Quantcast
Channel: አስተያየት
Viewing all 720 articles
Browse latest View live

የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ለከፍተኛ የሞት ቁጥር መመዝገብ መንስዔ ሆኗል

$
0
0

የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በአገሪቱ ለሚከሰተው 53 ከመቶ ሞት ምክንያት እንደሆነ ማይክሮ ኒውትረንት ኢኒሺዬቲቭ የተባለ ተቋም ያደረገው ጥናት አመለከተ፡፡ አደገኛ  የምግብ እጥረት፣ የአይረን ዕጥረት (አኔሚያ) የቫይታሚን ኤ እንዲሁም የአዮዲን እጥረት በአገሪቱ በስፋት የሚታዩ ችግሮች መሆናቸው በጥናቱ ተመልክቷል፡፡ 32 በመቶ ለሚሆነው የሕፃናት ሞትም የቫይታሚን ኤ እጥረት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

‹‹ኅብረተሰቡ አስፈላጊ የሆኑ ቫይታሚንና ሌሎች ንጥረ ነገሮች እጥረት ተጋላጭ ሆኗል፤›› ያሉት በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና የሥነ ምግብ ባለሙያ አቶ ድልነሳው ዘርፉ፣ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እንደ አቶ ድልነሳው ገላጻ፣ የምግብ ስብጥሩን ለማስፋት እየተሠራ ነው፡፡ የኅብረተሰቡን የእንስሳት ተዋፅኦ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ተጠቃሚነት ለመጨመር ልዩ ልዩ ሙከራዎች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የምግቦችን የንጥረ ነገር ይዘት የዳበረ ለማድረግ ሰው ሠራሽ የምግብ ማበልፀጊያ (ፉድ ፎርቲፊኬሽን) በስፋት እንዲሠራበት ለማድረግ የሚረዱ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው፡፡

መንግሥት ከዓመታት በፊት ባወጣው የብሔራዊ የሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ውስጥ ፉድ ፎርቲፊኬሽን አንዱ ነው፡፡ ‹‹ፉድ ፎርቲፊኬሽን ማለት በተፈጥሯቸው ንጥረ ነገር ያልያዙ ምግቦችን በአርቲፊሻል መንገድ በንጥረ ነገር እንዲበለጽጉ ማድረግና በፋብሪካ በሚቀነባበሩበት ጊዜ የንጥረ ነገር ይዘታቸውን የሚያጡ ምርቶች፣ በሰው ሠራሽ መንገድ በጥንረ ነገር እንዲዳብሩ የሚደረግበት ሒደት ነው፤›› የሚሉት አቶ ድልነሳው፣ አሠራሩ በጨው ላይ ተሞክሮ ውጤታማ እንደነበር፣ ነገር ግን በርካታ የጨው አምራች ኩባንያዎች በተገቢው ደረጃ እንዳልተገበሩት ተናግረዋል፡፡  

ለዘመናት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩ ምግቦች በተለያዩ አጋጣሚዎች የአዮዲን ንጥረ ነገር  ይዘታቸውን ሲያጡ ቆይተዋል፡፡ ይህም ብዙዎችን በአዮዲን እጥረት ምክንያት ለሚከሰቱ የተለያዩ የጤና ቀውሶች ሲዳርግ ቆይቷል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍም ከዓመታት በፊት በፉድ ፎርቲፊኬሽን መንገድ የአዮዲን ንጥረ ነገር የያዘ ጨው ለኅረተሰቡ እንዲቀርብ የተለያዩ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡ ለውጦችም እየታዩ ነው፡፡ የንጥረ ነገር ችግሮችን በስፋት ሊቀንስ እንደሚችልም ታምኖበት ነበር፡፡ ይሁንና  በ2006 እና 2007 ዓ.ም. በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መሠረት፣ ለኅብረተሰቡ እየቀረበ ያለው ተገቢው ንጥረ ነገር የያዘ ጨው መጠን  ከ25 በመቶ ሊበልጥ አልቻለም፡፡

ይህም በእንቅርት የሚጠቁ እናቶች ቁጥር 39.9 ከመቶ እንዲደርስ፣ ከስድስት እስከ 12 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ልጆች 35.8 ከመቶ በእንቅርት በሽታ እንዲጠቁ በሽታውም እንዲስፋፋ አድርጓል፡፡ የሌሎቹ ንጥረ ነገሮች እጥረትም ማኅበረሰቡን ለተለያዩ የጤና ችግሮች እየዳረገ ይገኛል፡፡  የአዮዲን እጥረት ብዙዎች በቀላሉ ሊድን በሚችል የጤና ችግር ሳቢያ የዓይን ብርሃናቸውን እንዲያጡ፣ 17 ከመቶ የሚሆኑ እናቶች ለደም ማነስ በሽታ እንዲጋለጡ ሰበብ ሆኗል፡፡

‹‹ችግሩን ለመከላከል ኩባንያዎችን ተቆጣጥሮ ማሠራት ብዙ የሚፈጥረው ለውጥ የለም፡፡ አምነውበት እንዲሠሩ ማድረግ ያስፈልጋል፤›› ያሉት አቶ ድልነሳው፣ የግንዛቤ ማሻሻያ ሥራዎች ሊሠሩ እንደሚገባም ይመክራሉ፡፡

አቶ ድልነሳው ይኼንን የጠቀሱት፣ ማይክሮ ኒውትረንት ኢንሺኤቲብ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ማክሰኞ ግንቦት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. በደሳለኝ ሆቴል ለምግብ አቀነባባሪ ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ባዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት ላይ ነው፡፡

በዕለቱ ስለ ማይክሮ ኒውትረንትና የቫይታሚኖች ጠቀሜታ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ለምግብነት እየቀረቡ ያሉ በፋብሪካ የተቀነባባሩ ምርቶች በምርት ሒደት የያዙትን ንጥረ ነገር ምን ያህል እንደሚያጡ፣ በዚህም በጤና ላይ የሚያደርሱት ቀውስ እንዲሁም ችግሩን ይቀርፋል ተብሎ ስለታሰበው የፉድ ፎርቲፊኬሽን አተገባበር ላይ  ለተሳታፊዎች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡

‹‹በግንዛቤ ማጣትና በሌሎች ምክንያቶች አብዛኛው ኅብረተሰብ ከሚመገበው ነገር አስፈላጊዎችን ንጥረ ነገር እያገኘ አይደለም፤›› ያሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒውቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሽብሩ ተመስገን ኮሌጁ በልዩ ልዩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሞች እንደሚያካሂድ፣ ከፕሮግራሞቹ መካከልም ከንጥረ ምግብ ጋር በተያያዘ ለኅብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እንደሚሠራ አብራርተዋል፡፡ ልዩ ልዩ ጥናቶችን በማውጣትም ለሕዝቡ እንዲደረስ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የተመጣጠነ የምግብ ችግር በተለይ በሕፃናት እናቶች ጤና ላይ የከፋ ችግር እያደረሰ ይገኛል፡፡ ለዚህም የያዙት ንጥረ ነገር በፋብሪካ በዝግጅት ሒደት (ፕሮሰሲንግ) የሚያጡና ንጥረ ነገር የሌላቸው ምግቦችን በፉድ ፎርቲፊኬሽን የተሟላ ንጥረ ነገር እንዲኖራቸው የግድ ይላል፡፡ ይህም ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነውን የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት ለመቋቋም እንደሚያስችል በጥናቱ ተገልጿል፡፡

Standard (Image)

በግንባታ ፈቃድ ዕጦት ተገምሶ የተሠራው ሕንፃ

$
0
0

አቶ ጳውሎስ ተክለማርያም ለተለያዩ የቢዝነስ አገልግሎቶች የሚውል ሕንፃ ለመገንባት እንቅስቃሴ ከጀመሩ አራት ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ የቢዝነስ ማዕከሉን ለመገንባት የሚያስችላቸውን ቦታ ሲያፈላልጉ ቆይተው ከአራት ዓመታት በፊት ቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ ስድስት ሁለት ቦታዎች ያገኛሉ፡፡

ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ በሚወስደው ዋና ጐዳና ከኢትዮ ሴራሚክ ሕንፃ ጐን ካገኙዋቸው ሁለት የተለያዩ ቦታዎች፤ አንደኛው 348 ካሬ ሜትር ሌላኛው ደግሞ 568 ካሬ ሜትር ስፋት የነበራቸው ናቸው፡፡ ሁለቱም ቦታዎች ሕጋዊ የግለሰብ ይዞታዎች መሆናቸውን በማረጋገጥ ከቦታው ባለቤቶች ጋር በመደራደር ለመግዛት ይወስናሉ፡፡

ኩታ ገጠም የሆኑትን ሁለት ቦታዎች ለመግዛት የወሰኑት በአንዱ ቦታ ብቻ ያሰቡትን ሕንፃ ለመገንባት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ በሁለት የተለያዩ ካርታዎች የተመዘገቡትን ቦታዎች ደባልቆ መሥራት ይቻላል የሚል እምነት ይዘው እንደነበር አቶ ጳውሎስ ይናገራሉ፡፡    

ስለዚህ እነዚህን ቦታዎች ቀላቅሎ በአንድ ካርታ አጠቃሎ መሥራት እንደሚቻል በማረጋገጥ አንደኛውን ቦታ በ1.5 ሚሊዮን ብር፤ ሁለተኛውን ደግሞ በ2.5 ሚሊዮን ብር ይገዛሉ፡፡ የሁለቱንም ቦታዎች ካርታ በስማቸው ያዞራሉ፡፡

የባለቤትነት ማረጋገጫውንና ካርታዎቹን በስማቸው ለማዞር ከ750 ሺሕ ብር በላይ ለመንግሥት ወጪ በማድረግ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት መውሰዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

ሕጋዊ መሥፈርቶችን ካሟሉ በኋላ ወደ ግንባታ ለመግባት ይዘጋጃሉ፡፡ እንደ እርሳቸው ገለጻ ዕቅዳቸው ሕንፃውን በአንድ ዓመት ገንብተው ማጠናቀቅ ነበር፡፡ ለዚህ እንዲረዳቸው ሁለቱን ቦታዎች በመቀላቀል አንድ ካርታ እንዲሠራላቸው ማድረግ ቀዳሚ ስለሆነ ይህንን ለማስፈጸም ወደሚመለከተው የአዲስ አበባ መሬት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ይሄዳሉ፡፡ ነገር ግን ሁለቱን ቦታዎች በአንድ በመቀላቀል ካርታ ማግኘት እንደማይችሉ ይገለጽላቸዋል፡፡

ይህ የማይቻል ከሆነ በተናጠልም ቢሆን በሁለቱም ቦታዎች ላይ ግንባታ ማካሄድ የሚያስችላቸው ፈቃድ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው በቶሎ ወደ ሥራ ለመግባት የነበራቸውን ምኞት ከማሳካት አኳያ በአማራጭነት የቀረበ እንደነበር የጠቆሙት አቶ ጳውሎስ፣ በአንደኛው ቦታ ላይ ግንባታ ለማካሄድ የሚያስችላቸውን የግንባታ ፈቃድ ሲያገኙ በሁለተኛው ይዞታቸው ላይ ግን ለግንባታ ፈቃድ ሳይሰጣቸው ይቀራል፡፡ በአንደኛው ይዞታቸው ላይ ግንባታ ለማካሄድ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘት ያልቻሉበት ምክንያት በቦታው ላይ የቀበሌ ቤት አለበት የሚል ነው፡፡

አቶ ጳውሎስ፣ ‹‹ቦታውን ስንገዛ የቀበሌ ቤት አልነበረም፡፡  ይህንንም ቀበሌውና ክፍለ ከተማው አረጋግጠዋል፡፡ የቀበሌ ቤት አርፎበት ነበር የተባለው ቤት በ24 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ቢሆንም፣ ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት የተሰጠው ምላሽ፤ የግንባታ ፈቃድ ሳይሰጥበት በቆየው ቦታ ላይ አለ የተባለው የቀበሌ ቤት ባይኖርም በጂአይኤስ ሲታይ ቤቱ መኖሩን ያሳያልና የግንባታ ፈቃድ መስጠት አይቻልም፤›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በቀበሌ ቤቱ ነዋሪ ነኝ የሚል ጠያቂ ያልቀረበ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ጳውሎስ፣ ይህን እውነታ ለግንባታ ፈቃጁ መሥሪያ ቤት ለማስረዳት ለዓመታት ወደ ከተማው አስተዳደር ቢመላለሱም የግንባታ ፈቃዱን ሊያገኙ እንዳልቻሉ ይገልጻሉ፡፡

ይህ ያልተጠበቀ ክስተት የእነ አቶ ጳውሎስን የመሥራት ፍላጐት ያደበዘዘ ሲሆን፣ ተስፋ ሳይቆርጡ የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ያደረጉት ሙከራም ሳይሳካ ቆይቷል፡፡ በዚህ  ውጣ ውረድ የሕንፃውን ግንባታ ባሰቡት ጊዜ ለመጀመር እንዳላስቻላቸው ያስታውሳሉ፡፡

በቦታው ላይ ግንባታ ማካሄድ ያልተቻለበት ምክንያት እንዲጣራ የአስተዳደሩ የሕግ ክፍል እንዲመረምረው ተደርጎም የሕግ ክፍሉ ካካሄደው ምርመራ በመነሳት አቶ ጳውሎስ ግንባታ ለማካሄድ የሚከለክላቸው ምንም ነገር እንደሌለ የሚያመላክት ማብራሪያ ይሰጣል፡፡  ከሕግ ክፍሉ ማብራሪያ በኋላም ቢሆን ግን የግንባታ ፈቃዱን ሊገኝ አልቻለም ይላሉ፡፡ ድርጊቱ የቱንም ያህል ቢያማርራቸውም ፈቃድ ይገኛል በሚል ተስፋ ያለሥራ ከመቀመጥ በማለት በአንደኛው ይዞታቸው ላይ ግንባታ ለመጀመር ይወስናሉ፡፡ ይህ ውሳኔ ቀላል እንዳልነበር የሚናገሩት አቶ ጳውሎስ፣ ዲዛይኑን በመቀየርና ባልተፈቀደላቸው ቦታ ላይ ሊያርፍ የሚችለውን የሕንፃ አካል በማስቀረት አዲስ ዲዛይን በድጋሚ ለማሠራት ይወስናሉ፡፡ አዲስ ያሠሩትን ዲዛይን ይዘው የግንባታ ፈቃድ ይጠይቃሉ፡፡ በአንደኛው ቦታ ላይ ግንባታ ማከናወን እንደሚችሉም ይፈቀድላቸዋል፡፡ ወደዚህ ውሳኔ የገቡት ግንባታ ለማካሄድ ፈቃድ እየተጠባበቁበት ባለው ቦታ ላይ ፈቃድ እንደሚያገኙ በማመንና በቀሪው ቦታ ላይ ሊያርፍ የሚችለውን የሕንፃ አካል ገጥሞ ለመሥራት በማሰብ ነበር፡፡ 

በሁለቱም ቦታዎች ላይ ለመገንባት በታሰበው ዲዛይን መሠረት ሕንፃውን መገንባት ቢቻልም፣ የታሰበውን የሕንፃ ዲዛይን ከፍሎ አንደኛውን ክፍል ብቻ መገንባታቸው ተጨማሪ ወጪ እንዲያወጡ አስገድዷቸዋል፡፡

ለአንደኛው ቦታ የግንባታ ፈቃድ ሳይገኝ ሌላኛው ሕንፃ ተገንብቶ ባለበት ከዚህ በኋላ ፈቃዱ ገና ለገና ተገኝቶ ቀሪውን የሕንፃ ክፍል ከተጠናቀቀው ሕንፃ ጋር አዋቅሮ መገንባቱም ቢሆን ላልተፈለገ ድካምና ወጪ የሚዳርጋቸው ስለመሆኑም ይገልጻሉ፡፡ ይህም ቢሆን ግን ከዚህ ውጭ አማራጭ ስለሌለ በዚህም መንገድ ቢሆን ቀሪውን የሕንፃ ክፍል ለመገንባት የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት ወደ ፈቃጁ አካል መመላለሳቸውን አላቆሙም፡፡

በአንደኛው ቦታ ላይ ሲካሄድ የቆየው የሕንፃ ግንባታ በአሁን ወቅት ተጠናቋል፡፡ ሕንፃውን ሙሉ የሚያደረገው ሌላኛው የሕንፃ ክፍል ግን የግንባታ ፈቃድ ባለመገኘቱ  ቦታው ታጥሮ እንዲቀመጥ አስገድዷል፡፡

24 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የቀበሌ ቤት አለ በሚል ሰበብ በሕጋዊ መንገድ የተያዘና ካርታ ያለው ቦታ ላይ ግንባታ እንዳይካሄበት ፈቃድ መከልከሉ ምንም ዓይነት አሳማኝ ምክንያት እንደሌለው አቶ ጳውሎሰ ሳይተቹ አላለፉም፡፡ የበለጠ አስገራሚው ነገር ከዚህ ቦታ ላይ ለመንገድ ተብሎ 77 ካሬ ሜትር ተቆርሶ መወሰዱ ነው፡፡ ለመንገድ ተብሎ ለተወሰደው 77 ካሬ ሜትር ቦታ ካሳ መከፈል የነበረበት ቢሆንም፣ ካሳ ያለመጠየቃቸውን አቶ ጳውሎስ ይናገራሉ፡፡ ይህንንም ያደረጉት ቀሪው ቦታ ለሕንፃው ግንባታ በቂ ሆኖ ስተለኘ ነው፡፡ ነገር ግን የግንባታ ፈቃድ ለመስጠት የተጠቀሰው በ24 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ የቀበሌ ቤት በመኖሩ ምክንያት መከልከሉ በአንፃሩ በመንገድ ግንባታው ከይዞታቸው ላይ የተወሰደው 77 ካሬ ሜትር ቦታ ታሳቢና ተመዛዛኝ አለመደረጉን ተችተዋል፡፡

እንደ አቶ ጳውሎስ ገላጻ፣ በአንደኛው ቦታ ላይ የግንባታ ፈቃድ ያልተገኘበት ምክንያት አሳማኝ ባይሆንም፣ ሙሉ ሕንፃውን ለመገንባት በነበራቸው ጉጉት ሳቢያ መፍትሔ ይሆናል በማለት ያቀረቡት ሌላ ሐሳብም ነበር፡፡ ይህም 24ቱ ካሬ ሜትር በከፍተኛ የሊዝ ዋጋ ተሰልቶ እንግዛው የሚል ነበር፡፡ ሐሳቡ አማራጭ በማጣት የቀረበ እንጂ የተሻለና ለእሳቸው የሚጠቅም ስለሆነ እንዳልነበር ይገልጻሉ፡፡ ነገር ግን ይህም የመፍትሔ ሐሳብ አወንታዊ መልስ አላገኘም፡፡ ‹‹ጉዳዩን መርምሮ ሊወስንልን የሚችል አካልም አላገኘንም፤›› ይላሉ፡፡ ስለዚህም ችግሩ ምን እንደሆነ ግራ መጋባታቸውን ይናገራሉ፡፡

አሁን ግን ነገሩ ስላስመረራቸው ድምፃቸውን በማሰማት መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ይጠይቃሉ፡፡ ሕንፃው ከሦስት ዓመት በፊት ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረና፣ የሕንፃው መጠናቀቅም ተከትሎ ለመንግሥትም ትልቅ ገቢ ያገኝ ዘንድ ያግዝ ነበር የሚሉት አቶ ጳውሎስ፣ የግንባታ ፈቃድ ያልተሰጠበት ምክንያት አሳማኘ ሊሆንላቸው እንዳልቻለና ለአማራጮችና ለሐሳቦችም ዝግ የሆነ አሠራር እንደገጠማቸው ገልጸዋል፡፡ የሕንፃው ግንባታ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃና ከሚያስገኘው ገቢ መንግሥት ሊሰበስብ የሚችለው ታክስ መታሰብ ነበረበት ያሉት አቶ ጳውሎስ፣ ለዜጐች የሚፈጥረው የሥራ ዕድል፣ በሙሉ ዲዛይኑ ሕንፃው ቢሠራ ለከተማው የሚሰጠውም ውበት ታሳቢ መደረግ እንደነበረበት ሞግተዋል፡፡

ከአስተዳደሩ የመሬት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚገልጸው ግን፣ ቅሬታ አቅራቢው አሁንም በተለያዩ እርከኖች ካሉ የቅሬታ ሰሚ አካላት  ዘንድ ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑ ነው፡፡ የቅሬታ አቀራረቡም እስከ ከንቲባው ጽሕፈት ቤት ድረስ ይዘልቃል፡፡ ከይዞታቸው ላይ ቦታ ተወስዶም ከሆነ ካሳ ማግኘት እንደሚገባቸው የሚገልጸው የጽሕፈት ቤቱ መረጃ፣ በዚህ ቦታ ላይ ተፈጥሯል የተባለውን ችግር መርምሮ ተጨማሪ ምላሽ ይሰጥበታል ተብሏል፡፡

ለግንባታ ፈቃድ ክልከላው መነሻ የሆነው የቀበሌ ቤት ከሆነም የቦታው ገዥዎች ይህንን ማረጋገጥ እንደነበረባቸውም ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡ በበኩላቸው አቶ ጳውሎስ ቅሬታቸውን ከንቲባው ጽሕፈት ድረስ ማድረሳቸውንና እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

      

Standard (Image)

የዓለም ባንክ ለመንገድ ደኅንነትና ለኮሪደሮች ልማት የ300 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀ

$
0
0

በ ብርሃኑ ፈቃደ

የዓለም ባንክ በዓለም አቀፉ የልማት ማኅበር (አይዲኤ) በኩል ይሰጣል ያለው ብድር በአዲስ አበባ የተመረጡ የመንገድ ኮሪደሮችን ለማሻሻል እንዲሁም በመላ አገሪቱ የመንገድ ደኅንነትን ለማስፈን የሚያስችሉ አሠራሮችን ለመተግበር እንዲያስችል በማሰብ የ300 ሚሊዮን ዶላር ወይም የ6.3 ቢሊዮን ብር ብድር ማፅደቁን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት ብድሩን ያፀደቀው፣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የመንገድ ላይ እንቅስቃሴ ችግር ለማቃለል ብሎም በመላ አገሪቱ የሚታየውን የመንገድ ደኅንነት ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችል ነው፡፡  በዚሁ መሠረት ‹‹የትራንስፖርት ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮጀክት›› ተብሎ ለሚጠራው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያነት ገንዘቡ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

በመሆኑም ብድሩ በአዲስ አበባ ያለውን የትራፊክ ሲግናልና የመቆጣጠሪያ ሥርዓት እንዲስፋፋ ከማገዝ ባሻገር በአዲስ አበባ ችግር በተመረጡ ዋና ዋና መንገዶች የእግረኞች መተላለፊያ መንገዶችን የማሻሻል፣ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅትን አሠራር የማሻሻል፣ የከተማ ትራንስፖርት አሰጣጥ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የኦፕሬሽንና የማኔጅመንት ችግሮቻቸውን በማቃለል ብቃታቸው እንዲዳብር ማድረግ በብድር በሚገኘው ገንዘብ ይከናወናሉ ተብለው ከሚጠበቁ ሥራዎች መካከል  እንደሚጠቀሱ ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከተጠቀሱት በተጨማሪም መንጃ ፈቃድ ለማውጣት የሚሠለጥኑ ለማጆች እንዲሁም ለፈተና የሚቀርቡ ሠልጣኞች የሚመዘኑባቸውን ሥርዓቶች ከማዘመን ባሻገር፣ የአሽከርካሪዎች ፈቃድን የተሽከርካሪዎች ምዝገባ ሊብሬዎችን ደኅንነቱ በተጠበቀ የመረጃ ቋት እንዲደራጁ የማድረግ ዓላማም በብድሩ የሚሸፈኑ ሥራዎች እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

ባንኩ በጠቀሰው መረጃ መሠረት በኢትዮጵያ በእያንዳንዱ አሥር ሺሕ ተሽከርካሪ ምክንያት በየዓመቱ 64 ሰዎች ለሕልፈት ይዳረጋሉ፡፡ ይህ መሆኑም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ገዳይ ተሽከርካሪዎች ከተንሰራፉባቸው አገሮች ስምንተኛዋ ቀንደኛ አገር ተብላ እንድትፈረጅ ምክንያት ሆነዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር በአገሪቱ የሚሽከረከሩት መኪኖች ብዛትና የሚደርሰው ጉዳትና አደጋ እጅጉን ያልተጣጣሙ ሆነው መገኘታቸውንም ባንኩ አትቷል፡፡ ምንም እንኳ ከሌሎች አቻ ከተሞች አኳያ በአዲስ አበባ የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁጥር አነስተኛ ነው ቢባልም፣ እያደገ የመጣው የትራፊክ መጨናነቅ በከተማው የትራፊክ ፍሰት ማኔጅመንት ላይ ጥያቄ እንዲነሳ እያስገደደ እንደሚገኝም ባንኩ ሳይጠቁም አላለፈም፡፡

ለመንገድ ትራፊክ አደጋ ከሚያጋልጡ ምክንያቶች ተርታ የሚመደበው በተለይ በአዲስ አበባ በቂ የእግረኞች መንገድ አለመኖሩ ሲሆን፣ እንደ የዓለም ባንክ መረጃ መሠረት፣ 65 ከመቶው የአዲስ አበባ የመንገድ ኔትወርክ፣ እግረኞች የሚረማመዱባቸው መንገዶች እጥረት አለበት፡፡

የዓለም ባንክ የመንገድ ሥርዓት ማሻሻያ ፕሮጀክትን ጨምሮ በኢትዮጵያ ለሚካሄዱ ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በየዓመቱ የሚሰጠው ብድር በአሁኑ ወቅት ከ1.8 ቢሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

 

Standard (Image)

ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቤት ያሉ ቤት ገዥዎች ጊፍት ሪል ስቴት አስረክባችኋለሁ ካለው ጊዜ በላይ አዘግቶብናል ሲሉ ወቀሱ

$
0
0
  • አልሚው የዘገዩት የምዕራፍ ሁለት ቤቶች በስድስት ወራት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃሉ ብሏል

በብርሃኑ ፈቃደ

‹‹በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ገንብቶ እንደሚያስረክበን ቃል ገብቶልን ነበር፤›› ያሉ ቤት ገዥዎች ጊፍት ሪል ስቴት እስከ ሰባት ዓመት ቆይቶም ቤታችንን ሊያስረክበን አልቻለም ሲሉ ወቀሱ፡፡ ግማሽና ከዚያም በላይ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላም ቢሆን በራሳቸው የቤቶቹን ማጠናቀቂያ ግንባታ ለማካሄድ መገደዳቸውን የገለጹም አሉ፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ማስገባታቸውን የገለጹና ፒቲሽን የተፈራረሙ ከሃምሳ በላይ ቤት ገዥዎች ለሪፖርተር በላኩት ደብዳቤ፣ ላለፉት ሰባት ዓመታት ቤት የማግኘት ፍላጎታቸው እንዳልተሟላ በመግለጽ፣ ሁለት አማራጮችን አቅርበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመርያ እንዲሰጡላቸው ጠይቀዋል፡፡ አንደኛው አማራጭ ሐሳብ ‹‹አልሚው መሬቱን ከመንግሥት ወስዶና በተገቢው ጊዜ ግንባታውን አጠናቆ በገባው ውል መሠረት እንዲያስረክበን አስፈላጊውን መመርያ እንዲሰጥልን፤›› የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው አቤቱታ ደግሞ ‹‹ቤት አልሚው የማይችል ከሆነ መንግሥት መሬቱን ለቤት ገዥዎቺ በማስተላለፍ ውጭውን ክፍል አልምተን ወደ ቤቶቻችን እንድንገባ እንዲያደርግልን፤›› የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡

ከጥር ወር ጀምሮ እንዲህ ያሉ ጥያቄዎች ለከፍተኛ የመንግሥት አካላት በማቅረብ ላይ የሚገኙት ቤት ገዥዎች፣ ለሚዲያ አካላትም ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ ቤት ገዥዎች እንደሚሉት፣ ጊፍት ሪል ስቴት በየካ ክፍለ ከተማ፣ ሲኤምሲ፣ አያት አካባቢ ገንብቶ እንደሚያስረክባቸው ውል በመግባት የሸጠላቸውን ቤቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ቁልፍ እንደሚያስረክባቸው ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና በውለታ ከተስማሙበት በላይ እስከ ሰባት ዓመት መቆየቱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ ሲኤምሲ፣ መሪ ሎቄ አካባቢ መጠነ ሰፊ ይዞታው  በመቶ የሚቆጠሩ የተለያዩ የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ላይ የሚገኘው ጊፍት ሪል ስቴት፣ በሁለት ወገን የሚነሱ የቤት ገዥዎችን ፍላጎት የማስተናገድ ጥያቄ ተደቅኖበታል፡፡

የተገነቡ ቤቶቻቸውን ተረክበው በአካባቢው መኖር የጀመሩ ቤት ገዥዎች  የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይኸውም መንገድ፣ ውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይልና ሌሎችም አቅርቦቶች እንዲሟሉላቸው የሚጠይቁ አሉ፡፡ ሌሎቹ ከነጭራሹ ቤቶቻቸው ተገንብተው እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ ናቸው፡፡ በተለይ የክረምቱ መግባትን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ወደ መኖሪያ መንደሩ የሚያስገባው ዋናው መንገድ በፍጥነት እንዲሠራ ይወተውታሉ፡፡ በፍጥነት እንደሚሠራ ተነግሯቸው እንደነበርም ይገልጻሉ፡፡ ክረምቱ እየበረታ የሚመጣባቸው ወራት በመቃረባቸውም የመንገድ ሥራው ሊጓተት እንደሚችል በመሥጋት ቤት ገንቢውን ይማጸናሉ፡፡

ሪፖርተር በቅርቡ በሲኤምሲ፣ አያት አካባቢ በሚገኘው የጊፍት ሪል ስቴት ምዕራፍ ሁለት የቤት ግንባታ ፕሮጀክት ሥፍራ በመገኘት እንደተመለከተው በርካታ ቤቶች በግንባታ ሒደት ላይ ይገኛሉ፡፡ በጅምር ላይ የሚገኙም ከዕይታ ውጭ አይደሉም፡፡ ገና መሠረታቸው የወጣ ቤቶችም ይታያሉ፡፡ ቤቶችን በራሳቸው ለማጠናቀቅ ከድርጅቱ ጋር ተነጋግረው እየሠሩ ያሉ ቤት ገዥዎች የሚያነሷቸው የየራሳቸው ጥያቄዎችም አልታጡም፡፡ ሌሎችም በቤት ግንባታው መጓተት ሳቢያ ያሰቡት ሊደርስ እንዳልቻለ የሚገልጹም ነበሩ፡፡

ይሁንና ጊፍት ሪል ስቴት የቤቶቹ ግንባታ መዘግቱን በመቀበል፣ ነገር ግን ግንባታው የዘገየባቸው ምክንያቶች ከአቅሙ በላይ በነበሩ ችግሮች እንደነበሩ ደጋግሞ ይገልጻል፡፡ ለምዕራፍ ሁለት የቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቱ የተረከበው መሬት ያስነሳው በርካታ ችግሮች ዋናውን ሚዛን ይደፋሉ፡፡ ቤት ገዥዎቹም እነዚህ ከይዞታ ይገባኛል፣ ከአካባቢ ሰፋሪዎች እንዲሁም ከመንግሥት በኩል ድርጅቱ ላይ የተጋረጡ ፈተናዎች እንደነበሩ ያምናሉ፡፡ ይጋራሉ፡፡ ይሁንና ድርጅቱ በማኔጅመንቱ ብቃት እነዚህ ያሉ ፈታኝ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት ይችል እንደነበርና ይህን ያህል ጊዜም ላይወስድበት ይችል እንደነበር ይገልጻሉ፡፡

ይህም ቢባል ግን ለጊፍት ሪል ስቴት በተሰጠ የግንባታ ይዞታ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ያስከተለው ውዝግብ፣ ይህ ውዝግብ እልባት ሳያገኝም በዚያው በይዞታው ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ያለአግባብ መታነጹ፣ ይህም እልባት ሳያገኝ ድርጅቱ ከይዞታው ውጭ ተጨማሪ ቦታ ወስዷል ተብሎ ብዙ ውጣ ውረድ ማጋጠሙ ዋና ዋና ፈተናዎች ለመሆናቸው አልሚውም ቤት ገዥዎቹም ይስማማሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ግን የግንባታ ግብዓቶች ዋጋ በየጊዜው እየናረ መምጣት፣ በተለይ የሲሚንቶ፣ የአርማታ ብረትና የሌሎች የቤት ማጠናቀቂያ ቁሳቁሶች የዋጋ ንረት ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡ በተፈለገው ጊዜ ውስጥም ግብዓቶቹን ለማግኘት አለመቻል ኩባንያው ከሚያነሳቸው ችግሮች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ከዚህ ጎን ከውጭ ለሚያስመጣቸው ግብዓቶች የውጭ ምንዛሪ እንደ ልብ ለማግኘት አለመቻልም ከችግሮቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ከዚህም ባሻገር በዚህ አካባቢ ከ90 ሺሕ ካሬ ሜትር በላይ ቦታ ከመንግሥት ቢረከብም፣ ከይዞታው በላይ ወስዷል በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክስ ቀርቦበት ሲከራከር መቆየቱም ተጠቃሽ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ሳቢያ ጉዳዩ በፍትሕ አካላት እልባት እስኪያገኝ ድረስ ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳይሰጠው የሚያስገድድ መመርያ ተላልፎበት የቆየው ጊፍት፣ ይህንን በመቃወም አቤቱታ ሲያሰማ መቆየቱም አይዘነጋም፡፡ ጊፍት ሪል ስቴት ከከተማ አስተዳደሩ በተዋረድ እስከ የካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር፣ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽሕፈት ቤትና ሌሎችም በርካታ ክርክሮችና ምልልሶች ሲያደርግ መቆየቱን የሚጠቅሱ ማስረጃዎችንም አቅርቧል፡፡  

በእነዚህ መሠረታዊ ችግሮች ሲናጥ መቆየቱን በመግለጽ በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ቤቶቹን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡ ለሪፖርተር ስለዝርዝር ሁኔታው ማብራሪያ የሰጡት የጊፍት ሪል ስቴት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ገብረየሱስ ኢጋታ፣ ኩባንያው ሙሉ ኃይሉን በመጠቀምና በሌሎች የግንባታ ጣቢያዎች የነበሩ የግንባታ ቁሳቁሶችንና የሰው ኃይሉን ወደ መሪ ሎቄው የግንባታ ጣቢያ በማዞር ቃል በገባው ጊዜ ውስጥ አጠናቆ፣ ለቤት ገዥዎች እንደሚያስረክብ አረጋግጠዋል፡፡ ይህንኑ አባባላቸውን ግንቦት 13 ቀን 2008 ዓ.ም. እዚያው ሲኤምሲ፣ መሪ ሎቄ አካባቢ በሚገኘው ምዕራፍ አንድ የመኖሪያ መንደር ተገንብተው ለቤት ገዥዎች የተላለፉ ቤቶች ርክክርብ ላይ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ጊፍት ሪል ስቴት በሲኤምሲና አያት አካባቢ ከሚያካሂዷቸው ሦስት የመኖሪያ መንደር ግንባታዎች ውስጥ፣ ከሲኤምሲ አደባባይ በ400 ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው መሪ ሎቄ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነባቸውን መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለነዋሪዎቹ ማስረከቡን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ በዚሁ ጊዜም በመጪዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ ሁለተኛውን መንደር ለማጠናቀቅና ለደንበኞቹ ለማስረከብ ዕቅድ ይዞ በመሥራት ላይ መሆኑንም ገልጿል፡፡

አቶ ገብረየሱስ እንደተናገሩት፣ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው ይህ መንደር፣ በ16 ሺሕ 400 ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤቶቹ ግንባታ መሠረተ ልማቱን ጨምሮ ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ መሆኑን የተናገሩት አቶ ገብረየሱስ፣ መንደሩ ለደንበኞች የተላለፉ 22 መኖሪያ ቪላዎችን ያካተተ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የእነዚህ መኖሪያ ቤቶች መጠናቀቅና ለደንበኞች መተላለፍ ሪል ስቴቱ እስካሁን ድረስ አጠናቆ ለደንበኞች ያስረከባቸውን ቤቶች ቁጥር 202 እንዳደረሰውም ተገልጿል፡፡

 

 

 

 

Standard (Image)

በእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራው የንግድ ልዑክ በማዕድንና በውኃ ቴክኖሎጂ ላይ እንደሚያተኩር ይጠበቃል

$
0
0
  • የቻይና ልዑካን በእሽሙር መሥራት የሚፈልጉባቸውን መስኮች ይፋ አድርገዋል

በብርሃኑ ፈቃደ

በእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔትናያሁ የተመራ ከ60 በላይ የእሥራኤል ኩባንያዎች ኃላፊዎች የሚሳተፉበት ልዑክ በኢትዮጵያ የሚያደርገው ጉብኝት ወቅት በማዕድን ዘርፍና በውኃ ቴክኖሎጂ መስኮች ላይ የንግድ ስምምነቶች ሊደረጉ እንደሚችሉ ተገለጸ፡፡

ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያኒን ኔትናያሁ፣ 60 የእሥራኤል ባለሀብቶችን አስከትለው እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡ በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያና በእሥራኤል መንግሥት በኩል የሚደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነቶችን ጨምሮ በሁለቱ አገሮች የንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ከሚደረጉት ስምምነቶች መካከል በማዕድን ዘርፍ፣ በውኃ ቴክኖሎጂና በመስኖ እንዲሁም በግብርና መስኮች የሚደረጉ ስምምነቶች እንደተሰጣቸው ከኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ አበበ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለሪፖርተር እንዳብራሩት፣ የሚመጡት ልዑካን ከመንግሥትና ከንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በተናጠል የሚያደርጓቸው ውይይቶች ይኖራሉ፡፡ ከመንግሥት አካላት ጋር ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ውይይት ላይ መንግሥት የእሥራኤል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያግባባበት መድረክ እንደሚሆን አቶ ደበበ ጠቅሰዋል፡፡

በሌላ በኩል በኢትዮጵያውያንንና በእሥራኤላውያን የንግድ ማኅበረሰብ አባላት በኩል የሚደረገው ምክክር፣ በጋራ ለመሥራት የሚያስችሉ ስምምነቶችን ታሳቢ ያደርጋል ያሉት አቶ ደበበ፣ ትብብር ይደረግባቸዋል ተብለው ከወዲሁ እየታዩ ያሉት መስኮችም የማዕድን ፍለጋ፣ ማውጣትና ማልማት ተግባራትን አካቶ፣ የውኃና የመስኖ ሥራዎች፣ የግብርና እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን መሠረት የሚያደርጉ ስምምነቶች እንደሚኖሩ አብራርተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በተለይ በማዕድንና በውኃ ብሎም በመረጃና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ የሚደረጉ ስምምነቶች ትልቁን ቦታ እንደያዙ ጠቅሰዋል፡፡

ከእሥራኤል ኤምባሲ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝትና ስለሚመጡት ንግድ ልዑካን መረጃ ለማግኘት ተሞክሮ፣ የስምምነት ሰነዶች ገና በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኙና ከቀናት በኋላ ይፋ መግለጫዎች እንደሚሰጡ ከመግለጽ በቀር ዝርዝር መረጃዎችን ከኤምባሲው ሊገኝ አልቻለም፡፡

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ኢትዮጵያን የጎበኙት የወቅቱ የእሥራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቪግዶር ሊበርማን፣ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ሊያደርጉ የሚችሉ የእሥራኤል ባለሀብቶችን በመምራት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ አስታውቀው ነበር፡፡ የቀድሞው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስከትለዋቸው ከመጡት 50 ያህል የእሥራኤል ባለሀብቶች ውስጥ በአቪዬሽን መስክ፣ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በውኃ ቴክኖሎጂና በሌሎችም መስኮች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት እንደሚፈልጉ ተገልጾ ነበር፡፡

ከዚህ ባሻገር በኢትዮጵያና በእሥራኤል መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የኢትዮ እሥራኤል ግንኙነት መዘከሪያ ሙዚየም በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በአማራና በትግራይ ክልሎች እንደሚቋቋም ይፋ ተደርጎም ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ከ100 ሺሕ በላይ ቤተ እሥራኤላውያን ወይም ፈላሻዎች በእሥራኤል እንደሚኖሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በሌላ በኩል ከቻይና እንደሚመጡ የሚጠበቁ የንግድ ልዑካንም ከኢትዮጵያውያን ጋር መሥራት የሚፈልጉባቸውን መስኮች ይፋ አድርገዋል፡፡ በመስከረም ወር ወደ አዲስ አበባ እንደሚመጡ የሚጠበቁት የቻይና ልዑካን የቻይና ቾንኪንግ የዓለም አቀፍ ንግድ ንዑስ ምክር ቤት አባላትና ባለሀብቶች ለአምስት ቀናት በሚያደርጉት ቆይታ ወቅት ከኢትዮጵያ የንግድ ማኅበረሰብ አባላት ጋር በተለያዩ የንግድና ኢንቨስትመንት መስኮች ላይ በጋራ ለመሥራት እንደሚፈልጉ ማስታወቃቸውን ከኢትዮጵያና ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በምክር ቤቱ መረጃ መሠረት ቻይናውያኑ በአውቶሞቢልና በሞተር ብስክሌት ማስመጣትና መገጣጠም ሥራ ላይ ከተሰማሩ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በእሽሙር መሥራት እንደሚፈልጉ ተጠቁሟል፡፡ ከዚህም ባሻገር በመድኃኒት አምራችነትና አስመጪነት፣ በቆዳና የቆዳ ምርት አምራችነት፣ በአግሮፕሮሰሲንግ፣ በአስመጪነትና ላኪነት፣ በአነስተኛ የግብርና ማሽነሪዎች አምራችነትና አስመጪነት መስኮችና በሌሎችም ዘርፎች ከተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋራ በመተባበር ወደ አገር ውስጥ የውጭ የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነቶችን ከማካሄድ ባሻገር በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የተመሩ የንግድ ጉዞዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተመራ የንግድ ልዑክም በዚሁ ዓላማ ወደ ኬንያ ማቅናቱ ታውቋል፡፡ 

ምንም እንኳ በየጊዜው ወደ አገር ውስጥና ከአገር ውጭም በተደጋጋሚ የንግድና የኢንቨስትመንት ጉዞዎች እየተበራከቱ ቢመጡም፣ እያንዳንዱ ጉዞ ያስገኘውን ውጤትና ጉዞውን ተከትሎም የተደረጉ የመግባቢያ ስምምነቶችና ድርድሮች ምን ያህሉ ወደ ተግባር እንደተለወጡ የሚያስረዱ መረጃዎችን ማግኘት አስቻጋሪ ሆኖ ይገኛል፡፡ ይሁንና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር የሚመራ የንግድና ኢንቨስትመንት ሥራዎችና እንቅስቃሴዎችን የሚከታተል ክፍል ተቋቁሞ እየሠራ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ የንግድ ማኅበራትንና ባለሀብቶችን ከውጭ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ እያገዘ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ይህም ቢባል ግን በርካታ የአገር ውስጥ ባለሀብቶችና ኩባንያዎች ባለባቸው የፋይንስ፣ የመደራደር፣ የክህሎትና የመሳሰሉት ችግሮች ምክንያት የሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነቶችን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ ሲሳናቸው እንደሚታይ የንግድ ምክር ቤቶች ተሞክሮ ይጠቁማል፡፡

 

 

Standard (Image)

ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው መንገዶችና ጉራ ማይሌ ገጽታቸው

$
0
0

የዚህ ዓመት ግንቦት እና ሰኔ ወራት በኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በኩል በተለየ ዓይን ሊታዩ የሚችሉ ወራት ናቸው ብሎ ለመናገር የሚያስደፍሩ ክስተቶች ተስተናግዶባቸዋል፡፡ በአጋጣሚ ይሁን አልያም ቀድሞ በተያዘ ፕሮግራም፣ በባለሥልጣኑ ቀደምት ታሪክ ውስጥ በአዲስ መልኩ ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የሚፈስባቸው በርካታ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የተፈረሙት በእነዚህ ሁለት ወራት ውስጥ ነበር፡፡

የባለሥልጣኑ ዓመታዊ መረጃ የሚናገረውም በሙሉ በበጀት ዓመቱ ከተፈረሙ 28 ፕሮጀክቶች ውስጥ የ12 ያህሉ ፕሮጀክቶች ስምምነቶች የተፈረሙትና እንካችሁ ገንብታችሁ አስረክቡ ተብሎ ለተቋራጮች የተላለፉትም በእነዚህ ሁለት ወራቶች ውስጥ ነው፡፡

ይህ ብቻም አይደለም፡፡ በተያዘው የሰኔ ወር የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ ውል ብቻ ሳይሆን ግንባታቸው የተጠናቀቁ ከስድስት በላይ መንገዶችም የተመረቁትና ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው የተነገረውም በሰኔ ወር ነው፡፡ ስድስት የመንገድ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሥራቸው ተጀመረ ተብሎ የግንባታ ማስጀመሪያ ሥርዓት መዘጋጀቱ በይፋ የተነገረውም በዚሁ በሰኔ ወር ነው፡፡

ይህ ሁሉ ግጥምጥሞሽ ታስቦበት የተደረገ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ባደረግነው ሙከራ ያገኘነው ምላሽ፣ ፕሮጀክቶቹ የተያዘላቸው የኮንትራት መፈራረሚያ ጊዜ በመደራረቡ እንጂ የተለየ ነገር አለመኖሩን ነው፡፡ ግንባታቸው የተጀመረውም ሆኑ ተገንብተው የተመረቁት ፕሮጀክቶች በዚህ ደረጃ የሚታዩ ናቸው፡፡

ይህም ሆኖ ባለሥልጣኑ በሳምንቱ መጨረሻ ብቻ ከአሥር ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚጠይቁ የመንገዶች ግንባታ ሥራን አስጀምሯል፤ አስመርቋል፣ ወይም ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡

ወደ ግንባታ የገቡ መንገዶች

ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ ግንባታ የገቡትና የግንባታ ጅማሬያቸውን በተመለከተ የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው ሁለት የመንገድ ፕሮጀክቶች ከ6.6 ቢሊዮን ብር በላይ ውጪ የሚጠይቁ እንደሆነ ነው፡፡ እንደ ባለሥልጣኑ መረጃ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ግንባታቸው ከተጀመሩት ሁለት መንገደች ውስጥ አንዱ ከነቀምት ቡሬ የሚዘልቀው የአስፓልት መንገድ ሥራ ነው፡፡ የዚህ ፕሮጀክት የግንባታ ስምምነት ከጥቂት ወራት በፊት መከናወኑ ይታወሳል፡፡

257 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለውና ከ5.7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ከሌሎች የግንባታ ኮንትራት ስምምነት በተለየ ሁኔታ ውለታ የተገባበት ስለ መሆኑም ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

እንደ ባለሥልጣኑ መረጃ በልዩ የኮንትራት ስምምነት በይፋ ሥራው የተጀመረው የነቀምት ቡሬ መንገድ በሦስት ርከን ተከፋፍሎ የሚገነባ ነው፡፡ የአገሪቱን ሰሜናዊና ምዕራባዊ ክፍሎችን ደረጃውን በጠበቀ የመንገድ መሠረተ  ልማት ለማስተሳሰር ያስችላል የተባለው ይህ ፕሮጀክት፣ ለአሠራር አመቺነት ሲባል  በሦስት ኮንትራት ተከፍሎ የሚካሄድ ነው፡፡ የመጀመሪያው የግንባታ ክፍል ከነቀምት-አንገር-ጉቲን-አንዶዴ ድረስ 86.1 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡ መንገዱን ከ1.85 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ ለግንባታ ጨረታውን አሸንፈው ሥራቸውን በጥምረት የጀመሩት አይኤል እና ኤፍኤስ ትራንስፖርንቴሽን ኔትወርክስ ሊሚትድ፣ ኤልሳ ሚክስ ኤስኤ (አይቲኤን ኤል ኤልሳ ሜክስ-ጆይንት ቬንቸር) የተባሉ የስፔንና የህንድ የሥራ ተቋራጮች ናቸው፡፡

የመንገዱ ሁለተኛው ክፍል ደግሞ አንዶዴ-አጋምላ 87.65 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፣ ከ1.83 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ሥራ በተጀመረበት ዕለት እንደተገለጸው፣ ይህንን የመንገድ ክፍል ለመገንባት አሸናፊ የሆነው ጄኤምሲ ፕሮጀክትስ (እንዲያን) ሊሚትድ የተባለ የህንድ የሥራ ተቋራጭ ነው፡፡

የመጨረሻውና ሦስተኛው የመንገዱ ክፍል አጋምላ-ቡሬ ሲሆን፣ 84.55 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን ነው፡፡ ይህንን የመንገድ ክፍል ከ2.08 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለመገንባት የጨረታው አሸናፊ ሆነው ግንባታውን የጀመሩት አይኤል እና ኤፍ ኤስ ትራንስፖርቴሽን ኔትወርክስ ሊሚትድ ኤልሳ ሜክስ ኤልኤ (አይቲኤን ኤል-ኤልሳ ሜክስ ጆይንት ቬንቸር) በጋራ በመሆን ነው፡፡ ይህም ከሦስቱ የመንገድ ክፍሎች ሁለቱን የሚገነቡት እነዚሁ የህንድና የስፔን ተቋራጮች ናቸው፡፡

የመንገዱ ግንባታ ነባሩን የማስፋት፣ አዳዲስ ድልድዮችን የመገንባት፣ ነባሮችን የመተካትና የማጠናከር፣ የትላልቅና የአነስተኛ የውኃ መተላለፊያ/ማፍሰሻ ቱቦዎችና ሌሎች በርካታ የመዋቅር ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ታውቋል፡፡

የነቀምት-ቡሬ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ የሚጀመረው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ ሲሆን፣ ከዚያ ተነስቶ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ደብረ ማርቆስ - ባህር ዳር ዋና መንገድ ላይ ከምትገኘው ቡሬ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው፡፡

በሦስት ተከፍሎ ለተለያዩ ኮንትራክተሮች የተሰጠው የነቀምት ቡሬ መንገድ፣ በኮንትራት ውሉ መሠረት ለማጠናቀቅ ስምንት ዓመት የተያዘለት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ የዚህን ያህል ጊዜ ቢያዝለትም በሦስት ዓመት ውስጥ ግንባታው እንዲጠናቀቅ፣ በቀሪው አምስት ዓመት ውስጥ ደግሞ ለጥገናና ለማስተዳደር የተሰጠ ነው፡፡ ለመንገድ ፕሮጀክቶቹ ማስፈጸሚያ የሚውለው አጠቃላይ ውጪ የሚሸፈነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡   

በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ግንባታ የገባው ሌላው የመንገድ ፕሮጀክት ደግሞ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ዞኖችን ያገናኛል የተባለው የሻቡ-ባኮ መንገድ ነው፡፡ የመንገዱ ግንባታ ቅዳሜ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ተጀምሯል፡፡ የመንገድ ግንባታውን ለማከናወን በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው የቻይናው ሲጂሲ ኦቨርሲስ ተቋራጭ ነው፡፡ የግንባታውን የማማከርና የቁጥጥር ሥራ የተረከቡት የሊባኖሱ ካህቲብና አላሚን ኢንጂነርስ ኤኤል እንዲሁም አገር በቀሉ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ነው፡፡

60.2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ የሚካሄድበት ይህ መስመር፣ ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሠረተ ልማት ያልተዘረጋበትና በጠጠር መንገድ ደረጃ የቆየ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

የዚህ መንገድ ግንባታ በሦስት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ወጪም በዓረብ ባንክ፣ በኦፔክና በኢትዮጵያ መንግሥት ይሸፈናል ተብሏል፡፡ የዚህ መንገድ መገንባት በተለይ በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካ የሚመረቱ ውጤቶችን ወደ ገበያ ማዕከላት ከማውጣት አንፃር የሚሰጠው ጠቀሜታ ከፍተኛ ስለመሆኑም ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡  

ባለሥልጣኑ ከሰሞኑ ካከናወናቸው ተግባራት ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቁ መንገዶችን ያስመረቀበት ፕሮግራም የሚጠቀስ ነው፡፡ ሰኔ 18 እና 19 ቀን ብቻ ሦስት የመንገድ ፕሮጀክቶች በይፋ ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉን አብሥሯል፡፡  

ከሦስቱ መንገዶች አንዱ የነቀምት-በደሌ የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ መንገዱ የአዲስ አበባ-ነቀምት-አሶሳን እና የአዲስ አበባ-ጂማ-ጋምቤላን ዋና ዋና መንገዶች በአቋራጭ የሚያስተሳስር ነው፡፡ ይህ መንገድ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የነበረ ሲሆን፣ ካለው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ አንፃር በአሁኑ ወቅት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ ተገንብቶ ለትራፊክ አገልግሎት ክፍት እንደሆነ ባለሥልጣኑ ገልጿል፡፡

95.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የነቀምት-በደሌ መንገድ ግንባታ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ ሲሆን፣ የመንገዱን ግንባታ ያካሄደው ሲጂሲ ኦቨርሲስ ኮንስትራክሽን ነው፡፡ የመንገዱን የማማከርና የቁጥጥር ሥራ ያከናወኑት የኢትዮጵያው ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስና የኬንያው ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ነው፡፡ የዚህ መንገድ ግንባታ አጠቃላይ ወጪ የተሸፈነውም ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከዓረብ ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት፣ ከኦፔክ ፈንድ እንዲሁም ከኩዌት ፈንድ በተገኘ ገንዘብ ነው፡፡

መንገዱ የአርጆ ዴዴሳ የስኳር ፋብሪካና ለፋብሪካው በግብዓትነት የሚውል፣ በ80 ሺሕ ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ የሸንኮራ አገዳ ምርት የሚገኝበት በመሆኑ፤ የሸንካራ አገዳ ምርቱን ወደ አርጆ ዴዴሳና ወደ ሌሎች በስኳር ፋብሪካዎች የማጓጓዝና ከስኳር ፋብሪካዎች የሚመረተውን ምርትም ወደ ገበያ ለማውጣት የሚያስችል ነው፡፡ እንዲሁም የበደሌ ቢራን ለተጠቃሚው በቀላሉ ለማድረስና የማዳበሪያ ፋብሪካ ውጤቶችን ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ትልቅ ፋይዳ ያለው መንገድ እንደሚሆንም ተመልክቷል፡፡ 

ሌላው በሳምንቱ የመጨረሻ ወደ አገልግሎት መግባቱ የተገለጸው የመንገድ ፕሮጀክት የመቀናጆ ደምቢዶሎ መንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ 188 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመቀናጆ-ደምቢዶሎ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በሦስት ኮንትራቶች ተከፍሎ ሲገነባ የቆየ ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት ኮንትራት አንድ ተብሎ የተሰየመውን የመቀናጆ-አደራ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት 52 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው፡፡

ይህን መንገድ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከ639 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የጠየቀ ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የዋለው አጠቃላይ ወጪ የተሸፈነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ የረጅም ጊዜ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡

የመንገድ ግንባታውን ያካሄደው ቻይና ሃይዌይ ሊሚትድ ግሩፕ የተባለ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡ የመንገድ ግንባታ ሥራው ተጀምሮ እስከሚጋመስ ድረስ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ሲያከናውኑ የነበሩት ራፍተን ኢንተርናሽናል እና ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ነው፡፡ ከፕሮጀክቱ ግማሽ አፈጻጸም በኋላ መንገዱ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ቪላዲያ አሶሲዬሽን ከሂትኮን ኢንጂነሪንግ ጋር በጋራ በመሆን የማማከር ተግባሩን አከናውነዋል፡፡

የዚሁ መንገድ ግንባታ ቀጣይና ሁለተኛ ኮንትራት የሆነው የአደራ-ጫንቃ የመንገድ ፕሮጀክት ሲሆን፣ 78.55 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነውም መንገድ ተጠናቅቆ በዚሁ ዕለት ተመርቋል፡፡

ከ712.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን የዚህ ፕሮጀክት አጠቃላይ ወጪ የተሸፈነውም ከዓለም ባንክ በተገኘ የረጅም ጊዜ ብድር ነው፡፡

የመንገዱን ግንባታ የካሄደውም ቻይና ኢንተርናሽናል የውኃና የኤሌክትሪክ ኮርፖሬሽን የተባለ የቻይና ዓለም አቀፍ ተቋራጭ ድርጅት ነው፡፡ የመንገድ ግንባታ ሥራው ተጀምሮ እስከሚጋመስ ድረስ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ሲያከናውኑ የነበሩት ራፍተን ኢንተርናሽናልና ቤዛ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ የተባሉ አማካሪ ድርጅቶች በጋራ በመሆን ነው፡፡ ከፕሮጀክቱ ግማሽ አፈጻጸም በኋላ መንገዱ ተገንብቶ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ረናርደት ኮንስልቲንግ ኢንጂነርስ ከዩናይትድ ኮንሰልቲንግ ጋር በጋራ በመሆን አከናውኗል፡፡ ይህ መንገድ በከተሞች የመንገድ ትከሻን ሳይጨምር 14 ሜትር እና በገጠር የመንገድ ትከሻን ሳይጨምር 7 ሜትር ስፋት አለው፡፡ በሁለቱ መንገዶች ላይ ያሉ አማካሪዎች መቀያየራቸው ከአሠራር ጋር የተያያዘ ነው ተብሏል፡፡ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ በመዘግየቱ የመጀመሪያ አማካሪዎች በኮንትራት ውሉ ላይ እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ መሥራት ስላለባቸው ነው፡፡ የግንባታ ጊዜው ከተራዘመ ደግሞ በአዲስ ኮንሠልታንት ማሠራት ግድ ስለሆነ ነው፡፡

የዚሁ መንገድ ግንባታ አካል የሆነው ኮንትራት ሦስት የመንገድ ፕሮጀክት የጫንቃ-ደምቢዶሎ የመንገድ ፕሮጀክት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ 65.85 ኪሎ ሜትር ርዘመት የሚሸፍን ነው፡፡ ከ689 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ይህም ፕሮጀክት ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የዋለውን አጠቃላይ ወጪ የተሸፈነው ከዓለም ባንክ በተገኘ የረጅም ጊዜ ብድር መሆኑ ታውቋል፡፡ ግንባታውን ያከናወነው ቻይሃ ሃይዌይ ሊሚትድ የተባለ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡  

የነቀምት ከተማ ተለዋጭ መንገድ ግንባታ ሥራ መጠናቀቅም ከሰሞኑ ተገልጿል፡፡ 3.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን ይህንን መንገድ የኢትዮጵያ መንገድ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ነው፡፡

ከ138.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ወጪ የወጣበትን የዚህን ፕሮጀክት ወጪ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑ ታውቋል፡፡ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ያከናወነው ደግሞ የትራንስፖርት ኮንስትራክሽን ዲዞይን አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡

የመንገዱ ስፋት በከተማ የመንገድ ትከሻን ጨምሮ 14 ሜትር እና የመንገዱ አካፋይ ደግሞ 1 ሜትር ስፋትያለው ሲሆን፣ በሁለቱም አቅጣጫ 2.5 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አለው፡፡

የተጠናቀቁት መንገዶችና የኮንትራክተሮቹ ዕጣ ፈንታ

በኢትዮጵያ የመንገድ ግንባታ ሥራ ውስጥ ተደጋግሞ እንደሚታየው ግንባታን በወቅቱ አጠናቅቆ የማስረከብ ችግር ከሰሞኑ አልቀው ከተመረቁ ወይም ለአገልግሎት በቁ የተባሉ ፕሮጀክቶች ላይም ታይቷል፡፡ ለአገልግሎት በቅተዋል የተባሉት የእነዚህ ሦስት የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ2011 ነው፡፡ የኮንትራት ስምምነቶቹ እንደሚያመለክተውም አንዳንዶቹ ፕሮጀክቶች ከግንባታ ጊዜያቸው ከሁለት ዓመት በላይ ዘግይተው የተጠናቀቁ ናቸው፡፡ እንደውም እንደ አንዳንድ ምንጮች ገለጻ ለትራፊክ ክፍት የሆኑት መንገዶች አነስተኛም ቢሆን የማጠናቀቂያ ሥራዎች ይቀራቸዋል፡፡ ቢሆንም ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል፡፡ ስለመመረቃቸውም ተነግሯል፡፡

ከሰሞኑ ለአገልግሎት የበቁት ሦስቱም የመንገድ ፕሮጀክቶች በመጀመርያው የኮንትራት ውል መሠረት የተያዘላቸውን ጊዜ ጠብቀው የተጠናቀቁ አለመሆንም ለተጨማሪ ወጪ ስለማስከተላቸው ይነገራል፡፡ ከዚህ አንፃር ለምሳሌ የኮንትራት አንድ ፕሮጀክት በ2014 የሚጠናቀቅ ነበር፡፡ ሆኖም ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በሁለት ዓመት ዘግይቶ የተጠናቀቀ ነው፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች ግን ለዚህ ፕሮጀክት መዘግየት ምክንያት ብለው የሚያስቀምጡት በአካባቢው ከባድ ዝናብና ሌሎች ምክንያቶች ስለነበሩና ይኽም አሳማኝ በመሆኑ  ለሦስት ኮንትራክተሮች ለአንድ ዓመት ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ኮንትራት ሁለት ደግሞ እስከዚህ ዓመት አጋማሽ ድረስ ግንባታውን እንዲጨርስ ተጨማሪ ጊዜ ተሰጥቶት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህንን ፕሮጀክት የያዘው ኮንትራክተር በተራዘመለት የጊዜ ገደብ ሥራውን አጠናቋል ተብሏል፡፡ ሆኖም ግንባታው በተገባለት  ቀድሞ ውል መሠረት ያልተጠናቀቀ ነው፡፡

በተለይ የኮንትራት ሦስት ፕሮጀክት ኮንትራክተር በተሰጠው ተጨማሪ ጊዜም ቢሆን ሊያጠናቅቅ አልቻለም፡፡ ሌላ ተጨማሪ ማራዘሚያ ጊዜ ባይሰጠውም፣ የመንገድ ግንባታው መቋረጥ ስለሌለበት ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ከሁለት ዓመታት በላይ ዘግይቶም መንገዱን ስለመረጨሱ ተጠቅሷል፡፡

እንደ ምንጮች ገለጻ ግን ይህ ኮንትራክተር በዝምታ ሊታለፍ እንደማይችል ተገምቷል፡፡ ግንባታውን አዘግይቶ ቢጨርስም በኮንትራት ውሉ መሠረት ላቃጠለው ጊዜ ከፕሮጀክቱ ወጪ ተሰልቶ እስከ 50 ሚሊዮን ብር ሊቀጣ ይችላል፡፡

ኮንትራት ሦስትም ተመሳሳይ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑንም እኚሁ ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ በእነዚህ ሦስት ፕሮጀክቶች ላይ የታየው የግንባታ መዘግየት የመንገድ ግንባታን በወቅቱ ያለማስረከብ ችግር የውጭ ኮንትራክተሮች ጭምር መሆኑን ያሳየ ስለመሆኑ ያስገነዘበ ሆኗል፡፡

 

Standard (Image)

በሎጂስቲክ አገልግሎት መስክ ያልተፈቱ ችግሮች

$
0
0

በኢትዮጵያ የወጪና ገቢ ዕቃዎችን ለማጓጓዝ የሚጠየቀው ዋጋ ከፍተኛ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡ የሎጂስቲክ ዋጋ ከሌሎች አገሮች ጋር በንጽጽር ይታይ ከተባለም ሰፊ ልዩነት ያለው ሆኖ ይገኛል፡፡ ዓርብ ሰኔ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. የአገሪቱን የሎጂስቲክ አገልግሎት በተመለከተ ተካሂዶ በነበረ የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸው፣ ለአገሪቱ የሎጂስቲክ አገልግሎት ዋጋ መወደድ አንዱ ምክንያት የአገሪቱ የትራንስፖርት አገልግሎት ዘመናዊ አለመሆኑ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በአጽንኦት እንደተገለጸውም ከፍተኛ ሆኖ የሚገኘውን የሎጂስቲክ ዋጋን ዝቅ ሊያደርጉ የሚችሉ ዘመናዊ አገልግሎቶች በትራንስፖርት ዘርፉ ውስጥ አለመታየታቸው ትልቅ ችግር ሆኗል፡፡ በውይይት መድረኩ የመወያያ ጽሑፋቸውን ያቀረቡት የኢትዮ ትራክ ኩባንያ መሥራች ዶ/ር አዛሪያስ ሙላቱ እንደገለጹት፣ በሎጂስቲክ ዘርፍ አንዱ ችግር ዘመናዊ የሎጂስቲክ አገልግሎትን በአግባቡ መተግበር አለመቻል ነው፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሎጂስቲክ አገልግሎት መስክ ያሉትን ችግሮችም ጠቁመው ነበር፡፡ ሌላው ቀርቶ በሳተላይት የታገዙ አቅጣጫ መጠቆሚያ ሥርዓት (ጂፒኤስ) የተተከለላቸው ተሽከርካሪዎች የተፈለገውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ያልተቻለበት አጋጣሚ በመፈጠሩ ዘርፉን ለማሳደግና ወጪን ለመቀነስ አላስቻለም፡፡

በኢትዮጵያ ያለው የትራንስፖርት አገልግሎት ዋጋ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ እየሆነ በመምጣቱ ከሌሎች አገሮች ጋር ለመወዳደር ከባድ ስለሚሆን የሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ማዘመንና ወጪ ቆጣቢ ማድረግ ተገቢ መሆኑ ተገልጿል፡፡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

አገልግሎቱን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስታጠቅ ብቻ ወጪን መቀነስ እንደማይቻል የጠቀሱት የውይይቱ ተሳታፊዎች፣ ሎጂስቲክን የሚመለከቱት መመርያዎች ሊስተካከሉ እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡

ኔትወርክና የሎጂስቲክ አገልግሎት

የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማዘመን አንዱ መፍትሔ የጂፒኤስ አገልግሎት በመትከል ተሽከርካሪዎች ወጪ ቆጣቢና አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል ነው፡፡ ጠቀሜታውም የጐላ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡ ነገር ግን ጂፒኤስ ተተክሎላቸውም ቢሆን ዘመናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል፡፡

ይህም የጂፒኤስ አገልግሎት የሚሰጠው በኔትወርክ በመሆኑ ነው፡፡ በኔትወርክ ችግር ሳቢያም ተሽከርካሪዎች ከቁጥጥር ውጪ ይሆናሉ፡፡ ምንም እንኳ ኔትወርክ በማያገኙበት ጊዜ እንቅስቃሴያቸውን የሚያመለክት ሪፖርት ቢያቀርቡም በወቅቱ ዕርምጃ ለመውሰድ ግን የኔትወርኩ መቆራረጥ እንቅፋት እየሆነ ነው፡፡

የኔትወርክ ችግር በዚህ ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ ተሽከርካሪው የጂቡቲን ድንበር ከተሻገረ በኋላ ግንኙነት የሚቋረጥ በመሆኑ የጂፒኤስ አገልግሎቱን ጐዶሎ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አዛርያስም ይህ ችግር እንዳለ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ በአገሪቱ 80 በመቶ የኔትወርክ ሽፋን መኖሩ ቢገለጽም፣ በተጨባጭ ግን በበርካታ አካባቢዎች የኔትወርክ መቆራረጡ እንደሚታይ አስረድተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ውጭ የጂፒኤስ አገልግሎት እንዲሠራ ዓለም አቀፍ ኔትወርኮችን መጠቀም አስፈላጊ ስለመሆኑም በመፍትሔነት ተቀምጧል፡፡

የሎጂስቲክስ ዋጋና ተያያዥ ችግሮች

የሎጂስቲክ ወጪን እንዴት መቀነስ ይቻላል የሚለው መሠረታዊ ጉዳይ እንደሆነ በመጥቀስ አስተያየታቸውን የገለጹት፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅትን የወከሉ ባለሙያ ናቸው፡፡ የሎጂስቲክ አገልግሎት ወጪ እጅግ ከፍተኛ የሚሆነው ከመነሻው ጀምሮ ነው ያሉት እኚህ ባለሙያ፣ የጭነት አገልግሎቱ ከመነሻው ወደብ ጀምሮ አገር ቤት እስኪደርስ ድረስ ብዙ የሚነካኩ ነገሮች ስላሉ ወጪውም በዚያው ልክ እየናረ እንደሚመጣ አብራርተዋል፡፡

ትልቁ ችግር ተቀናጅቶ ያለመሥራት ስለመሆኑም ገልጸዋል፡፡ ‹‹በሎጂስቲክ ሥራ ውስጥ የሚጠቀሱ እንደ ጉምሩክ፣ መንገድ ትራንስፖርት፣ የወደብ ድርጅትና የመሳሰሉት በቅንጅትና በእኩል ፍጥነት የማይሠሩ ከሆኑ አገልግሎቱ ይጓተታል፡፡ በተፈለገው ጊዜ ዕቃን ወደሚፈለገው ቦታ ማድረስ ስለማይቻል የማጓጓዣ ዋጋው ይጨምራል፡፡››

ሌላው የሎጂስቲክስ ችግር የዕቃ ማጓጓዣው ዘዴ አንድ ዓይነት ብቻ መሆኑ ነው፡፡ በአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ዕቃዎች የሚጓጓዙት በተሽከርካሪዎች ብቻ መሆኑ ለአገልግሎቱ የዋጋ ንረት ትልቁን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

መንግሥት የሎጂስቲክስ ዋጋ እንዲቀንስ የተለያዩ ጥረቶችን ማድረጉን የጠቆሙት እኚሁ ተወካይ፣ በተለይ ለማጓጓዣ የሚወጣው የጨረታ ዋጋ የተጋነነ በመሆኑ በድርድር ጭምር ዋጋው ቅናሽ የሚደረግበትን አግባብ እስከመከተል ተደርሷል ይላሉ፡፡ በጨረታ መሥራት ግዴታ ቢሆንም ከጨረታ በኋላ በድርድር ዋጋ የማስቀነስ ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ተደርጐ ዋጋው ውድ ሆኖ ይገኛል፡፡ እንዲህ ዓይነት አሠራሮች ያስከተሉትን ጉዳት በመመልከት አሠራሩ የሚሻሻልበት መንገድ ተጠንቶ ለመንግሥት መቅረቡን ገልጸዋል፡፡ የአገሪቱ የሎጂስቲክ አገልግሎት ለምን ውድ እንደሆነ ፍተሻ በሚደረግበት ጊዜ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ተጠቃሽ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ባለንብረቶቹ ለዋጋ መናር ከሚያቀርቧቸው መካከል አንዱ ምክንያት የመሠረተ ልማት አለመሟላት ነው፡፡

‹‹ባልተመቻቸ መሠረተ ልማት ውስጥ የምንሰጠው አገልግሎት ከፍተኛ ገንዘብ የወጣበትን ተሽከርካሪ ያለዕድሜው ስለሚገድለው ወጪያችንን በአጭር ጊዜ ለመመለስ ዋጋ ከፍ ማድረጉ የግዴታ አማራጭ ስለሆነ ነው፤›› ይላሉ፡፡ የጐማና የመለዋወጫ ዋጋን በማሰብ ጭምር ካልተሠራ አዋጭ አይሆንልንም የሚል ምክንያት እየሰጡ ነው፡፡

ለሎጂስቲክስ ዋጋ መናር የትራንስፖርት አገልግሎት እጥረት አንዱ መንስዔ ሆኖ የቀረበበት ሌላኛው ምክንያት ደግሞ በዕቅድ ያለመሥራት ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ የተሰነዘረው አስተያየት ምሳሌ ያደረገው የመንግሥት የማዳበሪያና የዕርዳታ ግዥዎች እንዲሁም ግብዓቶች በዕቅድ የሚስተናገዱበትን አሠራር በተገቢው አኳኋን ቀድሞ ያለማቀድ ነው፡፡

አንዳንዴ እነዚህ ምርቶች በአንድ ጊዜ ተጭነው የጂቡቲን ወደብ ያጥለቀልቃሉ፡፡ በ10 እና በ15 መርከቦች ተጭነው የሚመጡት እነዚህ ምርቶችና ዕቃዎች በቶሎ መነሳት አለባቸው ተብሎ የሚፈጠረው ትርምስ ለትራንስፖርት ዋጋ መወደድና እጥረት ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸው ተስተውሏል፡፡

ከጂቡቲ ወደብ በቀን ማስተናገድና ማጓጓዝ የሚቻለው እስከ 800 ተሽከርካሪዎች ብቻ ሲሆን፣ ከዚያ በላይ እስከ 1200 ተሽከርካሪዎች ዕቃ ማንሳት አለባቸው ከተባለ ግን ከአቅም በላይ በመሆኑና ችግሩን ይበልጥ ስለሚያባብሰው መንግሥት እነዚህን ምርቶች በዕቅድ ቢያስመጣ ተመራጭ ነው ተብሏል፡፡

የትራንስፖርት ድርጅቶችም ለአሽከርካሪዎች የሚከፍሉት ክፍያ አነስተኛ መሆን፣ ከሎጂስቲክስ አገልግሎት ጋር የተሳሰሩ መሥሪያ ቤቶች ደካማ አገልግሎት ለችግሩ መባባስ ተጠያቂዎች ናቸው ተብሏል፡፡  

ለሎጂስቲክስ አገልግሎት የታሰበው መፍትሔ

በውይይት መድረኩ ላይ መገንዘብ እንደተቻለው ለሎጂስቲክ አገልግሎት ዋጋ መናር አንዱ ምክንያት በተሽከርካሪዎች ብቻ ዕቃ ማጓጓዝ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ያለውን ችግር ለመቅረፍ የባቡር ትራንስፖርት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ አገልግሎት ሲጀመር በተወሰነ ደረጃ ለዕቃ ማጓጓዣ የሚወጣው ወጪ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በመጪው ጥቅምት 2009 ዓ.ም. ከጂቡቲ አዲስ አበባ የተዘረጋው ባቡር አገልግሎት ይጀምራል መባሉ ትልቅ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡

ነገር ግን እንዲህ ያሉ መፍትሔዎች ከተተገበሩ በኋላ ከጂቡቲ ተነስተው ወደ ተለያዩ ደረቅ ወደቦች የደረሱ ዕቃዎች በቶሎ የማይነሱ ከሆነ አሁንም የሎጂስቲክ ወጪው ተቃሏል ለማለት እንደማይቻል ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሞጆ ደረቅ ወደብ ብቻ ከ12 ሺሕ በላይ ኮንቴይነሮች ተከማችተው ያለመነሳታቸውን መረጃዎች እያሳዩ ነው፡፡ ኮንቴይነሮቹ እስከ 300 ቀናት ሳይነሱ የቆዩ ናቸው፡፡ ብዙ በቆዩ ጊዜም የዋጋ ንረትን እያስከተሉ እንደመጡ ተነግሯል፡፡

የተጋነነ የቀረጥ ዋጋ፣ የአገልግሎት አሰጣጡ መንቀርፈፍና የመሳሰሉት ለሎጂቲክ ችግሮች መባባስ ምክንያት መሆናቸውን ተሳታፊዎች ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

Standard (Image)

ዓባይ ቴክኒክና ንግድ ኩባንያ በሃያ ሚሊዮን ብር ካፒታል የንግድ መኪኖችን መገጣጠም ጀመረ

$
0
0

በብርሃኑ ፈቃደ

ዓባይና ቴክኒክና የንግድ አክሲዮን ማኅበር ከመንግሥት ይዞታነት ወደ ግል ከተዛወረ ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው መስክ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ የጀርመን ብራንድ የሆነውንና ፉቶን የተሰኘው ኩባንያ ያመረታቸውን ሚኒባሶችና ፒክአፖች በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡ ዓባይ ቴክኒክ በ20 ሚሊዮን ብር ካፒታል የመገጣጠም ሥራውን የጀመረባቸው ተሽከርካሪዎች ለከተማ ትራንስፖርትና ለግንባታው ዘርፎች እገዛ እንደሚያደርጉ የኩባንያው ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

የአክሲዮን ማኅበሩ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ምንተስኖት ታደሰ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በቀን አሥር ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም ይዞ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪውን ተቀላቅሏል፡፡ ይሁንና የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት እጥረትና ሌሎች ችግሮች ተደራርበው በቀን ሁለት መኪኖችን በመጋጣጠም ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

ኩባንያው ከሚገጣጥማቸው መካከል በከተሞች ውስጥ ለታክሲ አገልግሎት የሚውሉ 14 ሰው የመጫን አቅም ያላቸውን ሚኒባሶችን ገጣጥሞ ለማቅረብ እየሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት አቶ ምንተስኖት፣ በዋጋ ረገድም በአሁኑ ወቅት ባለው የገበያ ዋጋ መሠረት ለአንድ ሚኒባስ 590 ሺሕ ብር እንደተቆረጠለት ገልጸዋል፡፡ ሚኒባሶቹ DVVT-I (Dual Variable Valve Timing- with Intelligence) የተሰኘና የቅርብ ጊዜ ሥሪት ሞተር የተገጠመለት መሆኑን የተናገሩት አቶ ምንተስኖት፣ ፒክአፕ መኪናው ደግሞ የአሜሪካውን ካሚንስዝ ሞተር እንደተገጠመለት አስታውቀዋል፡፡ 

ከሚኒባሶቹ ባሻገር 735 ሺሕ ብር እንደሚያወጡ የተነገረላቸው ፒክአፕ ተሽከርካሪዎች ለገበያ መቅረባቸውን ታውቋል፡፡ የገበያው ፍላጎት በተለይም በትራንስፖርት ዘርፍ የሚታየው እጥረት ለኩባንያው ምቹ የገበያ ዕድል እንደሚፈጥር አቶ ምንተስኖት እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ መኪኖቹ የ50 ሺሕ ኪሎ ሜትር ወይም የሦስት ዓመት ዋስትና እንዳላቸውና ገበያ ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቀጠሮ ለሽያጭ መቅረባቸውንና በዱቤ ሽያጭም የ50 ከመቶ የባንክ ብድር በማመቻቸት እየተሸጡ እንደሚገኙ አቶ ምንተስኖት አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ለንግድ ተሽከርካሪዎች ያለው ፍላጎት ከሌሎች የመጓጓዣ መኪኖች ይልቅ ከፍ እንደሚል ዋና መሥሪያ ቤቱን በአሜሪካ ያደረገው ድሎይት ኩባንያ ያወጣው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ድሎይት ከወራት በፊት ያወጣውና በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እንዲሁም በናይጄሪያ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪዎች ላይ ያተኮረው የዳሰሳ ጥናት እንደሚጠቁመው፣ ከሦስት አገሮች ኢትዮጵያ በነፍስ ወከፍ ከአንድ ሺሕ ሰዎች ሁለቱ ብቻ መኪና የሚያሽከረክሩባት አገር ሆና ትገኛለች፡፡ በኬንያ ከአንድ ሺሕ ሰዎች 28ቱ ባለመኪና ሲሆኑ፣ በናይጄሪያም ከአንድ ሺዎች ሃያው ብቻ ባለመኪና መሆናቸውን የድሎይት መረጃ ያሳል፡፡

በኢትዮጵያ በመገጣጠሚያ መስክ ለመሰማራት ፈቃድ ከተወሰደባቸው 104 ያህል የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መካከል 31 የውጭ ኩባንያዎች ያስመዘገቡት መሆኑ ታውቋል፡፡ 73 ያህሉ ፕሮጀክቶች ደግሞ በአገር ውስጥ ኩባንያዎች ፈቃድ ቢጠየቅባቸውም፣ በጠቅላለው በተግባር ላይ የሚገኙት ገጣጣሚ ኩባንያዎች ግን ከአሥር እንደማይበልጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ምንም እንኳ በነፍስ ወከፍ ያለው የመኪና ባለቤትነትና ያለው ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም፣ በርካታ ገዥ አጥተው የተገጣጠሙ መኪኖች ተከማችተው እንደሚገኙም ይገለጻል፡፡ ለዚህ በምክንያትነት ከሚጠቀሱ ችግሮች መካከል የዋጋና ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጫና መሆኑን ገጣጣሚ ኩባንያዎች ሲናገሩ ይደመጣል፡፡

በድሎይት ጥናት መሠረት በኢትዮጵያ በያመቱ ለገበያ የሚቀርቡ አዳዲስ መኪኖች ብዛት 18 ሺሕ ያህል እንደሚገመት ይጠቅሳል፡፡ በአንፃሩ በአገሪቱ ጎዳናዎች ውስጥ እንደሚሽከረከሩ የሚገመቱት ከ570 ሺሕ በላይ መኪኖች ውስጥ ከ85 ከመቶ በላይ ያገለገሉ መኪኖች እንደሆኑ ይገመታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ ድርሻ እንደያዙ የሚነገርላቸው የቶዮታ ሥሪት ተሽከርካሪዎች እንደሆኑ ድሎይት ይጠቅሳል፡፡ በየዓመቱም ከአስምት እስከ ሰባት ሺሕ የሚደደርሱ ያገለገሉ የቶዮታ ሥሪት መኪኖች ወደ አገር ውስጥ ይገባሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በኬንያና በናይጄሪያም ተመሳሳይ አዝማሚያዎች ሲኖሩ፣ በኬንያ ከሚሽከረከሩት መኪኖች ውስጥ 80 ከመቶው ያገለገሉ ናቸው፡፡ በናይጄሪያ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መካከል 90 ከመቶ ያህሉ ያገለገሉ መሆናቸውን ድሎይት አስፍሯል፡፡

 

  

Standard (Image)

‹‹መንግሥት ሕግ ጥሶ ሲወስን ምክንያት ነበረው››

$
0
0

አቶ ዘሪሁን ቃሚሶን፤ የደቡብ ክልል ቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች የዘርፍ ማኅበር መሥራችና ፕሬዚዳንት 

 

በዳዊት ታዬ

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በደቡብ ክልል የሚገኙ የቡና አቅራቢዎች ከተለያዩ ባንኮች የተበደሩትንና በተቀመጠላቸው ገደብ መሠረት መመለስ ያልቻሉትን ብድር በሒደት መመለስ ይችሉ ዘንድ መፍትሔ ይሆናል ያለውን ውሳኔ በቅርቡ ለባንኮች አስተላልፏል፡፡ ቡና አቅራቢዎቹ የተከማቸባቸውን ዕዳ መክፈል ባለመቻላቸው ከፍተኛ ችግር ውስጥ ስለመግባታቸውና ያጋጠማቸው ኪሳራም በቢሊዮን ብር የሚገመቱ ንብረቶቻቸው ሐራጅ ሊባሉ መሆኑን በመሥጋት ሲገልጹ ስለነበር በዚሁ መነሻነት ብሔራዊ ባንክ ያሳለፈው ውሳኔ ነው፡፡ ውሳኔው ተበዳሪ ከሦስት ጊዜ በላይ የብድሩ መክፈልያ ጊዜ ሊራዘምለት እንደማይችል ከተቀመጠው የገዥው ባንክ መመሪያ ውጭ ባንኮች የቡና አቅራቢዎቹን ጥያቄዎች እንዲያስተናግዱ ያስችላቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ከተላለፈው ሰርኩላር ቀደም ብሎም የቡና አቅራቢዎቹ ለብድር ማስያዣነት ያቀረባቸው ንብረቶች በባንኰች እንዳይሸጥባቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡ በዚሁ ማሳሰቢያ መሠረት ባንኮች የተበዳሪዎቹን ንብረቶች በጨረታ ለመሸጥ የጀመሩትን እንቅስቃሴ አቁመዋል፡፡ የብሔራዊ ባንኩ ባሰራጫቸው ሁለት ሰርኩላሮች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች መደመጥ ጀምረዋል፡፡ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያልተለመደ የተባለው የመንግሥት ውሳኔ ግን ከብዙ ውጣውረዶች በኋላም ቢሆን የግድ መደረግ የነበረበት መሆኑን በመግለጽ የሚከራከሩም አሉ፡፡ ባንኮቹ ከተቀመጠላቸው መመሪያ ውጭ የቡና አቅራቢ ተበዳሪዎችን እንዲያስተናግዱ የተደረገበት ዋነኛ ምክንያትም ሊደርስ የሚችለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከፍተኛ መሆኑ ቀድሞ ስለታመነበት ነው፡፡ ከተለመደው ሕጋዊ አሠራር ውጭ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ለሁለት ዓመት የሚቆይ የብድር ማራዘሚያ እንዲሰጣቸው፤ ብድር ከፈለጉም ምንም ዓይነት እገዳ እንዳይኖርባቸው የተፈቀደው ችግሩ ምን ያህል ቢሆን ነው? የሚለውን ጥያቄ ያስከትላል፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች የመንግሥት ውሳኔ ትክክል ስለመሆኑ ያምናሉ፡፡ መንግሥት እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከቡና አቅራቢዎቹ በተደጋጋሚ የቀረቡ ጥያቄዎችና የመፍትሔ ሐሳቦችን የያዙ አማራጮች ቀርቦለት ሲመከርበት ቆይቶ የተወሰነ ስለመሆኑ ቡና አቅራቢዎቹን የሚወክለው የደቡብ ክልል የቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች ዘርፍ ማኅበር አመራሮች ይገልጻሉ፡፡ ይህ ባይሆን ኑሮ ግን ከፍተኛ ቀውስ ይከሰት ነበር ይላሉ፡፡ ቡና አቅራቢዎቹ ለገጠማቸው ችግር በደቡብ ክልል ብቻ ለብድር ማስያዣነት ያዋሏቸው ከ2,500 በላይ ሕንፃዎችና መኖሪያ ቤቶች ቤቶች በሃራጅ በጨረታ ሊሸጡ ተቃርበው እንደነበር ይጠቅሳሉ፡፡ በአነጋጋሪው የመንግሥት ውሳኔ ላይ የፊት አውራሪነቱን ሚና ተጫውቷል የተባለውን ማኅበር መሥራችና ፕሬዚዳንት አቶ ዘሪሁን ቃሚሶን ዳዊት ታዬአነጋግሯቸዋል፡፡ በደቡብ ክልል ተፈጠረ የተባለውን ችግርና አሁን የተደረሰበት ውጤት አጠቃላይ ይዘት ለማሳየትም ከኋላ ታሪኩ በመንደርደር የተደረገው ቃለ ምልልስ ተጠናቅሯል፡፡

ሪፖርተር፡- የማኅበሩ አፈጣጠር በክልሉ ከተከሰተው የቡና አቅራቢዎች ኪሣራ ጋር የተያያዘ ነው ይባላል፡፡ እርስዎም የማኅበሩ ምሥረታ ሐሳብ አፍላቂ ስለነበሩ የማኅበሩ አመሠራረትና የኋላ ታሪክ  ምን እንደሚመስል ቢነግሩን? አርሶ አደሮችስ እንዴት ነበር ወደ ቡና ማቅረብ ሥራ የገቡት?

አቶ ዘሪሁን፡- ማኅበሩ የተቋቋመው የመንግሥትን ፖሊሲ መሠረት በማድረግ ወደ ቡና ንግድ በገቡ የግል ቡና አቅራቢዎች ነው፡፡ በደርግ ጊዜ የታጠበ ቡና ሥራ በማኅበራት እጅ ይካሄድ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ ሥልጣን ሲይዝ፣ የእዝ ኢኮኖሚ ሥርዓት ፈርሶ ወደ ነፃ ገበያ በሚመጣበት ጊዜ በማኅበራት ብቻ ሲካሄድ የነበረው የታጠበ ቡና ንግድ ሥራ ግለሰቦችም እንዲገቡበት መመሪያ ወጥቷል፡፡ በመመሪያው መሠረት የታጠበ ቡና አቅራቢነትለ የግሉ ዘርፍንም አካተተ፡፡ ቡናው ያለው በአርሶ አደሩ ጓሮ ነው፡፡ የታጠበ ቡና የማቅረብ ሥራ ደግሞ ያለ ውኃ የማይካሄድ ስለሆነና ለአጠባ የሚፈለገውም ውኃ መገኛው ወንዝ በአርሶ አደሩ ደጃፍ የሚያልፍ በመሆኑ ይህንን ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ያስቻለ ነው፡፡ ይህንን ሀብት አገሪቱ ተግባራዊ ባደረገችው የኢኮኖሚ ፖሊሲ እንደተመለከተው የአካባቢው ሕዝብ ባለው ሀብት የመጠቀም መብትን ያጐናፀፈ ሆኗል፡፡ አርሶ አደሩ በቀዬው ያለውን ሀብት፣ በጓሮው ያለውን ወንዝ እንደ መዋጮ ይዞ ባህር ዛፍና አሸዋ ከአካባቢው ወስዶ፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመፈልፈያ፣ የመገንቢያና የሥራ ማስኬጃ ብድር ሰጥቶት ሥራ ውስጥ እንዲገባ አስችሎታል፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ የተደረገው መቼ ነበር? በአካባቢያችሁ ያሉ አርሶ አደሮች ወደ ቡና አቅራቢነት እንዴት እንደተሸጋገሩ ቢያስትውሱንና ከፍተኛ እንደሆነ በሚነገርለት ኪሳራ ውስጥ የተገባበት ምክንያትም ምንድን እንደነበር ቢገልጹልን?

አቶ ዘሪሁን፡- በ1986 ዓ.ም. ነው፡፡ በአዲሱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት የመጀመሪያውን መፈልፈያ በማቋቋም ወደ ሥራ የገቡት አቶ ሲላዳ ኤ የሚባሉ የአካባቢው ተወላጅ ናቸው፡፡ እኚህ ሰው ቀድሞም በኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት መፈልፈያ የነበራቸው ቢሆንም፣ በደርግ ተወረሰባቸው፡፡ ደርግ ሲወድቅ ቀድሞ ይሠሩበት የነበረው ቦታ ተፈቅዶላቸው ተመልሰው ወደ ቡና መፈልፈል ሥራቸው ገቡ፡፡ የእርሳቸው ዳግመኛ ሥራ መጀመር ጥሩ ምሳሌ ሆኖ ሌሎችም በመፈልፈያ ሥራ ውስጥ መግባት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆነ፡፡ ሁሉም አርሶ አደር ቡናውን፣ ወንዙን፣ መሬቱንና በአካባቢው ያለውን የግንባታ ግብዓቶች በመዋጮነት በሚያስያዝ በርካታ አርሶ አደሮች ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ማኅበር በመደራጀት  በቡና ማቅረብ ንግድ ውስጥ ገቡ፡፡ ነገር ግን ወደዚህ ንግድ ሲገቡ በቂ የንግድ ክህሎት አልነበራቸውም፡፡ የኋላ ታሪካቸውንም ብታይ በንግድ ሥራው ዕውቀት የሌላቸው ስለመሆኑ ትገነዘባለህ፡፡ ሆኖም በተፈጠረላቸው አጋጣሚ ንግዱን የጀመሩት ቡና ሁልጊዜ አትራፊ ያደርጋል በሚል ስሜት ነው፡፡  የአጋጣሚ ሆኖ ደግሞ አርሶ አደሮቹ ወደ ቡና ማቅረብ ሥራ በገቡበት ወቅት አገሪቱ የምንዛሪ ለውጥ ያደረገችበት ጊዜ ስለነበር በርካታ አርሶ አደሮች በእጃቸው ያለውን ቡና ሲሸጡ ከፍተኛ ገንዘብ አገኙ፡፡ ይህ ክስተት ቡና ሁልጊዜ አትራፊ እንደሚያደርግ በማመን ዋጋ እየጨመሩ ሥራውን መሥራት ቀጠሉ፡፡ በመሆኑም ከ1989 እስከ 1990 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ተሠራ፡፡ ከ1990 እስከ 1991 ዓ.ም. ግን የቡና አቅራቢዎች ከፍተኛ ኪሣራ ውስጥ ገቡ፡፡  

ሪፖርተር፡- የኪሣራው ምክንያት ምንድነው?

አቶ ዘሪሁን፡- በወቅቱ ለነበረው ከፍተኛ ኪሣራ ዋነኛ ምንጩ የዓለም የቡና ዋጋ መውደቅ ነው፡፡ የዓለም የቡና ዋጋ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ይከናወን በነበረ የእሸት ቡና ግዥዎች ምክንያት የተፈጠረ ቀውስ ነው፡፡ ሌሎች ምክንያቶችም ነበሩ፡፡

ሪፖርተር፡- ቡና አቅራቢዎች የዓለምን የቡና ዋጋ ሳይመዝኑ የተደረገ ግዥ የፈጠረው ችግር ነው ሲባል ምን ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ከመነሻው የነበው የእሸት ቡና ግዥ ነው፡፡ በውድ ዋጋ ገዝተው እዚህ አምጥተው የሚሸጡበት ዋጋ ዝቅተኛ ሲሆን ኪሣራው መጣ፡፡ በመግዛት እንጂ በመሸጥ አይደለም የምታተርፈው፡፡ ትርፍህ ስትገዛ ነው፡፡ ትርፍህ ስትገዛ ነው ማለት ለምሳሌ ከአምራቹ በአሥር ብር እንገዛለን እንበል፡፡ በአሥር ብር ስትገዛው ግን 15 ብር እንደምትሸጠው አውቀህ መሆን አለበት፡፡ ስለዚህ የትርፉ ግዥው ዋጋ ላይ መሠረት ያደረገ ነው ማለት ነው፡፡ በዚያን ወቅት ግን እንዲህ ያለውን መሠረታዊ ነገር ወይም የዓለም ቡና ዋጋን ግምት ውስጥ ሳያስገቡ በውድ ዋጋ ግዥውን ፈጸሙ፡፡ ይህንንም ያደረጉት በቀደመው ዓመት ትርፍ ስለተገኘ ዘንድሮም ትንሽ ጨምረን ብንገዛ ያተርፈናል ከሚል መነሻ በስሜት በመሠራቱ ነው፡፡ ቡና አያከስርም የሚለው ስሜት የፈጠረው ነው፡፡ ሆኖም ከፍተኛ ኪሣራ አመጣ፡፡ ያኔ ለሥራው ማስኬጃ ብድር የሰጠው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስለነበር፣ በተፈጠረው ኪሣራ ምክንያት አቅራቢዎቹ ብድሩን መክፈል ባለመቻላቸው ባንኩ ተበዳሪዎች ያስያዙትን ንብረት ለመሸጥ ጨረታ ማውጣት ጀመረ፡፡ ይህንን መቋቋም አልተቻለም፡፡ ይህንን ከፍተኛ ኪሣራ ለመቋቋም በኅብረት መሥራትና ድምፅን ማሰማት ግድ ሲሆን፣ የምንቀራረብ ሰዎች በጋራ ሆነን ማኅበሩን ልንፈጥረው ቻልን፡፡ ነገር ግን የግል ዘርፍ ማኅበራትን ለማቋቋም መመሪያም ደንቦችም አልወጡም፡፡ ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ መደራጀት አይከለከልም ብለን በመነሳት የክልሉን መንግሥት ስንጠይቅ ተባበረን፡፡ ሒደቱ ተግዳሮት የበዛበት ቢሆንም ማኅበሩ ግን ተቋቁሟል፡፡

ሪፖርተር፡-ማኅበሩን ለመመሥረት የእርስዎን ሐሳብ የተቀበሉና በመሥራች አባልነት የተመዘገቡ ቡና አቅራቢዎች ምን ያህል ነበሩ? በወቅቱ ለመክፈል ያልቻላችሁት ብድር መጠንስ ምን ያህል ነበር?  

አቶ ዘሪሁን፡- ሲጀመር የማኅበሩ አባላት 120 አካባቢ ነበርን፡፡ ያኔ የነበረብንም ዕዳ ከ300 ሚሊዮን ብር አይበልጥም ነበር፡፡ ምክንያቱም ያኔ የእሸት ቡና መግዣ ዋጋ አነስተኛ ስለነበር ነው፡፡ ቢበዛ አንድ ኪሎ እሸት ቡና ከሁለት እስከ አራት ብር ይገዛ ነበር፡፡ ስለዚህ የብድር መጠኑም በዚያው ልክ ነው፡፡ እንዲያውም በ1989 ዓ.ም. ገደማ አካባቢ የአንድ ኪሎ እሸት ቡና መግዣ ዋጋ ከ50 ሳንቲም እስከ አንድ ብር ነበር፡፡ ብዙ ገንዘብም አይጠይቅህም ነበር፡፡ ይህም ቢሆን ግን ብድሩን መመለስ አልተቻለም፡፡ ስለዚህ ችግራችንን አስረድተን መንግሥት እገዛ እንዲያደርግልን ጠየቅን፡፡ ነገር ግን ለኪሳራችን የኋላ ታሪካችን ችግርም የራሱ ድርሻ ነበረው፡፡

ሪፖርተር፡- የኋላ ታሪካችን ችግር አለው ሲሉ ምን ማለትዎ እንደሆነ ቢያብራሩልን?

አቶ ዘሪሁን፡- የኋላ ታሪካችን ወይም ወደ ሥራ ስንገባ ችግር ነበር ያልኩበት ምክንያት ወደ ሥራው የገባው አርሶ አደር የነጋዴነት ባሕሪይ ያልነበረው በመሆኑ ነው፡፡ በቃ ቡና ውስጥ ግባ በመባሉና መንግሥትም ገንዘብ ሰጥቶት ሥራውን የጀመረ በመሆኑ ነው፡፡ ቡና አቅራቢ እንዲሆን፣ የመፈልፈያ ባለቤት እንዲሆን ሲደረግ አርሶ አደሩ በጥሬ ገንዘብ አስተዋጽኦ አላደረገም፡፡ መዋጮው በዓይነት ነበር፡፡ ገንዘብ ወደ ማፍራቱ ገባ፡፡ ገንዘብ እያፈራ ሲሄድም ንግዱ እየገባው ነበር፡፡ ነገር ግን ንግዱን እንዴት ማስተዳደር እንዳለበት፤ በተለይ የዓለም ገበያን የመከታተል፤ የቡና ንግድን የዓለም ገበያ ችግሮች ለይቶ አለማወቅና፣ ቡና የዓለም ገበያ ተፅዕኖ እንዳለበት እንዲሁም የሚወሰነውም በዓለም ገበያ ስለመሆኑ ብዙም ግንዛቤ ባለመኖሩ ችግሩ የመጣው፡፡ ይህንን ለማስጨበጥ ቢሞከርም ለመመለስ አልተቻለም፡፡ ቡና ያተርፋል የሚል እምነት ብቻ ይዞ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ በንግድ ዙሪያ ያለው የግንዛቤ ችግር ነበረበት ያልኩት፡፡ በዚህ ምክንያት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በቡና ማቅረብ ሥራ ላይ ዕንግዳ ነበርን ብለዋል፡፡ በወቅቱ ብድሩን የሚሰጧችሁ ባንኮች አያማክራችሁም ነበር ማለት ነው? ባለሙያዎችስ አያግዛችሁም ነበር?

አቶ ዘሪሁን፡- ከአበዳሪ ባንኮች ዋናው ልማት ባንክ ነበር፡፡ መጀመሪያው ላይ ባንኩ ይህንን ይሠራ ነበር፡፡ ያማክር ነበር፡፡ ከ100 እስከ 200 የሚሆኑ መፈልፈያዎች በሉበት  ሁሉንም ተበዳሪ ለማማከር ግን አቅም ይጠይቃል፡፡ በየቅርንጫፉ የሚመድበው ሁለትና ሦስት ሰዎችን ስለነበር ሁሉንም መከታተል አይችልም፡፡ የገቢና ወጪ ሥርዓቱን ከመመልከት የዘለለ አልነበረም፡፡ በኋላ ላይ የብድሩ መክፈያ ጊዜ ደርሷል ከማለት ያለፈ የባንኮች እገዛ አልነበረም ሊባል የሚችልበት ደረጃ ላይ ተደረሰ፡፡ እንዲህ ባለው ሁኔታ ጭምር ነው ወደ ኪሳራ የተገባው፡፡ መንግሥትን እነዚህ ችግሮች አሉብን፣ አንዴ ስንመታ መነሳት አልቻልንምና ደግፉን ወደ ማለት የገባነው፡፡ ቡና ሲሰጥህ ዳጐስ ያለ ነገር ያመጣል፡፡ ሲያከስርህም የዚያን ያህል ይወስድብሃል፡፡ ስለዚህ ከተመታህ በኋላ አስቸጋሪ ነው፡፡ ለመመለስም እንደገና ቡና መሥራት አለብህ፡፡

ስለዚህ ቀደም ብሎ በነበረው አሠራር ስንከስር መፈልፈያዎቹን ልማት ባንክ ይረከባቸውና በሃራጅ ይሸጣቸዋል፡፡ በሃራጅ ሲሸጥ ደግሞ ቡና አቅራቢው ገንዘብ በእጁ ስላልነበረው ንብረቱን ማስጣል አይችልም፡፡ ባልተጠበቀ መንገድ በሚፈጠር ኪሳራ ለባንክ ብድሩን መክፈል ባለመቻሉ ለማስያዣ የተጠቀመበት ንብረት ከእጁ እየወጣ ሄደ፡፡ ሀብቱም በዚሁ ሥርዓት የመጣ ነውና አሁንም ቡና አቅራቢው ተደግፎ መንግሥት የሆነ ነገር አድርጐለት የክህሎትም የፋይናንስም ድጋፍ ተደርጐለት ከችግሩ መውጣት አለበት ብለን ሐሳብ አቀረብን፡፡ ይህንን ሐሳብ ስናቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡ መመሪያ ተሰጠን፡፡  

ሪፖርተር፡- ምን ዓይነት መመሪያ ነበር የተሰጠላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- ባንኮች ብድሮቹን አስታመው ተበዳሪዎቹን ደግፈው ከገቡበት ችግር እንዲያወጡ ማለት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በሰጡት መመሪያ መሠረት በዚያን ወቅት የተፈጠረብንን ችግር አለፍነው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ መመሪያ በወቅቱ ያለባችሁን ብድር መክፈል አስቻላችሁ? መፍትሔስ ተገኘ?

አቶ ዘሪሁን፡- የነበረብንን ብድር አስታመሙ፡፡ ተጨማሪ ዋስትና አቅርቡ እየተባለም የሥራ ማስኬጃ ተሰጠ፡፡ ማኅበሩም ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በመሆን መቆጣጠርና የግዥ ሥርዓቱን መከታተል ጀመረ፡፡ ነፃ ገበያ ነው ቢባልም ግብይቱ የዓለም ገበያን መሠረት ያደረገ ስለሆነና ዋጋውም ሊዋዥቅ ስለሚችል መረጃዎችን እየተከታተልን በዚያ መሠረት መሄድ አለብን ብለን እየሠራን ነበር፡፡ በዚህም ማንሰራራት ተቻለ፡፡ ነገር ግን ልማት ባንክ ቀስ በቀስ እየወጣ መጣ፡፡

ሪፖርተር፡- ልማት ባንክ የወጣው ለቡና ሥራ ከሚሰጠው ብድር ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎ፡፡ ልማት ባንክ ለትልልቅ ኢንዱስትሪዎች ብድር ወደ መስጠቱ ይሂድ ተባለ፡፡ የቡና አቅራቢዎች ተበዳሪዎችን የግል ባንኮች ይረከቡ ተባለ፡፡ ይህ ሲሆን ደግሞ የግል ባንኮች ብድር ለመስጠት ማስያዣ ይፈልጋሉ፡፡ ከልማት ባንክ ስንበደር መፈልፈያውን ብቻ በማስያዝ 400 ሺሕ ብር ይሰጡን ነበር፡፡ ተጨማሪ ማስያዣ ካለህ ደግሞ የተወሰነ ገንዘብ ይጨምርልሃል፡፡ ሥራው የሚፈልገውን ያህል ገንዘብ ነው የሚሰጥህ፡፡ ስለዚህ የእኛ ብድሮች ወደ ግል ባንኮች ሲዛወሩ ማስያዣና ሥራውን የሚገልጽ ፈቃድ ያቀረበ በሙሉ ተበዳሪው ያቀረበው ዝርዝር ለቡናው ምን ያህል ገንዘብ ያስፈልገዋል? ሳይባል ከቡናም ውጭ ላለው ሥራውም ገንዘብ በብዛት መስጠት ተጀመረ፡፡

ሪፖርተር፡- ለቡና ተብሎ የተሰጠ ብድር ለሌላ ሥራ እየዋለ ነበር ማለት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ለቡና ተብሎ የተሰጠ ለሌላ የዋለም አለ፡፡ እዚህ ላይ አላግባብ የተደረገ ነገር አለ፡፡ የግል ባንኮች ዋና ዓላማቸው ትርፍ ነው፡፡ በሕዝብ ገንዘብ የተቋቋሙ ናቸው፡፡ ባለ አክሲዮኖች አሏቸው በየዓመቱ ትርፍ ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን ሌሎች ነገሮችን ከግምት ውስጥ አላስገቡም፡፡ በማበደር ብዙ ትርፍ ታገኛለህ፡፡ በዚህ አመለካከት ነው ሲሄዱ የነበሩት፡፡ ብዙ ዋስትና ያቀረበ ብዙ ገንዘብ ይበደራል፡፡ የእሸት ቡና ግዥ ዋጋ እየጨመረ ሲሄድ ብዙ ቡና ለመሰብሰብ ብዙ ገንዘብ ያስፈልግሃል፡፡ የአንድ ኪሎ እሸት ቡና ዋጋ ከ50 ሣንቲም ተነስቶ ሰባትና ስምንት ብር ገባ፡፡ ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ደግሞ ብዙ ማስያዣ ያስፈልገሃል፡፡ ይህ አካሄድ ግን አንድ ነገር አመጣ፡፡ አቅራቢው ብዙ ገንዘብ ለመበደር የግድ ለብድሩ ማስያዣ የሚሆን ንብረት እንደሚያስፈልገው በመረዳት በእጁ ያለውን ገንዘብ ለባንክ ማስያዣ ይሆነኛል በማለት ቤት ወደ መገንባት ገባ፡፡ ቡና አቅራቢዎቹ በየዓመቱ ከሚያገኙት ገንዘብ ወደ ከተማ መጥተው ቤት መገንባት ጀመሩ፡፡ ግንባታውን የሚያከናውኑት  በዋስትና ለማስያዝ ነው፡፡ ነገር ግን በእጃቸው ያለውም ንብረት ለዋስትና አልበቃ ሲላቸው የቤተሰቦቻቸውን፣ የጓደኞቻቸውን ቤቶች እያስያዙ ለሥራ ማስኬጃ ዕጥረት ማቃለያነት አዋሏቸው፡፡

ሪፖርተር፡- በአካባቢያችሁ ያሉ አቅራቢዎች የሌሎች ሰዎችን ንብረት ለብድር  ማስያዣነት ሲያቀርቡ ለባለንብረቱ ኮሚሽን እንደሚከፍሉም ይነገራል፡፡

አቶ ዘሪሁን፡- አዎ፡፡ ቤት ላስያዘለት ሰው ከሚበደረው ገንዘብ ላይ በማስላት ኮሚሽን ይከፍላል፡፡ በቀረው ደግሞ ይሠራል፡፡ ይህ አካሄድ መጠላለፍ ፈጥሯል፡፡ በሌላ በኩል መንግሥት ቡናው ተሰብስቦ ለማዕከላዊ ገበያ ይቀርብለታል፤ ይሸጣል፡፡ ዶላር ይመጣል፡፡ ባንክ በምንም ዓይነት መንገድ ይሁን ወለዱን ያገኛል፡፡ መሃል ላይ ግን ቡና አቅራቢው በየጊዜው በሚመጣበት ኪሣራ እየተመታ ሄደ፡፡ ከዚያም ከማይወጣበት ችግር ውስጥ ገባ፡፡

ሪፖርተር፡- ችግሩ እየተባባሰ የመጣው ከመቼ ጀምሮ ነው ማለት ይቻላል?

አቶ ዘሪሁን፡- ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ነው፡፡ በመሃልም የመንገዳገድ ነገር ነበር፡፡ በእኛ ጥናት ወደዚህ ችግር የከተቱን የተለያዩ ምክንያቶች ሊሆኑ አንዱ ለቡና ትኩረት አለመሰጠቱ ነው፡፡ ቡና ከታች ሲሰበሰብ ለግዥው የሚሆን የሥራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት እንዴት ይቀረፋል ተብሎ አለመሠራቱ በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ መንግሥት በሚፈልገው መጠን ቡና እየቀረበለት ቢሆንም ታች ያለው ችግር አልታየም ነበር፡፡ እኛም ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ የሥራ ማስኬጃ እጥረት ስለመኖሩ በተደጋጋሚ ስንገልጽ ነበር፡፡ የአንድ ኪሎ እሸት ቡና መግዣ 10 ብር በሚደርስበት ጊዜ ግዥ ፈጽሞ ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ ወደማይችልበት ደረጃ ይደርሳል ብለን ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ ለላኪዎች እንደሚደረገው በአነስተኛ ወለድ ለእሸት ቡና መግዣ ይሆን ዘንድ የመፈልፈያዎቹ ግምት በትልቅ ዋጋ ተሰልቶ ብድር ይፈቀድ ብለናል፡፡ መንግሥት ቁጥጥር እያደረገ ይሠራ ብለናል፤ ትኩረት ግን አላገኘም፡፡ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ስናሳስብ ቆየን፡፡ ሌላው የምርታማነት ችግር ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የምርታማነት ችግር ሲሉ?

አቶ ዘሪሁን፡- ምርታማ አለመሆን ነው፡፡ ትኩረት አልተሰጠውም፡፡ ቡና አራት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ነው ያለው፡፡ በፊት ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ነበር፡፡ ደርግ ቡናና ሻይ ሚኒስቴር አቋቁሞ ነበር፡፡ ኢሕአዴግ ከገባ በኋላም ለተወሰነ ጊዜ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ተብሎ ሲሠራ ነበር፡፡ በኋላ ቡና ግብርና ሚኒስቴር ውስጥ ገባ፡፡ እንደ ማንኛውም ሰብል መታየት አለበት ተብሎ የተደረገ ነው፡፡ በእኛ እምነት ግን ቡና እንደ ማንኛውም ሰብል መታየት የለበትም፡፡

ሪፖርተር፡- ቡና እንዲህ በተለየ መታየት አለበት ስትሉ ምን ምክንያት ኖሯችሁ ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ምክንያቱም ቡና ዶላር የማምጣት አቅሙ በየጊዜው እየጨመረ ነው፡፡ በምርቱም ሆነ በገበያ ባህሪው ልዩ እንክብካቤ ያስፈልገዋል፤ ባለቤት ይፈልጋል፡፡ ጥያቄያችንም ይሄ ነው፡፡ ጥያቄያችን ስናቀርብ ቆይተናል፡፡ በዚህ መካከል የጠቀስኩልህ ቀውስ ተፈጠረ፡፡ የቀውሱ መፈጠር ደግሞ የሥራ ማስኬጃ ካፒታል እጥረት በማስከተሉ ቡና አቅራቢው የአማቹን፣ የጓደኞቹን፣ የዘመዶቹን በአጠቃላይ የሦስተኛ ወገን ንብረትን ሆነው በዋስትና የተያዙ ቤቶች በሙሉ ብድሩ መክፈል ሳይችል ሲቀር ወደ ሃራጅ ሽያጭ ተገባ፡፡ ታውቃለህ በዚህ ችግር በሐዋሳ ከተማ ብቻ ወደ 2,400 ቤቶች በብድር ዋስትና ምክንያት ተይዘዋል፡፡ እነዚህ ቤቶች በሙሉ ግን የቡና ነጋዴው አይደሉም፡፡ የሦስተኛ ወገን ብረቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ከ2,400 በላይ ቤቶች ከተሸጡ ከ10 ሺሕ በላይ ሰዎች ይፈናቀላሉ ማለት ነው፡፡ መፈናቀሉም ተጀምሮ ነበር፡፡ ምክንያቱም ባንኮች ያበደሩትን ገንዘብ ለማስመለስ ቤቶቹን ወደመሸጡ ገብተው ነበር፡፡ የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ደግሞ ባንኮች አንድን ብድር ከሦስት ጊዜ በላይ ማራዘም አልችሉም ይላል፡፡ ስለዚህ ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ባንኮች ብድሩን ሦስት ጊዜ ቢያራዝሙ 2006 ላይ የተራዘው ጊዜ አለቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ንብረቶቹን ለማትረፍ የሚያስችል አቅም ሊፈጠር አልተቻለም፡፡

ከ2005 እስከ 2006 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ችግሩ ከባድ በመሆኑ ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ብሔራዊ ባንክን በማስፈቀድ ተጨማሪ ማራዘሚያ ጊዜ ተጠየቀ፡፡ ተፈቀደ፡፡ አሁንም ግን ከቀውሱ መውጣት አልተቻለም፡፡ ስለዚህ ቀውሱ ካልተስተካከለ የብድር መክፈያውን ጊዜ ማራዘም መፍትሔ አይሆንም ማለት ነው፡፡

ሌላ ሰው ንብረቱን ሊያሲዝልህ አለመፈለግም መጣ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን ልትነግድ የማትችልበት ደረጃ ላይ ተደረሰ፡፡ ባንክም ያንተን ብድር ከሦስት ጊዜ በላይ ካራዘመ በኋላ ብድር አይሰጥም፡፡ ስለዚህ ንብረቶቹ ሊሸጡ ሆነ፡፡ ይህ ክስተት ሐዋሳን የባንክ ከተማ አድርጓታል፡፡ አሁን እየተፈናቀለ ያለው ነጋዴው ብቻ አይደለም፡፡ ኅብረተሰቡ ነው፡፡ ለክልላችን ፖለቲካዊና ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ነው፡፡ የተፈጠረውን ቀውስ ከመንግሥት ጋር በመነጋገር ለመቅረፍ ኃላፊነት አለብን፡፡ መፍትሔ ይሆናል የተባለ ሐሳብም ተፈጠረ፡፡ ማራዘም መፍትሔ አይሆንም፡፡ ከ2004 እስከ 2006 ብድሩ እየተራዘመ መጣ፡፡ ነገር ግን ብድርን ከሦስት ጊዜ በላይ ማራዘም ስለማይቻል የክልሉ መንግሥትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባደረጉልን ድጋፍ እንደገና ባንኮች የተበዳሪዎችን ብድር መክፈያ ጊዜ እንዲያራዝሙ ፈቀዱ፡፡

ሪፖርተር፡- ከባንኰቹ የተበደራችሁት ምን ያህል ይሆናል?

አቶ ዘሪሁን፡- የብድሩ መጠን ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- በአጠቃላይ የቡና አቅራቢዎች ለወሰዱት ብድር ያስያዟቸው ንብረቶች መጠንስ ምን ያህል ይሆናል?

አቶ ዘሪሁን፡- ወደ ሁለት ቢሊዮን ብር ይደርሳል፡፡

ሪፖርተር፡-የተያዙት ቤቶች በሐዋሳ ብቻ ነው ወይስ ከሐዋሳ ውጭም አሉ?

አቶ ዘሪሁን፡- ከሐዋሳ ውጭ ያሉም አሉ፡፡ ዲላ ላይ አሉ፡፡ አለታ ወንዶና ሌሎች ቦታዎችም አሉ፡፡ ትልቁን ቁጥር የያዘው ግን የሐዋሳ ከተማ ነው፡፡ አሁን ቀውሱን እጅግ አሳሳቢና አስፈሪ አድርጐት የነበረው በሐዋሳ ከተማ በባንክ ዕዳ የተያዙት ከ2,400 በላይ ቤቶች ጉዳይ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በተለያዩ ወቅቶች የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ተደርጐ ብድሩ ባለመክፈሉ የተሸጡ ቤቶችና ንብረቶች አሉ?

አቶ ዘሪሁን፡- የተሸጡ ንብረቶች አሉ፡፡ እስካሁን እንኳ 18 የቡና መፈልፈያዎችና 78 ቤቶች ተሸጠዋል፡፡

ሪፖርተር፡- ማኅበራችሁ ጉዳዩን አጠንክሮ በመያዝ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያልታሰበ ውሳኔ እንደወሰን አድርጓል እየተባለ ነው፡፡ ብድር እንዲራዘምላችሁ የሚያስችል የተለየ ዕድል እንዲሰጣችሁ ተደርጓል፡፡ ብሔራዊ ባንክ እናንተን ለማገዝ ብሎ ከመመሪያ ውጭ ውሳኔ እስከማስተላለፍ የደረሰው ከችግር ትወጣላችሁ ብሎ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህንን ያህል መስዋዕትነት ከተከፈለላችሁ በኋላስ ብድሩን ከፍላችሁ ከገባችሁበት ቀውስ ወጥታችሁ ውጤታማ የምትሆኑት እንዴት ነው?

አቶ ዘሪሁን፡- ተመሳሳይ ችግር ከዚህ ቀደም በማኅበራት ላይ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ብድር ዋስትና አይጠይቃቸውም፡፡ መንግሥት ዋስትና ይወስዳል፡፡ ምክንያቱም በኅብረት የተደራጁ አርሶ አደሮች ናቸው ተብሎ ስለሚታሰብ መፈልፈያው ብቻ ይያዝና ቀሪው ገንዘብ የመግዛት አቅማቸው በፈቀደው መሠረት በመንግሥት ዋስትና አማካይነት ገንዘብ ይበደራሉ፡፡ እንደዚህም ተደርጐላቸው ችግር ውስጥ ገቡ ለምን ሲባል በቂ የመንግሥት ክትትልና ድጋፍ ስላልነበር፡፡ እንዲሁም ሥራውን የሚመሩ ሰዎች ብቃትና ሥራውን በአግባቡ ባለመያዛቸው ነው፡፡ ይህ እንደታወቀ ማኅበራቱ ብድሩን እንዲያገኙ መንግሥት ዋስትና ገብቷልና መንግሥት ገንዘቡን ክፈል ሲባል የክልሉ መንግሥት አጣብቂኝ ውስጥ ገባ፡፡ ምክንያቱም የተበደሩት የአገር ገንዘብ ነው፡፡ ልማት ባንክም ቢያበድር ገንዘቡ የሕዝብ ነው፡፡ ስለዚህ ምን እናድርግ ለሚለው መንግሥት ሌላ ዋስትና ገብቶ አብሮና ተከታትሎ እንዲሠራ፤ ሌላው ቀርቶ ከባንክ የሚያወጡት ገንዘብ በትክክል ቡና ላይ ስለመዋሉ እያረጋገጡ ደግፈው በመሄዳቸው ዛሬ የይርጋ ጨፌና የሲዳማ ዩኒየኖች ከፍተኛ ገንዘብ ያላቸው በቢሊዮን የሚቆጠር ሀብት እንዲያፈሩ ያደረጋቸው መንግሥት ነው፡፡

አሁንም ለእኛ ተብሎ የተወሰነው ውሳኔ ዝም ብሎ አይደለም፡፡ ብድር ይራዘም፣ ንብረታችን አይሸጥ ሲባል ለሁለት ዓመት ይህንን ጉዳይ የሚከታተል ኮሚቴ እንዲሰየም ተደርጐ ነው፡፡ ከአበዳሪ የፋይናንስ ተቋማት፣ ከመንግሥት፣ ከቡና አቅራቢው መንግሥት የሚመርጠው አምስት አባላት ያለበት ኮሚቴ አለ፡፡ ሥልጠና ይሰጣል፡፡ የገንዘብ ፍሰቱ ቁጥጥር ይደረግበታል፡፡ እስከዛሬ የነበው አንዱ ክፍት ክትትልና ድጋፍ አለማድረግ ነበር፡፡ ምክንያቱም ገንዘብ ይሰጡና የብድር መክፈያ ጊዜ ሲደርስ ብቻ ነው ባንኰቹ የሚደውሉት፡፡ ቢሯቸው ሆነው ገበያው እንዴት ነው የሚቆጣጠሩት፡፡ በዚያ ገንዘብ ተበዳሪው መኪና ይግዛበት፣ ቤት ይሥራበት ወይም ሌላ ነገር ያድርግበት የመከታተልና የመደገፍ ሥራ አልነበረም፡፡ አሁን ግን እንዲህ ዓይነቱ ሥራዎች ይሠራሉ፡፡ 

ሪፖርተር፡- እዚህ ላይ መሠረታዊ የሆነ ሌላም ጉዳይ አለ፡፡ ችግሩ ባንኮች ላይ ብቻ እንዲነጣጠር ማድረጉ ተገቢ የማይሆንበት ምክንያት አለ፡፡ በእናንተ ዘርፍ ብቻም ሳይሆን በሌሎችም በኩል ተበዳሪዎች የወሰዱትን ገንዘብ ከተበደሩበት ዓላማ ውጪ ለሌላ ነገር ሲያውሉ ይታያሉ፡፡ በቡና አቅራቢዎች ውስጥም  ብድርን ለሌላ ዓላማ እያዋሉ ተቸግሬያለሁ የሚሉ ባንኰችም አሉ፡፡ እንዲያውም አንዱ ችግር ይህ ስለመሆኑ ይታመናል፡፡

አቶ ዘሪሁን፡- አዎን አሉ፡፡ ቡና ያመጣው ኪሣራ ብቻ አይደለም፡፡ አስተዳደራዊ ጉድለትም አለ፡፡ ይኼ ደግሞ የኋላ ቀርነት ውጤት ነው ብዬሃለሁ፡፡ ችግር በራሱ እንድትገዛ ያደርጋል፡፡ አሁን እንዲህ ዓይነት ክፍተቶች ይደፈናሉ፡፡

ሪፖርተር፡- ስንት ዓመት ነው ኋላቀር በሆነ የንግድ አሠራር የተፈጠረ ችግር ነው እየተባለ ምክንያት የሚቀርበው? ቡና አንድ ዓመት ከሰጠ በቀጣዩ ላይሰጥ ይችላል፡፡ ከዚህ ቀውስ ለመውጣት ምን ትጠብቃላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- እንዲህ የሚባለው እስከዚህች ምዕራፍ ብቻ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ይህ የመጨረሻችን ነው ትላላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- አዎ፡፡ ይህንን የምንለው እኛ ይህንን ችግር ለክልል መንግሥት አሳውቀን፣ በማውገዝ ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት ጠይቀናል፡፡ ውሳኔውን ሰጥቶናል፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው የእኛ ኃላፊነት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ምን ታደርጋላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- መንግሥት ይህንን ውሳኔ የወሰነልን ከሕጉ በጣም ርቆ በመምጣት ነው፡፡ ሕገ ጥሶ ሲወስን ግን ምክንያት ነበረው፡፡ ይህም ሕዝባዊ መንግሥት ስለሆነ ነው፡፡ አስረግጬ ልነግርህ የምፈልገው የሚያዳምጥ መንግሥት ያለን በመሆኑ የተወሰነ ውሳኔ መሆኑን ነው፡፡ ይህንን ዕድል መስጠቱ ራሱ ሕዝባዊነት ነው፡፡ ይሄ ውሳኔ ሲወሰን የብሔራዊ ባንክ ኃላፊ እስከመቼ ነው እንዲህ የምንደግፋችሁ ብለውናል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ወደዚህ ውሳኔ ለመግባት መንግሥት ምን ያህል እንደተጨነቀ ነው፡፡ ወደዚህ ውሳኔ ባይገባ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐች እንደሚፈናቀሉ በመረዳት ነው፡፡ ለነጋዴው ብቻ ተብሎ አይደለም፡፡ በዚህ ችግር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ስለተፈጠረና ከዚህም በላይ እንዳይሄድ ስለታሰበ ነው፡፡ ይህንን ዕድል በአግባቡ ሠርተንበት ውጤት እንዲመጣ የተወሰነ ነው፡፡ ይህንን ተአምራዊ ውሳኔና ባገኘነው ዕድል በመጠቀም የሚያስፈልገውን ነገር ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ሠርተን መለወጥ ነው፡፡ አጥፊዎችንም እንቆጣጠራለን፡፡ አላስፈላጊ ውድድሮችንም እየተዋጋን እንሠራለን፡፡ በተሰጠን ዕድል ለመጠቀም ለአባሎቻችን ሥልጠና እንሰጣለን፡፡ 

ሪፖርተር፡- ይህ ውሳኔ ግን ብደር መክፈል የሚችለውንም የማይችለውንም ያጠቃልላል፡፡ ይህ እንዴት ይለያል?

አቶ ዘሪሁን፡- አሁን የምናስተምረው ብድር የመክፈል አቅም ያለው ብድሩን ቢከፍል ዕዳውን ነው የሚቀንሰው ብለን ነው፡፡ ችግር ያለባቸውና የሌለባቸውን ለይተን እናውቃለን፡፡

ሪፖርተር፡- በማኅራችሁ የዚህ ዕድል ተጠቃሚዎች ምን ያህል ትሆናላችሁ?

አቶ ዘሪሁን፡- 250 አካባቢ እንሆናለን፡፡ አባሎቻችን 400 አካባቢ ናቸው፡፡ ዕድሉ እነሱንም ይመለከታል፡፡

ሪፖርተር፡- በሐዋሳ ከተማ ውስጥ ከ2,400 በላይ ቤቶችና ሕንፃዎች በባንክ ዕዳ ከተያዙ የእናንተ ቁጥርና የተያዘው ንብረት መጠን ግን አይመጣጠንም?

አቶ ዘሪሁን፡- ምን መሰለህ፡፡ አንዱ ተበዳሪ ሰው እኮ የ30 ሰው ቤት ነው የሚያስይዘው፡፡ ለምሳሌ 10 ሚሊዮን ብር ለመበደር ከፈለግህ ሁለት ቤቶች ለባንክ ማስያዣነት ብታቀርብ አይበቃም፡፡ ስለዚህ ባንኩ አንዱን ቤት ለማስያዣነት ለመጠቀም የሚያወጣው ግምት አንድ ሚሊዮን ብር ከሆነ አሥር ሚሊዮን ብር ለመበደር አሥር ቤቶች ያስፈልጉሃል ማለት ነው፡፡ 38 ቤት ያስያዘ ሰው አለ፡፡ የ38 ሰዎችን ቤት አስይዞ የተበደረው ብድሩን ባለመክፈሉ ከስሯል፡፡ ቤቶቹም ለጨረታ ቀርበው ነበር፡፡ ለዚህ ነው መንግሥት የወሰነው ውሳኔ ትክክለኛ የሆነው፡፡ ሕዝባዊ መንግሥት ነው የምልህም ለዚህ ነው፡፡ ይህ ባይሆን ኑሮ ዛሬ የለንም ነበር፡፡ ከከፋ ነገር ወጥተናል፡፡ በምድር ላይ ሊሰጠን የሚችለው በላይ ዕድል ስለተሰጠን አሟጠን እንጠቀምበታለን፡፡ 

Standard (Image)

አደገኛ አትክልቶች

$
0
0

በድልድዩና በወንዙ መካከል ያለው ርቀት ከፍተኛ ቢሆንም ጥቂት የማይባሉ አባ ወራዎች ከድልድዩ ሥር በወንዙ ዙሪያ ሰፍረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ከመኖሪያ ቤቶቹ ፊት ለፊት በሚገኘውና መጠነኛ ስፋት ባለው ቦታ ላይ እንደ ቆስጣ፣ ሠላጣ፣ ጥቅል ጐመን፣ የሀበሻ ጐመን፣ ቃሪያ፣ ቲማቲም ያሉ የጓሮ አትክልቶችን ያለማሉ፡፡ የወንዙ ስያሜ ቡልቡላ ይባላል፡፡

የቡልቡላ ወንዝ እንደ አብዛኛዎቹ የአዲስ አበባ ወንዞች ከየኢንዱስትሪውና ከየመኖሪያ ቤቱ በሚለቀቁ ፍሳሾች ተበክሏል፡፡ በውስጡ ደረቅ ቆሻሻ፣ ላስቲክና ሌሎችንም ይዟል፡፡ ተፈጥሯዊ ቀለሙም በጥቁር ተተክቷል፡፡ መጠፎ ጠረንም አለው፡፡ በዙሪያው የሠፈሩት አባ ወራዎች ሁኔታው ብዙም የሚያስጨንቃቸው አይመስሉም፡፡ እንዲያውም ከወንዙ ጎን ባለው ቦታ ላይ የሚያለሟቸውን አትክልቶችና ፍራፍሬዎች ውኃ የሚያጠጡት ከወንዙ እየቀዱ ነው፡፡ የሚያመርቷቸውን አትክልቶች በኪሎ ከአምስት እስከ 11 ብር በማስከፈል ለቸርቻሪዎች ያስረክባሉ፡፡ በዚህ መልኩ ኑሯቸውን ሲገፉ ዓመታት አልፈዋል፡፡ ነገ ግን ዋጋ ያስከፍላቸው ጀምሯል፡፡ የሚጠቀሙበት የወንዝ ውኃ በቆዳቸው ላይ የጤና ችግር እየፈጠረ ይገኛል፡፡ በሚያለሙት አትክልት ላይም ችግር ሊፈጥር እንደሚችል ጠርጥረዋል፡፡ ነገር ግን የወንዙን ውኃ ከመጠቀም ሉቦዝኑ አልቻሉም፡፡     

ትንንሽና ትልልቆቹን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ከ70 በላይ ወንዞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እንደ ቡልቡላ ያሉ እነዚህ ወንዞች ለተለያዩ ግልጋሎቶች መዋል ሲችሉ በተገቢው መንገድ ንጽሕናቸው ባለመጠበቁ ግን ለአካባቢና ለሰዎች ጤና ጠንቅ አድርጓቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ ወንዞች ከፋብሪካዎችና ከተለያዩ ተቋማት በሚወጡ ኬሚካሎች የተበከሉ ናቸው፡፡ ከየቤቱ የሚወጣ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዞች መቀላቀሉም አደገኛነታቸውን አባብሶታል፡፡ ይሁንና በከተማው ባለው የቦታ ጥበት ምክንያት አማራጭ ያጡ ብዙዎች በወንዞቹ ዙሪያ ሰፍረው የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን ይመራሉ፡፡ አትክልትና ፍራፍሬም ያለማሉ፡፡ ይህ ተግባር ግን በነዋሪዎች ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ በከተማ ግብርና የተሰማሩ ድርጅቶችም የግብርናው አካል ናቸው፡፡ ከቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በተገኘ መረጃ መሠረት፣ በከተማዋ 112 ፈቃድ ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬ አልሚዎች ይገኛሉ፡፡ አብዛኛዎቹም በእነዚህ በተበከሉ ወንዞች አካባቢ የሚያለሙ ናቸው፡፡

‹‹ወንዞቹ ከመጠን ባለፈ ተበክለዋል፡፡ ለእርሻም ሆነ ለሌሎች አገልግሎቶች መዋል አይችሉም፤›› በማለት ከዚህ ቀደም አስተያየታቸውን የገለጹት፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ሳይንስ ማዕከል ተባባሪ ፕሮፌሰርና በአዲስ አበባ ወንዞችና ወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት የብክለትና ሳኒቴሽን ፕሮግራም መሪ ዶ/ር ሥዩም ለታ ናቸው፡፡

እንደ ዶ/ር ሥዩም ገለጻ፣ የከተማዋ የላይኛው ተፋሰሶች በመጠን አነስተኛ ናቸው፡፡ በተለይም በበጋ ወቅት የተፋሰሶቹ መጠን የለም ለማለት በሚያስደፍር መጠን ይቀንሳሉ፡፡ የታችኛው ተፋሰሶች በተቃራኒው ሙሉ ይሆናሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ከየቤቱና ከየተቋማቱ የሚለቀቁ ፍሳሾች ወደየተፋሰሶቹ ስለሚገቡ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ዓመቱን ሙሉ የሚፈሱ የሚመስሉት ወንዞች አደገኛ የሚባሉ ቢሆኑም በታችኛው ተፋሰስ በተለይም በትንሹ አቃቂ እና በፒኮክ ወንዝ አካባቢ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻ በስፋት ሲለማ ይታያል፡፡

በዚህ መልኩ የሚለሙት አትክልትና ፍራፍሬዎች ‹‹ሄቪሜታልስ››፣ የተለያዩ ኬሚካሎችና ለጤና ጐጂ ተህዋስያንን በውስጣቸው ይይዛሉ፡፡ ይህም በተመጋቢዎች ላይ ከፍተኛ የጤና ቀውስ ይፈጥራል፡፡ ‹‹እኛው ብክለቱን ስንልክ እነሱ ተቀብለው በምርት መልሰው ይልኩልናል፤›› የሚሉት ዶክተር ሥዩም፣ ሦስት አራተኛ የሚሆነው የከተማው የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ከዚህ እንደሚገኝ በመግለጽ ጉዳዩ የተለየ ትኩረት እንደሚሻ አሳስበዋል፡፡

ለጤና ካላቸው ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በበርካቶች ለምግብነት የሚመርጧቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ዝርያዎች በአገሪቱ በስፋት ይገኛሉ፡፡ በተለይም በአፅዋማት ወቅት በስፋት ለምግብነት ስለሚውሉ፣ የሚኖራቸው ገበያም የደራ ነው፡፡ በየፍራፍሬ መደብሩ ለሽያጭ የሚቀርቡ የአትክልቶችና ፍራፍሬዎች ዓይነትና መጠንም ከወትሮው በተለየ ይጨምራል፡፡ አትክልት ብቻ የሚመገቡ (ቬጂቴሪያን) ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያው እንደ ፆሙ ወቅት ባይሆንም ሞቅ እንዲል አድርጐታል፡፡

ሰለሞን ይባላል (ስሙ ተቀይሯል)፡፡ ከዚህ በፊት የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ያዘወትር ነበር፡፡ ይህም ተክለ ሰውነቱ የተስተካከለ እንዲሆን ረድቶታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከሥራ ጋር ስላልተመቸው ስፖርቱን አቋርጧል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሰውነት ክብደቱ እይጨመረ ሄደ፡፡ ክብደቱም በአንድ ጊዜ ከ73 ኪሎ ወደ 90 ኪሎ ደረሰ፡፡

ሁኔታው ያሳሰበው ሰለሞን፣ ክብደቱን ለመቆጣጠር በእግር መጓዝ፣ አትክልትና ፍራፍሬ መመገብን የዕለት ተግባሩ አደረገ፡፡ የሀበሻ ጐመን፣ ቆስጣ፣ ሠላጣ፣ ቲማቲም፣ አቮካዶ እና ሌሎች ፍራፍሬዎችን ገዝቶ የሚመገበው በሰፈሩ ከሚገኝ የአትክልትና ፍራፍሬ መደብር ነው፡፡ ‹‹ከገጠር አምጥተው ለቸርቻሪዎቹ የሚሸጡት ገበሬዎች ናቸው፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ዙሪያ እንደሚመረትም አውቃለሁ፤›› በማለት አብዛኛዎቹ በከተማ ውስጥ የሚለሙት ፍራፍሬዎችና አትክልቶች በተበከሉ ወንዞች ውኃ መሆኑ አሳስቦት እንደማያውቅ በሚያመለክት ስሜት ይናገራል፡፡

በከተማዋ አብላጫው የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ የሚካሄድበት አትክልት ተራም አብዛኛውን ምርት የሚቀርብለት እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚያለሙ አርሶ አደሮችና ተቋማት ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በተገኘው መረጃ መሠረት፣ በከተማው 112 ፈቃድ ያላቸው የአትክልትና ፍራፍሬ ጅምላ አከፋፋዮችና 9,488 በችርቻሮ ንግድ ሥራ የተሰማሩ ሰዎች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል አብዛኛዎቹ በአትክልት ተራ የሚነግዱ ናቸው፡፡ በከተማው የሚካሄደው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በተበከሉ ወንዞች ዙሪያ መሆኑ ከሚፈጥረው የጤና ቀውስ ባለፈ በጣዕምም ሆነ በመልክ በሌላ አካባቢ ከሚመረቱ አትክልቶች በቀላሉ እንደሚለይ የአትክልት ተራ ነጋዴዎች ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ልዩነቱን ነገሬ የሚሉ በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው፡፡ ብዙዎቹ አትራፊ እስከሆነ ድረስ ከየትም ቢመጣ ግድ ያላቸው አይመስሉም፡፡

‹‹አትክልትና ፍሬፍሬ በከተማዋ በአራቱም ማዕዘን ይመጣል፡፡ ነገር ግን በትክክል ከየት ቦታ እንደሚመጣ፣ በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚመረት አላውቅም፤›› የሚለው የአትክልት ተራው ነጋዴ በዓሉ ሠይፈ ነው፡፡ መደብሩ በማንጐ፣ በብርትኳን፣ በፓፓያ፣ በቲማቲም፣ በቆስጣ፣ በሠላጣ፣ በአናናስ እና በሌሎችም የአትክልና ፍራፍሬ ዘሮች ተሞልቷል፡፡ መደብሩ አይጓደል እንጂ ምርቱ ከየትም ቢመጣ አያሳስበውም፡፡ የተመረተበትን ቦታ ጠይቆና አጣርቶ የሚሸምት ደንበኛም አጋጥሞት አያውቅም፡፡

ከጅምላ ነጋዴዎች ማንጐ በኪሎ 8 ብር ተቀብሎ እስከ 10 ብር ይሸጣል፡፡ ፓፓዬም በኪሎ 12 ብር በመግዛት 14 ብር እንደሚሸጥ ይናገራል፡፡ በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ከተሠማራ ዓመት ሆኖታል፡፡ አካባቢው ለንግድ ዓይነተኛ ቦታ በመሆኑ፣ በቀን የሚያገኘው ገቢ ጥሩ የሚባል ነው፡፡ በቀን እስከ 10,000 ብር ያገኛል፡፡

በአትክልት ተራ መነገድ ከጀመረ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ቴዎድሮስ ታረቀኝ ነው፡፡ ቴዎድሮስ ከበዓሉ በተለየ የፍራፍሬና የአትክልት ምርቶች ከየት አካባቢ እንደሚመጡ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ የሀበሻ ጐመን፣ ቆስጣና ሠላጣ ከዚሁ ከአዲስ አበባ በተለይም ከአቃቂና ከቡልቡላ እንደሚመጡ ይናገራል፡፡ ምርቱን አትክልት ተራ ድረስ የሚያቀርቡት ገበሬዎች በመሆናቸው ዋጋቸው ቅናሽ እንዳለው ይናገራል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሌላ አማራጭ መጠቀም ጀምሯል፡፡ ‹‹ከአዲስ አበባ ዙሪያ የሚመጡ ምርቶች በተበከሉ ወንዞች ዳር ስለሚመረቱ የተለያዩ የጤና ችግሮች እንደሚያስከትሉ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ደግሞም እኛ በራሳችን የምናያቸው ልዩነቶች አሉ፡፡ እዚህ የሚመረቱት ጣዕማቸው ደስ አይልም፡፡ ለምሳሌ እዚህ የሚመረተው ሠላጣ ቀጫጫና ተባዮች የበዙበት ነው፡፡ ገበያ ላይ የሚቀርበውም ከነሥሩ ተነቅሎ ነው፤›› የሚለው ቴዎድሮስ፣ አልፎ አልፎ ሠላጣ ከኮምቦልቻ፣ የሀበሻ ጐመን ከአሠላ እንደሚያስመጣ ይናገራል፡፡ ሌሎች እንደ ካሮት፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም፣ ድንች ያሉ ምርቶችን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚያመጡላቸው ጅምላ አከፋፋዮች አሉ፡፡

እንደ ቴዎድሮስ ገለጻ፣ በአትክልት ተራ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ጥቂት የማይባሉ ነጋዴዎች ለገበያ የሚያቀርቧቸውን ምርቶች የሚያስመጡት ከሌሎች ከተሞች ነው፡፡ ከሌላ ቦታ የሚመጡት ምርቶችም እዚህ ከሚመረቱት በጥራት የተሻሉ በመሆናቸው ዋጋቸው ወደድ ይላል፡፡ የተጠየቁትን ዋጋ የመክፈል አቅሙ ያላቸው ጥቂት ነጋዴዎች ብቻ ይገበዩዋቸዋል፡፡ የተቀሩት ገበያ ለሚያቀርቡት ምርት ብዙም ግድ የሌላቸው በብዛት ሕገወጥ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ነጋዴዎች ሙሉ ለሙሉ የሚያቀርቡት ምርት በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚመረቱትን ነው፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚመረቱ አትክልትና ፍራፍሬዎች ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው አመዝኗል፡፡ በጤና ላይ በማያደርሱት ቀውስ አደገኛ የሚባሉት ሄቪ ሜታልስ የሚባሉት ናቸው፡፡ ሶዲየም፣ ማግኒዚየም፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም፣ ክሮሚየም፣ አርሴኒክ፣ ካድሚየም፣ ኮፐር፣ ሊድ፣ ኒኬል፣ ዚንክ፣ ሜርኩሪ፣ ኮባልት፣ ሊድ ከሄቪሜታልስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እነዚህ ንጥረ ነገሮች በተወሰነ መጠን በሰውነት ውስጥ እንዲኖሩ ይገባል፡፡ ከመጠን በላይ በሚሆኑበት ጊዜ ግን ለጤና አደገኛ ይሆናሉ፡፡ የአፈር መሸርሸር፣ ጐርፍ፣ ከኢንዱስትሪ የሚወጡ ኬሚካል አዘል ፍሳሾችና ሌሎችም ንጥረ ነገሮቹ ከመጠን በላይ እንዲከሰቱ ምክንያት ናቸው፡፡ አርሴኒክ፣ ካድሚየም፣ ክሮሚየም፣ ኮፐር፣ ሊድ፣ ኒኬልና ዚንክ በፍሳሽ ውስጥ በስፋት ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች መካከል ይመደባሉ፡፡ የንጥረ ነገሮቹ ከመጠን ያለፈ ክምችት በሣንባ፣ በኩላሊት፣ በጉበት በጭንቅላት ላይ ጉዳት ይፈጥራል፡፡ አቅም ማነስ፣ የደም ችግርና ሌሎችም የጤና ቀውሶች በእነዚህ ንጥረ ነገሮች የሚከሰቱ ናቸው፡፡

እ.ኤ.አ. በ2007 የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ በቄራ፣ በፒኮክ፣ በአቃቂ፣ በመካኒሳ እንዲሁም በቡልቡላ አካባቢ በሚበቅሉ አትክልቶች ማለትም በጥቅል ጐመን፣ በካሮት፣ በሀበሻ ጐመን፣ በድንች፣ በሠላጣ እና በቆስጣ ውስጥ የንጥረ ነገሮቹ ከፍተኛ ክምችት ታይቷል፡፡ በተለይም በአቃቂ ወንዝ አካባቢ የሚበቅሉ አትክልቶች ላይ ከፍተኛ የኮባልት ክምችት መኖሩን፣ በቄራ አካባቢ የሚመረቱት ላይ ደግሞ ከፍተኛ የኒኬል፣ የኮፐር፣ የዚንክ፣ የማንጋኔዝና የአይረን ክምችት ታይቷል፡፡ አቃቂ አካባቢ በሚለሙ አትክልቶች ላይም እንዲሁ ከመጠን ያለፈ የማንጋኔዝና የሊድ ንጥረ ነገር ክምችት ተመዝግቧል፡፡ ይህም ለበርካታ አዲስ አበቤዎች የጤና ሥጋት መሆኑ በጥናቱ ተመልክቷል፡፡

በምርት ላይ ሳሉ ከሚያጋጥመው ብክለት በተጨማሪ ተመጋቢው ጋር እስኪደርስ ባለው ሒደት ውስጥ በሚፈጠር የአያያዝ ችግርም በተመጋቢው ላይ ሌላ የጤና ችግር እየተፈጠረ ነው፡፡ ችግሩ በብዛት የሚታየውም የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ሆኗል፡፡

ከአዲስ አበባ የምግብ፣ የመድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን በተገኘው መረጃ መሠረት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ላይ የተሰማራ አንድ ድርጅት በቂ የደንበኞች ማስተናገጃ ቦታ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ማጠቢያ ክፍልና ሌሎችንም መሥፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡ የድርጅቱን አካባቢያዊ ሁኔታ በተመለከተም ዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡ አንድ የፍራፍሬና አትክልት መነገጃ ተቋም ለጐርፍና ለናዳ ተጋላጭ ባልሆነ ቦታ ላይ እንዲቋቋም፣ ከቆሻሻ መጣያ ሥፍራ የራቀ እንዲሆን፣ ከመጥፎ ሽታና ከኬሚካል በፀዱ ቦታዎች እንዲሠራ ይጠበቃል፡፡ በአጠቃላይ ተቋማቱ በሰው ጤናና ደኅንነት ላይ አደጋ ከሚያስከትሉ ነገሮች የራቁ እንዲሆኑ ግድ ይላል፡፡

ይሁንና ይህ ድንጋጌ ከወረቀት ባለፈ ምን ያህል ተፈጻሚ መሆን እንደተሳነው ለማየት የአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ በስፋት የሚከናወንበት አትክልት ተራን መቃኘት በቂ ነው፡፡ ባለሥልጣኑ ካወጣው መሥፈርት በተቃራኒ አጠቃላይ ቦታው በከተማው ከሚገኙ ለጐርፍ ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡ አካባቢው ረግረጋማ ባይሆንም ከፍተኛ የቆሻሻ ክምችት የማይለየው ነው፡፡ የተበላሹ አትክልትና ፍራፍሬዎችን ጨምሮ ሌሎች ተረፈ ምርቶች ያለገደብ ይጣሉበታል፡፡ በመጥፎ ጠረኑም ይታወቃል፡፡

ሳይሸጡ ቆይተው እንደ መበስበስ ያሉ ፍራፍሬዎችን ለጁስ መሥሪያነት የሚሸጡ፣ የተጣሉና የወዳደቁ ፍራፍሬና አትክልቶችን ሰብስበው የሚሸጡ ‹‹ጐርጓሪዎች››ም ችግሩን ይበልጥ አደገኛ አድርጐታል፡፡ አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ በተበከሉ ወንዞች ዙሪያ የሚመረቱ አትክልትና ፍራፍሬዎች ጥቅም ላይ ሳይውሉ በቆዩ መጠን መርዛማነታቸው ይጨምራል፡፡ በተለይ በጥሬያቸው የሚበሉት ለከፋ የጤና ችግር ይዳርጋሉ፡፡

ሪፖርተር በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ፣ የኅብረተሰብ ጤና ምርምርና አደጋዎች ቁጥጥር ዋና የሥራ ሒደት ኃላፊ አቶ አብርሃም ተስፋዬ ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

‹‹በወንዞች ዳር ማምረት መልካም ቢሆንም ወንዞቹ ከየቤቱና ከየኢንዱስትሪው በሚወጡ ፍሳሾች የተበከሉ በመሆናቸው በአካባቢው የሚለሙ አትክልትና ፍራፍሬዎች ለጤና አደገኛ ናቸው፤›› የሚሉት አቶ አብርሃም፣ እስካሁን በዚህ ምክንያት የተከሰተ ወረርሽኝ አለመኖሩን ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በከተማው ውስጥ ለተከሰተው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ወረርሽኝ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል እንደሚገመት፣ ለዚህም በአትክልት ተራና በሌሎች አካባቢዎች አትክልትና ፍራፍሬዎችን በክሎሪን ታክመው እንዲቀርቡ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአትክልትና ፍራፍሬ ንግድ ሥራ የተሰማሩ ንግድ ቤቶችም በክሎሪን አጽድተው እንዲያቀርቡ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህኛው ሳምንትም አትክልት ተራን ለማጽዳት ተችሏል፡፡        

በጊዜያዊነት ከተወሰደው ዕርምጃ ባሻገር ፋብሪካዎች ወደ ወንዞች የሚለቀቁትን ፍሳሽ እንዲያክሙ፣ ከወንዝ ጋር የተያያዙ የመፀዳጃ ቤት ቱቦዎችም ሌላ አማራጭ እንዲፈጠርላቸው በማድረግ ዘላቂ መፍትሔ መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

‹‹ወንዞቻችን ተገቢውን ጥቅም እንዲሰጡ ብክለቱን ከምንጩ መቆጣጠር ያስፈልጋል፤›› የሚሉት የብክለትና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት መሪው ዶ/ር ሥዩም፣ ችግሩን ለመቅረፍ ፕሮጀክቱ የተለያዩ ሥራዎች ለመሥራት ማቀዱን ይናገራሉ፡፡ ወደ ወንዞቹ ከየአቀጣጫው የሚለቀቁ ፍሳሾች በየምንጫቸው እንዲጣሩ ማድረግ የፕሮጀክቱ ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ጐን ለጐንም የተበከሉትን ወንዞች የሚያፀዱ ተክሎችን በወንዞች ዙሪያ ማልማት ያስፈልጋል፡፡

Standard (Image)

ለአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የታቀደው ማስፋፊያ

$
0
0

በተለያዩ ዘርፎች የንግድ ትርዒቶች ሲዘጋጁና ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡ በዚህ መስክ የንግድ ምክር ቤቶች ድርሻ ጐልቶ ይታያል፡፡ በንግድ ትርዒት ዝግጅት ሥራ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በንግድ ትርዒቶች ላይ የሚሳተፉ የውጭ ኩባንያዎች ቁጥርም ዕድገት እየታየበት ስለመምጣቱ ይነገራል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ኤግዘቢሽን ማዕከል ብቻ ከ44 በላይ የንግድ ትርዒቶችና ባዛሮች በያመቱ ይካሄዳሉ፡፡ የንግድ ትርዒቶች ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ቢታመንም ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች ማሳያነት የሚሆን ደረጃውን የጠበቀ ምቹ ሥፍራ የላትም፡፡ ይህ ደግሞ የንግድ ትርዒቶችን ዝግጅት ጐዶሎ አድርጐታል፡፡ ከቢዝነሱ አሁን ከሚገኘው የበለጠ ተጠቃሚ እንዳይኮንም እንቅፋት መሆኑ በተደጋጋሚ ሲነገር ቆይቷል፡፡ እርጅና የተጫጫነው ብቸኛው የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልም ቢሆን ለዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች ብቻ ሳይሆን ለተራ ዝግጅትም አልመጥን እያለ መምጣቱን በርካቶች  ሲተቹበት ቆይተዋል፡፡ አማራጭ ባለመኖሩ ግን ዓለም አቀፍ ስያሜ ያላቸው የንግድ ትርዒቶች በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ታጭቀው እንዲካሄዱ አስገድዷል፡፡ አዲስ አበባ ስሟን የሚመጥን የንግድ ትርዒት ማዕከል እንዲኖራት ለማስቻል የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የጀመረው እንቅስቃሴም ቢሆን ሲጓተት ቆይቷል፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ ዘመናዊ የንግድ ትርዒት ማሳያና የኮንቬንሽን ማዕከል ለመገንባት ቦታ የተረከበው ከ12 ዓመታት በፊት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ከዕቅዱ 12 ዓመታት ዘግይቶም ቢሆን ይህ ፕሮጀክት በቅርቡ ወደ ግንባታ ይገባል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጐን ለጐን አንድ ለእናቱ የሆነውን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደ አዲስ ለማስገንባት ወደሚያስችል አዲስ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡ ከ40 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያካበተውን ማዕከል እንደ አዲስ ለመገንባትና ለዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች ምቹ ለማድረግ የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት፤ በንግድ ትርዒት ዝግጅትና ማስተዳደር ሥራ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ አስቆጥሯል ከተባለው ፌራ ሚላኖ ከተባለ የስፔን ኩባንያ ጋር በአጋርነት ለመሥራት ያደረገው ስምምነት ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን መልሶ ለመገንባት ስለተደረገው ስምምነትና በኢንዱስትሪው ዙሪያ ስለሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ጌታቸው ረጋሳን ዳዊት ታዬአነጋግሯቸዋል፡፡

 

ሪፖርተር፡- ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በመዋዋል የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን እያስተዳደራችሁ ነው፡፡ ነገር ግን ማዕከሉ አንድ የንግድ ትርዒት ማሳያ ሊኖረው የሚገባውን ይዘት ያላሟላ፣ አገልግሎቱም ያልተመቸ ነው፡፡ ይህንን ማዕከል ዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲኖረው መልሶ ለመገንባት ጥረት ስለመጀመሩ ተነግሯል፡፡ ስለ ኤግዚቢሽን ማዕከሉና ወደፊት ስለተያዘው ዕቅድ ቢነግሩኝ?

 

አቶ ጌታቸው፡- ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ ንግድ ምክር ቤታችን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን የማስተዳደር ሥራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የነበረን ውል እንደገና ታድሶ የማስተዳደሩን ሥራ አሁንም እየሠራን ነው፡፡ እንዳልከውና እንደሚታየውም ማዕከሉ ያረጀና አገልግሎት መስጫዎቹም በሙሉ የደከሙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ በንግድ ምክር ቤታችን በኩል በያመቱ በምናካሂደው ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ላይ ከ300 በላይ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ይሳተፋሉ፡፡ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ አይተው በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራትና ቢዝነሶቻቸውን ለማስተዋወቅ የሚመጡ ኩባንያዎች፣ የንግድ ትርዒት ማሳያውን ሥፍራ ሲመለከቱ ግር ይላቸዋል፡፡ ምክንያቱም ስለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሰምተው የመጡት ኩባንያዎች የንግድ ትርዒት ማሳያው ሥፍራ የሰሙትን ያህል ወይም የአገሪቱን የዕድገት ደረጃ የሚገልጽላቸው ባለመሆኑ ነው፡፡   

በአጠቃላይ ሲታይ ማዕከሉ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አይደለም፡፡ ኋላቀር ነው፡፡ ሕንፃዎቹ፣ ማሳያዎቹ፣ ሽንሽኖቹ ሳይቀር ኋላቀር ናቸው፡፡ የማዕከሉ ይዘት ሲያስጨንቀን ቆይቷል፡፡ ይህ ሁኔታ አሳሳቢ ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ያሳስበን የነበረው ከሚመጡት ተሳታፊዎች መካከል በርካቶቹ ዳግመኛ አለመምጣታቸው ነው፡፡ በእርግጥ አገሪቱ ውስጥ ባለው መልካም ዕድል እየተሳቡ የሚመጡ አሉ፡፡ የንግድ ትርዒት ማሳያው ሥፍራ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ያለመዋቀሩ ግን ሁልጊዜ አስቸጋሪ ነው፡፡ ማዕከሉን ለማሻሻል ስንመክርበት ቆይተናል፡፡ ባለበት ሁኔታ ብናሻሽለው ምን ያህል ወጪ ይጠይቀናል? ብለን ነገሩን ስንፈትሽ ቆይተናል፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተለያዩ አማራጮችን ተመልክተናል፡፡ ልምድ ለማግኘት ይረዳናል በማለት የተለያዩ አገሮች የንግድ ትርዒት ማሳያዎችን ጎብኝተናል፡፡ የዱባይና የኢስታምቡል ኤግዚቢሽን ማዕከሎችን አይተናል፡፡ የሚላንን ኤግዚቢሽን አይተናል፡፡ ወደ ባርሴሎና በመሄድ ፌራ ሚላኖ የሚባለውን ኤግዚቢሽን ጎብኝተናል፡፡ ፌራ ሚላኖ በዓለም ትልልቅ ከሚባሉት የኤግዚቢሽን ማዕከሎች አንደኛ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ነው፡፡ በተለይ ትርዒት በማዘጋጀትና በማደራጀት የታወቁ ናቸው፡፡ ወደዚህ ሥራ የገቡት እ.ኤ.አ. በ1842 ነው፡፡ የካበተ ልምድ አላቸው፡፡ ስለዚህ የእነሱን ማዕከልና አጠቃላይ አሠራራቸውን በማየት ጥሩ ተሞክሮ አግኝተናል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ከእነርሱ ጋር በመነጋገር በእኛ አገርም እንድንገነባው ጥያቄ አቅርበንላቸዋል፡፡ እነሱ ጥናቱን ለማጥናት ፈቃደኛ ሆነዋል፡፡ በባርሴሎና ከንቲባ ጋባዥነትም በክቡር ከንቲባ ድሪባ ኩማ የተመራ የልዑካን ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ባርሴሎና በመጓዝ ኤግዚቢሽን ማዕከሉን በመጐብኘትና አዲስ አበባ ላይ ደረጃውን የጠበቀ ማዕከል ለመገንባት እንደሚቻል በመነጋገር ከተስማማን በኋላ የመጀመሪያው የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡

ሪፖርተር፡- በእናንተና በስፔኑ ኤግዚቢሽን ማዕከል መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ይዘቱ ምን ነበር?

አቶ ጌታቸው፡- የተፈረመው መግባቢያ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን በተሻለ ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እንዲያካሂዱልን ነው፡፡ ለምናስገነባው ማዕከል የዲዛይን ሥራ መሥራት የስምምነቱ አንድ አካል ነው፡፡ ከአንድ ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ላይ የተፈረመው ስምምነት በአጠቃላይ ሥራውን የማስጀመርና የተሟላ ጥናት ለማጥናት እንዲቻል ነው፡፡ ጥናቱና የዲዛይን ሥራው እስከ ጥቅምት 2009 ዓ.ም. ተጠናቅቆ እንዲቀርብ ለማድረግ ነው፡፡ በዚህ ስምምነት መሠረት ፌራ ሚላኖ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን መልሶ ለመገንባት የሚያስችል ጥናትና የፕሮጀክቱን ዲዛይን በጥቅምት 2009 ዓ.ም. አጠናቀው ያስረክቡናል ማለት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጋር በጋራ የምታስተዳድሩት ተቋም ነው፡፡ እናንተ እያስተዳደራችሁ፤ ገቢውን በመካፈል የምትሠሩበት ነው፡፡ ከአዲሱ ኩባንያ ጋር በአጋርነት እንሠራለን ካላችሁ አብሮ መሥራቱ በምን መልኩ የሚሆን ነው?

አቶ ጌታቸው፡- የፌራ ሚላኖን ተሞክሮ ስናይ፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ ባለቤቶች የባርሴሎና ከተማ አስተዳደርና የባርሴሎና ንግድ ምክር ቤት ናቸው፡፡ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የአሠራር ሒደት አለው፡፡ ማዕከሉን የገነቡትም በጋራ ከባንክ ተበድረው ነው፡፡ ንግድ ምክር ቤቱ የባንክ ዋስትና ከመንግሥት ተፈቅዶለት የተወሰነ ገንዘብ ተበድሯል፡፡ የባርሴሎና ከተማ አስተዳደርም ከባንክ ብድር ከተፈቀደለት በኋላ ሁለቱም ያገኙትን ገንዘብ አጋጭተው ማዕከሉን በጋራ በመገንባት ማስተዳደር ጀመሩ፡፡ የንግድ ትርዒት ማሳያ ቦታዎቹ በባህሪያቸው ያለግሉ ዘርፍ ተሳትፎ መንግሥት ለብቻው የሚሠራቸው አይደሉም፡፡ ይህ ተሞክሯቸው ትኩረት የሰጠንበት ነው፡፡ አካሄዱ እንግዲህ ወደፊት ከግንባታው በኋላ የሚታይ ይሆናል፡፡ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ አኳያ ምክር ቤታችን ከአስተዳደሩ ጋር በአጋርነት መሥራቱን ይቀጥልበታል፡፡

ሪፖርተር፡- ጥያቄዬ ግን ከአጥኚው ኩባንያ ጋር የሚኖራችሁ አጋርነት  እንዴት ይገለጻል የሚል ነው፡፡

አቶ ጌታቸው፡- እሱንም ከጥናታቸው ጋር አያይዘው የሚያመጡት ነው፡፡ ጥናቱን ጨርሰው ካቀረቡልን በኋላ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡ የከተማው አስተዳደርና የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በጋራ የማልማትና በጋራ የመሥራት አጋርነት መኖር እንዳለበት ከወዲሁ ታስቧል፡፡ ነገር ግን ከጥናቱ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡ ለምን ታሳቢ ይሆናል ከተባለም የንግድ ትርዒት ሥራዎች በባህሪያቸው ያለ ግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በመንግሥት ብቻ የሚሠሩ ባለመሆናቸው ነው፡፡ በዱባይም ሆነ በሚላን እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ያለውን ልምድ ስናይ፣ መንግሥት በዚህ ሥራ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን የግሉ ዘርፍ የሚሳተፍባቸው ናቸው፡፡ የዓለም ተሞክሮ ይኼው ነው፡፡ አጋርነቱም ይቀጥላል፡፡ በተለይ የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽንና ኮንሽንሽን ማዕከልን ለማስገንባት የተጀመረው አጋርነትና በጋራ የመሥራቱ ሒደት እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ሪፖርተር፡- ከስፔኑ ኩባንያ ጋር ስምምነት ስታድጉ ጉዳዩን ለአዲስ አበባ አስተዳደር አቅርባችሁ ነበር? ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላስ የሚኖራችሁ ሚና ምንድን ነው?

አቶ ጌታቸው፡- ሁኔታውን አጥንተን ሐሳቡን አቀረብን፡፡ የማዕከሉ ባለቤት የከተማ አስተዳደሩ ስለሆነ እኛ በተናጠል ሄደን ልንፈራረም አንችልም፡፡ የባለቤትነት ጥያቄ አለበት፡፡ ስለዚህ ሐሳቡን አቀረብን፡፡ ሐሳባችንን በደስታ ነበር የተቀበሉት፡፡ የእኛ ድርሻ ሊሆን የሚችለው ከጥናቱ ውጤት የሚመጣ ነው፡፡ ባለቤቱ የከተማው አስተዳደር ነው፡፡ እኛ ማኔጅመንቱን ነው የወሰድነው፡፡ በዚሁ መሠረት ጥናቱ ተጠንቶ ይመጣል፡፡ ጥናቱ የሚለውና ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ተወስዶ በጋራ የምንሠራበት ሞዴል ይዘረጋል፡፡ በእርግጠኝነት ግን ይሄ ነው ለማለት አሁን ጊዜው አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ያረፈበት ቦታ ትልቅ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊያስገነባ እንደማይችል ይነገራል፡፡ አሁን ባለው ቦታ ብቻ እየታሰበ ያለውን ዓይነት ማዕከል መገንባት ይቻላል?

አቶ ጌታቸው፡- ቢሆንም ሊሰፋ የሚችልበትን ዕድል፣ የማዕሉን ይዘት ጥናቱ ያሳየናል፡፡ በጥናቱ መሠረት እንዲሁም ከሚያቀርቡት የግንባታ ዲዛይን ይህንን ያህል ቦታ ያስፈልጋል ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ በዚህ መሠረት ይሠራል፡፡ ማስፋቱ ግን ግዴታ ነው፡፡ አሁን ባለው ቦታ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ኤግዚቢሽን ማዕከል መገንባት አይቻልም፡፡

ሪፖርተር፡- በኤግዚቢሽን ማዕከሉ ዙሪያ ያለው ቦታ ወደፊት ለሚገነባው ማዕከል ሊውል እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ ቦታው ተፈቅዶላችኋል?

አቶ ጌታቸው፡- ይኼ የአስተዳደሩ ሥራ ነው፡፡ እንደ ሐሳብ ጥናቱ ሲመጣ የሚካተት ይመስለኛል፡፡ በዚህ መልኩ ነው የምናየው፡፡ የጥናቱ ውጤትም ወደፊት የሚሆነውን ያሳየናል፡፡ አሁን ያለው ቦታ ግን ለሚባለው ዓላማ በቂ እንዳልሆነ የጋራ መግባባት አለ፡፡

ሪፖርተር፡- ስለዚህ ተጨማሪ ቦታ ያስፈልጋል? ዲዛይኑም ይህንን አገናዝቦ የሚሠራ ነው ማለት ነው?

አቶ ጌታቸው፡- ብለን እንገምታለን፡፡

ሪፖርተር፡- ከኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ ጋር በተያያዘ ከዓመታት በፊት የተጀመረውና እስካሁን ተግባራዊ ያልሆነው የአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል አለ፡፡ የዚህ ማዕከል ግንባታ ይጀመራል ከተባለ ቆይቷል፡፡ የዚህ ግንባታ ሳይጀመር ግን የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከልን መልሶ ለመገንባት እየተንቀሳቀሳችሁ ነው፡፡ አንዱን ሳትጨርሱ ወደሌላው መሄድ አይሆንባችሁም?

አቶ ጌታቸው፡- ለዚህች ከተማ በአጠቃላይ የሚያስፈልጋት የኤግዚቢሽን ማዕከል ስንት ነው? እንደ ኢኮኖሚው እንቅስቃሴና እንደ አስፈላጊነቱ የሚታይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ኮንቬንሽን ማዕከሎች የሉም፡፡ የአገሪቱ ተነጻጸሪ ተጠቃሚነት የሚታየውም የአፍሪካ ማዕከል ከመሆኗ ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ የአዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ፕሮጀክት ትልቅ በመሆኑ ግንባታው ተጠናቅቆ ሥራ እስኪጀምር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየሠራን እንቆያለን፡፡ ዞሮ ዞሮ ሁለቱም የተለያየ ተግባር ይኖራቸዋል፡፡ አዲስ አፍሪካ ትልልቅ ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒቶች የሚዘጋጁበት ይሆናል፡፡ ይኼኛው በመለስተኛ ደረጃ ይሠራል፡፡ ተመጋጋቢ ሥራ እንዲሠሩ ታሳቢ ተደርጐ የሚሠራ ነው እንጂ ተወዳዳሪ አያደርጋቸውም፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ ያሉትን የኤግዚቢሽን ማዕከሎች ኡጋንዳ፣ ኬንያና ሩዋንዳ ለመሥራት ሐሳብ አላቸው፡፡ እኛ ቶሎ ወደ ሥራ መግባታችን በምሥራቅ አፍሪካ ተነፃፃሪ ተጠቃሚ የመሆን ዕድሉን ለመውሰድ ያስችለናል፡፡    

ሪፖርተር፡- ከስፔኑ ፌራ ሚላኖ ጋር ባደረጋችሁት ውል ለጥናቱና ለዲዛይን ሥራው ምን ያህል ትከፍላላችሁ?

አቶ ጌታቸው፡- እስከ ስድስት ሚሊዮን ብር ይደርሳል፡፡

ሪፖርተር፡- ሲኤምሲ አካባቢ ይገነባል የተባለው አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽንና የንግድ ትርዒት ማዕከል የግንባታ ፕሮጀክት አሁን በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

አቶ ጌታቸው፡- የመጀመሪያውን የግንባታ ምዕራፍ ለመጀመር ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቷል፡፡ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው በማስገባት ላይ ናቸው፡፡ ስለዚህ በቅርቡ የመጀመሪያው ክፍያ ተከፍሎ ሥራ እንጀምራለን ብለን እንጠብቃለን፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አፍሪካ ኮንፌንሽንና የንግድ ትርዒት ማዕከል እስካሁን ምን ያህል አክሲዮን ሸጧል፡፡ ምን ያህል ባለአክሲዮኖችስ አሉት?

አቶ ጌታቸው፡- ባለአክሲዮኖቹ ብዙ ናቸው፡፡ ትልቁን ድርሻ ከያዙት ውስጥ የከተማው አስተዳደር አንዱ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ150 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ገዝቷል፡፡ ሁለተኛው በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ እነሱ ወደ 115 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ አክሲዮን ገዝተዋል፡፡ ከፊሉን የአክሲዮን ዋጋ አስገብተዋል፡፡ ቀሪውን ያስገባሉ ብለን እየጠበቅን ነው፡፡ ንግድ ምክር ቤታችን ለጊዜው የ10 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ገዝቷል፡፡

ሪፖርተር፡- እስካሁን ምን ያህል አክሲዮን ሸጣችኋል?

አቶ ጌታቸው፡- የ300 ሚሊዮን ብር አክሲዮን ሸጠናል፡፡ የአንድ ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው አክሲዮን ለመሸጥ እየተዘጋጀን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የንግድ ትርዒቶች ደረጃ እንዴት ይመዘናል? በአጠቃላይ ኢንዱስትሪውስ ምን ይመስላል?

አቶ ጌታቸው፡- የንግድ ትርዒት ማዘጋጀት በንጉሡ ጊዜ የተጀመረ ነው፡፡ ኤክስፖ ይባል ነበር፡፡ በደርግ ጊዜ የግል ዘርፉ ብዙም ስላልነበር ተቀዛቀዘ፡፡ በአጠቃላይ ግን ከ20 ዓመት ወዲህ፣ በተለይ ንግድ ምክር ቤቱ በንግድ ትርዒት ሥራ ዘርፍ ውስጥ ከገባበት ጊዜ ወዲህ በርካታ ለውጦች ታይተዋል፡፡ ወደዚህ ሥራ ስንገባ ንግድ ትርዒት ብዙም የሚታወቅ አልነበረም፡፡ በመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ እንኳ ግንዛቤው አልነበረም፡፡ ሥራው ከኢኮኖሚና ከንግድ ዕድገት ጋር የሚመጣ ነው፡፡ ላለፉት 20 ተከታታይ ዓመታት ኤግዚቢሽን አካሂደናል፡፡ በዚህ መነሻነት የተሠራው ሥራ ብዙ ለውጥ ታይቶበታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ብቻ በዓመት ከ44 በላይ የንግድ ትርዒቶች ይካሄዳሉ፡፡ የውጭ ተሳታፊዎችም ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል፡፡ ስለዚህ  የቦታው ጥበት ካልሆነ በቀር ቢዝነሱ አዋጭ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በያመቱ የሚካሄዱና በዓላትን ታከው የሚሰናዱ ዝግጅቶችን ለማካሄድ ከፍተኛ ዋጋ እየቀረበ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ እንዴት ይታያል?

አቶ ጌታቸው፡- እንዲህ ዓይነቱ ዝግጅት ባዛር ነው የሚባለው፡፡ ዕቃ የሚሸጥበት ነው፡፡ ንግድ ትርዒት ስንል ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት ብቻ ነው፡፡ ሽያጭ ማካሄድ አይመከርም፡፡ ስለዚህ ባዛር በዓላትን አስታከው ሰዎች በርካሽ ዋጋ እንዲገበያዩ ዕድል ከመፍጠር አኳያ የመጣ፣ እንዲያውም ከሶሻሊስት ሥርዓቱ ጋር የተጀመረ ነው ሊባል ይችላል፡፡ ሰዎች በበዓል ወቅት በርካሽ ዋጋ ዕቃ እናገኛለን ብለው የሚጠቀሙበት የተለመደ አካሄድ ነው፡፡ ይህ ከእኛ አካሄድ ጋር ብዙ የሚገናኝ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- እናንተ ናችሁና ማዕከሉን የምታስተዳድሩት፣ ጨረታውንም የምታወጡት ይህ አካሄድ እንዴት ይታያል?

አቶ ጌታቸው፡- ከማስተዳደር ጋር ሲተያይ ነፃ ጨረታ ነው የምናካሂደው፡፡ ስለዚህ በቢዝነሱ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች እርስ በርሳቸው በሚያደርጉት ውድድር ነው ዋጋው ወደላይ የወጣው፡፡ እኛ ዋጋ አንወስንም፡፡ ሌላው ቀርቶ መነሻ ዋጋ አናወጣም፡፡ ገበያው በሚሰጠው ውድድር ነው ዋጋው እዚህ ደረጃ የደረሰው፡፡

ሪፖርተር፡- የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የንግድ ምክር ቤቱ ነበር፡፡ ይመለስ ተብሎ ሙግት ተጀምሮም ነበር፡፡

አቶ ጌታቸው፡- ዱሮ ማዕከሉ የንግድ ምክር ቤቱ ነበር፡፡ እንዲያውም ለማዕከሉ አንዳንድ የውኃና የመብራት የተከፈለባቸው ደረሰኞችም የእሱ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው የሚባል ነገር አለ፡፡ ነገር ግን በፍርድ ቤት አዋጅ ተወርሷል፡፡ ማዕከሉ ብቻ ሳይሆን ሕንፃውም ተወርሷል፡፡ የሚወረስ ንብረት ሁሉ የፌዴራል መንግሥት ንብረት ነው፡፡ ስለዚህ አስተዳደሩ ይህንን ማዕከል እንዲያስተዳድር የፌዴራል መንግሥት እንደሰጠው ነው ታሳቢ የሚደረገው፡፡ ይህ ሥራ የግሉን ዘርፍ ያማከለ ስለሆነ፣ ንግድ ምክር ቤቱ ቢያስተዳድረው የበለጠ ውጤታማ ይሆናል ተባለ፡፡ እንደተባለውም በገቢም ሆነ ዘርፉን በማሳደግ ረገድ ውጤታማ ሆነናል፡፡

Standard (Image)

ፔጆና መስፍን ኢንጂነሪንግ በውቅሮ መገጣጠሚያ ፋብሪካ አዋቅረዋል

$
0
0

በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረው የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና አምራች፣ ከሚያመርታቸው የቤት አውቶሞቢሎች መካከል የተወሰኑ ሞዴሎችን በኢትዮጵያ መገጣጠም ጀመረ፡፡ የፔጆ ተሽከርካሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መገጣጠም የጀመሩት በፔጆና በመስፍን ኢንጂነሪንግ መካከል በተደረሰ ስምምነት መሆኑ ታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ከመቐለ 40 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው ውቅሮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የመስፍን ኢንጂነሪንግ የተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ ፋብሪካ አማካይነት የሚገጣጠሙት አውቶሞቢሎች ሦስት ዓይነት ሞዴሎች ናቸው፡፡

መገጣጠሚያ ፋብሪካው ሰኔ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በይፋ በተመረቀበት ወቅት እንደተገለጸው፣ በመጀመሪያው ዙር በፋብሪካው ተገጣጥመው ለገበያ ከሚቀርቡት ሦስት የፔጆ ሞዴል አውቶሞቢሎች በተጨማሪ ሌሎች የቤት አውቶሞቢሎችም ይገጣጠማሉ፡፡

መስፍን ኢንጂነሪንግ በውቅሮ ከተማ የፔጆ አውቶሞቢሎችን በመገጣጠም የጀመረው ሥራ ሌላም ትልቅ ራዕይ የተሰነቀበት መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይህም በአገሪቱ ትልቁን የተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ መንደር ወደ መመሥረት የሚሸጋገርበት እንደሚሆን መነገሩ ነው፡፡

ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ይጠይቃል የተባለው ግዙፉ የተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ፣ በሒደትም ወደ ሙሉ የመኪና አምራችነት ለማሳደግ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቀት እየተገጣጠሙ የሚገኙት የፔጆ ሥሪት አውቶሞቢሎችም በመስፍን ኢንጂነሪንግ የተጀመረውን የመገጣጠም ሥራ ለመንደርደሪያነት እንደሚያግዙ ተገልጿል፡፡

የመስፍን ኢንጂነሪንግ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሃብተ ሃዱሽ እንደሚገልጹት፣ የተሽከርካሪ ተጠቃሚዎችን ቁጥርና የአገሪቱን የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ተሽከርካሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

መስፍን ኢንጂነሪንግ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠም ወደ ማምረት ለመሸጋገር የሚያስፈልገውን ጥናት በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝና ለማምረቻ ቦታ ግንባታም 50 ሔክታር መሬት እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡ ቦታውን የማግኘቱ ሒደት እንደተጠናቀቀም ወደ ሥራ ይገባል ተብሏል፡፡

የፈረንሳዩ አውቶሞቢል አምራች ፔጆ፣ ከመስፍን ኢንጂነሪንግ ጋር ባደረገው ስምምነት መሠረት በውቅሮ ሥራ የጀመረው መገጣጠሚያ ፋብሪካ፣ ለፔጆ ኩባንያ በአፍሪካ ሦስተኛው ተቋም ለመሆን በቅቷል፡፡ ከኢትዮጵያ ባሻገር በሞሮኮና በናይጄሪያ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች አሉት፡፡

የኢፈርት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አዜብ መስፍን እንደገለጹት፣ መስፍን ኢንጂነሪንግ ከዚህ ቀደም የቻይናዎቹን ጄሊ የቤት አውቶሞቢሎች ሲገጣጥም ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ከፈረንሳዩ ኩባንያ ጋር የፔጆ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም መጀመሩ የኩባንያው እንቅስቃሴ እያደረገ መምጣቱን አመላካች እንደሆነ ያሳያል ብለዋል፡፡ መስፍን ኢንጂነሪንግ፣ ከጄሊና ከፔጆ የቤት አውቶሞቢሎች በተጨማሪ ከታዋቂው የጀርመን ኤምኤኤን (MAN) ኩባንያ ጋር በቅርቡ ባደረገው ስምምነት መሠረት፣ የኤምኤኤን ከባድ ተሽከርካሪዎችን ገጣጥሞ ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁንም ከ250 በላይ የኤምኤኤን ተሽከርካሪዎችን በመገጣጠም ለደንበኞቹ ማስረከብ እንደጀመረ ከመስፍን ኢንጂነሪንግ ኃላፊዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከአራቱ የመስፍን ኢንጂነሪንግ ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች አንዱ በሆነው በአውቶሞቲቭ ዘርፍ የቤትና የከባድ ተሽከርካሪዎችን ከመገጣጠም ባሻገር፣ ከህንድ ኩባንያ ጋር በመሆን ትራክተር ገጣጥሞ ለገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚኝ ታውቋል፡፡

በመስፍን ኢንጂነሪንግ የሚገጣጠሙት የፔጆ ተሽከርካሪዎች አሁን ባለው የመገጣጠም አቅም መሠረት በዓመት እስከ አንድ ሺሕ ተሽከርካሪዎችን ለገበያ ማቅረብ የሚችልበት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ እንደ ገበያው ሁኔታም የምርት መጠኑን መጨመር እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

በምረቃ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የፔጆ ኩባንያ የመካከለኛው ምሥራቅና የአፍሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ክርስቶፈር ኡመር እንደገለጹትም፣ በኢትዮጵያ በሦስት ሞዴሎች የተጀመረው የመገጣጠም ሥራ ሌሎች ተጨማሪ ሞዴሎችን በማስከተል ዓመታዊ የመገጣጠም አቅሙን እያሳደገ ይሄዳል፡፡

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም ኩባንያቸው ሊመጣ መቻሉንም ጠቅሰዋል፡፡ ከኩባንያዎቹ የሥራ ኃላፊዎች እንደተገለጸው በአሁኑ ወቅት ለገበያ የሚቀርቡት ሦስቱ የፔጆ ተሽከርካሪዎች ዋጋ ከውጭ መጥተው ይሸጡ ከነበረበት ይልቅ እስከ 15 በመቶ ቅናሽ ይኖራቸዋል፡፡

በመስፍን ኢንጂነሪንግ የፔጆ ተሽከርካሪዎች የምረቃ ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ብሪጅት ኮሬት፣ የትግራይ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አዲስ ዓለም ባሌማ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር መብራህቱ መለስ እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ባለሥልጣናት ተገኝተዋል፡፡

መስፍን ኢንጂነሪንግ ከአንድ ሚሊዮን ብር ባነሠ ካፒታል የተቋቋመ ኩባንያ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የሚያንቀሳቅሰው ካፒታል ከ25 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወይም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ መድረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

  

Standard (Image)

ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት አዲስ ሥራ አስፈጻሚ ተሰየመ

$
0
0

በኢትዮጵያ የጠለፋ ዋስትና አገልግሎት በመስጠት የመጀመሪያው አገር በቀል ኩባንያ ሆኖ የተመዘገበውን የኢትዮጵያ ሪ ኢንሹራንስ ኩባንያን በሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ በተሰየሙት በቀድሞ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ የወንድወሰን ኢተፋ ምትክ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተሰየመ፡፡

ከድርጅቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ መንግሥታዊውን የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት እንዲመሩ የተሰየሙት ላለፉት ሁለት ዓመታት የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን በኦፕሬሽን ምክትል ሥራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ነፃነት ለሜሳ ናቸው፡፡

አቶ የወንድወሰን ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሥራ አስፈጻሚነት መልቀቃቸው እንደታወቀ፣ አቶ ነፃነት ኃላፊነቱን ተቀብለው በጊዜያዊነት እንዲሠሩ ተወክለው ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ደግሞ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲሠሩ መመደባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አዲሱ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት፣ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት መደቦች ለ16 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆንም ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲሠሩ መቆየታቸው ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በአገሪቱ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ውስጥ በመንግሥት ባለቤትነት ለአርባ ዓመታት ሲንቀሳቀስ የቆየ ኩባንያ ነው፡፡ የደርግ መንግሥት እስከወደቀበት ድረስ የአገሪቱ ብቸኛ መድን ሰጪ ኩባንያ ሆኖ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ የኢንሹራንስ ገበያውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ በመያዝ ቢዘልቅም፣ ከ1983 ዓ.ም. በኋላ በመድን ኢንዱስትሪው መስክ የግል ዘርፉ መሳተፍ እንደሚችል ከተፈቀደ በኋላ የገበያ ድርሻው ላይ ሌሎችም ኩባንያዎችና ግለሰቦች በአክሲዮን ተደራጅተው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ከጠቅላላው የአገሪቱ የኢንሹራንስ ገበያ ውስጥ የመድን ድርጅት የገበያ ድርሻ 38 ከመቶ ገደማ እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 62 በመቶ የሚሆነውን የገበያ ድርሻ 16ቱ የግል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ተቀራምተውታል፡፡ የመድን ድርጅት በዚህ ሳቢያ የገበያ ድርሻው እየቀነሰ ቢመጣም፣ አሁንም ድረስ በአገሪቱ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ አብላጫውን የገበያ ድርሻ እንደያዘ ይገኛል፡፡ በተለይ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የገበያ ድርሻው ቀስ በቀስ እየወረደ መምጣቱ እየታየ ነው፡፡ አዲሱ ዋና ሥራ አስፈጻሚም የድርጅቱ የገበያ ድርሻ አሁን ካለበት መጠን እንዳይወርድ ብዙ እንደሚሠሩ ይጠበቃል ተብሏል፡፡

 

Standard (Image)

በአሜሪካ ሊካሄድ የታሰበው የሪል ስቴት ዓውደ ርዕይ ባንኮችንም ተሳታፊ እንደሚያደርግ ተገለጸ

$
0
0

በያመቱ በቋሚነት እንደሚካሄድ የተገለጸው የሪል ስቴት ዓውደ ርዕይ፣ ዘንድሮ በጅማሬው በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ እንዲዘጋጅ መታቀዱንና በንግድ ትርዒቱም አምስት ባንኮችን ጨምሮ 22 የሪል ስቴት አልሚዎች እንዲሳተፉ መጋበዙን የዓውደ ርዕዩ አዘጋጅ 251 ኮሙዩኒኬሽንስ ኩባንያ አስታውቋል፡፡

ኩባንያው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ይፋ እንዳደረገው፣ በመጪው መስከረም ወር ሊካሄድ የታቀደው የሪል ስቴት ዓውደ ርዕይ በዳያስፖራው ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ ጥያቄ ለሆነው የቤት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መድረክ እንዲፈጥር ለማስቻል ታስቦ መዘጋጀቱን የ251 ኮሚዩኒኬሽንስ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ አዲስ ዓለማየሁ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

አቶ አዲስ እንዳብራሩት፣ በያመቱ እንዲካሄድ የታሰበው የሪል ስቴት ዓውደ ርዕይ ኢትዮጵያውያን የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በብዛት በሚገኙባቸው አገሮች ተዘዋውሮ የሚካሄድ ነው፡፡ በዚህም መሠረት የዋሺንግተኑ መሥራችና የሁለት ቀናት ዓውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ ከኢትዮጵያ የሚያቀኑት ባንኮችና ሪል ስቴቶችን ጨምሮ እስከ አምስት ሺሕ የሚደርሱ የዋሺንግተንና የአጎራባች ከተሞች ነዋሪዎች እንደሚገኙበት አቶ አዲስ ገልጸዋል፡፡

በአሜሪካው የዓውደ ርዕይ ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው የተጠቀሱት አምስቱ ባንኮች ዘመን፣ ዓባይ፣ ቡና፣ አዋሽ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆናቸውን አቶ አዲስ ጠቅሰዋል፡፡ በዓውደ ርዕዩ የሚሳተፉት የሪል ስቴት አልሚዎችም እስካሁን ካሳዩት የሥራ አፈጻጸም አኳያ ተመርጠው ለጉዞ መጋበዛቸውን ተናግረዋል፡፡ የባንኮቹ ተሳታፊነት ሁለት ገጽታ እንደሚኖረው የጠቀሱት አቶ አዲስ፣ አንደኛው ባንኮቹ በብድር አቅርቦት እንዲሳተፉ የሚያስችላቸውን ዕድል እንደሚፈጥር አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ባንኮቹ ብድራቸው እስኪመለስ ድረስ የቤት ገዥዎችን ቤቶች በእኩል ባለቤትነት በመያዝ ለብድሩ ማስያዣነት እንደሚያውሉት፣ ይህም በቤት ገዥዎችና በአልሚዎች መካከል መተማመንን ለመፍጠር እንደሚያግዝ አብራርተዋል፡፡ በሁለተኛነትም ባንኮቹ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስለሚሆናቸው ጭምር በዓውደ ርዕዩ ለመሳተፍ መሻታቸው ከዚህም አኳያ ጠቀሜታ ስላለው መሆኑም ተብራርቷል፡፡

ይሁንና በአገሪቱ በሪል ስቴት ግንባታ ዘርፍ እየተሳተፉ ከሚገኙት ኩባንያዎች ውስጥ በርካቶቹ በተለያዩ ምክንያቶች ለቤት ገዥዎች ቤት ማስረከብ ተስኗቸው ቆይተዋል፡፡ ጥቂት የማይባሉትም ከቤት ገዥዎች የሰበሰቡትን ገንዘብ ይዘው የጠፉና የፈረሱ ኩባንያዎች ሆነዋል፡፡ በዚህ ሰበብ ጉዳት ከደረሰባቸውና ገንዘባቸውን ውኃ ከበላባቸው መካከል አብዛኞቹ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ናቸው፡፡

ይህ መሆኑ ከሪል ስቴት አልሚዎችና ገንቢዎች ባሻገር መንግሥትን በተጠያቂነት የሚተቹም አሉ፡፡ ምክያቱም መንግሥት የሪል ስቴት ዘርፉን በአግባቡ መቆጣጠር የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘጋ ልቅ ስለተወው፣ ገንዘብ ሳይኖራቸው ከገዥዎች ገንዘብ ሰብስበው እልም የሚሉ፣ መሬት ሳይኖራቸው በጨበጣ የሚንቀሳቀሱ በርካታ ሪል ስቴት አልሚዎች ታይተዋል፡፡

እንዲህ ባለው ሁኔታ ውስጥ የሚገኘውን የቤት ልማት ዘርፍ ማስተዋወቁ ለምን እንዳስፈለገና ተዓማኒነትስ ይኖረዋል ወይ ተብለው ከሪፖርተር ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ አዲስ፣ ምንም እንኳ የሪል ስቴት ዘርፍ የሚገኝበት ሁኔታ ብዙም አስደሳች ባይሆንም በውጭ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለው የቤት ፍላጎት ግን ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ፍላጎት ለማስተናገድ የሚያስችል ሥራ መሥራት ግድ እንደሚል አብራርተዋል፡፡

በዚህ መነሻነትም እስካሁን ከሚንቀሳቀሱ የሪል ስቴት አልሚዎችና ገንቢዎች ውስጥ በታማኝነት ቤት መገንባት የቻሉና ያስረከቡ፣ እየዘገቡም ጭምር ቢሆን እየሠሩ ያሉ ኩባንያዎች በዓውደ ርዕዩ ተሳታፊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡ ለተሳትፎ የምርጫ መሥፈርት መሆኑም የተገለጸው ይኸው መሆኑን የተናገሩት አቶ አዲስ፣ እንደ ከዚህ በፊቱ እንዲሁ ልንገነባ ነው ልንሠራ ነው ስላሉ ሳይሆን መሬት ላይ የሚታይ ሥራ የሠሩት ኩባንያዎች ብቻ እንዲሳተፉ እንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡

በያመቱ እንደሚሰናዳ የተገለጸው የሪል ስቴት ዓውደ ርዕይ፣ የጀመሪያውን በአሜሪካ ለማካሄድ የተቆረጡት ቀናት ከመስከረም 7 እስከ 8 ቀን 2009 ዓ.ም. ያሉት ናቸው፡፡ ከአሜሪካው ዓውደ ርዕይ ቀጥሎ በካናዳ፣ በእንግሊዝና በተለያዩ የአውሮፓ አገሮች እንዲሁም በእሥራኤል እንደሚካሄድ አቶ አዲስ ገልጸዋል፡፡

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፣ ከናይጄሪያ በመቀጠል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች በአሜሪካ ይኖራሉ፡፡ በጠቅላላው ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን በመላው ዓለም እንደሚኖሩ ሲገመት ከዚህ ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚቆጠሩት በሰሜን አሜሪካ እንደሚገኙ ይገመታል፡፡ 

Standard (Image)

አገር በቀሉ አማካሪ ድርጅት የምሥራቅ አፍሪካ የሆቴል ገበያን ከዱባይ አቻው ጋር በመሆን ለማዳረስ መነሳቱን ገለጸ

$
0
0
  • ካማከራቸው አሥር ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ሁለቱ ሥራ ጀምረዋል

 

ዓለም አቀፍ የኮከብ ደረጃ ያላቸው ሆቴሎችን ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በማጣመር እንዲሠሩ በማማከር የሚንቀሳቀሰው ካሊብራ ሆስፒታሊቲ ኤንድ ቢዝነስ የተሰኘው አገር በቀሉ አማካሪ ድርጅት፣ ከዱባዩ አሌፍ ሆስፒታሊቲ ኩባንያ ጋር በመሆን የምሥራቅ አፍሪካ የሆቴል ገበያን በበላይነት ለመምራትና አገሮችን ለማዳረስ የሚያችለውን አጋርነት መመሥረቱን አስታወቀ፡፡

የካሊብራ ሆስፒታሊቲ ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ነዋይ ብርሃኑ ለሪፖርተር እንዳስታወቁት፣ ኩባንያው በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ በቅርቡ ከተመሠረተው አሌፍ ኩባንያ ጋር በፈጠረው አጋርነት መነሻነት ዓለም አቀፍ የሆቴል ንግድ ሥራ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ባለሀብቶችን በማማከር ከመሳተፍ ባሻገር በአስተዳደር መስክም አሌፍን ያግዛል፡፡

በሁለት የቀድሞ የሒልተን ባለሟሎች (አቶ ነዋይ ብርሃኑና አቶ ዮናስ ሞገስ) የተቋቋመው ካሊብራ የሆቴል ማማከርና የንግድ ሥራዎች ድርጅት፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአሥር ያላነሱ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ከአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር በመሆን እንዲሠሩ ሲያመቻች ቆይቷል፡፡

ከእነዚህ ሆቴሎች ውስጥ ጎልደን ቱሊፕ የተሰኘው የኔዘርላንድስ ብራንድና የአሜሪካው ዊንድሃም ሆቴል ግሩፕ ኩባንያ ከሚያስተዳድራቸው ብራንዶች መካከል ራማዳ የተሰኘውና በኢትዮጵያ ራማዳ አዲስ ተብሎ የተሰመየውን ሆቴል ማማከሩና ወደ አገር እንዲመጣ በማድረግ መሳተፉ ይታወቃል፡፡ ራመዳ አዲስ ቅዳሜ፣ ሰኔ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ቀላል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በማዘጋጀት ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡  ካሊብራ ከውጭ ሆቴሎች ባሻገር፣ የአምስት ኮከብ ደረጃ ያገኘውን ካፒታል ሆቴልና ስፓ በማማከርም ተሳትፏል፡፡

ከጥቅት ወራት በፊት በዱባይ ከተመሠረተው አሌፍ ኮንሰልታንሲ ኩባንያ ጋር ባደረገው የአጋርነት ስምምነት መሠረት፣ በኢትዮጵያና በምሥራቅ አፍሪካ በትልልቅ ብራንድ ሆቴሎች ከሚተዳደሩት በመለስ ያሉ ሆቴሎችንም በዓለም አቀፍ ብራንዶች ደረጃ ልክ ለማስተዳደር መዘጋጀቱን አቶ ነዋይ ገልጸዋል፡፡

የዱባዩ አሌፍ ኮንሰልታሲ ኩባንያ መሥራች ባኒ ሐዳድ፣ የዊንድሃም ሆቴል ግሩፕ የአፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ ምክትል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ራማዳ የተሰኘው የዊንድሃም ብራድ ሆቴል በአዲስ አበባ ሥራ እንዲጀምር ስምምነቱን በአዲስ አበባ መፈራረማቸው አይዘነጋም፡፡ ከ130 በላይ ክፍሎች ያሉት ራማዳ አዲስ ከሚሊኒየም አዳራሽ ዝቅ ብሎ የተገነባ ባለአራት ኮከብ ሆቴል ሲሆን፣ አሌፍ ኮንሰልታንሲ በኢትዮጵያ ማሟሻ ያደረገውን ቤስት ዌስተርን የተባለውን ሆቴል የማስተዳደር ሥራውን እንደሚጀምር በቅርቡ ይፋ አድርጓል፡፡ 

እስካሁን ከውጭ የሆቴል ብራንዶች ጋር የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን በመደራደርና በማስማማት አንድ ሆቴሎች በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ ምክንያት የሆነው ካሊብራ፣ ሌሎች አምስት ተጨማሪ ሆቴሎችንም ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ ለማድረግ ማደራደር መጀመሩን አስታውቋል፡፡ እስካሁን ከመጡት ሆቴሎች 4,000 ዜጐች የሥራ ዕድል እንደሚያገኙም ይጠበቃል ተብሏል፡፡

ካሊብራ ሆስፒታሊቲ በሆቴል ኢንዱስትሪ መስክ በኢትዮጵያ የሚታየውን የባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ ያስችላል በማለት ወደፊት የማሠልጠኛ አካዴሚ ለመመሥረት ማቀዱን የገለጹት አቶ ነዋይ፣ ሌሎች ውጥኖችን ኩባንያው በመንደፍ ወደ ተግባር ሊተረጉማቸው መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

ብርሃን ባንክ ከእጥፍ በላይ ጭማሪ ያሳየበትን የ365 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ታወቀ

$
0
0

ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ በተገባደደው በጀት ዓመት የ365 ሚሊዮን ብር በማስመዝገብ አምና ካገኘው 139 ሚሊዮን ብር አኳያ ከሁለት እጥፍ በላይ ትርፍ ከታክስ በፊት ማግኘቱ ታወቀ፡፡
ከባንኩ ምንጮች በተገኘው መረጃ መሠረት በተገባደደው በጀት ዓመት ባንኩ ያስዘመገበው ትርፍ ባለፈው ዓመት ከተመዘገበው ይልቅ የ226 ሚሊዮን ብር በላይ ጭማሪ ያለው ትርፍ በማስመዝገቡ ከ162 ከመቶ በላይ ለውጥ ያሳየበትን ውጤት በማስመዝገብ አፈጻጸሙን በጥሩ ውጤት አሟሽቷል፡፡
ምንም እንኳ ከባንኩ ይፋዊ መግለጫዎችን ማግኘት ባይቻልም ባንኩ በአሁኑ ወቅት 103 ያህል ቅርንጫፎችን በመክፈት እ.ኤ.አ. በ2014/15 ከነበረበት ደረጃ ይልቅ በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ የባንኩ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ባንኮች በዓመቱ ያስመዘገቧቸውን የሥራ አፈጻጸሞች በማስመልከት እንዲሁም የፋይናንስ አቅምና ሌሎች እንቅስቃሴያቸውን የሚያመለካክቱ የፋይናንስና ክንውን መረጃዎችን ለባለአክሲዮኖች ይፋ ማድረግ እንደሚጀምሩ በሚጠበቅበት በዚህ ወቅት ያልተጠበቀ ውጤት እያሳዩ ስለሆናቸው ከወዲሁ ከታየው አንዱ የሆነው ብርሃን ባንክ፣ ከሁለት ዓመት በፊት ያስዘመገበው ትርፍ ከዓምናው አኳያ ያሳየው ጭማሪ ከ14 በመቶ ያልበለጠ እንደነበርና ለዚህም በርካታ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ያወጣው ወጪ መጨመር አንዱ ምክንያት እንደነበር ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ባንኩ ባለፈው በጀት ዓመት ሁለት ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ማበደሩና፣ ተቀማጩ ሒሳቡም ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ ካለፈው ዓመት የባንኩ የፋይናንስ ሪፖርት ለመረዳት እንደተቻለው፣ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ሲገመት የባንኩ የተከፈለ ካፒታልም ከ570 ሚሊዮን ብር በላይ ማሻቀቡ ተመልክቷል፡፡
ከጥቂት ዓመታት ወዲህ የግል ባንክ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀሉ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ብርሃን ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙት መካከል የሚመደብ ነው፡፡ በቅርብ የተመሠረቱት ባንኮች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀምጠዋል ተብሎ የሚጠበቀውን የሁለት ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል መጠን የማሟላታቸው አቅም ላይ ሥጋት ቢደቅንም፣ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ማሟላት እንደሚችሉ በርካቶቹ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡
በአንፃሩ የአንዳንዶችን የተከፈለ ካፒታል መጠን በእጥፍ የሚበልጥ ዓመታዊ ትርፍ በማስመዝገብ ላይ የሚገኙ አንጋፋ የንግድ ባንኮችም በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ እየታዩ ነው፡፡ በቅርብ እየተፎካከሩ የሚገኙት ዳሸን ባንክና አዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ለዚህ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ባለፈው ዓመት በአገሪቱ ሪከርድ የተባለውን የ980 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያስዘመገበው ዳሸን ባንክ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ምንም እንኳ የዘንድሮ የዳሸን ባንክ አፈጻጸም ይፋ ባይደረግም፣ አዋሽ ባንክ ከምን ጊዜውም ሪከርድ የሆነውን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማስመዝገብ የግል ባንኮችን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡

Standard (Image)

ለጥጥ ምርት ትንሳዔ የሚሻው ዕቅድ

$
0
0

የጥጥ ምርት መጥንና ጥራት በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሽቆልቆሉን ለማሻሻልናየምርቱን አቅርቦት መጠን ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም እንዲቻል ለማድረግ ስትራቴጂ እየተቀረጸ ሲሆን፣ ጥጥ በአሁኑ ወቅት የሚገኝበትን በመመልከት የወደፊትን አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ጥናት ይፋ ተደርጓል፡፡
የጥጥ ምርት በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ለሚመለከታቸው አካላት ይፋ የተደረገው ጥናት፣ የቅድመ ስትራቴጂክ ዕቅድ አካል ሲሆን፣ ጥናቱ በጥጥ ዘርፍ ውስጥ የሚታዩትን ልዩ ልዩ ችግሮች፣ የአመራረትና የምርታማነት ክፍተቶች እንዲሁም መፍትሄዎች ላይ ያተኮረ ጥናት የተካሄደበት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ለመጪዎቹ አሥር ዓመታት የሚያገልግል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ለመንደፍ መነሻ የተደረገው ይህ ጥናት፣ በጥጥ ምርት ላይ በአሁኑ ወቅት እየታዩ ካሉት ችግሮች ውስጥ፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የጥጥ ምርት ቀደም ብሎ ከነበረው ጋር ሲተያይ እየቀነሰ መምጣቱ ተገልጿል፡፡ በዚህ መሠረት አሁን ላይ ያለው የጥጥ ምርት መጠን ከ100 እስከ 150 ሺሕ ቶን የሚገመት ሲሆን፣ በአንጻሩ የአገሪቱ የጥት ምርት ፍላጎት ከ220 ሺሕ ቶን በላይ ሆኖ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከ70 ሺሕ በላይ የአቅርቦት ክፍተት እንደሚታይ አስተያየት ሰጪዎች ይጠቅሳሉ፡፡
ለጥጥ ምርት ማሽቆልቆል የጥራት፣ የግብአት አጠቃቀም ችግር፣ የዋጋ፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንዲሁም ለጥጥ ምርት ይውሉ የነበሩ የእርሻ መሬቶች ለስኳር ማሳነት መዋላቸው ዋነኛ መንስዔዎች ተብለው ከሚጠቀሱት ውስጥ መሆናቸው ተነስቷል፡፡ የግብኣት ዕቃዎች ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር የጥጥ ጥራት ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ መምጣት ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ያስገደዱት የኢትዮጵያ የጥጥ ዘርፍ፣ በአሁኑ ወቅት የጨርቃ ጨርቅ አምራቾች በብዛት እየገቡ መሆናቸው ታክሎበት አስፈላጊውን የጥጥ ምርት በአገር ውስጥ አምርቶ ለማቅረብ እንዳልተቻለ አስተያየት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረተውን ጥጥ ቀደም ብሎ ከነበረው መጠን አኳያ ዝቅተኛ እየሆነ እንዲመጣ አስገድደዋል ከተባሉት ሌሎች ምክንያቶች መካከል የጥጥ መዳመጫ መሣሪያዎች በቂ አለመሆን፣ የእርሻ ዘዴዎች ዘመናዊ አለመሆን እንዲሁም የተሻሻሉ ግብርና ዘዴዎች እንደልብ አለመገኘታቸው፣ ለችግሩ መንስዔ ከሆኑት ውስጥ ይመደባሉ፡፡ በጥናቱ እንዲህ ያሉት ችግሮች ስለመበራከታቸው ተንጸባርቋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የጥጥ ምርትን በመስኖና ወቅቱን በጠበቀ የእርሻ ሥራ በመታገዝ፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ በአማካይ በጥጥ መሸፈን የተቻለው መሬት 80 ሺሕ ሄክታር እንደሚደርስ ጥናቱ ይጠቅሳል፡፡ ከዚህ ውስጥ ሁለት ሦስትኛው ድርሻ የሰፋፊ ጥጥ እርሻዎች መሆኑም በጥናቱ ቀርቧል፡፡ በአንጻሩ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የለማው የጥጥ መጠን በአማካይ 135 ሺሕ ቶን ይገመታል፡፡ አሁንም ከዚህ ውስጥ ሦስት አራተኛው ድርሻ የሰፋፊ እርሻዎች መሆኑ ተመልክቷል፡፡
አቶ ፍስሐ ተክሌ፣ የሮው አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ አቶ ፍስሐ በሰጡት አስተያየት መሠረት፣ የኢትዮጵያ የጥጥ ምርታማነት ከ100 ሺሕ እስከ 150 ሺሕ ቶን ድረስ ያህል የሚገመት ሲሆን ይህም ውጤት ቢሆን ቀደም ባሉት ጊዜያት ሲመዘገብ የቆየ ነው፡፡
ለስትራቴጂክ ዕቅዱ አጋዥ በሆነው ጥናት መሠረት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የጥጥ ምርት ምርታማነት መጠን ከ77.5 ወደ 66.2 ከመቶ ማሽቆልቆሉ ተገልጿል፡፡ በተለይ የኢትዮጵያ የጥጥ ምርት እየተጠቀመ ያለው የጥጥ ዘር ከ30 ዓመት በላይ ያስቆጠረ መሆኑና አዲስና ዘመናዊ ዘር ሲመጣ በተገቢው መንገድ አለመጠቀም፣ ዝቅተኛ የግብርናና የእርሻ አሠራር ጥናት መኖሩ፣ የሠራተኞች እጥረት፣ የመስኖ ተፋሰስ አለመዳበር፣ የፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር፣ የውጭ ምንዛሪ ማጣት ተደጋግመው በጥጥ ዘርፍ ውስጥ ዋነኛ ችግሮች ተደርገው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በአገሪቱ በጠቅላላ ያለውን የጥጥ ፍላጎት ለማሟላትና ከ30 በመቶ በላይ የሚሆነውን የምርት ጉድለቱን ለማሟላት የአገሪቱን የጥጥ ምርት ፖሊሲ ማስተካከል ላይ ትኩረት መስጠት ወሳኝ እንደሆነ አቶ ታደሰ ኃይሌ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል፡፡
ሦስት ክልሎች ማለትም አማራ፣ አፋርና ትግራይ በጠቅላላው ከአገሪቱ የጥጥ ምርት ውስጥ 70 ከመቶውን የሚሸፍኑ ሲሆን፣ ከ60 ሺሕ እስከ 70 ሺሕ ቶን ድረስ የሚገመት ምርት ሲያመርቱም ቆይተዋል፡፡ ይሁንና አሁን ላይ እየታየ ላለው የምርቱ ማሽቆልቆል አንዱ ምክንያት በአፋር ክልል የሚገኘው የጥጥ ምርት መሬት በስኳር ማሳ መሸፈኑ አንዱ ስጋት ነው፡፡ በትግራይ ክልል ዝቅተኛ የዝናብ መጠን መከሰቱና በአማራ ክልልም ቢሆን በየጊዜው እየታየ ባለው ከፍተኛ የአየር ንብረት መዋዥቅ ሳቢያ የጥጥ ከምንጊዜውም ይልቅ እየቀነሰ በመምጣት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ በጥጥ ምርት ከምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ውስጥ የ50 ከመቶ የሚሆነውን ድርሻ የመሸፈን አቅም ቢኖራትም፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ ያለው የጥጥ የምርት መቀነስን ለማሻሻል በስትራቴጂው መሠረት እንዲሁም ጥናቱ የሚያነሳቸወው ችግሮችን መነሻ በማድረግ የሚጠቆሙ ችግሮች ላይ መፍትሔዎች ተብለው የቀረቡ፣ የጥጥ ምርቱን ለማሻሻል ግብዓት ይሆናሉ የተባሉ አቅጣጫዎችም ተቃኝተዋል፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመረተ የሚቀርበው ጥጥ በዓለም ገበያ ከሚቀርበው ጥጥ አኳያ ጥራቱ የወረደ ቢሆንም የሚሸጥበት ዋጋ ከፍተኛ መሆኑ ግን በዘርፉ የበለጠ ስተሬቴጂካዊ አቅጣጫ አስቀምጦ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አመላክቷል፡፡
በሁለት ወራት ውስጥ ይፋ የሚደረገው የአገሪቱ የጥጥ ምርትና ምርታማነት ስትራቴጂ ተጠናቆ ወደ ተግባር ሲገባ፣ በምርቱ ላይ ክፍተት ካልተፈጠረ በስተቀር ከውጭ የሚገባውን ምርት ሊያስቀር የሚችል የምርት መጠን በአገር ውስጥ እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል መሆኑ ተገልጾ፣ የጥጥ ምርትን በመስኖ ጭምር በመታገዝ የአገር ውስጥ የውጭ ባለሀብቶችን በብዛት ተሳታፊ እንደሚያደርግ አቶ ታደሰ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ባለሀብቶችን በተመለከተም ሲገለጽም በደቡብ ኦሞ ዞን ዙሪያ ኤልሲ የተባለ ኩባንያ በ500 ሔክታር መሬት ላይ እያደረገ ያለው የማልት እንቅስቃሴ ሌሎችም ኢንቨስተሮች ወደ ዘርፉ ሊመጡ የሚችሉበትን ፍንጭ ይሰጣል በማለት አክለዋል፡፡
አቶ አብርሃ ኃይለሥላሴ ብሌን ጸጋዬ ቢዝነስና ኢንዱስትሪ ለተባለው ድርጅት የምርት መምሪያ ኃላፊ ሲሆኑ፣ በአፋር ክልል በጥጥ ምርት ላይ የሚሳትፍ ድርጅት ቢሆንም፣ በዘርፉ ላይ እየታየ ያለው ችግር በተለይ የግብዓት ወጪዎችን ለመሸፈን የገንዘብ እጥረት ድርጅቱ እያጋጠመው በመሆኑና የብድር ሊመቻችለት አለመቻሉ ኩባንያው የሚገጥመው የምርት ሒደት ችግር እንዲባባስ አድርጎታል ብለዋል፡፡
እስካሁን በተበጣጠሰ መንገድ ይካሄድ የነበረውን የጥጥ ምርት ለማሳደግ እየተደረጉ ያሉ ጥናቶችን በአንድ ስትራቴጂ ማዕቀፍ ውስጥ አዋቅሮ ለማስኬድ መነሳት፣ ወደፊትም ምርትን ከመጨመር፣ ግብርናውን ዘመናዊ ከማድረግ፣ ፋይናንሱንና የግብዓት ችግሮችን ከመፍታት አኳያ የሚሠሩ ሥራዎች ከውጭ የሚገቡትን የጥጥ ምርቶች ለመቀነስ እንደሚረዱ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምርት አቅረብን ገዥ ጠፋ›› በማለት ጥጥ አምራቾች ለሚያቀርቡት ጥያቄ ምላሹ፣ በጥራት አምርቶ ማቅረብ መሆኑንና በጥራት ማቅረብ ከተቻለም ገዢ እንደማይጠፋ አቶ ታደሰ ገልጸዋል፡፡
ምርቱን ለገበያ ለማቅረብ የገበያ ትስስር መፍጠር ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ስትራቴጂክ ዕቅዱ ጠቃሚ እንደሆነ፣ በተጨማሪም በጥጥ ምርት ገበሬው የተሻለ ገቢ እንዲኖረውና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ምርት እንዲገኝ ያደርጋል ብለዋል፡፡ በትልልቅ ገበያዎች ላይም ምርት ማቅረብ እንዲቻልና የውጭና የአገር ውስጥ ነጋዴዎች እንዲሳተፉ ማድረግም በግብይት ሰንሰለት ውስጥ የሚታዩ ማነቆችዎችን ለመፍታት ከሚረዱ መፍትሄዎች መካከል እንደሚመደብ ተብራርቷል፡፡

Standard (Image)

የአርጀንቲና ኩባንያ አዲስ የጥርስ ሕክምና መስጫ ምርት ለአፍሪካ ለማቅረብ ኢትዮጵያን ማከፋፈያ ማዕከል ማደረጉን አስታወቀ

$
0
0

- የ50 ሚሊዮን ዶላር ምርት ለማቅርብ ማቀዱን ገልጿል

ዋና መሥሪያ ቤቱን በአርጀንቲና ያደረገውና ቬንዳኖቫ ግሩፕ የተሰኘው ኩባንባ፣ በዓለም ጥቅም ላይ ሲውል ገና አዲስ እንደሆነ የተነገረለትን የጥርስ ሕክምና መስጫ ቴክኖሎጂ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚያመጣ፣ ኢትዮጵያን መነሻ በማድረግም ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች የማከፋፈል ዓላማ እንዳለው አስታውቋል፡፡
ኩባንያው በአርጅቲና ማምረት ከጀመረ አራት ዓመታት ያስቆጠረውንና የተጎዳ ወይም የተቦረቦረ የጥርስ ክፍልን ለማከም የሚውለው ቅባት መሰል የጥርስ ሕክምና መስጫ ‹‹ብሪክስ-3000›› ተብሎ የሚጠራውን ምርት ለማምጣት ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቅባት መሰል የጥርስ ሕክምና መስጫ፣ የታመመ ወይም የተቦረቦረን ጥርስ ያለ ምንም ማደንዘዣና መቦርቦሪያ አማካይነት በደቂቃዎች ውስጥ ለማከም የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን የኩባንያው ኃላፊ፣ ጆርጅ ሌይን ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ምርቱን በማስመልከት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አስታውቀዋል፡፡ ጆርጅ ሌይን በአርጀንቲና ከ58 ያላነሱ ኩባንያዎችን በግሩፕ በማቀፍ የሚንቀሳቀሰውን ቬንዳኖቫ ግሩፕ ኩባንያ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ይመራሉ፡፡
የጥርስ በሽታን ለማከም፣ በተለይም የተቦረቦሩ ጥርሶችን ለማጠብና ለመሙላት ይውላል የተባለው ይህ ምርት፣ በጥርስ ሕመምና በተምዶ በሚካሄደው የሕክምና ሒደት ሳቢያ የሚደርሰውን ጉዳትና አልፎ አልፎም የሚከሰተውን ሞት ለመቀነስ አስተዋጽኦ እንዳለው የጠቀሱት ሌይን፣ በአንዱ ምርት ብቻ አሥር የተቦረቦሩ ጥርሶችን ለማጠብና ለመሙላት የሚችል ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ምርቱ ሲጀመር ለሕፃናት ተብሎ የተፈበረከ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ተሻሽሎ አዋቂዎችም እንዲጠቀሙበት በሚያስችል መልኩ እየተመረተ ለዓለም በመቅረብ ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል፡፡
በብዛት በላቲን አሜሪካ አገሮች ዘንድ ሰፊ የገበያ ድርሻ እንዳለው የተገለጸው ብሪክስ-3000 የጥርስ ሕክምና መስጫ፣ በአፍሪካ ካ አገሮች እስካሁን ደቡብ አፍሪካ ምርቱን በሰፊው ስትጠቀም ቆይታለች ያሉት ሌይን፣ በአሁኑ ወቅት ግን ኢትዮጵያ በማዕከልነት ተመርጣ ምርቱን ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለማከፋፈል ኩባንያቸው ማቀዱን ገልጸዋል፡፡ የኩባንያው ወኪል ጽሕፈት ቤትም በኢትዮጵያ ተከፍቶ ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር ግን ሚረር የንግድና አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ የቬንዳ ኖቫ ግሩፕ ኩባንያ ዋና ወኪል በመሆን እንደሚሠራ በተደረገው ስምምነት መሠረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በጅምላ በማስመጣት ማከፋፈል እንደሚጀምር የሚረር ኩባንያ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ወንድሙ አስታውቀዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ በገለጹት መሠረት፣ ሆስፒታሎች፣ የጥርስ ሕክምና ማዕከሎች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ሌሎችም ድርጅቶች በሚሰጡት የምርት ትዕዛዝ መሠረት ምርቱ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
ቬንዳኖቫ ለኢትዮጵያ ገበያ ሊያቀርብ ያቀደው የምርት መጠን 50 ሚሊዮን ዶላር እንደሚገመት አስታውቋል፡፡ ሆኖም በዋጋ ረገድ አሥር ጥርሶችን ለመሙላት የሚውለው አንዱ ብሪክስ-3000 ምርት፣ በ50 ዶላር ለገበያ እንደሚቀርብና አንድ ጥርስ ለመሙላት የሚጠይቀው ወጪም አምስት ዶላር ብቻ እንደሚሆን የኩባንዎቹ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡ አሁን ባለው አሠራር ለአንድ ጥርስ ሙሊት እንደየ ተጨባጭ ሁኔታው እስከ 150 ዶላር እንደሚጠየቅ ሌይን በሰጡት ማብራሪያ ጠቅሰዋል፡፡
የምርቱን የጥራት ደረጃና የብቃት ሁኔታን በሚመለከት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የቬዳኖቫ የአትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ወልደ ጻዲቅ፣ የምርቱ ደኅንነት ተፈትሾ፣ የጥራት ደረጃው በመረጋገጡ ፈቃድ ቢትዮጵያ ፈቃድ ማግኘት የሚያስችለውን ሒደት ጨርሶ እየተጠባበቀ እንደሚገን ገልጸዋል፡፡ ሌይን በበኩላቸው ከዓለም የጤና ድርጅትና ከአርጀንቲናው የምግብ፣ መድኃኒትና የህክምና መሣሪያዎች አስተዳደር ተቋምና ከመሰሎቹ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

Standard (Image)

አስተዳደሩ ለኤግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ የግማሽ ቢሊዮን ብር ተጨማሪ አክሲዮን ገዛ

$
0
0

• ከንግድ ኅብረተሰቡ የበለጠ ብዙ አክሲዮኖች በመግዛት የኩባንያው ከፍተኛ ባለቤት ሆኗል ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚጠይቅ ለተገመተው የአዲስ አፍሪካ ኤግዚቢሽንና ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ በድጋሚ ለሽያጭ ከቀረቡ አክሲዮኖች ውስጥ የአዲስ አበባ አስተዳደር የግማሽ ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖችን ገዛ፡፡ ከአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ አስተዳደሩ ተጨማሪ 500 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖችን የገዛው ለሁለተኛ ጊዜ ለሽያጭ ከቀረቡትና አንድ ቢሊዮን ብር ዋጋ ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና በ20 ኩባንያዎች መሥራችነት ለማዕከሉ ግንባታ የተቋቋመው የአክሲዮን ማኅበር፣ ለሁለተኛ ጊዜ ለሽያጭ ካቀረባቸውና አንድ ቢሊዮን ብር ዋጋ ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ ግማሽ ያህሉን አክሲዮኖች የገዛው በሥሩ በሚያስተዳድራቸው አምስት ተቋማት ስም ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁለተኛው ዙር ከገዛቸው ውስጥ 415 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች በባለቤትነት በሚያስተዳድረው፣ የአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ስም የገዛ መሆኑን ከንግድ ምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ቀሪዎቹን የ85 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው አክሲዮኖች በአንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት፣ በአዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ በአዲስ ኢንተርፕራይዝ፣ በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅትና በቅርቡ ወደ ሥራ በገባው ሸገር አውቶብሶች ኩባንያ በኩል መግዛቱ ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ አቶ ጌታቸው ረጋሳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር በመጀመያው ዙር ለሽያጭ ከቀረቡትና 300 ሚሊዮን ብር ዋጋ ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ገዝቶ ነበር፡፡ አሁንም በሁለተኛው ዙር ለሽያጭ እንዲውሉ ከተዘጋጁትና አንድ ቢሊዮን ብር ዋጋ ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን በመግዛት በአጠቃላይ አክሲዮን ኩባንያው ለሽያጭ ካወጣቸው 1.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ካላቸው አክሲዮኖች ውስጥ 650 ሚሊዮን ብር የሚያወጡትን አክሲዮኖች ሊገዛ ችሏል፡፡ ይህም አስተዳደሩ የአክሲዮን ኩባንያው ውስጥ ያለውን ድርሻ በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ የማዕከሉ ዋነኛ ባለቤት መሆኑን ያረጋገጠበት ሆኗል፡፡ እንደ አቶ ጌታቸው ገለጻ፣ አዋጭ መሆኑ በተጠናው ቢዝነስ ውስጥ ዜጐች በተለይም የግሉ ዘርፍ አክሲዮን በመግዛት የኩባንያው ባለድርሻ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ቢሆንም፣ አስተዳደሩ ብልጫ ያለውን አክሲዮን በመሰብሰብ ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ በመጀመሪያው ዙር ለሽያጭ ከቀረቡት አክሲዮኖች ውስጥ ብዙ በመግዛት አስተዳደሩ አብላጫውን እጅ ሲወስድ፣ ከአስተዳደሩ ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን አክሲዮን የገዙት ደግሞ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ናቸው፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት ዳያስፖራዎች፣ በመጀመሪያው ዙር የአክሲዮን ሽያጭ ወቅት 115 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ለመግዛት ቃል ገብተው ግማሽ ያህሉን ገንዘብ ከፍለዋል፡፡ ቀሪዎቹ አክሲዮኖች በተለያዩ ግለሰቦችና ኩባንያዎች የተያዙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ይህ ስብጥር ግን አሁንም የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑን አመላክቷል፡፡ የግሉ ዘርፍ በአክሲዮን ግዥ ያሳየው ተሳትፎ ዝቅተኛ ነው የሚለውን አስተያየት አቶ ጌታቸውም ይጋሩታል፡፡ ማዕከሉ የግሉ ዘርፍ ከመንግሥት ጋር በጋራ የሚሠራበት እንደመሆኑ መጠን የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም፣ ቀሪዎቹን አክሲዮኖች እንዲገዛና የማዕከሉ የባለቤትነት ድርሻውን እንዲያሳድግ ጥረት ይደረጋል ተብሏል፡፡ የፕሮጀክቱን አዋጭነትና አስፈላጊነት በማመን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች አስተዳደሩ እንደገዛው ሁሉ፣ የግሉ ዘርፍም ይህንን ማድረግ እንደሚጠበቅበት አቶ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡ ከአዲሱ የአንድ ቢሊዮን ብር የአክሲዮኖች ሽያጭ ውስጥ አስተዳደሩ የገዛው 500 ሚሊዮን ብር በመሆኑና ቀሪዎቹ 500 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በመግዛት የማዕከሉ ባለቤትነት ድርሻቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው አቶ ጌታቸው አሳስበዋል፡፡ በአክሲዮን ኩባንያው መጀመሪያ ለሽያጭ ከቀረቡት 300 አክሲዮኖች ውስጥ የ10 ሚሊዮን ብር አክሲዮኖችን የገዛው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ በሁለተኛው ዙር የአክሲዮን ሽያጭ ሒደትም ተጨማሪ አክሲዮኖችን እንደሚገዛ ይጠበቃል፡፡ ከአቶ ጌታቸው ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በምክር ቤቱ ስም ተጨማሪ አክሲዮኖችን ለመግዛት ታቅዷል፡፡ ይሁን እንጂ ንግድ ምክር ቤቱ ሊገዛ ከሚችለው አክሲዮን ይበልጥ የግሉ ዘርፍ የባለቤት ድርሻው ከፍ እንዲል ኩባንያዎችና በንግድና ኢንቨስትመንት ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አክሲዮኖችን ቢገዙ የበለጠ ትርጉም ይኖረዋል ብለዋል፡፡ በሁለት ምዕራፎች ተከፍሎ የሚገነባው ማዕከል፣ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ይፈጃል ተብሎ ሲገመት፣ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታም ከሦስት ወራት በኋላ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ግንባታውን ለማከናወን ዓለም አቀፍ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሒደት ላይ ሲሆን፣ አሸናፊ የሚሆነው ሥራ ተቋራጭም እስከ ሐምሌ ወር 2008 ዓ.ም. መጨረሻ ድረስ ውጤቱ በይፋ ይታወቃል ተብሏል፡፡ በመስከረም 2009 ዓ.ም. አሸናፊው ተቋራጭ ወደ ግንባታ ሥራ እንዲገባ ለማድረግ መታቀዱንም ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ በአገሪቱ ትልቁ የኤግዚቢሽን ማዕከል ይሆናል የተባለው ማዕከል ከ12 ዓመታት በፊት እንዲገነባ ሲወጠን በንግድ ምክር ቤቱና በንግድ ኅብረተሰቡ ትብብር እንዲሠራ ታስቦ ነበር፡፡ ሆኖም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት በንግድ ምክር ቤቱ አቅም ብቻ መሥራት ከባድ በመሆኑና የፕሮጀክቱ ይዘትም መስፋት እንዳልበት በመታመኑ፣ ግንባታውን ከመንግሥት ጋር በጋራ እንዲካሄድ ፕሮጀክቱም በትርፍ አመንጪነቱ የተሻለ እንዲሆን በአክሲዮን ኩባንያ ደረጃ ተዋቅሯል፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ሐሳብ አፍላቂና በግንባታ ሒደቱም ዋናው አስተባባሪ የሆነው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ ለማዕከሉ ግንባታ 110 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ከመንግሥት መረከቡ ይታወሳል፡፡ የኤግዚቢሽንና የኮንቬንሽን ማዕከሉ ለንግድ ትርዒቶች ማሳያና ማቅረቢያ ከሚገነቡት አዳራሾች በተጨማሪ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎችን የሚያካትት ነው፡፡ በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ ሁለት የኤግዚቢሽን ማዘጋጃ አዳራሾችና የቋሚ ኤግዚቢሽን ማሳያ አዳራሾች፣ ለባንክና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎችና የስብሰባ አዳራሾች ተካተዋል፡፡ በሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታም ባለአምስት ኮከብ ሆቴልን ጨምሮ ልዩ ልዩ የንግድ ትርዒቶች ማሳያ አዳራሾችንና ከማዕከሉ ከዕለት ሥራ ጋር የተያያዙ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ሕንፃዎችም እንደሚገነቡ ይጠበቃል፡፡ የማዕከሉ ግንባታ አዲስ አበባን የአፍሪካ የንግድ ማዕከል ለማድረግ ዓላማ ያለው በመሆኑ ጭምር፣ የአፍሪካ አገሮች የየራሳቸው የንግድ ትርዒት ማሳያ ሥፍራ ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡ ማዕከሉ እንደ አትራፊ ኩባንያ የተቋቋመ በመሆኑ፣ ከሚሰጠው አገልግሎት የሚያገኘው ትርፍ በገዙት አክሲዮን ብዛት ልክ የትርፍ ድርሻ ያከፋፍላል፡፡ የመጀመሪያው ግንባታ እንደተጠናቀቀ ወደ ንግድ ሥራ የሚገባ በመሆኑ፣ ከዚህ የሚገኘው ገቢ ለሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ እንደሚውል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Standard (Image)

አንድ መቶ ቡና አቅራቢዎች ያለባቸውን ብድር ወደ መንግሥት ባንክ ሊያዛውሩ ነው

$
0
0

ያለባቸውን የብድር ዕዳ የመክፈያ የዕፎይታ ጊዜ ከተሰጣቸውና ለብድር ያስያዙት ንብረት እንዳይሸጥባቸው ዕድሉን ካገኙ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች ውስጥ አንድ መቶ ተበዳሪዎች በግል ባንኮች ውስጥ የነበራቸው የብድር ዕዳ ወደ መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማዛወር እየተዘጋጁ መሆኑ ታወቀ፡፡ የደቡብ ክልል ቡና አጣቢዎች፣ አበጣሪዎችና አቅራቢዎች የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ኃላፊዎች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከአባሎቻቸው መካከል ብድራቸውን በፍላጎታቸው ወደ ንግድ ባንክ ለማዛወር ጥያቄ የሚያቀርቡ አባላት እየተጠበቁ ነው፡፡ ቡና አቅራቢዎቹ በተለያዩ የግል ባንኮች ውስጥ የነበረባቸው ዕዳ ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለማዛወር መዘጋጀት የጀመሩት በመንግሥት ውሳኔ መሠረት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያለባቸውን ብድር ወደ መንግሥት ባንክ በማዘዋወርና የመክፈያ ጊዜውም እንዲራዘም ተደርጎ በተሰጣቸው ተጨማሪ ዕድል ለመጠቀም ነው ተብሏል፡፡ የማኅበሩ ፍላጎት ግን ሁሉም የዕድሉ ተጠቃሚዎች ብድራቸውን ወደ መንግሥት ባንክ እንዲያዞሩ ነበር፡፡ ሆኖም ብሔራዊ ባንክ ብድር የማዛወሩ አሠራር በፍላጎት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን በመወሰኑ ምክንያት እስካሁን አንድ መቶ ተበዳሪዎች ወደ ንግድ ባንክ ብድር ለማዛወር ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ ብሔራዊ ባንክ ባልተለመደ አኳኋን በደቡብ ክልል ያሉ ቡና አቅራቢዎች፣ ከባንኮች የተበደሩትን ብድር ለመክፈል ባለመቻላቸው ለብድር ያስያዙት ንብረት እንዳይሸጥባቸው፣ ብድራቸውን ለመክፈልም በብድር አመላላስ ላይ ከተቀመጠው ሕግ ውጪ በሆነ መንገድ እንዲስተናገዱ ከሰጣቸው ዕድል በተጨማሪ በግል ባንኮች የሚፈለግባቸው ወደ መንግሥት ባንክ እንዲዛወር ተወስኗል፡፡ የማኅበሩ አመራሮች እንደገለጹት፣ በመንግሥት የተሰጣቸውን ዕድል ለመጠቀም ከግል ባንኮች ወደ ንግድ ባንክ ብድራቸውን ለማዞር የሚችሉ ተበዳሪዎች፣ ብድሩ እንዲዛወርላቸው የሚጠበቅባቸውን ማመልከቻም በቅርቡ ያስገባሉ፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ብድራቸውን ለመክፈል ያልቻሉ ሆኖም ከፍተኛ ግምት ያለው ንብረታቸው በባንክ ዕገዳ እንዳይሸጥባቸው ለመታደግ ሲባል መንግሥት የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው የፈቀደላቸው፣ በደቡብ ክልል የሚገኙ ቡና አቅራቢዎች ቁጥር ከ400 በላይ እንደሆነ ታውቋል፡፡ ሆኖም ከነዚህ ቡና አቅራቢዎች መካከል በግል ባንኮች የሚፈለግባቸውን ብድር ወደ ንግድ ባንክ ያዛውራሉ የተባሉት አንድ መቶ ያህል ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ የዕድሉ ተጠቃሚዎች ብድር ከየወሰዱባቸው ባንኮች ጋር በመደራደር የብድር ማራዘሚያ ጊዜ ይፈቀድላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የብድር ዝውውሩ የሚከናወነው በፈቃደኝነት ላይ ተመሥርቶ ሲሆን፣ ብድሩ ይዛወርልን ብለው ያመለከቱ አቅራቢዎችን ጥያቄ የኢትዮጵያ ንግድ ከተቀበለው፣ ተበዳሪዎቹ በግል ባንኮች የሚፈለግባቸውን ዕዳ ባንኩ ከፍሎ ብድራቸውን ማስተዳደር እንደሚጀምር ይጠበቃል፡፡ በብሔራዊ ባንክ መመርያ መሠረት፣ ተበዳሪዎች ከሦስት ጊዜ በላይ የብድር መክፈያ ቀነ ገደብ እንደማይራዘምላቸው ቢያስቀምጥም፣ ይህ መመርያ ግን በእነዚህ ቡና አቅራቢዎች ላይ እንዳይፈጸም ተወስኗል፡፡ በመሆኑም ባንኮች የብድር መክፈያ ቀነ ገደቦችን በማራዘም የሰጧቸውን ብድሮች ለማስመለስ በጋራ ይሠራሉ፡፡ ተበዳሪዎቹም ተጨማሪ ብድር ለማግኘት የሚያስችላቸው ዕድል የሚመቻችላቸው በመሆኑ ቡና የማቅረብ ሥራቸው እንዳይስተጓጎልባቸው ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡ የደቡብ ክልል ቡና አቅራቢዎች በሐዋሳ ከተማ ብቻ ከ2,400 በላይ የሚሆኑ ሕንፃዎችና ቤቶችን ለቡና ማቅረብ ሥራቸው ያስያዙ ሲሆን፣ በባንኮች የተያዘው ንብረት አጠቃላይ ግምት ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚሆን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ማኅበሩ መንግሥት የተሰጠውን ዕድል በአግባቡ ለመጠቀም በሥሩ ላሉ አባላቱ የግንዛቤ ማስጨበጫና የክትትል ሥራዎችን ማከናወን እንደሚጀምር ገልጿል፡፡ በመንግሥት የተላለፈውን ውሳኔ እንዲያስፈጽም የተዋቀረው ኮሚቴም ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

Standard (Image)
Viewing all 720 articles
Browse latest View live