Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

4.7 ቢሊዮን ብር የወጣበት መንገድ ሥራ ጀመረ

$
0
0

ከ4.7 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣበትና አዲስ አበባን በሁለት አቅጣጫ ከአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ ጋር የሚያገናኘው የአቃቂ ለቡና የአቃቂ ጎሮ (አይቲ ፓርክ) ውጫዊ የቀለበት መንገድ ተጠናቅቆ ሙሉ ለሙሉ ለትራፊክ ክፍት መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን እንዳስታወቀው፣ 28 ሜትር የጎን ስፋት ያለው ይህ መንገድ ስድስት ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ በግራና በቀኝ በኩል ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ የተገነባ ነው፡፡

የአዲስ አዳማን የፍጥነት መንገድ በገነባው የቻይናው ሲሲሲሲ ኮንስትራክሽን የተገነባው ይህ መንገድ ከጠየቀው ጠቅላላ ወጪ ውስጥ 75 በመቶው የተሸፈነው ከቻይና ኤክዚም ባንክ በተገኘ ብድር ነው፡፡ 25 በመቶው በኢትዮጵያ መንግሥት ተሸፍኗል፡፡

ከዋናው የተሽከርካሪ መንገድ በተጨማሪ በግራና በቀኝ የእግረኛ መንገድ ያለው ሲሆን፣ በቀጣይ የዚህ መንገድ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እየታየ ከስድስት ወደ አሥራ ሁለት ከፍ እንዲል ታስቦ ክፍት ቦታ የተተወለት ስለመሆኑም ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡ ይህም አራት መኪኖችን በአንድ ጊዜ የሚያሳልፉ የማስተንፈሻ መንገዶች ሁለት በግራ፣ ሁለት በቀኝ የሚጨምር እንደሆነ መረጃው ያስረዳል፡፡

መንገዱ የስድስት ትልልቅ የድልድይ ግንባታ፣ አራት ማሳለጫዎች እንዲሁም የአንድ የባቡር ማቋረጫን ያካተተ ነው፡፡ የመንገዱ መገንባት የአገሪቱ የወጪና ገቢ ንግድን በዋናነት የምታስተናግድበት የጂቡቲ ወደብ መስመር በሆነው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ክፍል በመሆኑ፣ መንገዱ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት ኢንዳስተናገዱ ዕድል ይሰጣል ተብሏል፡፡

የአቃቂ-ለቡና የአቃቂ ጎሮ (አይቲ ፓርክ) 28.1 ኪሎ ሜትር ውጫዊ የቀለበት መንገድ ፕሮጀክት በየካቲት ወር 2006 ዓ.ም. ግንባታው የተጀመረ ሲሆን፣ በውሉ መሠረት በኅዳር 2009 ዓ.ም. የሚጠናቀቅ ቢሆንም ኮንትራክተሩ አስቀድሞ ዋና ዋና ሥራዎችን እንዳጠናቀቀ ባለሥልጣኑ ይገልጻል፡፡

14.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአቃቂ-አይት ፓርክ (ጎሮ) መንገድ ከተማዋን በምሥራቅና በሰሜን ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያገናኝ ሲሆን፣ 13.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአቃቂ-ለቡ የመንገድ ፕሮጀክትም ከተማዋን በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ለማገናኘት ያስችላል፡፡

የውጫዊ ቀለበት መንገዶቹ መገንባት በአሁኑ ወቅት በአቃቅ ቃሊቲ መንገድ ላይ ያለውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ያቃልላል ተብሎ ይታሰባል፡፡ የዚሁ መንገድ የመጀመርያ ክፍል የሆነው የአዲስ አበባ-አዳማ 84.6 ኪሎ ሜትር የፍጥነት መንገድ ግንባታ 11.2 ቢሊዮን ብር ተመድቦለት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

Standard (Image)

Viewing all articles
Browse latest Browse all 720

Trending Articles