Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

የኢትዮጵያና የቼክ ኩባንያዎች ሽርክና ማኅበር በሻኪሶ የወርቅ ፍለጋ ፈቃድ ተሰጠው

$
0
0

በኢትዮጵያና በቼክ ሪፐብሊክ ኩባንያዎች የተመሠረተው ሞራቪያ የማዕድን ኩባንያ፣ በኦሮሚያ ክልል በኦዳ ሻኪሶ ወረዳ፣ በጉጂ ዞን 92 ካሬ ኪሎ ሜትር በሚያካልሉ በአምስት ብሎኮች የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ለማካሄድ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የሽርክና ማኅበሩ ለሪፖርተር እንዳስታወቀው፣ ለመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ፍለጋ ለማካሄድ የሚስችለውን ፈቃድ በማግኘት፣ ከማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ጋር ስምምነት የተፈራረመው ባለፈው ሳምንት፣ ነሐሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ነበር፡፡

አቶ ዳዊት ሽብሩ የሞራቪያ ሽርክና ማኅበር ባለቤት ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ በሻኪሶ የወርቅ ፍለጋ ለማካሄድ ውለታ የገባው ኩባንያ ከፍለጋው በኋላ በሚያገኘው ውጤት ላይ ተመሥርቶ የማልማት ሥራ ውስጥ የመግባት ፍላጎት አለው፡፡

በወርቅ ማዕድን ፍለጋ ሥራ ለተቋቋመው ማኅበር ውስጥ የቼክ ሪፐብሊኩ ሞራቪያ የብረታ ብረት አምራች ኩባንያ በዓለም ላይ ከሚታወቁ ብረታ ብረት አምራቾች አንዱ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዳዊት፣ ኩባንያው በተለይ በእስታፋ ብረት ወይም ዋየር ሮድ አምራችነቱ ይበልጡን እንደሚንቀሳቀስ ጠቅሰዋል፡፡ ኩባንያው የሚያመርታቸው ልዩ ልዩ የብረታ ብረት ውጤቶች ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የባቡር መስመር ዝርጋታ ሥራ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ይጠቀሳሉ፡፡

አቶ ዳዊት ከዚህ ቀደም ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከመሠረቱትና ኳድራንት ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባሻገር፣ ኒውኢራ የተባለውን ለሴራሚክ፣ ለመስታወትና ለሌሎችም ኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚሆኑ ምርቶችን ለማምረት የተቋቋመ ነው፡፡ ኩባንያው በደቡብ ክልል በኢንዱስትሪ ማዕድናት ምርት መስክ ለመሥራት ፈቃድ መውሰዱ ታውቋል፡፡ ሞራቪያ የማዕድን አምራች ኩባንያ፣ ወደፊት በታንተለም ምርትና ሌሎችም እሴት ተጨምሮባቸው ወደ ውጭ ሊላኩ በሚችሉ የማዕድናት ምርቶች ላይ የመሰማራት ዕቅድ እንዳለውም አቶ ዳዊት አብራርተዋል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles