Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

የሲንጋፖር ኩባንያዎች በአገልግሎት መስክ መሰማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ

$
0
0

ለአራት ቀናት በአዲስ አበባ ቆይታ ያደረጉ 20 የሲንጋፖር ንግድ ልዑካን፣ በኢትዮጵያ የትምህርት፣ የጤና እንዲሁም የሆቴል መስኮች ላይ ከአገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ፡፡

ኩባንያዎቹን የመራው አስኮት የተባለው የሲንጋፖር ግዙፍ ኩባንያ፣ ከእስያ ባሻገር፣ በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በአፍሪካ በሚንቀሳቀስባቸው አፓርታማዎችን ሙሉ በሙሉ አሟልቶ በማስተዳደርና ባለቤት በመሆን ለአፓርታማ ሆቴልነት በማብቃት ሲሆን፣ በኢትዮጵያም በዚህ መስክ አብረውት ሊሠሩ ከሚችሉ ኩባንያዎች ጋር ተነጋግሯል፡፡ ከዚህ ኩባንያ ባሻገር ዊልማር ኢንተርናሽናል፣ ኦላም ኢንተርናሽናል የተባሉትን ጨምሮ በርካቶቹ ከአገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር መሥራት የጀመሩና አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ያሳዩ ሆነዋል፡፡

ዊልማር ኢንተርናሽናል ከዚህ ቀደም ከአልሳም ኩባንያ ጋር በጋራ በመሆን የሳሙና፣ የፓልም ዘይት ማጣሪያ፣ የሰሊጥ ማቀነባበሪያና ሌሎችም 14 ያህል ልዩ ልዩ ፋብሪካዎችን የሚያቅፍ ግዙፍ ፋብሪካ ለመገንባት መስማማቱና መሬት መረከቡ ይታወሳል፡፡ እንደ ዊልማር ሁሉ ኦላም ኩባንያም በአግሪ ቢዝነስ መስክ በተለይ በቅባት እህሎች በቡና በሌሎችም የተለያዩ የግብርና ውጤቶች መስክ ለመሥራት እንደ ሙለጌ ቡና ያሉትን ኩባንያዎች አነጋሯል፡፡

ከዚህ በሻገር አይኢ የተባለው የትምህርትና ሥልጠና ኩባንባም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና መስክ ለመሥራት ከትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች ጋር መነጋገሩ ታውቋል፡፡ ሌሎችም በጤና፣ በማዕድንና በነዳጅ መስክ ለመሠማራት ከመንግሥትና ተወካዮችና ከግል ኩባንያዎች ጋር ተነጋግረዋል፡፡

በሲንጋፖር የንግድ ፌዴሬሽን አማካይነት በየዓመቱ እየተካሄደ ዘንድሮ ሦስተኛ ዓመቱን የያዘው የሲንጋፖር ንግድ ልዑካን ጉብኝት ከሌሎች ይልቅ በዚህ ዓመት የተሻለ ለውጥ ቢታይበትም ነገሮች በሚፈለገው ፍጥነት መሄድ እንዳልቻሉ፣ የፌዴሬሽኑ ዳይሬክተር ኮዲ ሊ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ይሁንና ቀስ በቀስ የሚመጡትን ለውጦች በትዕግሥት ወደ ውጤት ለመለወጥ የፌዴሬሽኑ አባላት ተስፋ እንዳላቸው ሊ ጠቅሰዋል፡፡

ዘንድሮ ከኢትዮጵያ ባሻገር ሩዋንዳን የጎበኘው የሲንጋፖር ልዑካን በኪጋሊ ቆይታው የተሻለ ፍላጎት፣ ከሩዋንዳ መንግሥት ማየቱን ሊ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በሲንጋፖር የመከላከያና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም በሲንጋፖር የደቡብ ምሥራቅ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር ሞሐመድ ማሊኪ ቢን ኦስማን የተመራው የሲንጋፖር የንግድ ፌዴሬሽን ከ100 የኢትዮጵያ አቻው ጋር ተነጋግሮ፣ የእርስ በርስ የንግድ ድርድር ሲያደርግ ቆይቶ ተመልሷል፡፡

ዶ/ር ማሊኪ በንግግራቸው እንደጠቀሱት በኢትዮጵያና በሲንጋፖር መካከል የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቢኖርም፣ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት የነበረው የንግድ ልውውጥ መጠን 25 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ያስመዘገበ እንደነበርም ጠቁመዋል፡፡

ምንም እንኳ በሁለቱ አገሮች መካከል የንግድ ግንኙነቱ ደካማም ቢሆን ባለፈው ሳምንት በሲንጋፖር በተስተናገደው አፍሪካ ሲንጋፖር የቢዝነስ ፎረም ወቅት በኢትዮጵያና በሲንጋፖር መንግሥታት መካከል ተደራራቢ ታክሶችን ለማስቀረት ስምምነት መደረጉን ዶ/ር ማሊኪ አስታውሰዋል፡፡

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles