡

የቁፋሮውንና የሕንፃ ሥራዎቹን ለየብቻ ለማካሄድ ማሳቡ ኩባንያውን ለተጋነነ ወጪ እንደሚያደርገው ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የኩባንያው የጨረታ ሒደት ላይ እንደ ችግር የታየው ለሕንፃ ሌላኛው ነጥብ፣ የተመረጠው አማካሪ ድርጅት በወቅቱ በነበረው መመዘኛ መሠረት መሥፈርቱን አያሟላም የሚል አቤቱታ መቅረቡ ጭምር ነበር፡፡  

የንብ ኢንሹራንስ ኃላፊዎች ግን ጨረታውን ለሁለት ከፍሎ ማውጣቱ፣ በተለይም የቁፋሮውን ሥራ የሚመለከታቸውን ኩባንያዎች ብቻ እንዲሳተፉበት ማድረጉ ተገቢና ትክክል ብለው በማመናቸው የተደረገ መሆኑን መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ በተለይ የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ዙፋን አበበ በዚህ ውሳኔ የፀና አቋም እንዳላቸው መግለጻቸው አይዘነጋም፡፡ በቅርቡ የኩባንያው ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች ባሳተፉበት ስብሰባም ይኸው የሕንፃ ግንባታ ጉዳይ ተነስቶ፣ የሕንፃ ግንባታው ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት እንዲከናወን መስማማታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ኮሚሽኑ የደረሰበትን ድምዳሜ በደብዳቤ ካሳወቀ በኋላ የንብ ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ተሰብስቦ ኮሚሽኑ በሰጠው ምክረ ሐሳብ ላይ እንደተወያየ ለማወቅ ተችሏል፡፡

እንደ ሪፖርተር ምንጮች ከሆነ ግን በኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት ጨረታውን ማካሄድ ቦርዱን በሐሳብ የከፋፈለ ነበር፡፡ በተለይ የማኔጅመንት አካላትና የተወሰነ የቦርድ አባላት በኮሚሽኑ ውጤት ባለመደሰታቸው ለደብዳቤው ምላሽ ይሰጥ የሚል ሐሳብ ነበራቸው፡፡ ሆኖም ኩባንያው የሕንፃ ግንባታውን እንደ ቀድሞ ነጣጠሎ ያካሂድ ወይም ጨረታው አጠቃላይ የግንባታ ሥራውን ያጠቃልል በሚለው ጉዳይ ላይ ቦርዱ የመጨረሻ ውሳኔውን እንደሚያስተላልፍ እየተጠበቀ ነው፡፡

ንብ ኢንሹራንስ የዋና መሥሪያ ቤቱን ሕንፃ ለመገንባት ያቀደው በቦሌ መንገድ (ጆሞ ኬንያታ ጎዳና) ከሜጋ ሕንፃ አጠገብ ከግለሰቦች በገዛው 1,400 ካሬ ሜትር ቦታ ሲሆን፣ ቦታው ላይ ሊገነባ የታቀደውም 18 ወለሎች ያሉት ሕንፃ ነው፡፡ ለግንባታ የሚሆነውን ቦታ የገዛውም ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት እንደሆነ ታውቋል፡፡    

Standard (Image)

የኢትዮጵያ ተሞክሮዎች የታዩበት የአፍሪካ ማኑፋክቸሪንግ ጉባዔ

$
0
0

መነሻውን በሩዋንዳ ኪጋሊ ያደረገው የአፍሪካ ኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕከል ዘንድሮ ሁለተኛውን ጉባዔውን በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡ በዚህም በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በመገምገም ያሉትን ለውጦችና ተግዳሮቶች የሚቃኙ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡

ከግንቦት 28 እስከ ግንቦት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በሒልተን ሆቴል በተካሄደው ጉባዔ ከ30 አገሮች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ የጉባዔው የክብር እንግዳ በሚንስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ውጤታማነት ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ ናቸው፡፡

ዶ/ር አርከበ የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍን፣ የኢንዱስትሪ መሠረተ ልማት ሥራዎችን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትንና የመሳሰሉትን ነጥቦች ከኢትዮጵያ፣ ከናይጄሪያና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች አኳያ እያጣቀሱ ከቬትናም ጋር በማነፃፀር አፍሪካ በተለይም ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡

በአፍሪካ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ሲመዘገብ ቆይቶ ድንገት ከአራት ዓመታት ወዲህ ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ እንደ ናይጄሪያ ያሉ ትልልቅ ኢኮኖሚያዊ አቅም ያላቸውን አገሮች የሚፈታተን አደጋ እንደተደቀነ ባተተው ንግግራቸው፣ ናይጄሪያ በአፍሪካ ግዙፍ የነዳጅ ሀብት ክችምት ካላቸው አገሮች ተርታ እንደመሠለፏ ከ90 በመቶ ያላነሰውን የውጪ ምንዛሪ ገቢ የምታገኝበት ሸቀጥ ነበር፡፡ ይሁንና በዓለም ገበያ የታየው የሸቀጦች ገበያ መዳከም ሳቢያ ገቢዋ ማሽቆልቆሉ ሲገሰግስ የቆየውን የኢኮኖሚ ዕድገት እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ዶ/ር አርከበ አጣቅሰዋል፡፡

ያላደጉ አገሮች መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ለማምጣት በየዓመቱ እስከ ስምንት በመቶ የሚገመት የኢኮኖሚ ዕድገት ቢጠበቅባቸውም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሊያስመዘግቡ የቻሉት ግን አምስት በመቶና ከዚያ ያነሰ እንደነበር ሲጠቀስ ላለፉት 15 ዓመታት በአፍሪካ የታየው የዕድገት ጉዞም በአማካይ ከሦስት በመቶ ያልበለጠ በመሆኑ የሚፈለገውን የማዋቅራዊ ለውጥ ሊያመጣ እንዳልቻለ ዶ/ር አርከበ ባቀረቡት ጽሑፍ ጠቅሰዋል፡፡ በዚህ ዓመትም ሆነ በመጪው ዓመት የሚጠበቀው ዕድገት ብዙም ልዩነት እንደማይታይበት ከዚህ ይልቅ በኢትዮጵያ የሚገመተው የኢኮኖሚ ዕድገት 7.5 በመቶ ሊሆን እንደሚችል የዓለም ባንክን የቅርብ ትንበያ አጣቅሰው፣ አገሮች እንዲህ ያለውን ዕድገት ዘላቂ ለማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪዎቻቸውን መገንባት አማራጭ እንደሌለው አስምረውበታል፡፡

ቬትናምና ናይጄሪያን ባነፃፀሩበት ኢኮኖሚያዊ ዓውድ ናጄሪያ በኢኮኖሚ አቅም የበላይነቱን ይዛ ተገኝታለች፡፡ ይኸውም አማካይ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 3000 ዶላር ሲሆን፣ የቬትናም ግን ከ2000 ዶላር በታች ሆኖ ይገኛል፡፡ ይህም ቢባል ግን በብዙ ጎኑ ቬትናም ከናጄሪያ አብላጫ የምትይዘበት አቅም አላጣችም፡፡ ትልቁና ዋናው ደግሞ ቬትናም የገነባችው የአምራች ዘርፍ ነው፡፡ ከ40 በመቶ ያላነሰው የኢኮኖሚው ዘርፍ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚወከልባት ቬትናም፣ ከ90 በመቶ በላይ የወጪ ንግዷን ገቢ የምታገኘውም ከዚሁ ዘርፍ ነው፡፡ በአንፃሩ በናይጄሪያ ነዳጅ ከፍተኛው የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ ሆኖ ይገኛል፡፡ ከ20 በመቶ በታች ድርሻ ያለው አምራች ኢንዱስትሪዋ በሌሎች እንደ ንግድና አገልግሎት ባሉት መስኮች የተዋጠ ነው፡፡

ይህንን አመክዮ መነሻ በማድረግም መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት የግድ መካከለኛ ገቢ መሆን አይጠይቅም ያሉት ዶ/ር አርከበ የኢትዮጵያን ተሞክሮዎችም ለታዳሚዎቹ አጋርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በመሠረተ ልማት መስክ፣ በትምህርት፣ በግብርና በሌሎችም ያስመዘገበቻቸውን ለውጦች አመላክተዋል፡፡ በባቡር፣ በታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ምንጮች ግንባታ፣ በመንገድ መሠረተ ልማት አውታሮች ገንባታ የተካሄዱትን እንቅስቃሴዎች ጠቅሰዋል፡፡ በትምህር ረገድ በአንድ ወቅት ከልማት አጋሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበው ምክር በመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህህርት ላይ ኢትዮጵያ አተኩራ እንድትሠራ የሚያሳስብ ምክር ሲለገሳት እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር አርከበ፣ መንግሥት ይህንን ምክር ውድቅ በማድረግ ዩኒቨርሲቲዎችን፣ የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛዎችን ማስፋፋቱን እንደረጠ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ከ30 በላይ ዩኒቨርሲቲዎችን በመክፈት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምሩቃን ከማፍራት ባሻገር፣ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ የነበሩትን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በጀርመን የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ ትምህርት መሠረት የተስፋፉ ከ1,300 በላይ ማሠልጠኛዎችን ለመገንባት እንደተቻለ አብራርተዋል፡፡

በመሠረተ ልማት መስክ ከሚደረገው ኢንቨስትመንት በዋቢነት የጠቀሱት በኢትዮጵያ የሚካሄደው አዋጭነት ነው፡፡ በምሥራቅ አፍሪካ ውስጥ የምትገኝ ‹‹አንዲት አገር›› 700 ሜጋዋት ኃይል ለማመንጨት ያወጣችውና ኢትዮጵያ 1,870 ሜጋዋት የሚያነጨውን ግልገል ጊቤ ለመገንባት ያወጣችው እኩል መሆኑ፣ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን መገንባት ብቻም ሳይሆን የአፈጻጸምና የፕሮጀክት ትግበራም ለመዋቅራዊ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን ምሳሌ ያደረጉት ዶ/ር አርከበ፣ በፖለቲካዊ ጫና ምክንያት ከውጭ ምንጮች ግድቡን ለመገንባት የሚያስፈልገውን አምስት ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማግኘት ባለመቻሉ ከአገር ውስጥ ምንጮችና ከሕዝቡ መዋጮ በመነሳት ለመገንባት መቻሏም በማሳየት የተጠቀሙበት የለውጥ ምሳሌ ነበር፡፡

በአንፃሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለመዋቅራዊ ለውጥ ተስፋ ከሚደረጉ ጥቂት አገሮች ተርታ መሆኗን የጠቀሱት በዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ልማት ቡድን የምርምር አጋር የሆኑት ኒል ባልቺን ናቸው፡፡ ኒል እንዳብራሩት ከሆነ ዘጠኝ አገሮች በውጭ ኢንቨስትመንት የታገዘ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የመገንባት አቅም እንዳላቸው ተረጋግጧል፡፡ ኢትዮጵያ በተካተተችበት በዚህ ምድብ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያና ኡጋንዳ እንዲሁም ዛምቢያ ተካተዋል፡፡ ይሁንና ከእነዚህ አገሮች ውስጥ በተለይ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክና ናይጄሪያ በወጪ ንግድ ላይ ያተኮረ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሚገነቡ ተብለዋል፡፡

አገሮችን በዘጠኝ ዋና ዋና ጠቋሚ መመዘኛዎች የፈረጀው የእነ ኒል ጥናት፣ ዝቅተኛ ተመራጭነት ያላቸው ከፍተኛ ተስማሚነት ካላቸው በመለየት አስቀምጧል፡፡ ለአብነትም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የኤሌክትሪክ ኃይል ግድብ ማመንጫ እየገነባች የምትገኝ ብትሆንም፣ እስካሁን ስታቀርብ የቆየችው የኤሌክትሪክ ኃይል ከሌሎች አገሮች አኳያ ሲታይ ርካሽ የሚባል ሆኗል፡፡ ርካሽ ሲባል ግን ውድ የሚያደርጉት መመዘኛዎችም ቀርበው ኢትዮጵያን ዝቅተኛ ውጤት ያሰጠበት መለኪያም ታይቷል፡፡ ይኸውም አስማማኝነት የጎደለውና ባሻው ጊዜ ቦግ እልም የሚል የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ማቅረቧ አገሪቱን በዝቅተኛ ተስማሚነት ደረጃዎች ውስጥ ከሚስቀምጧት መካከል የሚመደበው ነው፡፡

ዶ/ር አርከበ አበክረው እንደተናገሩት ከሆነ አገሪቱ ከፍተኛ የሰው ኃይል የሚጠይቁ ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ የስኳር ልማት፣ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ከሚጠቀሱት ውስጥ በጉልህ ይነገርላቸዋል፡፡ መንግሥት በአሥር ዓመት ውስጥ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስባቸው ዘርፎች መካከል የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በትልቁ ይቀመጣል፡፡ በተለይ የአምራች ኡንዲስትሪውን ለማስፋፋት የኢንዱትሪ ፓርኮች ግንባታ በተመራማሪዎቹ ዘንድ ለኢትዮጵያ ነጥብ አስገኝቶላታል፡፡ ይህም ቢባል ግን የኢንዲስትሪ ሠራተኞች ምርታማነት እጅጉን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት አገሪቱ ከምታደርገው መስፋፋትና ከምታከናውናቸው የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እኩል ለአምራች የሰው ኃይሏም ትልቅ ትኩረት በመስጠት መሥራት ይጠበቅባታል ተብሏል፡፡

እንዲህ ያሉትን እውነታዎች በማስጨበጥ የአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዕድገት በሌላው አካባቢ ከሚታየውም ይልቅ የተሻለ አቅም እንዳለው የታየበቱ ጥናት፣ በተለይ ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ በጣት የሚቆጠሩ አገሮች በማኑፋክሪንግ ኢንዱስትሪዎቻቸው የተመረቱን ለውጭ ገበያ በማቅረገቡ ረገድ ለውጥ ያሳዩ በማለት አስቀምጧል፡፡ ኢትዮጵያ በአማካይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ ዓመታዊ ዕድገት በማሳየት ዘጠኙን አገሮች ብትመራም፣ በአገልግሎት ጥራትና በኢንቨስትመንት ምቹነትና ተስማሚነት፣ በእሴት ጭመራና በመሳሰሉት ነጥቦች ተወስደውባታል፡፡

የአፍሪካን የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን መደገፍ (ሰፖርቲንግ ኢኮኖሚክ ትራንስፎርሜሽን) በተሰኘው የጥናት ውጤት መሠረት፣ ኢትዮጵያ በቀላል ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመልካም ተራማጅነት ከመጠቀሱት ዘጠኑ አገሮች በጠቅላላ ውጤት አራተኛውን ደረጃ አግኝታለች፡፡ ዛምቢያ፣ ናይጄሪያና ኬንያ ኢትዮጵያን ሲቀድሙ፣ ሞዛምቢክ፣ ሩዋንዳ፣ ጋና፣ ታንዛንያና ኡጋንዳ ይከተላሉ፡፡

ለውጭ ገበያዎች የሚያመርቱ 16 ኩባንያዎችን ያቀፈው የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ልዩ ልዩ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ምርቶችን መላክ ጀምሯል፡፡ ከሐዋሳ ፓርክ ቀድሞ ሥራ የጀመረው የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክም እንዲሁ በርካታ የአልባሳት ውጤቶችን ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡ ትልልቅ አምራቾች የሚገኙበት ማምረቻ ነው፡፡ ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር ያላነሰ የውጭ ምንዛሪ ገቢ እንደሚገኝ ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ መንግሥት ከግብርና ሸቀጦች ወጪ ንግድ ይልቅ በኢንዱስትሪ ምርቶች ተፎካካሪ ለመሆን 13 የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመትከል ላይ ይገኛል፡፡

የአገሪቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከውጭ ገበያ ባሻገር በአገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች ከውጭ የሚገቡትን በመተካት ረገድም ሚናቸው እየጎላ መምጣቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ በሚኒስቴሩ ሥር ከሚተዳደሩ፣ ተጠሪ ተቋማት አንዱ የሆነው የኬሚካልና የኮንስትክሽን ኢንዱስትሪዎች ልማት ኢንስቲትዩት በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት የፕላስቲክ፣ የጎማ፣ የበርና መስኮት ፍሬሞች፣ የወረቀት፣ የኅትመትና የምርት ማሸጊያ ምርቶችና የመሳሰሉት አገር ውስጥ በብዛት እየተመረቱ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ወጭ ማዳን እንደቻሉ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትራስፎርሜሽን ማዕከል በምሕፃረ ቃሉ አሴት የተሰኘው ይህ ተቋም፣ በእንግሊዙ ተራድኦ ድርጅት ዩኬ ኤድ በሚደገፈው የኦቨርሲስ ደቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት አማካይነት በየዓመቱ በአፍሪካ የሚታየውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ለማገዝና ለማጥናት የሚሠራ ተቋም ነው፡፡

 

 

 

 

Standard (Image)

‹‹መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የሰጠንን መብት ምርት ገበያው በአዋጅ ነጠቀን››

$
0
0

 

አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ፣ የደቡብ ቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች ማኅበራት ምክር ቤት ሊቀመንበር

የኢትዮጵያ የቡና ግብይት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉበት በዘርፉ ተዋናዮች ስምምነት ተደርሶበት አዲስ የቡና የለውጥ አሠራር ውስጥ መተግበር ጀምሯል፡፡ እስካሁን የነበሩት አሠራሮችን ይቀይራሉ የተባሉ አዳዲስ የቡና ግብይት ዘዴዎችም እንደሚተገበሩ ይጠበቃሉ፡፡ በግብይቱ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው እንደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያሉ ተቋማትም የእስከዛሬው አሠራራቸውን እንደሚቀይሩና በአዲሱ ሪፎርም የተቃኙ ሒደቶችን እንደሚከተሉ ይጠበቃል፡፡ የቡና ግብይት ሥርዓቱን የሚለውጥ አሠራር ለመቅረጽ ከአንድ ወር በላይ በፈጀ ውይይት ባለድርሻ አካላት አሉ ባሏቸው ችግሮች ላይ ተነጋግረው መፍትሔ እንዳስቀመጡም ተገልጿል፡፡ ከፖሊሲ አውጪዎች ጀምሮ፣ ቡና አልሚዎች፣ ላኪዎች፣ አቅራቢዎች፣ የቡና አምራች ማኅበራት፣ የውጭ ቡና ገዢዎች፣ ተወካዮችና ተመራማሪዎችም ተሳትፈውበታል፡፡ ይህ ሪፎርም የዓመታት ጩኸታችን የተሰማበት ነው፣ ስናቀርብ የነበው ጥያቄያችን ምላሽ ያገኘበት ነው የሚሉ ድምጾች እየተደመጡ ነው፡፡ ሊታይ የሚችለው ለውጥ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህንኑ ተከትሎ የሚተገበሩ አሠራሮች የኢትዮጵያ የቡና ግብይት አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይቀይራሉ በማለት ከሚሞግቱ አካላት መካከል  የቡና አቅራቢዎች ዘርፍ ይገኝታል፡፡ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ምሥረታ ጀምሮ የተፈጠረው አሠራር የኢትዮጵያን ቡና እየጎዳ ነው በማለት ጥያቄ ሲያቀርቡ ከቆዩት ውስጥ የደቡብ ቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አንዱ ነው፡፡ ለቡናው ሪፎርም የዚህ ማኅበር ተደጋጋሚ ጥያቄና በተደራጀ አኳኋን ሲቀርቡ የነበሩ ጥናታዊ ጽሑፎችም እንዳገዙ የማኅበሩ ሊቀመንበር አቶ ዘሪሁን ቃሚሶ ይናገራሉ፡፡ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚጠበቀው አዲሱ አሠራር፣ የቡና አቅራቢዎችን መብት በምርት ገበያው ውስጥ የቆየውን ገዳቢ አሠራር እንደሚለውጥ ይነገራሉ፡፡ አቶ ዘሪሁን በአዲሱ ሪፎርም የምርት ገበያው ቦርድ አባል ሆነው ተሰይመዋል፡፡ ዳዊት ታዬበቡና ሪፎርም ዙሪያና በተያያዥ ነጥቦች ዙሪያ አቶ ዘሪሁን ቃሚሶን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የቡና ግብይትን ለመለወጥና አሉ የሚባሉ ችግሮችን ለመፍታት ሪፎርም ተጀምሯል፡፡ የግብይቱ ማነቆዎች ምንድን ነበሩ? ወደ ሪፎርም የተገባውስ እንዴት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ችግሩ ብዙ ነው፡፡ በጥልቅ ስታየው ግን አጠቃላይ የቡና ግብይት ሥርዓቱ በችግሮች የተተበተበ ነበር፡፡ በተለይ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ መመሥረት ጋር ተያይዞ ከታች ጀምሮ ግብይት እንድትፈጽም የሚያስገድዱ አሠራሮች፣ ለአገሪቱ የቡና ገበያ እንቅፋት እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ታች ያለው ግብይት ለቡና ጥራት እንቅፋት ነበር፡፡ የሪፎርሙ ጠያቂዎችና ባለቤቶች እኛ ነበርን ማለት እችላለሁ፡፡ ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ በሲዳማ ቡና አቅራቢዎች ማኅበር ተደራጅተን ቡና ትኩረት ስለማጣቱ ስንናገር ነበር፡፡ የዘርፉን ችግር ስንናገር ቆይተን በአዲስ የማኅበራት አደረጃጀት 2000 ዓ.ም. እንደገና ተቋቁመን ይህንኑ ጥያቄ ስናቀርብ ነበር፡፡ በዚህ መካከል የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሲመጣ ዘመናዊ ግብይቱንም ተቀብለናል፡፡ ለምርት ገበያው ሐሳብ አፍላቂና መሥራች ዶ/ር ኢሌኒ ገብረ መድኅን ከፍተኛ አቀባበል አድርገንላቸዋል፡፡ ምክንያቱም አዲስ የመጣው አሠራር የእኛንም ጥያቄ ይመለሳል የሚል እምነት ስለነበረንም ነው፡፡ ምርት ገበያው ለአንድ ዓመት ከሠራ በኋላ የቡና ግብይት ችግር የበለጠ እየተባባሰ መጣ፡፡ አቅራቢዎች የባለቤትነት መብታችን ተነጠቀ፡፡ መንግሥት በሕገ መንግሥቱ የሰጠንን መብት ምርት ገበያው በአዋጅ ነጠቀን፡፡

ሪፖርተር፡- ይህንን ሲሉ እንዴት እንደሆነ ግልጽ ቢያደርጉልኝ?

አቶ ዘሪሁን፡- ከባንክ ብድር ወስደን ቡና እንገዛለን፡፡ በምርት ገበያው የመጀመሪያ ደረጃ የግብይት ማዕከል አለ፡፡ ለአርሶ አደሩ አቅራቢያ በሆነ አካባቢ የሚቋቋም ነው፡፡ አርሶ አደሩ ቡናውን ለማዕከሉ ያቀርባል ተብሎ ቢጀመርም በአብዛኛው ግን ቡናውን ለደላላ ማቅረብ ጀመረ፡፡ እኛ እንደ አቅራቢ ከአርሶ አደሩ ጋር የነበረን ግንኙነት ተቋረጠና ግንኙነታችን ከደላሎች ጋር ሆነ፡፡ ደላሎቹ ቡናውን ሲሰበስቡ ውለው የፈለጉትን ዋጋ አውጥተው ይሸጡልሃል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ሦስት ዓይነት ቡና ነው የምንገዛው፡፡ አረንጓዴ የተሸመጠጠ ቡና፣ ቀይዳማ ቡና እንዲሁም ቀይ እሸት ቡና እንገገዛለን፡፡ እነሱ ግን ሦስቱን ደባልቀው ይዘረጋሉ፡፡ ኪሎ እንዲያነሳላቸውም ውኃ ውስጥ በማሳደር በሁለተኛው ቀን ይሰጡሃል፡፡ አልወስድም ማለት አትችልም፡፡ ምክንያቱም ገንዘብህን መጀመሪያ ስለሰጠሃቸው የግድህን ትወስዳለህ፡፡ ስለዚህ ከጥራት አንፃር የተሻለ ለውጥ ያመጣል የተባለው አሠራር አልሠራም፡፡

ሪፖርተር፡- ስለዚህ ታች ያለው የቡና ግብይት ችግር ነበረው ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን! በአስተሳሰብ ደረጃ ማለት ነው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በራሳችን ገንዘብ ማዘዝ አልቻልንም ነበር፡፡ ቡናው የእነሱ ስለሆነ፣ አንተ በገንዘብህ  የምትገዛውን አውቀህ ዋጋ ለመስጠት እንኳ አትችልም፡፡ አንተ ገንዘብ ተበድረህ ታመጣለህ፣ በገንዘብህ ግን አታዝበትም፡፡ ማዘዝ ማለት በዚህ ገንዘብ ይህንን ያህል እገዛለሁ ስትል ነው፡፡ ቀድመህ በሰጠኸው ገንዘብ ምክንያት በዚህ ዋጋ ካልሆነ አልሸጥልህም ውሰድ ከተባልክ በገንዘብህ እያዘዝክ አይደለም ማለት ነው፡፡ እስካሁን በነበረው አሠራር የሆነው ይህ ነው፡፡ እንደ አቀራቢ አንተ ቡናውን ለመሰብሰብ ገንዘቡን ከባንክ ስለተበደርክ ያንን ቡና አምጠተህ ፈልፍለህ፣ አስጥተህና አድርቀህ ለገበያ ታቀርባለህ፡፡ ይህ ቡና ግን በመጀመሪያ ግዥ ጣቢያ እንደ ነጋዴ ተደራድረህ የገዛኸው ቡና አይደለም፡፡ ቡናውን ጭነህ አምጥተህ በምርት ገበያው የመመርመሪያ ማዕከል ስትደርስ ጭነቱን አስረክበህ ትመለሳለህ፡፡ ቡናህን የሚያስመረምሩልህ በኮሚሽን የሚሠሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ቡናው የሚቀመሰው በኮሚሽን ነው፡፡ የሚራገፈው በኮሚሽን ነው፡፡ በዚህ መንገድ መጋዘን የሚገባውን ቡናህን አታየውም፡፡ ይህንን ሒደት ቦሌ ኤርፖርት ሔደህ ሰው እንደመሸኘት ቁጠረው፡፡ ምርት ገበያው በራፍ ላይ ያስረከብከውን ቡና ዕጣ ፈንታ የምታውቀው በስልክ ደውለህ ነው፡፡ ስንተኛ ወጣ? ደረጃውን አለፈ ወይ? ተራገፈ ወይ እያልክ ስትከታተል ቆይተህ በመጨረሻው የሚሸጥልህ አገናኝ የሚባለው አዲስ አበባ ያለው ባለወንበር ነው፡፡ ይህ የሚያሳይህ የገዛ ቡናህን ተደራድረህ መሸጥ የማትችል መሆኑን ነው፡፡ ተደራድረህ ያልገዛህበትንና ተደራድረህ ያልሸጥከበት አሠራር ንግድ አይደለም የምለው ለዚህ ነው፡፡ ስለዚህ በመቀማማት ውስጥ ነው ያሳለፍነው ማለት ይቻላል፡፡  

ሪፖርተር፡- እስካሁን በነበረው አሠራር እንዲህ ያለው ችግር መኖሩን ለማሳወቅ ምን ያህል ሞክራችኋል? የቡና ገበያ ሥርዓት ምቹ ካልነበረ የአሁኑ ዓይነት ዕርምጃ ለምን ከዚህ ቀደም አልተወሰደም?

አቶ ዘሪሁን፡- አሁን የነገርኩህን ብቻም ሳይሆን ሌሎችን ነጥቦች ዘርዝረን ችግር ላይ መሆናችንን አቅርበናል፡፡ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድም ሳላስቀር አቅርቤያለሁ፡፡  ይህንን ችግር አስተካክሉ፤ አደጋ ውስጥ ነን፤ የቡና ጥራት እየተበላሸ ነው ብለናል፡፡ እኛ ብቻ ሳንሆን፣ የውጭ ገዥዎችም ልክ እንደኛው ሥጋታቸውን አቅርበዋል፡፡ አሠራሩን ተመልክተው ይኼ አሠራር አያስኬዳችሁም፣ ቡናችሁን ያጠፋባችኋል ብለው ምክረ ሐሳብ ጽፈዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ይኼ አያስኬዳችሁም ያሉት የምርት ገበያውን አሠራር ማለት ነው?  ቡና ገዥዎቹ ለማነው ደብዳቤ የጻፉት?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን! የምርት ገበያውን አካሄድ ነው፡፡ የጻፉትም ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ነበር፡፡ እኛ ይህ አሠራር ችግር እንዳለው ስንናገር የመጀመሪያው ዓመት ላይ ተፈትሾ ነው፡፡ በሁለተኛው ዓመት የምርት ገበያው አሠራር አያስኬድም ተባለ፡፡

ሪፖርተር፡- ይኼ ማለት ምርት ገበያው ወደ ሥራ በገባ በሁለተኛው ዓመት ማለትም በ2003 ዓ.ም. ማለት ነው? በዚያን ወቅት የምርት ገበያው አሠራር አያስኬድም ያላችሁበት የተጨበጠ ምክንያት ነበራችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን በ2003 ዓ.ም. ነበር፡፡ ይህ አካሄድ በኢትዮጵያ የቡና ጥራት ላይ ችግር እንደሚፈጥር በመገንዘባችን ነበር፡፡ የቡና የባለቤትነት መብት ተወስዶብናል፡፡ በአገሪቱ ቡና ላይ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉ በርካታ ክፍተቶች እንዳሉ በመረዳታችን ነው፡፡ ይህንን የሚያሳዩ ጽሑፎችን በዓመት ለሦስት ጊዜ ያህል እያዘጋጀን ስናቀርብ ነበር፡፡ በአሠራሩ ደላላው ተደራድሮ በፈረሱላ 50 እና 100 ብር ለራሱ እላፊ ይዞ እንኳ ሽጥልኝ ስትለው አይሸጥህም፡፡ የታዩት የቡና ዘርፉ ውድቀቶች  የመጡት እኮ በግብይት ሥርዓቱ ችግር ምክንያት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከመጀመሩ በፊት የነበረው የቡና ጥራት ትኩረት ተነፍጎታል ይባል ነበር፡፡ የቡና ኤክስቴንሽን ላይ ክፍተት መኖሩን፣ በቡና ላይ የሚደረግ ምርምር አነስተኛ መሆኑን፣ በጠቅላላው ለቡና የተሰጠው ትኩረት አናሳ እንደሆነ ጠቅሰናል፡፡ ስለ ሰብል ምርቶችና ስለ ግብርና ሲነሳ፣ ቡና ከመጀመሪያም ያደገ ነው እየተባለ ከቡና ይል ስለበቆሎ ነበር የሚወራው፡፡ ስለዚህ ለስምሪት የሚወጣው ካድሬም ከላይ የመጣ አቅጣጫ ነው ይልና ብዛት ያለውን የቡና ማሳ ትቶ ስለበቆሎ እያወራ ነው ብለን ችግሩን በመተንተን አመልክተናል፡፡   

ሪፖርተር፡- እንዲህ ላሉት ችግሮች ተጠያቂው የምርት ገበያው አሠራር ብቻ ነው ሊባል ይችላል?

አቶ ዘሪሁን፡- ሌሎች ምክንያቶችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ችግሩ ቡና ላይ የመጡ ሰዎች ቡናን አለማወቃቸው ነው፡፡ እነሱ የሠሩ በሚመስላቸውም ዘርፉ ግን እየተጎዳ ሄዷል፡፡ ሰዎቹ በትምህርት ብቃት ችግር የለባቸውም፡፡ በዕውቀት ደረጃ ችግር የለባቸውም፡፡ በአስተሳሰብ ደረጃ አገርን ሊጎዳ የሚችል ነገር እንደማይሠሩ የሚታወቅ ነው፡፡ አሠራራቸው ግን ማነቆ ነበረው፡፡ ለእነሱ ሥራ የሆነው ነገር ለእኛ ግን አደጋ ፈጠረ፡፡ ይህንን ስንነግራቸው ስላልገባችሁ ነው ይሉናል፡፡ ይኼ ማለት ታመህ ሐኪም ቤት ሔደህ ሕመምህን ለሐኪሙ እያስረዳኸው አልታመምክም፣ በሽታ የለብህም እንደማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ ትግል ስናደርግ ቆይተን ቀውሱ እየመጣ ሲሄድ መንግሥትም ጉዳዩን መረዳት ጀመረ፡፡ በቅርቡ የመጨረሻው ውሳኔ ከተወሰነ ወዲህ ሌሎች ጥናቶችን ለማድረግ ሲሞከር ያየናቸው ነገሮችም ነበሩ፡፡

 ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት ጥናቶችና ናቸው? ምን ለማመላከት የሚረዱ ናቸው?

አቶ ዘሪሁንየአገሪቱን ቡና ወደ ውጭ ለመላክ የሚፈጅብህን ወጪ የሚመለከቱ ናቸው፡፡ በጥናቱ መሠረት ኢትዮጵያ ቡና ለመላክ የምታወጣው ወጪ ከፍተኛ መሆኑ ታይቷል፡፡ የብራዚል፣ የኮሎምቢና የቬትናም የቡና ገበያ ሥርዓት ምን እንደሚመስል ተፈትሾ፣ ከጥናቱ መረዳት እንደሚቻለው የብራዚል የቡና የኤክስፖርት ወጪ አሥር በመቶ፣ የኮሎምቢያና የቬትናም የቡና የኤክስፖርት ወጪ ደግሞ አራትና አሥራ አራት በመቶ ነው፡፡ የእኛ ግን 40 በመቶ ነው፡፡ ይህ የተፈጠረው የቡና ግብይቱ ውስጥ ተደራራቢ ወጪ የሚጠይቁ አሠራሮች ስለሰፈኑበት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የኤክስፖርት ወጪ የሚባለው እንደምን ያሉትን የሚያጠቃልል ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- የኤክስፖርት ወጪ የሚሰላው ከታች ቡናውን ስትገዛ ጀምሮ ያለብህን ወጪ አካቶ ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ቡና ለመግዛት ለደላላ ትከፍላለህ፡፡ ቡና ሲበተን የሥራ ማስኬጃ ወጪ አለው፡፡ የአጣቢና የለቃሚ ደመወዝ አለ፡፡ ይህንን ከተወጣን በኋላ ደግሞ ወደ ምርት ገበያው ስንመጣ ሌላ ወጪ ይጠብቀናል፡፡ የመጋዘን፣ በድጋሚ ሌላ የደላላ ወጪ አለ፡፡ የገበያ ወጪም ይደመራል፡፡  በሌሎች አገሮች ግን የገበያው ሰንሰለት አጭር ነው፡፡ ወጪውም ትንሽ ነው፡፡ በሌሎች አገሮች አርሶ አደሩ፣ የቡና ገዥውና ኤክስፖርተሩ ነው የሚገናኘው፡፡ የእኛ ሰንሰለት ግን ረዥም ነው፡፡ በየቦታው የምትከፍለው ይበዛል፡፡ በዚህ ረዥም ሰንሰለት ውስጥ ያሉት ደግሞ ምንም እሴት የማይጨምሩ ዋጋ ግን የሚጨምሩ ናቸው፡፡ አሁን በተወሰነው መሠረት ግን ቡና ለመላክ ይወጣ የነበረውን ወጪ በግማሽ ለመቀነስ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡   

ሪፖርተር፡- ረዥም የተባለውን የቡና ገበያ ሰንሰለት ማሳጠር ብቻ ሳይሆን፣ ቡናን ለመላክ ይወጣል የተባለውን ወጪ ለመቀነስ ሲወሰን ምን ታሳቢ ተደርጎ ነው?  የሚጠበቁትን አንዳንድ ለውጦችም ቢጥቀሱልን?

አቶ ዘሪሁን፡- ቡናውን ራሳችን እንድንገዛና እንድንሸጥ ይፈቅዳል፡፡ በመኪና ላይ እንድንሸጥ፣ በስማችን እንድንሸጥ፣ ሸቀጥነቱ ቀርቶ ወደ ኋላ በመሔድ የቡናውን መነሻ እንድናውቅና እንድንመጣ የሚያደርግ ነው፡፡ አሁን በተወሰነው መሠረት ነው ወደ ሥራ ለመግባት የተዘጋጀንበት መንገድም በጥያቄያችን መሠረት መቶ በመቶ ምላሽ ስላገኘን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- እርስዎ ቡና አቅራቢ እንደመሆንዎ ይተገበራል የተባለው አዲስ የቡና ግብይት አሠራር ያስገኛል የሚሉት ተጨባጭ ለውጥ ምንድን ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ለምሳሌ ከቡና አቅራቢዎች አንፃር የባለቤትነት መብታችን ተመልሷል፡፡ ከአርሶ አደር ጋር ተደራድረን ቡና ልንገዛ የምንችልበት ዕድል ተፈጥሯል፡፡ እኛም የአርሶ አደር ልጆች እንደመሆናችን እየተጋገዝን ለውጥ ለማምጣት በር ይከፈትልናል፡፡ በደላላ ሳይሆን በቀጥታ እንገዛለን፡፡ ያዘጋጀነውን ቡና አምጥተን በማስመርመር በቡናችን ስም ተደራድረን እንድትሸጥ ተወስኖልናል፡፡ ገዥ ካገኘንም ቡና ገዝተው ኤክስፖርት ከሚያደርጉ ላኪዎች ጋር በመተሳሰር የሁለትና የሦስት ዓመት ውል ተዋውለን ቡና ልንሸጥ የምንችልበት ዕድል ተፈጥሯል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ጥሩ ዋጋ አግኝተህ ቡናህን ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችልህ ብቃት ላይ ስትደርስ፣ ቡና ከማሳ ላይ ልትጭን የምትችልበት ዕድል እንዲኖር ተወስኗል፡፡ እንዲህ ያሉ መሠረታዊ ጉዳዮች መወሰናቸው ለዓመታት ስናቀርብ የነበረው ጥያቄ በአግባቡ እንዲመለስልን አስችሏል፡፡ ይህንን ውሳኔ መሬት ለማውረድ እየተሠራ ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- አዲሱ አሠራር የምርት ገበያውን የአሠራር ድርሻ እንደሚነካካ ግልጽ ነው፡፡ ይህ አዲስ አሠራር የሚተገበር ከሆነ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ሚና ምን ሊሆን ይችላል? በቅርቡ እንደተገለጸው አዲሱ አሠራር ሲተገበር ምርት ገበያው የልዩ ጣዕም ቡና ከሚባለው ውጭ ሌላውን ቡና ማገበያየቱ ይቀራል፡፡ ስለዚህ አዳዲስ ለውጦች ቢኖሩም በምርት ገበያው ነው የምትገበያዩት ወይስ ሌላ የግብይት መንገድ አላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን! ግብይቱ በምርት ገበያው በኩል ይቀጥላል፡፡ ምርት ገበያን ከቡና አንፃር ካየኸው ስሙ ነው እንጂ ያለው አሠራሩን ግን አፍርሰነዋል፡፡ ምርት ገበያው ቡናን ተረክቦ እንደ ሸቀጥ አንድ መጋዘን ላይ ከምሮ ለላኪ ነበር የሚሸጠው፡፡ በአዲሱ ለውጥ ግን ላኪ ቡናው የማን እንደሆነ አውቆ ነው የሚገዛው፡፡ እኔም ለማን እንደምሸጥ አውቄ ነው የምሸጠው፡፡ ስለዚህ ምርት ገበያው በአንድ መጋዘን ተመሳሳይ ደረጃ ያለውን ቡና እንደ ስኳር በአንድ መጋዘን አከማችቶ መሸጡ ቀረበት ማለት ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ምርት ገበያው እስካሁን ግብይቱን የሚያስፈጽመው በአገናኞች ነበር፡፡ ከአሁን በኋላ ግን አገናኝ የምንለውን አካል በአማራጭ እንጠቀምበታለን፡፡ የምርት ገበያው አሠራር እኔ ባዘጋጀሁልህ አንድ በር ውጣ የሚል ሆኖ ነበር የቆየው፡፡ አሁን ግን አማራጮች እንዲከፈቱ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ቡናህን ቀርበህ መሸጥ ትችላለህ፡፡ የሚልከውም ገብቶ መግዛት ይችላል፡፡ ጊዜ ከሌለውና ታማኝነቱ ካለ ታማኝ ሆነው ሲገዙ የነበሩ ባለወንበሮች ቡና ሊገዙልህ ይችላሉ፡፡ ሊሸጡልህም ይችላሉ፡፡ ስለዚህ አንድ ብቻ  የነበረችውን መግቢያና መውጪያ በር አማራጮች እንዲኖሯት አሰፋልን ማለት ነው፡፡ ምርት ገበያው እስከ ዛሬ የተጓዘው በዚህች አገር ወጪ፣ በቡና ባለቤቶችና በቡና ተገበያይ አካላት ወጪና ኪሳራ ነው፡፡ ምርት ገበያው የዘመናዊ ግብይት ሞዴል ነው፡፡ እሱን ወደኋላ አንመልሰውም፡፡ ሶፍትዌር የመቀያየር ጉዳይ ግን ይኖራል፡፡ ቡና በአንድ ማዕከል ማገበያየት ስላለበት ይኼንን ሥራ ይሠራል፡፡ ሥራው ይቀጥላል፡፡ የገንዘብ ቅብብሎሹ ቀድሞ በተዘረጋው መንገድ መሄድ አለበት፡፡ መሠረታዊውን የአሠራር ችግር ግን አፍርሰነዋል፡፡   

ሪፖርተር፡- መሠረታዊ አሠራሩ እንዲፈርስ ተደርጓል ሲሉ ምን ማለትዎ ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- አንዱ የምርት ገበያው መሠረታዊ ችግር የባለቤትነት መብትን መግፋቱ ነበር፡፡ ቡናህን በስምህ ለመሸጥ መብት ያሳጣ የነበረው አሠራሩ ተቀይሯል፡፡ በዚህ በር ብቻ ግባ በዚህ በር ብቻ ውጣ የሚለው ነገር ቀርቶ የመውጪያና የመግቢያ አማራጭ በሮች ተከፍተዋል፡፡ እኔ ያደረኩልህ፣ እኔ የፈጠርኩልህ ነገር ብቻ ነው ትክክል ተብሎ ሲሠራበት የነበረውን በጋራ በነበረን ውይይት መድረክ ይኼ አካሄዱ ጥፋት መሆኑ ታውቆ ወደ አዲስ አሠራር እንድንገባ ተስማምተናል፡፡ ሠራን የሚሉትን ነገር በሪፖርት ሲያቀርቡ ይታይ የነበረው የገንዘብ ልውውጡ ነበር፡፡ ነገር ግን በሌላ ጎን ጥፋት እየተፈጠረ ነበር፡፡ ኤክስፖርቱ መውደቁን የምታውቁት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ለቡና የወጪ ንግድ መውደቅ አንዱ የምርት ገበያው አሠራር ነበር ብላችሁ ታምናላችሁ ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን! ነገርኩህ እኮ፡፡ እኛ ብቻ ሳንሆን የውጭ ቡና ገዥዎችም የምርት ገበያው ለቡና አዋጭ አይደለም በማለት ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ የእናንተ ቡና 16 ዓይነት ልዩ ልዩ ዝርያ ያለው ነው፡፡ ምርት ገበያው ግን ይህንን ሁሉ በአንድ ደባልቆ ነው የሚያቀርበው፡፡ ወደኋላ በመሔድ ለማገኘት የሚቻሉትንና የልዩ ጣዕም ቡናችንን አይሸጥም፡፡ ምርት ገበያው እኮ ይህንን ነው ያፈረሰው፡፡ ምርት ገበያው እንደሚታወቀው የዘመናዊ ግብይት ሞዴል ነው ነገር ግን የተለያየ ጣዕምና ባህርይ ያላቸው ቡናዎችን በራሳችን ስም እንዲሸጡ አያደርግም ነበር፡፡ ለምሳሌ የሲዳማ አካባቢ ያለ የፌሎ ቡና በስሙ ቢሸጥ የተሻለ ዋጋ ያስገኛል፡፡ ታች ድረስ ያሉ ተጠቃሚዎች ቡናውን ያውቁታል፡፡ ስለዚህ የተሻለ ክፍያ ይከፍላሉ፡፡ አሁን ቡናው ተቀላቅሎ በዚያ ላይ መደባለቅ ተፈቅዶ ስለሚሸጥ ኢትዮጵያዊ ቡና አልፈጠርም ነበር፡፡ ዓለም የሚያውቀው የኢትዮጵያን ቡና ሳይሆን ሌላ ቡና ነው፡፡ ምክንያቱም አንዱ ከሌላው ሲደበላለቅ ስለነበር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ እንዴት ነው የአገሪቱን ቡና የሌላ ቡና የሚያሰኘው?

አቶ ዘሪሁን፡- የጅማና የሲዳማ ቡናዎችን ቀላቅለህ ካቀረብክ ሌላ ስም ነው መሰየም ያለብህ፡፡ የተደበላለቀ ጣዕም ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- በአዲሱ አሠራር የአንድ አካባቢ ቡና ከሌላው ሳይቀየጥ በየአካባቢው ስም ለገበያ ይቀርባል ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ቡናችን በየአካባቢው ስም የሚሄድበት አሠራር እየተፈጠረ ነው፡፡ በቅርቡ በርካታ ገዥዎች በነበሩበት በአሜሪካ በተደረገ የቡና ንግድ ትርዒት ወቅት፣ ስለ አዲሱ አሠራር ገለጻ የተደረገላቸው ገዥዎች ይህን ካደረጋችሁ እኛም እንመለሳለን ብለዋል፡፡ እውነት ለመናገር መንግሥት ምላሽ ለመስጠት ፈጣን ነው፡፡ ሕዝብን ያዳምጣል፡፡ በቡና ዘርፍ ግን ከጉዳት በኋላ ነው የሰማው፡፡ ባይነገረው ኑሮ ችግር አልነበረውም፡፡ እየነገርነውም ችግሩ እየተፈጠረ ነው፡፡ ሳያውቁት እየሠራን ነው የሚሉ ሰዎች ለእነሱ ሥራ የመሰላቸው ነገር ለእኛ ሞት ሆነ፡፡   

ሪፖርተር፡- አዲሱን አሠራር ወደ መሬት ለማውረድ የተለያዩ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ ነገር ግን አሠራሩን ለመተግበር ፍጥነት አልታየም፡፡ አሠራሩን ወደ መሬት ለማውረድ ከባድ ይሆናል እየተባለ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ብዙ ለውጥ ያመጣል ያላችሁት ይህ አሠራር በትክክል ለመተግበሩ ምን ያህል እርግጠኞች ናችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- አገር ከዚህ በላይ ሊጎዳ አይገባም፡፡ ለውጡ ይመጣል፡፡ የውጭ ምንዛሪ ገቢ በማስገኘት ቡናን የሚበልጥ ነገር እስካሁን አልተገኘም፡፡ ስለዚህ መንግሥት እስካሁን ያጣውን ነገር ሊመልስ የሚችልበት ዕድል በእጁ አለው፡፡ ይኼ ለእኛ ብቻ ተብሎ የሚደረግ ነገር አይደለም፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቡና የመንግሥት ነው፡፡ እኛ ኮሚሽን ነው የምንወስደው፡፡ እንደ አገር በኢኮኖሚው ወደፊት እንሄዳለን ከተባለ የውጭ ምንዛሪውን በማብዛት ተጠቃሚ መሆን መቻል አለብን፡፡ መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ እየሠራ ባለበት ወቅት ይህንን አሠራር ወደታች ለማውረድ ይዘገያል ብዬ አላስብም፡፡ ይህንን አሠራር ወደታች ለማውረድ በአዲስ አስተሳሰብ እየተሠራ ነው፡፡ የምርት ገበያውና ለመተግበር አዲስ ቦርድ ለምርት ገበያው አደራጅቶ ይህንንም ወደ ታች አውርዱ ተብሎ ወደ ሥራ ተገብቷል፡፡ እስካሁንም የተወሰኑ ነገሮች መውረድ ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራዎቹ ረዥም ጊዜ የሚወስዱ ናቸው፡፡ ከችግሩ አንፃር ቸኩለህ በመግባት የበለጠ እንዳታበላሽው መጠንቀቅ አለብህ፡፡ ስለዚህ ይህ እንዳይሆን እየተሠራ ነው፡፡ ጊዜ መውሰዱ ትክክል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በአገራችን ይህ ለውጥ እንዲመጣ የማይፈልጉ አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- በምን ምክንያት?

አቶ ዘሪሁን፡- በጦርነት ውስጥም እኮ የሚነግዱ አሉ፡፡

ሪፖርተር፡- የምርት ገበያው አሠራር ይለወጣል ከተባለ ከሚታሰቡ ጉዳዮች መካከል አንዱ በምርት ገበያው ትልቅ ቦታ ወይም ወንበር ያላቸው አገበያዮች ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል?

አቶ ዘሪሁን፡- እነዚህ ወንበሮች ለአዲሱ አሠራር የገበያ አማራጮች ይሆናሉ፡፡ በመጀመሪያ እኮ ችግር ውስጥ የተገባው በእነዚህ ወንበሮች ብቻ ተገበያዩ በመባሉ ነው፡፡ ወንበር አማራጭ ነው መሆን ያለበት፡፡ በዚህ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር ተማምነናል፡፡ ሁሉም በላድርሻ አካላት ተስማምተውበታል፡፡ ወንበሩ ምንም ሊሆን ይችላል፡፡ ለገበያ ነው የተፈጠረው፡፡ አማራጭ ነው መሆን ያለበት፡፡ በታማኝነት የቆዩት ወንበሮች አሁንም ይቀጥላሉ፡፡ ሌቦቹ ደግሞ ይወጣሉ፡፡ ባለወንበሮቹ ይወዳደራሉ ማለት ነው፡፡ ውድድሩ ታማኝነትና ቅልጥፍና ያመጣል ማለት ነው፡፡ እንደቀድሞ ግዴታ ሳይኖር እነርሱም በምርጫ ይሰሠራሉ፡፡ ወንበሮች ይጥፉ የሚል ነገር ግን የለም፡፡ እንዲህ ያሉት ነገሮች ሲቀሩ ቡናን ለመላክ ይጠይቅ የነበረው ወጪ ይቀንሳል፡፡ ወጪውን ወደ 20 በመቶ ማውረድ የሚቻለው እንዲህ ዓይነቱን ድርብርብ ወጪ በመቀነስ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ወደ አሥር በመቶ ይወርዳል፡፡ ስለዚህ በግዴታ ሲገበያዩ የነበሩት ወንበሮች መንግሥት ሱቅ ከፍቶ እንደጣቸው ነው የሚቆጠረው፡፡ እነዚህ ሱቆች ደግሞ ከዚህ ብቻ ግዛ ይሉሃል፡፡

ሪፖርተር፡- ለአዲሱ አሠራር የሚሆኑ መመርያዎች ፀድቀው ሥራ ላይ ይውላሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡ ይኼ ከሆነ በእርግጥ ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ቡና መጠንና የሚሰጠው ዋጋ ይጨምራል?

አቶ ዘሪሁን፡- መጠኑ በሒደት ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ለውጭ ገበያ የሚቀርበው ምርት ግን ያድጋል፡፡ ምክንያቱም ይህንን የአሠራር ለውጥ ሲጠባበቁ የነበሩ ቡናችንን የሚፈልጉ የቀድሞ ደንበኞቻችን አሉ፡፡ ስለዚህ ያለምንም ጥርጥር የዓለምን ገበያ ያገናዘቡ ሽያጮች ይኖራሉ፡፡ ገበያው በእጃችን ነው፡፡ ኢትዮጵያ በዓለም የምትታወቀው በቡና ነው፡፡ ይህንን ለመመለስ ከባድ አይደለም፡፡ አሁን ራሳችንን አስተካክለን ነው የምንሄደው፡፡

ሪፖርተር፡- ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተወያይተውበት የሚደረግ ለውጥ ከሆነ ከአንድ ወር በላይ ፈጀ በተባለው ውይይት ምን ያህል ተማምናችኋል?

አቶ ዘሪሁን፡- የሚገርምህ ባለድርሻ አካላት የሚባሉት በዚህ ሒደት ውስጥ ሦስት ናቸው፡፡ አርሶ አደሩ፣ አቅራቢ፣ ኤክስፖርተሩ፣ የውጭ ገዥ ኩባንያዎች ተወካዮች አሉ፡፡ ዋነኛ ተዋናዮች እነዚህ ናቸው፡፡ ሁሉም ተጎድተው የቆዩ ናቸው፡፡ ገዥዎች የሚፈልጉትን ዓይነት ቡና ማግኘት አልቻሉም፡፡ ላኪዎችም ጥራት የጎደለው ቡና ነበር የሚልኩት፡፡ የሚሠሩት ከገበያ ላለመውጣት ነበር፡፡ ብሶቱም ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ እኛ አቅራቢዎችም በሕገ መንግሥት የተሰጠንን መብት የተነጠቅንበት ነበር፡፡ ስለዚህ በመድረኩ ሁሉም ወደ ስምምነት ለመድረስ ያስቻለው ችግሬ ብሎ ያቀርብ የነበረው ጥያቄ ስለተፈታ ነው፡፡ ችግር የነበረበት አካልም ያስተካክል ተብሎ በመወሰኑ ነው፡፡ ለሁላችንም አገራችንን ማዕከል ያደረገ መግባባት ላይ ነው የተደረሰው፡፡ በተለይ የገበያው ሒደት ችግር ነበረበት የሚለው ጉዳይ የበለጠ ስላግባባን ነው መፍትሔ ይሆናል ወደ ሚለው ነጥብ የተገባው፡፡ ስለዚህ ትልቅ ተስፋ አለን፡፡ አዲሱ አሠራር ወደታች ይወርዳል፡፡ መንግሥት ያመነበትም ስለሆነ በትክክል ይተገበራል፡፡ ሥራው የአስፈጻሚ አካላቱን ጥንካሬ ይጠይቃል፡፡ ለዚህም ጠንካራ ቦርድ ተመሥርቷል፡፡ ገበያው የሚመራው በቦርድ ነው፡፡ የአዲሱን የቡና ሪፎርም የሚከታተል ብሔራዊ ምክር ቤት ይቋቋማል፡፡ አጠቃላይ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡

ሪፖርተር፡- በአዲሱ አሠራር ይተገበራል ከተባለው አንዱ የቡና የመኪና ላይ ሽያጭ መፈቀድ ነው፡፡ ይህ ምን ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ቀደም ብሎ በነበረው አሠራር ረዥም ሰንሰለቶችን አልፎ የመጣው ቡና መጋዘን ከገባ በኋላ ነበር የሚሸጠው፡፡ ከየትም ይምጣ ቡናው አንድ ላይ ይከማቻል፡፡ ይህ አሁን ቀርቷል፡፡ ቡናው የመጣበት አካባቢ በሰርተፍኬት መገለጽ ነበረበት፡፡ ቡናው መኪናው ላይ እያለ አጠቃላይ የጥራት ደረጃው ተለይቶ እዚያው መኪና ላይ ሆኖ ለጨረታ ይቀርባል፡፡ ይህ መሆኑ በተለይ ከጥራት አኳያ ይቀርቡ የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል፡፡ የተለያዩ የቡና ዓይነቶችን ቀላቅሎ ሲሸጥ የነበረውን አሠራር ያስቀራል፡፡ ከመኪናው ሳይወርድ ገዥው ቡናውን የሚያዘጋጅበት ቦታ ማድረስ ሁሉ ያስችላል፡፡ በአካባቢህ ስያሜ ቡናህን ለመሸጥ ትልቅ ዕድል ይፈጥርልሃል፡፡ ስለአተገባበሩ መመሪያ ይዘጋጃል፡፡ በነፃ ግብይት ለመፈጸም የሚያስችል ነው፡፡ በጥቅሉ አዲሱ አሠራር ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛዋ ላኪ አገር እንድትሆን የተያዘውን ዕቅድ ለመተግበር ትልቅ መሣሪያ ይሆናል፡፡

Standard (Image)

ለሕክምና ባለሙያዎች የሥራ ላይ አደጋ የመድን ሽፋን መስጠት ተጀመረ

$
0
0

 

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጄነራል ኢንሹራንስ አክስዮን ማኅበር፣ በአገሪቱ የመጀመሪያውን ለሕክምና ባሙያዎች እንዲሁም በመስኩ ለተሠማሩ የተለያዩ አካላት የመድን ሽፋን የሚሰጥ አዲስ አገልግሎት ማቅረብ ጀመረ፡፡

ኩባንያው ይህንን አገልግሎት መጀመሩን በማስመልከት ሐሙስ ሰኔ 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ባካሔደው ሥነ ሥርዓት ወቅት፣ ‹‹ዶክተርስ ኤንድ ፕራክትሺነርስ ፕሮፌሽናል ኢንደሚኒቲ፤›› በሚል መጠሪያ አዲስ የኢንሹራንስ አገልግሎት ለገበያ ማቅረቡን ያስታወቀው ኩባንያው፣ ዶክተሮችና ሌሎችም የሕክምና ባለሙያዎች የሙያ ግዴታቸውን በሚወጡበት ወቅት በሚፈጠር ችግር ምክንያት ሊመጣባቸውን የሚችል የሕግ ተጠያቂነት ሥጋትን ለማቃለል የሚያስችል እንደሆነ ገልጿል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች አገሮች የተለመደ ቢሆንም፣ ከኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ፣ ከተጠቃሚዎች ፍላጎትና ከመግዛት አቅም ጋር ተገናዝቦ ለመጀመሪያ ጊዜ ለገበያ መቅረቡን የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽመልስ ገብረጊዮርጊስ ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የኢንሹራንስ አገልግሎት ታካሚዎች በሐኪሞችና በጤና ባለሙያዎች ላይ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት የሚቀርብባቸውን የሕግ ተጠያቂነት የሚሸፍን ሲሆን፣ በወንጀል የሚቀርብ ተጠያቂነት ግን በመድን ሽፋኑ እንደማይካተት ኩባንያው አስታውቋል፡፡

የሐኪሞችም ሆነ ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን የሚጠቀሰው ኩባንያው፣ በአሁኑ ጊዜ  ከ11,000 በላይ ሐኪሞች፣ 4,460 አዋላጅ ነርሶች፣ 668 ሰመመን ሰጪ ባለሙያዎች፣ 1,042 የጥርስ ሐኪሞች፣ 682 የጨረር ሕክምና ባለሙያዎች እና 628 የባዮ ሚዲካል ሳይንቲስቶች በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አክስዮን ማኅበር፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሕክምና ዘርፍ ውስጥ እየታየ ያለውን አወንታዊ ለውጥ እንዲሁም የባለሙያዎች ቁጥር መጨመርን ግምት ውስጥ በማስገባት አዲስ የመድን አገልግሎት ለመስጠት መነሳቱን አስታውቋል፡፡ በተለይ ከሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ እየታዩ ያሉ ጉዳቶች እየጨመሩ በመምጣታቸው ሳቢያ፣ አገልግሎት ሰጭዎችንም ሆነ ተገልጋዮችን በመድን ሽፋን ለማገዝ የሚረዳ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ የሕክምና ዶክተሮችና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ለኅብረተሰቡ የዕለት ተዕለት አገልግሎቶችን በሚሰጡበት ሒደት የሚያጋጥማቸውን ያልተጠበቀ የአደጋ ሥጋት መታደግ ስለሚቻልበት መንገድ ጥናት ሲያካሂድ ከቆየ በኋላ ለመተግር የተነሳበት የመድን ዓይነት እንደሆነም ከኩባንያ ኃላፊዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

 የኢንሹራንስ አገልግሎቱን ለመጀመር ያካሔደው ጥናትም የሕክምና ዶክተሮችና የጤና ባለሙያዎች ከአቅም በላይ በሆነ ያልታሰበ ክስተት በታካሚዎች ላይ በሚያደርሱት ጉዳት አለያም ስህተት ምክንያት ሕጋዊ ተጠያቂነት ሲመጣባቸው   ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት ሲያመራ ይታያል፡፡ በዚህ አግባብ የሚቀርብባቸውን ክስ ለመከላከል ታሳቢ  ያደረገ የመድን ሽፋን ነው፡፡ እንደሚደርሰው ጉዳት ሁኔታ ለተጎጂ ታካሚዎች ካሳ የመፈጸም ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑም በፋይንንስ አቅማቸው ላይ የሚደርሰውን ተፅዕኖ ለመገንዘብ እንደተቻለም ኩባንያው ያስረዳል፡፡

የካሳ ክፍያ ጣሪያው ኢንሹራንስ በሚገቡት የሕክምና ባለሙያዎች ውሳኔ መሠረት እንደሚፈጸም የኩባንያው ምክትል ሥራ አስፈፃሚ አቶ ብሥራት ኃይለሥላሴ ገልጸዋል፡፡ የመድን ካሳው እስከ ምን ያህል መጠን ሽፋን ይሰጣል?  ለሚለው ጥያቄ፣ የሕክምና ባለሙያው ከሚያጋጥመው የአደጋ ሥጋትና ከሥራው ባህሪይ፣ ከመክፈል አቅሙና ከፍላጎቱ ጋር እንደሚያያዝ ገልጸዋል፡፡ የመድን ውሉ እንደ ማንኛውም ሕይወት ነክ ያልሆነ ኢንሹራንስ በየዓመቱ የሚታደስ በመሆኑ፣ በዓመት ለምን ያህል ጉዳቶች የመድን ሽፋን እንደሚያስፈልጋቸው አስበው የሚገቡበት እንደሆነም አቶ ብሥራት ተናግረዋል፡፡

የአገልግሎቱን መጀመር አስመልክቶ ከሕክምና ባለሙያዎች ስለተሰጠው ግብረ መልስ በተሰጠው ማብራሪያም አገልግሎቱን ፈልገው እስካሁን ሊያገኙ እንዳቻሉ የሕክምና ባለሙያዎቹ እንደገለጹላቸው ያመለከቱት ኩባንያው ኃላፊዎች፣ የሕክምና ባለሙያዎች ማኅበራትም የአገልግሎቱን መጀመር በእጅጉ እንደሚፈልጉት መናገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ መድን ሽፋን ያላቸው ባለሙዎች አማካይነት አደጋ ቢደርስ፣ አደጋው ስለመድረሱ ማረጋገጫ የሚሰጠው አካል ማን ነው ለሚለውን በተመለከተ ለኩባንያው ኃላፊዎች ጥያቄ ቀርቦ ነበር፡፡ ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት አቶ ብሥራት ‹‹ኩባንያችን ጉዳቱን እንዴት ይወሰናል የሚለውን ቀድሞ አስቦበታል፡፡ አደጋው መፈጸሙ እንዴት ይረጋገጣል የሚለው በጣም አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑም ይህን የሚያጣራ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የተቋቋመ ቡድን አለ፡፡ በኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ውስጥ በተቋቋመ ክፍል የሚተዳደረው ይህ ቡድን በሚወሰነው መሠረት የካሳ ክፍያዎች ይፈጸማሉ፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ሜድኮ ሌጋል›› የሚባለው ይህ ቡድን ከተለያዩ የሕክምና ዘርፎች የተውጣጡ ባለሙያዎችን ማካተቱን የጠቀሱት አቶ ብሥራት፣ አደጋ ሲደርስ የሕክምና አሰጣጡ ወይም ሐኪሙ ጥፋት አለበት፣ የለበትም የሚለውን ውሳኔ የሚሰጡትም እነዚሁ ባለሙያዎች እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡ ስለዚህም በሕግ በተቋቋመ አካል በመኖሩ ውሳኔ አሰጣጡ እንደማያስቸግር ተናግረዋል፡፡

የመጀመሪያው ዘመናዊ ሆስፒታል በመሆን ዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል በ1894 ዓ.ም. ገደማ በንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ተቋቁሞ ሥራ ከጀመረ ጀምሮ፣ የጤናው ዘርፍ በለውጥ ሒደት ውስጥ እንደሚገኝ ያስታወሰው ኩባንያው፣ በአሁኑ ጊዜ ልዩ ልዩ የጤና አገልግሎቶች በመንግሥታዊና በግል ተቋማት እየቀረቡ፣ ተደራሽነታቸውም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

የሕክምና ሥልጠና የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማስፋፋታቸውም የሐኪሞችና የጤና ባለሙያዎች ቁጥር እንዲያድግ አግዟል፡፡ ከ12 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩ የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ሦስት ብቻ እንደነበሩም ኩባንያው አስታውሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ 28 የመንግሥት፣ ስምንት የግል ከፍተኛ የሕክምና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ሲኖሩ፣ በዓመት 2,000 ተመራቂዎችን የማፍራት አቅም አላቸው፡፡ በመሆኑም ይህንን ዘርፍ ከኢንሹራንስ አገልግሎት ጋር ማስተሳሰሩ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የዶክተሮችና የታካሚዎች ምጣኔ በአሁኑ ወቅት አንድ ለ15,000 መድረሱ ተጠቁሟል፡፡ መንግሥት ይህንን ምጣኔ አንድ ለ10,000 እንደሆን የማድረግ ዕቅድ ያለው በመሆኑ፣ በቅርብ ዓመታት ውስጥ ተከፍተው አገልግሎት እንደሚሰጡ የሚጠበቁት 13 ዩኒቨርሲቲዎች ሥራ ሲጀምሩም፣ የሐኪሞችና የታካሚዎች ምጣኔ አሁን ካለውም መጠን እንደሚቀንስ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያው ካስተዋወቀው የኢንሹራንስ አገልግሎት በተጨማሪ በሕይወት ነክ ኢንሹራንስ ዘርፍ ‹‹የትምህርት ቤት ክፍያ ዋስትና›› እንዲሁም ‹‹ሴቶችን ያማከለ የቡድን የሕይወት ብድር ማይክሮ ኢንሹራንስ›› የተባሉትን በማዘጋጀት ለገበያ እያቀረበ የሚገኝ ኩባንያ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

ኩባንያው የተጠቃሚዎችን የኢንሹራንስ ፍላጎቶችን በማጥናትና የባለሙያዎቹን የፈጠራ አቅም በመጠቀም አዳዲስ የኢንሹራንስ ዓይነቶችን ለገበያ በማቅረብ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን ድርሻ የማስጠበቅ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ አቶ ሽመልስ ጠቅሰው፣ በቅርቡም ተጨማሪ የኢንሹራንስ አገልግሎቶችን ይፋ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል፡፡

 

Standard (Image)

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የኬንያን በመብለጥ ከስምንት በመቶ በላይ እንደሚያድግ ይጠበቃል

$
0
0

 

  • የውጭ ኢንቨስትመንት በብዛት ከሚመጣባቸው አምስት አገሮች ተርታ ተመድባለች

ከሰሞኑ የኬንያ መገናኛ ብዙኃን የኬንያ የኢኮኖሚ የበላይነት በኢትዮጵያ መወሰዱን ሲዘግቡ ከርመዋል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ የዓለም ባንክ ይፋ ባደረገው ትንበያ መሠረት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ (ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት አኳያ) በ8.3 በመቶ እንደሚያድግ ባንኩ ይፋ አድርጓል፡፡

ኬንያውያኑ የዜና አውታሮች እንዳስተጋቡት ከሆነ የኬንያ የምሥራቅ አፍሪካ የበላይነት አክትሟል፡፡ ጊዜው የኢትዮጵያ ሆኗል ብለዋል፡፡ የዓለም ባንክን መረጃ መሠረት ያደረጉት መገናኛ ብዙኃኑ፣ ኢትዮጵያ የኬንያን ኢኮኖሚ በ3.6 ቢሊዮን ዶላር በመብለጥ በቀጣናው ግዙፉን የኢኮኖሚ አቅም ለመፍጠር የቻለችው በየዓመቱ ያስመዘገበችው ባለሁለት አኃዝ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ያወጣውን መረጃ ዋቢ በማድረግም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለፈው ዓመት በ73 ቢሊዮን ዶላር የሚለካ አቅም እንደነበረው፣ ከካቻምናው የ64.7 ቢሊዮን ዶላር ይልቅም በተያዘው ዓመት (እ.ኤ.አ. 2017) ወደ 78.3 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያድግ ትንበያውን በማውጣቱ፣ ኢትዮጵያን ከኬንያ ብልጫውን ለመውሰድ እንዳበቃት ሲዘገብ ሰንብቷል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ የኢኮኖሚ አውራነቷን ከሁለት ዓመት በፊት ለኢትዮጵያ ያስረከበችው ኬንያ በበኩሏ፣ ካቻምና ያስመዘገበችው የኢኮኖሚ መጠን ግዝፈቱ በገንዘብ ሲተመን 64 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ነበር፡፡ ዓምና የ69 ቢሊዮን ዶላር ግምት የነበረው ኢኮኖሚዋ፣ በዘንድሮው እንቅስቃሴው 75 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ የሚገመት በመሆኑ ከኢትዮጵያ አኳያ ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በታች ሆኗል፡፡

ኬንያውያን ተንታኞች በበኩላቸው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግዙፍ መንሳት አስተዋጽኦ አድርገዋል ያሏቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር መብዛት፣ የሕዝቡ መብዛትም ለአገር ውስጥ ገበያ የፈጠረው አቅም እንዲሁም ለውጭ ባለሀብቶች እንደልብ የቀረበው ርካሽ የሰው ኃይል ይገኙበታል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት ከኬንያ በእጥፍ ይበልጣል፡፡

ምንም እንኳ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ግዙፍ ሆኗል፣ ዓመታዊ ዕድገቱም ፈጣንና አብላጫ ያለው ቢባልለትም የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብታም የሚያሰኝበት ደረጃ ላይ ግን አልደረሰም፡፡ ኬንያውያንም ይህንኑ በመጥቀስ ከኢትዮጵያ እንደሚበልጡ ይናገራሉ፡፡ ይኸውም የኬንያ የነፍስ ወከፍ ገቢ (የአንድ አገር የኢኮኖሚ አቅም ለጠቅላላው ሕዝብ ሲካፈል የሚገኝ አሐዝ) ኬንያውያን ከኢትዮጵያውያን ይልቅ ሀብታሞች እንደሆኑ ያረጋግጣል፡፡ በዚህ ዓመት እንደሚኖር በሚታሰበው የኢኮኖሚ ዕድገትና በሕዝቡ ብዛት መሠረት (92 ሚሊዮን እንደደረሰ ታስቦ)፣ የኢትዮጵያውያን አማካይ የነፍስ ወከፍ ዓመታዊ ገቢ 848 ዶላር ወይም 18,650 ብር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ማለት ነው፡፡

በአንፃሩ ኬንያውያን የሚያገኙት ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከ1,650 ዶላር በላይ፣ በብር ሲገለጽ 36,300 ብር ስለሚደርስ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ በእጥፍ የሚበልጥ የገቢ ብልጫ ያላቸው፣ ሀብታሞች ኬንያውያኑ እንደሆኑ አሐዞቹ ያረጋግጣሉ፡፡ ኬንያ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ የምትመደብ አገር መሆኗም የታወቀ ነው፡፡ በአንፃሩ ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ መመደቧም እውነት ነው፡፡

ይህም ቢባል ግን በኬንያና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ዕድገት ልዩነት የሚያሰፉ የኢንቨስትመንት ሁናቴዎችም ይስተዋላሉ፡፡ አንደኛው አብነት በመንግሥት የሚካሄዱ ልዩ ልዩ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታ የሚጠቀስ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ያህል ፈርጀ ብዙ አይሁን እንጂ የኬንያ መንግሥትም በመንገድ፣ በባቡር፣ በኤሌክትሪክ ኃይል፣ በትምህርትና ጤና በሌሎችም መስኮች የሚጠቀሱ አንኳር የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችን ያከናውናል፡፡

ከመንግሥት ኢንቨስትመንት በተጨማሪ ግን በውጭ ባለሀብቶች የሚካሄዱ ኢንቨስትመንቶችም ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መበራከት ወሳኙን አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም መሠረት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የንግድና የልማት ጉባዔ የዚህ ዓመት የኢንቨስትመንት ሪፖርት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚጠቀሱ የኢንቨስትመንት መዳረሻዎች አንዷ ሆኗለች፡፡ በአንጎላ የ14 ቢሊዮን ዶላር ዓመታዊ የውጭ ኢንቨስትመንት መጠን ከሚመራው ጎራ የተሰለፈችው ኢትዮጵያ፣ ከግብፅ፣ ከጋና እና ከናይጄሪያ በመከተል በአፍሪካ ዋና ዋና የውጭ ኢንቨስትመንት መዳረሻ ተብለው ከተደለደሉ አገሮች አንዷ መሆኗን የተመድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2016 የተመዘገበው የውጭ ኢንቨስትመንት 3.2 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር የጠቀሰው ይኸው ሪፖርት፣ እንዲህ ያለው የኢንቨስትመንት መጠን የተመዘገበው የዓለም የሸቀጥ ንግድ እጅጉን እየተቀዛቀዘ በቀጠለበት፣ የውጭ ኢንቨስተሮችም ወደ አፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በታች ወዳሉት አገሮች ለመምጣት መነሳሳቱን ባጡበት ወቅት መሆኑ ግምት እንደሚሰጠው የሚያስገድድ የኢንቨስትመንት መጠን መሆኑን አመላክቷል፡፡

 በዚያም ላይ በኢትዮጵያ የሚገነቡ መሠረተ ልማቶችና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የሚያሳየው ለውጥ ኢትዮጵያ ላስመዘገበችው የውጭ ኢንቨስትመንት ዕድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል ያለው ይህ ሪፖርት፣ ኢንስትመንቱ የ46 በመቶ ዕድገት እንደነበረውም አትቷል፡፡

ምንም እንኳ በኢንቨስትመንትም ሆነ በኢኮኖሚያዊ ዕድገት የኢትዮጵያ ግስጋሴ ይህን ያህል ቢነገርለትም በሕዝቡ የዕለት ኑሮ መንጻበረቅ መጀመሩ ላይ ብዙ  ይቀረዋል፡፡ የኑሮ ውድነት በተለይም የምግብና የሌሎች ሸቀጦች ዋጋ በየጊዜው መናር፣ የከተማም ሆነ የገጠር ነዋሪውን የድህነት መጠን፣ የሥራ አጥነት ወዘተ ችግሮችን በመቀነስ ዕድገቱ የሚያደርገው አስተዋተዋጽኦ በብዙ የሚጠበቅ ይጠበቃል፡፡

ይህ እንዳለ ሆኖ ደጋግሞ የሚከሰተው የድርቅ አደጋ፣ ውዝፍ የብድር ዕዳ ክፍያ፣ ዕምና እንደተከሰተው ያለ የፖለቲካ ትኩሳት የሚያጋጥም ከሆነ በኢንቨስትመንቱም ሆነ በኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ምሁራን ይስማሙበታል፡፡ የዕድገቱም ዘላቂነት እንዚህና መሰል አንገብጋቢ ጉዳዮች እንደሚወስኑት ኬንያውያኑም ሆኑ የአገር ቤት ሰዎች ይስማማሉ፡፡

 

Standard (Image)

‹‹ጥናታችን በመጠኑም ቢሆን ጽንፈኝነት እንዳለ የሚያሳይ ቢሆንም መንግሥት ኢንተርኔት ለመዝጋት ሰበብ ሊሆነው አይችልም››

$
0
0

 

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፣ የሚዲያ ኤክስፐርት

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር) መቀመጫቸውን በደቡብ አፍሪካው ዊትዋተርስራንድ ዩኒቨርሲቲ ያደረጉ የሚዲያ ኤክስፐርት ናቸው፡፡ ኢጂኒዮ ተነፃፃሪ የሚዲያ ሕግና ፖሊሲ ላይ በማተኮር ይሰሩበት ከነበረው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ሴንተር ፎር ሶሽዮ-ሌጋል ስተዲስ ለቀው ዊትስ ዩኒቨርሲቲን የተቀላቀሉት እ.አ.አ. በ2016 ነው፡፡ ይሁንና አሁንም የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ አሶሼት ሪሰርች ፌሎው ናቸው፡፡ ከለንደን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ፒኤችዲ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ ከኦክስፎርድ በፊት በካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካና ዓለም አቀፍ ጥናቶች የትምህርት ክፍል ሠርተዋል፡፡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በአዲስ አበባ፣ እንዲሁም ለጣሊያን ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በሮም ይሠሩ ነበር፡፡ የኢጂኒዮ የጥናትና ምርምር ሥራዎች በተለይ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገሮችን የተመለከቱ የሚዲያና የፖለቲካ ለውጥ ጉዳዮች፣ እንዲሁም በመላው ዓለም እየተመነደጉ ያሉ ልዩ የሆኑ የኢንፎርሜሽን ማኅበረሰብ ሞዴሎች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ኢጂኒዮ በርካታ የጥናት ፕሮጀክቶችን የመሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በምሥራቅ አፍሪካ፣ የሰላም ግንባታና በአገር ግንባታ ላይ ያለውን ሚና የሚገመግመው፣ እንደ ቻይና ያሉ በመመንደግ ላይ የሚገኙ ኃይሎች በአፍሪካ ሚዲያና ቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ እየጨመረ የመጣውን ሚናቸውን ለመረዳት የተካሄደው፣ እንዲሁም ከምርጫ በፊት በኢንተርኔት አማካይነት የሚሠራጩ የጥላቻ ንግግሮች ባህሪና ተፅዕኖን ለመተንተን የተካሄደው ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የኢጂኒዮ የፒኤችዲ ጥናት በኢትዮጵያ ልማትና አለመረጋጋት ያላቸውን ግንኙነት የሚመረምር ሲሆን፣ በአገሪቱ ላይ ከ12 ዓመታት በላይ የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ ኢጂኒዮ በቅርቡ በግብፅ ካይሮ የናይል ቤዚን ካፓሲቲ ቢዩልዲንግ ኔትወርክና የዩኔስኮ ወተር ኤዱኬሽን ኢንስቲትዩት በመተባበር አዘጋጅተውት በነበረ ሥልጠና ላይ በአሠልጣኝነት ተሳትፈው ነበር፡፡ ሥልጠናው በናይል ላይ የሚሠሩ ሳይንቲስቶችና ጋዜጠኞች እየተመጋገቡ በሚሠሩበት መንገድ ላይ ግንዛቤ ለመስጠት ያለመ ነበር፡፡ በሥልጠናው የተሳተፈው ሰለሞን ጐሹ በኢትዮጵያ ስላለው የሚዲያ ነፃነትና የሥልጠናውን ጭብጥ በተመለከተ ኢጂኒዮን አነጋግሯቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡-በአፍሪካ ስላለው ወቅታዊ የሚዲያ ይዞታና የትኞቹ አገሮች የተሻለ አፈጻጸም እያሳዩ ስለመሆኑ ምን ይላሉ? ኢትዮጵያስ በአንፃራዊነት የት ትገኛለች?

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- አንዱን አገር ከሌላው አገር ጋር በማነፃፀር ደረጃ በማውጣት አላምንም፡፡ በኢትዮጵያ፣ በኬንያ፣ በሶማሊላንድ፣ በሩዋንዳና በተለያዩ አገሮች ካካሄድኩት ጥናቶች መረዳት የቻልኩት እነዚህ አገሮች ኮሙዩኒኬሽንን በተመለከተ የራሳቸው በጎ ጎን ያላቸው ቢሆንም፣ ይህን በዓለም ላይ ካለ የትኛውም አገር ኮሙኒኬሽን መዋቅር ጋር በቀላሉ ማነፃፀር እንደማይቻል ነው፡፡ በኬንያ ላይ በሠራሁት አንድ ጥናት ከታዘብኳቸው ጉዳዮች አንዱ በአገሪቱ የራዲዮ ቶክሾውስ በጣም ተወዳጅ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ደግሞ የመጣው እንደ ጣሊያንና እንግሊዝ በመሳሰሉ ሌሎች ቦታዎች ባልተለመደ ሁኔታ በፕሮግራሞቹ በሚስተናገዱ በንቁ ተሳትፎ የታጀቡ ክርክሮች የተነሳ ነው፡፡ ንቁ ተሳትፎው ደግሞ የመጣው በፕሮግራሞቹ የግለሰቦች ድምፅ ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰቡም መሰማት አለበት ከሚለው እምነት ነው፡፡ ሁሌም ግንዛቤ ውስጥ የማንከተው አንዱ ነገር በሚዲያ የሚነገሩ ነገሮች በመንግሥት ዝቅተኛ መዋቅር የሚገኙ አካባቢዎች ላይ ለውጥ ሊያመጡ የመቻላቸውን ዕድል ነው፡፡ በአፍሪካ እንዳየሁት  በብሔራዊ ደረጃ በአብዛኛው ተግዳሮትና ክፍተት ነው የሚሰማው፡፡ ነገር ግን በተዋረድ መዋቅሮች የሚዲያ ለውጥ የማምጣት ኃይል ይታያል፡፡

የአፍሪካ ሚዲያ ምን እንደሚመስልና ምን መምሰል እንዳለበት፣ እንዲሁም ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትን ጨምሮ በሕግ ማዕቀፍና በተግባራዊ አፈጻጸም መካከል ያለውን ተቃርኖ በተመለከተ ትልቅ ክርክር ይደረጋል፡፡ ለምሳሌ የካሜሩናዊው ምሁር ፍራንሲስ ንያምኖህ ሥራዎች የአፍሪካ ሚዲያ ልዩ ባህሪያት ምን እንደሚመስሉ ለማስገንዘብ የሚጥሩ ናቸው፡፡ ሌላኛው ደቡብ አፍሪካዊ ምሁር ኸርማን ዋሰርማን በኢንተርኔት ምንነት ላይ ተፈጥሯል ከሚባለው ዓለም አቀፋዊ ስምምነት በተቃራኒ፣ የአፍሪካን የኢንተርኔት ታሪክ ለመገንባት መጠየቅ ያሉብንን ጥያቄዎች ለማሳየት ይሞክራል፡፡ ስለዚህ አገሮቹን ከማነፃፀር ይልቅ በተጫባጭ በየአገሮቹ ያለውን ሁኔታ ማሳየት ይመረጣል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ አስደናቂ ለውጥ በማምጣት ላይ ብትሆንም፣ ለክርክር ምኅዳር ከመፍጠርና ሁሉም ወገን የሚያርፍበት መካከል ላይ ያለ ከባቢ ሁኔታ ከመፍጠር አንፃር ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ነች፡፡ ሚዲያው ከረጅም ጊዜ ጀምሮ እጅግ ጽንፍ የያዘ ነው፡፡ ከጋዜጠኝነትና ከተለያዩ ሙያዎች የመጡ ግለሰቦች በአገሪቱ ተቃራኒ ጫፍ ላይ የሚገኙ አካላት ተገናኝተው የሚያወሩበት አማካይ ሥፍራ ለመፍጠር በርካታ ሙከራዎች ሲያደርጉ አይቻለሁ፡፡ ይኼ በጣም ቅር የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡ እርግጥ ነው ጉዳዩ አወዛጋቢ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆነ በውስጡ ያሉ ግለሰቦች ይኼ አማካይ ሥፍራ እንዲኖር ዕድል የሰጡ መስለው ሁኔታው ለጊዜው እንዲኖር ካደረጉ በኋላ መልሰው በከፍተኛ ሁኔታ ሲዘጉት ይታያል፡፡ ሰዎች ማንም ጋዜጠኛ ወደ እስር ቤት ሊገባ አይገባም ሲሉ እሰማለሁ፡፡ እኔ በግሌ የምቃወመው እስሩን ሳይሆን ዓላማውን ነው፡፡ ማንም ቢሆን ባይታሰር ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን ጽንፍ የያዙ ጋዜጠኞች ላይ መንግሥት የሆነ ዕርምጃ ቢወስድ እረዳለሁ፡፡ ሆኖም ለእኔ ልብ የሚሰብር ሆኖ ያገኘሁት ድልድይ የሚገነቡና ከኅብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም እስከ አብዮታዊ ዴሞክራሲ፣ እንዲሁም የመንግሥትን ልማታዊ መንግሥት ነኝ ጨምሮ የአገሪቱን ተቋማዊ አደረጃጀት የሚያከብሩትንም ጭምር ሲዘጋ ማየቴ ነው፡፡ ይኼ አገሪቱን ወደ ኋላ የሚያስቀር ነው፡፡ ምክንያቱም የአገሪቱን ጥቂት ባለ ብሩህ አዕምሮና ምርጥ ወንድና ሴቶች ልጆችን እየተከታተሉ ዕርምጃ መውሰድ ለረጅም ጊዜ ዘላቂ አይሆንም፡፡      

ሪፖርተር፡- ከኢንተርኔት መስፋፋት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ላይ በሠሩት አንድ ጥናትዎ በከፍተኛ ወጪ የሚገነባው የኢንተርኔት መሠረተ ልማት የፖለቲካ መሣሪያ እንደሆነ ተከራክረዋል፡፡ ይኼ ከኢትዮጵያ ጋር በተለይ የተያያዘ ችግር ነው? ወይስ በአኅጉሩ በስፋት የተለመደ ጉዳይ ነው? 

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- በአኅጉሩ ቴሌኮሙዩኒኬሽንን በሞኖፖሊ የያዙ አገሮች ኢትዮጵያና ጂቡቲ ብቻ ናቸው፡፡ የኢትዮዽያ ፖሊሲ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ቢያንስ በአጭር ጊዜ የመቀየር ሐሳብ የለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት መሞገስ ያለበት አንድ ጉዳይ ቢኖር ዜጎችን እስከ መጨረሻው ተዋረድ ዘልቆ ለመድረስ ያለው ቁርጠኝነት ነው፡፡ ከተሜና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ብቻ ሳይሆን የተገለሉ ማኅበረሰቦችንም ለማካተት ይሞክራል፡፡ በአገሪቱ ካለው ብዝኃነትና አስቸጋሪ መልክዓ ምድር አንፃር ይህን ማድረግ ቀላል አይደለም፡፡ ነገር ግን ወደዚህ ግብ ለመድረስ የተመረጠው ስትራቴጂ በሞኖፖል የሚፈጸም በመሆኑ ማንንም አሸናፊ የሚያደርግ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን፣ የኢትዮ ቴሌኮም የቴክኒክ ተቀጣሪዎችን፣ እንዲሁም ፈንድ ያደረገውንና ሥራው ላይ ያሉ የቻይና ኩባንያዎች ተወካዮችና ሌሎች ሰዎችን ቃለ ምልልስ በማድረግ እንደተረዳሁት የትኛውም ወገን ደስተኛ አይደለም፡፡ ውድድር ባለመኖሩና ጫና ስለሌለ የቴሌኮም አገልግሎትን የማሻሻል ፍላጎት የለም፡፡ የአገልግሎት ጥራቱ እጅግ የወረደ በመሆኑ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሕዝብ ግን ቅሬታውን እያቀረበ ነው፡፡ ይህ አገልግሎት እንዲሻሻል በተለይ ከቴክኒክ አንፃር ሁሉም አካል የበኩሉን እንዲወጣ ዕድል ሊሰጠው ይገባል፡፡ ውድቀትንም ሆነ ስኬትን በታማኝነት መግለጽና መወያየት ያስፈልጋል፡፡ ዘርፉን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረግ የማድረግ ዕቅድ ከሌለ ቢያንስ ባለው ሥርዓት ውስጥ አማራጮችንና ማትጊያዎችን በማምጣት፣ ሁሉም ወገኖች እንዲወዳደሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ እስካሁን ይኼ እየሠራ አይደለም፡፡   

ሪፖርተር፡- መንግሥት ኢንተርኔት የምዘጋው በዚሁ አማካይነት የሚንሸራሸሩ ጽንፍ የረገጡ ሐሳቦች የአገሪቱን የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው በሚል ምክንያት ነው፡፡ አንዱ የምርምር ሥራዎ በኢንተርኔት የሚሠራጩ የጥላቻ ንግግሮችን የተመለከተ ነው፡፡ የጥናቱ ግኝቶች ምንድን ናቸው? የባለድርሻ አካላትስ አስተያየት ምን ይመስላል?

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- ጥናታችን በሌሎች አገሮች እንዳለው ሁሉ በኢትዮጵያም የጥላቻ ንግግርና የጽንፈኝነት መገለጫዎች እንዳሉ ያሳያል፡፡ ይህ ‹‹መቻቻል››የሚል ርዕስ የሰጠነው ጥናት በዓይነቱ ለየት ያለ ስለሆን እንኮራለን፡፡ አማርኛ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባሉ ኢትዮጵያዊያን የሚነገር በመሆኑ በፌስቡክ የሚንሸራሸሩ አደገኛ ንግግሮችን በቁጥር መግለጽ መቻላችን፣ በኢትዮጵያም ሆን በመላው ዓለም የተለየ ጥናት አድርጎታል፡፡ ውጤቱ ለሁሉም በግልጽ ተደራሽ እንዲሆን የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም የተገኘው ቁጥር 0.7 በመቶ እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ ጥናታችን በመጠኑም ቢሆን ጽንፈኝነት እንዳለ የሚያሳይ ቢሆንም መንግሥት ኢንተርኔት ለመዝጋት ሰበብ ሊሆነው አይችልም፡፡ ሌላው በጥናቱ ይፋ የሆነው ነገር ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮች በአብዛኛው የሚመጡት ከተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች አለመሆኑን ነው፡፡ በተቃራኒው ጥቂት ተከታይ ሰዎች ናቸው ይህ አዝማሚያ ያላቸው፡፡ ለዚህ በሰጠነው ትርጉም መሠረት ይህን የሚያደርጉት የመገለል ስሜት ካላቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የመጡ ናቸው፡፡ በአገሪቱ መፃኢ ዕድልና በሕይወታቸው ላይ ተፅዕኖ ባላቸው ፖሊሲዎች ላይ የመካተት ስሜት የላቸውም፡፡

ስለዚህ ኢንተርኔት የጥላቻ ንግግርን ከማንሸራሸር በላይ ሌሎች ንቅናቄዎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል፡፡ የተለየ የፖለቲካ አቅጣጫ ላላቸውና አገሪቱ በምን መንገድ መሄድ እንዳለባት የተለየ ሐሳብ ላላቸው ሰዎች መድረክ ሆኖም ያገለግላል፡፡ ይኼ አግባብነት ያለው አጀንዳ በመሆኑ በመንግሥት ተቀባይነት ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ድምፆች ጽንፈኛ ቢሆኑም ሌሎች ድምፆች ተገቢ ጥያቄ ያላቸው በመሆኑ ሊሰሙ ይገባል፡፡ በዚህ ሒደት የትውልድ ለውጥ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት፡፡ በተማሪዎች ንቅናቄ ጊዜ የተፈጠረው ጽንፍ የያዘ ልዩነት ሳቢያ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታት ተገቢ የሆኑ ክርክሮች እንዳይደረጉ እንቅፋት ሆኗል፡፡ በጥናታችንም የዚያ ትውልድ አባላት የፖለቲካ ሐሳባቸውን ሲገልጹ የጠብ አጫሪነት አዝማሚያ እንደሚታይባቸው ተገንዝበናል፡፡ በተቃራኒው የአዲሱ ትውልድ አባላት ከመንግሥት ጋር ወይም ሥልጣን ላይ ካለው ኃይል ጋር አተካሮ ውስጥ ከመግባት ይልቅ፣ ለውይይት ክፍት በመሆን አማራጭ ሐሳቦችን በማቅረብ ላይ እንደሚያተኩሩ ነው ያየነው፡፡

ሪፖርተር፡- የናይል ቤዚን አገሮች ሚዲያ የናይል ጉዳይን ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ እንደ ሚዲያ ባለሙያ የናይል ጉዳይ የሚዲያ ሽፋንን እንዴት ያዩታል?

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡-በአንፃራዊነት ለናይል ጉዳይ አዲስ ነኝ፡፡ ስለዚህ የምሰጠው አስተያየት በመማር ላይ ያለ ሰው አስተያየት ነው የሚሆነው፡፡ በአብዛኛው በሚዲያ እንደተለመደው ለናይል ጉዳይ የሚሰጠው ሽፋን ከግጭት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ግጭት እስካለ ድረስ ለግጭት ሽፋን መሰጠቱ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ ነገር ግን ግጭት ለመኖሩ ዕውቅና ከሰጠን በኋላ እሱን የምንሸፍንበት የተለያየ መንገድ ይኖራል፡፡ ግጭቱ ምን ያህል የተወሳሰበ እንደሆነ ለማብራራት የተለያዩ አካላትን ድምፅ ማካተት ይቻላል፡፡ የ21ኛው ክፍለ ዘመን በፈጠረው ዕድል በመጠቀም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚንፀባረቁ የግለሰብ አስተያየቶችን በሚዲያ ዘገባዎች ማካተት ይቻላል፡፡ ይህ ግን በአብዛኛው ተግባር ላይ ሲውል አይታይም፡፡

ሪፖርተር፡- ጋዜጠኞች የናይል ጉዳይ ላይ ሚዛናዊ ዘገባ መሥራትና በተመሳሳይ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እንደ ዜጋ እንዴት ማስከበር ይችላሉ?

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- ይኼ ብሔራዊ ጥቅም የሚባል ጽንሰ ሐሳብ በግሌ ያበሳጨኛል፡፡ በአጠቃላይ በአፍሪካና በመላው ዓለም ከተንሰራፋው የብሔርና ብሔርተኝነት ጽንሰ ሐሳብ ጋር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተጋጨሁ ነው፡፡ ቀደም ብሎ የጠራ ርዕዮተ ዓለም በመቅረፅና እሱንም በመግለጽ፣ እንዲሁም የፓን አፍሪካኒዝም ስሜትን በማቀንቀን የሚታወቁት የመለስ ዜናዊ አንዳንድ ሐሳቦችን አደንቅ ነበር፡፡ እርግጥ ነው ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ፕሬዚዳንት እንደሚያደርገው የኢትዮጵያን ያስቀደመ እንቅስቃሴ ነበር የሚያደርጉት፡፡ እ.ኤ.አ. በ1950ዎቹ፣ በ1960ዎቹ እና በ1970ዎቹ ለአፍሪካ አርዓያ የሚሆኑ የሚዲያ ውጤቶች ነበሩ፡፡ በወቅቱም የቀድሞ ጋዜጠኞች የነበሩት ክዋሜ ንክሩማህንና ጆሞ ኬንያታን የመሳሰሉ ሰዎች ከአገር የዘለለ ርዕይ አስፈላጊነትን ይሰብኩ የነበረ ቢሆንም፣ ብሔራዊ ንቅናቄዎችን በሚያገለግል መንገድ የተቃኘ መሆኑ ግን አልቀረም፡፡ የተለያዩ አገሮችን ለሚያካልለው ናይል የፓን አፍሪካኒዝም ስሜት ሊጠቅም ይችላል፡፡ በብሔርተኝነት ዘመን የፓን አፍሪካኒዝም ስሜት ጥቅም ላይ የማይውል ከሆነ ምናልባትም ጋዜጠኞች መልሰው ሊያመጡት ይገባል፡፡ ጋዜጠኞች አንዱ መጠየቅ ያለባቸው ጥያቄ ከአፍሪካ አኅጉር በቀላሉ መውጣት የማይችለው ውኃ ይህን ሁሉ ግጭት ሲፈጥር፣ ከአፍሪካ እየወጡ ሌሎች አገሮችን የሚጠቅሙ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶች ለምን ተመሳሳይ ችግር እንደማይፈጥሩ ነው፡፡     

ሪፖርተር፡- ሥልጠናው አንዱ ትኩረት ያደረገበት ጉዳይ ጋዜጠኞች በናይል ጉዳይ ላይ ከሚሠሩ ባለድርሻ አካላት ጋር እንዴት ተቀናጅተው እንደሚሠሩ ነው፡፡ ጋዜጠኞች ሚዛናዊ ሆነው ሙያቸውን አክብረው መሥራትና በተመሳሳይ የራሳቸው አጀንዳ ሊኖራቸው ከሚችለው እነዚህ አካላት ጋር በትብብር ሊሠሩ የሚችሉት እንዴት ነው?

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- በዚህ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች ሐዘን ይሰማኛል፡፡ በተለይ የኅትመት ጋዜጠኞች በኢንተርኔት በነፃ ከተለያዩ ምንጮች ከሚገኝ መረጃ በሚገጥማቸው ውድድር የተነሳ ከፍተኛ ጫና ውስጥ ናቸው፡፡ በዚህ ጫና ላይ ጋዜጠኞች በናይልና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ኤክስፐርት እንዲሆኑ መጠበቅ ከባድ ነው፡፡ ጋዜጠኞች አንዳንድ ጉዳዮች አከራካሪ መሆናቸውን ለመረዳት የግድ ዝርዝር ዕውቀት አያስፈልጋቸውም፡፡ በብሔራዊና በዓለም አቀፍ ሚዲያ ላይ በሚሰጡ አስተያየቶች ሐሰተኛ የሳይንስ መረጃ እንደሚሰጥም አስተውለናል፡፡ እነዚህ ሐሰተኛ ቁጥሮች እንዲታረሙና ውይይት እንዲደረግባቸው ጋዜጠኞች ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡  

ሪፖርተር፡- እንደ ሚዲያ ባለሙያነትዎ በናይል ጉዳይ ላይ ሚዲያው የትብብርንም ሆነ የግጭት አቅጣጫን ተከትሎ ሽፋን ሲሰጥ እንዳዩ አምናለሁ፡፡ ይህን የተፈጥሮ ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደርና ለመጠቀም እንዲቻል፣ ከዚህ አንፃር ሊቀየሩ የሚገባቸው ተጋዳሮቶች ምንድን ናቸው?  

ኢጂኒዮ ጋግሊያርዶኔ (ዶ/ር)፡- እንደዚህ ዓይነት ሥልጠናዎች ላይ ጋዜጠኞች እርስ በርስ ሲከባበሩና ለሌሎች ሰዎች ሐሳብም አክብሮታቸው የሚታይ ቢሆንም፣ ጋዜጠኞች ወደ አገራቸው ሲመለሱ በሥራዎቻቸው ይህ ስሜት አይታይም፡፡ ለዚህ ከላይም ሆነ ከታች የሚመጣው ጫና አስተዋጽኦ እንዳለው እረዳለሁ፡፡ ነገር ግን ጋዜጠኞቹ ለብሔራዊ ታዳሚዎቻቸው ሲጽፉ ከዚህ ስሜት ውስጥ ጥቂቱን እንኳን ይዘው ቢቆዩ ትልቅ መሻሻል ያመጣ ነበር፡፡ አንዳንዴ ጋዜጠኞች ሚዛናዊና ገለልተኛ ናቸው የሚል አስተሳሰብ ሲንፀባረቅ አያለሁ፡፡ ነገር ግን አንዳንዴ ጋዜጠኛው የራሱን ስሜት ሲያካፍል ብቻ ነው ሁሉንም መረጃ በዓውድ በዓውዱ ማሳየት የሚችለው፡፡ ከናይል ጉዳይ አንፃር ይኼ አስፈላጊ ነው፡፡ ግጭቶች በአግባቡ ከተያዙ ብዙ ልንማርባቸው እንችላለን፡፡ ከግጭት በኋላ ሰዎች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ዋጋዎች ላይ ዳግም ግምገማ ሊያደርጉና የተፈጠሩትን ስህተቶች ሊያዩ ይችላሉ፡፡

 

Standard (Image)

ቀርፋፋውን ኢንዱስትሪ ለማነቃቃት ንግድ ምክር ቤት የቢዝነስ ሩጫ አሰናድቷል

$
0
0

 

መንግሥት በአገሪቱ የኢኮኖሚ መቀዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት ኢንዱስትሪ መር ጉዞ ጀምሬያለሁ ካለ ሰነባቷል፡፡ በመጀመርያውም ሆነ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች እየተተገበሩ ቢሆንም፣ በዘርፉ የሚፈለገው ውጤት ሊመዘገብ አልቻለም፡፡

በጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት ከማኑፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ከጠቅላላው የአገራዊ ኢኮኖሚ ድርሻው ከአምስት በመቶ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ቢሆን ሊመዘገብ የቻለው የግንባታ ዘርፉ በ8.5 በመቶ በማደጉ ነው፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዓመታት የግምገማ ሪፖርት እንሚያሳየውም በኢንዱትሪ ዘርፍ ውስጥ ዋናው የዕድገት አንቀሳቃሽ የኮንስትራክሽን ዘርፍ ነበር፡፡

በዚሁ ግምገማ መሠረት የአገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ድርሻ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ አገሮችም ሳይቀር በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም ከግብርና ዘርፍ ወደ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱትሪ ዘርፍ የሚደረገውን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚደረገው ርብርብ መስፋፋት እንዳለበት የሚጠቁም ነው፡፡ ዘርፉ ተፈላጊውን ውጤት እንዲያስመዘግብ ደግሞ የግል ባለሀብቱ ድርሻ ከፍተኛ እንደሆነ ይሰመርበታል፡፡  

የግል ባለሀብቶች ግን በሚፈለገው መጠን ወደ አምራች ዘርፉ እየመጡ አለመሆናቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡ እንደ ንግድ ምክር ቤት ያሉ የግሉ ዘርፍ ወኪል ተቋማትም አባሎቻቸውም ሆኑ ሌሎች አካላት በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እንዲሳተፉ የሚያግዙ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ እንደማይታዩ ይነገራል፡፡

በመንግሥት ውጥን በቀላል ማኑፋክቸሪንግ መስክ ኢትዮጵያን የአፍሪካ እንብርት  ለማድረግ እንዲቻል የግሉ ዘርፍ አስተዋጽኦ እንደጠበቀ ሁኖ ዘርፉን ወደ ማኑፋክቸሪንግ እንዳይመጣ ያላስቻሉ ምክንያቶች እንዳሉ፣ የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሰሎሞን አፈወርቅ ይገልጻሉ፡፡ ችግር ሆነው ከሚታዩት አንዱ በቂ የግንዛቤ ሥራ አለመሠራቱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ቢዘገይም ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር ዓይነተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት እንዲደረግበት በማሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን ማዘጋጀት ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ‹‹ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ!›› በሚል ርዕሥ ያዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ማሟሻ ሆኗል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የንግድ ትርዒትና ኩነት ዳይሬክተሮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ባግናወርቅ ወልደ መድኅን እንደሚጠቅሱት፣  ለኢኮኖሚው ዋልታ በሆነው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ ባለሀብቶች ገብተው እንዲሠሩ የተለያዩ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ ሆኖም የሚያጠግብ ለውጥ አልመጣም፡፡ ስለዚህ በተለየ ዘዴ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ የቢዝነስ ሩጫ ለማሰናዳት ተነስተናል ይላሉ፡፡ እንደሳቸው ገለጻ፣ የግሉ ዘርፍ በሚጠበቀው መጠን ወደ ማኑፋክቸሪንግ ያልገባበት አንዱ ችግር ግንዛቤ ማስጨበጥ ስላልተቻለ ነው፡፡  

ወ/ሮ ባግናወርቅ አባባላቸውን ለማጠናከር በቢዝነሱ ዓለም በተለይም በአስመጪነት ከ60 ዓመታት በላይ የቆዩ፣ የአንድ አንጋፋ ነጋዴን ተሞክሮ በምሳሌነት ይጠቅሳሉ፡፡

‹‹እኝህ አዛውንት ነጋዴ ይህንን ያህል ዓመት ፍሪጅ በማስመጣት ሲሠሩ የቆዩ ናቸው፡፡ ፍሪጅ እያስመጡ ይሸጣሉ፡፡ ይህንን ሲሠሩ ነው ያረጁት፡፡ ልጆቻቸውም ይህንኑ ሥራ ቀጥለዋል፡፡ የተለወጠነ ነገር የለም፡፡ ነገር ግን ፍሪጁን እዚህ እንዲገጣጠም ባያደርጉ ራስዎንም አገርዎንም ይጠቅማሉ ስንላቸው፣ ‹ይህንን ማነገረኝ ታዲያ?› ነበር ያሉት››፡፡  

ስለዚህ ባለሀብቱ ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍ እንዲገባ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ አልተሠራም የሚለው ምክንያት የሚያስኬድ በመሆኑ፣ ንግድ ምክር ቤቶችም ድርሻቸውን ለመወጣት፣ ‹‹ለኢንዱስትሪ ልማት እንሩጥ!›› በሚል ርዕሥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰናዳ የቢዝነስ ሩጫ የግንዛቤ ውድድር መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በመጪው እሑድ፣ ግንቦት 27 ቀን 2009 የሚካሄደው ይህ ሩጫ፣ በየዓመቱ በቋሚነት ለማካሄድ የታሰበ ሲሆን፣ ሩጫው 3,000 ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል፡፡ እስካሁንም ከ2,000 በላይ መመዝገባቸው ታውቋል፡፡

አቶ ሰለሞን ስለሩጫው እንደገለጹት፣ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወተው የኢንዱስትሪ በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ፣ የአገር ውስጥ ባለሀብቱ ተሳታፊ እንዲሆን መንደርደሪያ ሊሆን እንደሚችል ታስቦ የተሰናዳ ነው፡፡

እስካሁን በነበረው አካሄድ በተለያዩ ስብሰባዎች የምክክር መድረኮችና በተመሳሳይ መንገዶች የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ወደ ኢንዱስትሪ በመግባት ኢንቨስት እንዲደርጉ መረጃው ቢተላለፍም፣ በታሰበው ልክ ባለሀብቱ ተሳታፊ ሊሆን አይችልም፡፡

በኢንዲስትሪው ዘርፍ የውጭ ኢንቨስተሮች አብላጨውን ድርሻ ሲይዙ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ግን ወደ ዘርፉ ለመግባት ያላቸው ተነሳሽነት ዝቅተኛ በመሆኑ ይህ እንዲለወጥ የሚረዳ ግንዛቤ ለመፍጠር የተሰናዳ የሩጫ ውድድር ነው፡፡ ዘርፉን ለማገዝ በተገነቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሳይቀር የውጭ ባለሀብቶች ብልጫውን እየወሰዱ ነው ያሉት አቶ ሰሎሞን፣ ይህ አካሄድ ሥጋት እንደሚያሳድር ይናገራሉ፡፡ አገራዊውን ባለሀብት በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚኖረውን ተሳትፎ በማቀጨጭ አደጋ ላይ ሊጥል ስለሚችል ባለሀብቱ ዓይኑን ወደ ኢንዱስትሪው እንዲጥል የተለየ ነገር እናድርግ በሚል ለኢንዱስትሪ እንሩጥ በማለት አዘጋጅተነዋል ብለዋል፡፡

ወደ ኢንዱስትሪ ለሚደረገው ሽግግር እንዲረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫው  የሩጫ ፕሮግራም በቂ አይደለም ያሉት ወ/ሮ ባግናወርቅ፣ ሌሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልቶችም ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡ መጪውን የቢዝነስ እንቅስቃሴ ያገናዘበ፣ አገራዊ ጠቀሜታ ያለውን ሥራ ለመሥራት ሌሎች ዘዴዎችን መጠቀም አለብን ይላሉ፡፡

አቶ ሰለሞን እንደሚጠቅሱት ዘርፉን ለመቀላቀል ችግር የሚያጋጥማቸው ከሆነም ችግሩን ለመፍታት የንግድ ምክር ቤቱም እገዛ ያደርጋል፡፡ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በተለያዩ የምክክር መድረኮች ችግሮችን በማሳየት መፍትሔ እንዲሰጥባቸው ለማድረግ ጥረታችን ይቀጥላል ያሉት አቶ ሰለሞን፣ የንግዱ ኅብረተሰብ በኢንዱስትሪ ውስጥ በመግባት ኢንቨስትመንቱን ማስፋፋት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

የንግድ ማኅበረሰቡን ጨምሮ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ አትሌቶች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም አካላት ይሳተፉበታል የተባለው የቢዝነስ ሩጫ አምስት ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡ ከመስቀል አደባባይ ተነስቶ በጋንዲ ሆስፒታል በኩል በሜክሲኮ አደባባይ ዞሮ ቡናና ሻይ ሕንፃ ሲደርስ ይጠናቀቃል፡፡

Standard (Image)

ለጃፓን ባለሀብቶች የሚውል ልዩ የኢንዱስትሪ ዞን በቦሌ ለሚ ሁለት ሊገነባ ነው

$
0
0

በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ በሚገነባው የቦሌ ለሚ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ለጃፓን አምራቾች የሚውል ልዩ የኢንዱስትሪ ዞን ለመመሥረት የሚያግዝ የመግባቢያ ስምምነት ይፈረማል፡፡

ረቡዕ ሰኔ 7 ቀን 2009 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና በጃፓን ወገን የሚፈረመው የመግባቢያ ስምምነት፣ በቦሌ ለሚ ሁለት ውስጥ ለጃፓኖች ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለማምረት የሚውል ልዩ የኢንዱስትሪ ዞን ለመመሥረት እንደሚያስችል ይጠበቃል፡፡

ስምምነቱን በጃፓን ወገን የሚፈርሙት ተሞኒየስ የተባለው የጃን የኢንቨስትመንት ኩባንያ ሲሆን፣ ዘፊር የተሰኘውና በካምቦዲያ የፕኖም ፔን ልዩ ኢኮኖሚክ ዞን ባለድርሻ የሆነው የዚህ ኩባንያ ወኪሎች እንደሚሆኑ ከጃፓን ኤምባሲ እንዲሁም ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2012 የተመሠረተው ቶሞኒየስ ኩንያ፣ በጃፓን የሪል ስቴት ዘርፍ እንዲሁም የደረቅ መርፌ ሕክምና ማዕከል በሰፊው ይንቀሳቀሳል፡፡ ከዚህም ባሻገር በካምቦዲያ ትልቁ እንደሆነ የሚነገርለት፣ የፕኖም ፔን ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ባለድርሻ በመሆን ያስተዳድራል፡፡

መንግሥት የጃፓን ባለሀብቶች በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ለማድረግ በብዙ ሲወተውት ከርሟል፡፡ የዚህ ልዩ ዞን ስምምነት ወደ ተግባር መሸጋገር ከቻለም ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ ጃፓናውያን አምራቾች እንደሚሳተፉበት የሚጠበቅ፣ መንግሥትም በጉጉት የሚጠብቀው ፕሮጀክት ነው፡፡

ይሁንና እስካሁን ባለው ሒደት መንግሥት እንደሚፈልገው መጠን የጃፓን ባለሀብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት አልተቻለውም፡፡ ጃፓናውያኑ የኢትዮጵያ መንግሥት የጃፓንም ሆነ የሌሎች ያደጉ አገሮች አምራቾች የሚፈልጓቸውን የመሠረተ ልማት አውታሮች ማሟላት አልቻለም ይላሉ፡፡ ለአብነትም እንደ ሐዋሳ ወይም እንደ ቦሌ ለሚ አንድ ያሉ ሰፋፊ የማምረቻ ሼዶችን መደርደሩን አይቀበሉትም፡፡ ጃፓኖች ባለሀብት ከአንድ ሔክታር በታች፣ አነስተኛ መሬት ላይ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸው፣ በራሳቸው የዲዛይንና የማምረቻ ቦታ አገባብ ሥርዓት መሠረት መሥራት እንደሚፈልጉ ደጋግመው ይገልጻሉ፡፡

ጃፓኖቹ በተለይ የኢትዮጵያ መንግሥት በኢንቨስትመንት ሕግ፣ በቀረጥ ነፃና በኢንቨስትመንት ሕጎችና በሌሎችም መስኮች የሚደጉ ማሻሻያዎችና ለውጦች ጥያቄ እንደሚፈጥሩባቸው ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ መንግሥት የሚያወጣቸው መመርያዎችና ደንቦች ተለዋዋጭነት ሥጋት እንደፈጠሩባቸው ሲገልጹ ይደመጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ ቢባልም ግን ለጃፓኖች በሚያመቻቸው መንገድ፣ በራሳቸው ዲዛይንና የግንባታ ፍላጎት መሠረት የኢንዱስትሪ ፓርክ መገንባት የሚችሉበትን ቦታ ማዘጋጀቱን ይፋ ካደረገ ሦስት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ፣ የጃፓን አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም በሚል ርዕስ በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነበር የኢትዮጵያ መንግሥት ለጃፓኖቹ የኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ የሚውል መሬት ማዘጋጀቱን ይፋ ያደረጉት፡፡

በጃፓኖች የተቀዛቀዘ ምላሽ የመንግሥት ባለሥልጣናት ያን ያህል ደስተኞች እንዳልሆኑ እየታየ ነው፡፡ ይሁንና እንደ ፒቪኤች ያሉ የአሜሪካ ኩባንያዎች መምጣታቸው ግን የጃፓኖቹን ፍላጎት ሳይቀስቀስ እንዳልቀረ ይገመታል፡፡

ምንም እንኳ የጃፓን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት ለማድረግ ያሳዩት ፍላጎት የተቀዛቀዘ ይሁን እንጂ የጃፓን መንግሥት ግን በኢትዮጵያ የሚታዩ የውጭ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታቱ እንቅስቃሴዎችን እየተከታተለ መረጃውን እንደሚያደርስ የጃፓን ኤምባሲ ሲያስታውቅ ቆይቷል፡፡

ከዚህ ባሻገር የጃፓን ንግድና ኢንቨስትመንትን በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ለማድረግ የሚሠራ ተቋም ጽሕፈት ቤትም ሥራ ከጀመረ ወራትን ማስቆጠሩ፣ ጃፓን በኢትዮጵያ ስላላት የወደፊት ፍላጎት ማሳያ ሆኖ እየቀረበ ነው፡፡ የጃፓን ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋም (ጄትሮ) ጽሕፈት ቤቱን የከፈተው በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ተደጋጋሚ ጥያቄ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ይኸው ተቋም የጃፓን ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግ ተገቢውን መረጃ በመተንተን የማሠራጨት ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

የዓለም ባንክ የቦሌ ለሚ ምዕራፍ ሁለት ግንባታን ጨምሮ የቅሊንጦ ኢንዲስትሪ ፓርኮችን ለመገንባት የሚያስችል የ250 ሚሊዮን ዶላር ብድር መስጠቱ ይታወሳል፡፡ ፓርኩ በ186 ሔክታር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን፣ ምንም እንኳ ረጅም ጊዜ ቢፈጅም በቅርቡ ይጠናቀቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ አንዱ ነው፡፡

እስካሁን የተገነቡትን ቦሌ ለሚ አንድና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ኤኮ ፓርክን ጨምሮ 13 የኢንዱትሪ ፓርኮች ግንባታ እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የኮምቦልቻና የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ተጠናቆ በሰኔ ወር መጨረሻ እንደሚመረቁ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

 

 

 

Standard (Image)
Viewing all 720 articles
Browse latest View live